20 Apr 2026, 16:23 UTC96 views8 reactionsread 9 August 2026 🛐 "እግዚአብሔር ፊት የተንበረከከ... ማንም ፊት አይንበረከክም!"
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ!
በሕይወታችን ውስጥ ከምንም ነገር ፊት መቆም የምንችለው እግዚአብሔር ፊት ስንበረከክ ብቻ ነው። የሕልቃና ሚስት የሐና ታሪክ ይህንን እውነት በሚገባ ያስተምረናል።
የሐና እንባ እና የጌታ ፊት
ሐና መካን ስለነበረች ባላንጣዋ ፍናና ታበሳጫትና ታስለቅሳት ነበር። ሐና ግን ለቅሶዋን ይዛ ወደ ሰው አልሄደችም፤ ወደ ቤተ መቅደስ እንጂ።
"እጅግም ተከዝታ ነበርና ወደ እግዚአብሔር ጸለየች፥ በጽኑምአለቀሰች።" (1ኛሳሙኤል1፥10)
እግዚአብሔር ፊት ያለቀሰ... በምንም አያለቅስም!
ሐና እግዚአብሔር ፊት የልቧን አፈሰሰች፤ በእርሱ ፊት ተንበረከከች። ውጤቱ ግን የሚከተለው ነበ…
🔥5❤2🥰1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
19 Apr 2026, 08:31 UTC90 views5 reactionsread 9 August 2026 💫ኩራት(Ego) የውስጥ ጠላትህ ነው!!!
ብዙ ሰዎች Egon እና በራስ መተማመንን ያደባልቁታል። ልዩነቱ ግን ግልጽ ነው። በራስ መተማመን የሚመጣው ከችሎታና ከእውነት ነው፤ "እችላለሁ" ይላል።
Ego ግን የሚመጣው ከፍርሃትና ከትዕቢት ነው፤ "ከሰው እበልጣለሁ" ይላል።በራስ መተማመን በሩን ይከፍታል፤ Ego ግን በሩን በፊታችን ላይ ይዘጋዋል።
Ego "ሁሉንም አውቃለሁ" ይላል። ሁሉንም አውቃለሁ የሚል ሰው ደግሞ አዲስ ነገር መማር አይችልም። አንድን ትልቅ ተራራ ለመውጣት መጀመሪያ ከግርጌው መሆን እንዳለብህ ሁሉ፣ ወደ ትልቅ ደረጃ ለመድረስም ዝቅ ብሎ መማርን ይጠይቃል። ትልቅ ለመሆን መጀመሪያ ትንሽ ለመሆን መፍቀድ አለብህ። Egoህ እንዲመራህ ከፈቀድክ፣ …
🥰3🔥2
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
18 Apr 2026, 16:56 UTC206 views4 reactionsread 9 August 2026 ኢየሱስ እጅ ሲገባ... ታሪክ ይቀየራል!"
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ!
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ አንድ ድንቅ ታሪክ አለ። በምድረ በዳ የተራቡ ብዙ ሺህ ሕዝቦች ባሉበት፣ አንድ ትንሽ ልጅ አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ ይዞ ቀረበ።
📍 የልጁ መስዋዕትነት እና የጌታ እጅ
ልጁ ያቺን ምሳ ለጌታ ሲሰጥ፣ በሰዎች ዕይታ "ምሳውን አጣ" ወይም "ባዶ እጁን ቀረ" ሊባል ይችላል። ለራሱ ብቻ የምትበቃውን ለጌታ አሳልፎ ሰጠ። ነገር ግን ያቺ ጥቂት ነገር በኢየሱስ እጅ ስትገባ የሆነውን ተመልከቱ፦
በረከት ሆነች፦ በልጁ እጅ ሳለች "ምሳ" ነበረች፤ በኢየሱስ እጅ ስትገባ ግን "በረከት" ሆነች። ጌታ አመሰገነባት፣ ባረካትም።
ተባዛች፦ ጥቂቷ ነገር አምስት ሺህ ወንዶ…
🙏2❤1👏1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
17 Apr 2026, 04:48 UTC62 views3 reactionsread 9 August 2026 ራሱን የቻለ ኩል ይስማል!" — ራስህን ሁን! 🦁
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ! ✨
ዛሬ ትንሽ ጠንከር ያለ እውነት እንነጋገር። በሶሻል ሚዲያ ዓለም ውስጥ ብዙ ሰው "ማንነቱን" ረክሶ "ምስሉን" (Profile) ለማሳመር ሲሮጥ ይታያል። ነገር ግን እውነተኛ ሕይወት በፕሮፋይል ፒክቸር አትቀየርም።
📍 እኔ የምፎካከረው ከራሴ ጋር ነው!
የእኔ ትልቁ ውድድር ከትላንትናው ማንነቴ ጋር ነው። ዛሬ ከትላንት የተሻለ ሰው መሆን እንጂ የሌላውን ሰውሕይወት ኮፒ ማድረግ አላማዬ አይደለም።
"እስቲ እንወዳደር" ካላችሁ ግን... የምወዳደረውም ከእናንተ ጋር ሳይሆን "ከአባታችሁ" ጋር ነው። የሌላውን ሰው ስኬት እንደራስ ለማድረግ ከመሞከር በፊት የራስህን ታሪክ ስራ።
📍 የፕሮፋይል…
🔥2👏1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
15 Apr 2026, 18:13 UTC72 views3 reactionsread 9 August 2026 መቼም ቢሆን "እግዚአብሔር ታሪክ አይበላሽበትም!"
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ!
ሕይወት አንዳንዴ መስመር የሳተች፣ ነገሮች ሁሉ የተበላሹና የማይመለሱ ሊመስሉ ይችላሉ። ነገር ግን አንድ ትልቅ ሚስጥር ልንገራችሁ፦ እኛ የምናመልከው አምላክ የተበላሸውን ታሪክ አርሞ ለክብር የሚያበቃ ታላቅ ደራሲ ነው።
📍 ታሪክ የማይበላሽበት መሆኑን የምናይባቸው 3 ነጥቦች፦
1. የተሸጠው ዮሴፍና የታሪኩ መቆለፊያ ዮሴፍ በወንድሞቹ ተሸጠ፣ በሰው ቤት ባሪያ ሆነ፣ ባልሰራው ወንጀል ታሰረ። በሰው ዓይን የዮሴፍ ታሪክ "ተበላሽቷል"። ነገር ግን መጨረሻው እንዲህ ሆነ፦
"እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን... ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለበጎ አሰበው።" (ዘፍጥረት 5…
🔥2❤1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
15 Apr 2026, 18:05 UTC64 views3 reactionsread 9 August 2026 ምንም አይደለም!
ተስፋ ይቁረጡብህ ምንም አይደለም፣ ፊታቸውን ያዙሩብህ ምንም አይደለም፣ አይስሙህ፣ ይግፉህ፣ አለመቻልህን ይንገሩህ፣ ስህተትህን ያጉሉት፣ ጥረትህን ዋጋቢስ ያድርጉት ምንም አይደለም። ቢረማመዱብህ እንኳን አቀርቅረህ ስራ፣ ችላ ቢሉህም ወደአንተ እንዲመጡ አትለምናቸው። በራስህ ተስፋ አትቁረጥ፣ አይንህን ከራስህ ላይ አትንቀል፣ ራስህን ለመውደድ አንዳች መስፈርት እንዳታወጣ። አንዳንዶች ወዳጅ መስለው የጠላትነት መርዛቸውን ይረጩብሃል፣ አንዳንዶች የሚረዱህ መስለው የሚፈልጉትን ወስደው ይሔዳሉ፣ አንዳንዶችም የልብህ ሰው መስለው ተጫውተውብህ ይጠፋሉ። ምንም ይሁንብህ ነገር ግን በሰው መጥፎ ተግባር ምክንያት አንገትህን ደፍተህ አትቅር፣ በጠላቶችህ እኩይ…
❤3
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
14 Apr 2026, 08:15 UTC68 views1 reactionsread 9 August 2026 Photo
በ30 ዲናር መሬት በሚገዛበት ዘመን የ300 ዲናር ሽቶ ሰብሮ እግር ላይ ማፍሰስ መነካት ይጠይቃል።
@temuali
❤1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
13 Apr 2026, 15:06 UTC73 views2 reactionsread 9 August 2026 ደክመህ ስትታይ ጠላት ከሚሆን ወዳጅ... እግዚአብሔር ይጠብቅህ!"
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ!
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እጅግ አስደንጋጭ ከሆኑ የታሪክ ክፍሎች አንዱ በ2ኛ ሳሙኤል 20 ላይ የሚገኘው የኢዮአብና የአሜሳይ ታሪክ ነው።
እግዚአብሔር በህይወቴ ውስጥ ቦታ በሰጠዋቸው ሰዎች ያስተማረኝ ድንቅ ትምህርት ።
ኢዮአብ ወደ አሜሳይ ቀርቦ "ወንድሜ ሆይ፥ ደኅና ነህን?" አለው። በቀኝ እጁም ሊስመው አገጩን ያዘ። አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ያለውን ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም በዚያ ሰይፍ ሆዱን ወጋው፤ አሜሳይ ግን እዚያው ወደቀ። (2ኛ ሳሙኤል 20፥9-10)
ከዚህ ታሪክ የምንማረው ትልቅ ትምህርት፦
የ"ሰላምታ" ተንኮል፦ ኢዮአብ ሰይፉን የሳለው "ደኅና…
❤2
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
12 Apr 2026, 12:09 UTC83 views1 reactionsread 9 August 2026 ቤዛነት (Redemption)፦ የመለኮታዊ ግዢና የመተካት ምስጢር
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ!
ዛሬ በክርስትና አስተምህሮ ውስጥ እጅግ መሠረታዊ የሆነውን "ቤዛነት" (Redemption) የተሰኘውን ቃል ጥልቅ ትርጉም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር እናጠናለን።
1. በብሉይ ኪዳን፦ ቤዛነት እንደ "ዋጋ ከፍሎ ነፃ ማውጣት"
በብሉይ ኪዳን ቤዛነት የሚለው ቃል (Ga'al) የሚያመለክተው አንድን በባርነት ያለን ሰው ወይም የጠፋን ርስት ዋጋ ከፍሎ መመለስን ነው።
የፋሲካው በግ ምልክት፦ እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት የወጡት በበጉ ደም ቤዛነት ነው።"እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ ከግብፅ ከባርነት ቤት እንዳወጣን... በኲርን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ።" (ዘፀአት 13፥14-1…
🥰1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
12 Apr 2026, 08:29 UTC69 views3 reactionsread 9 August 2026 ልዩነቱን እናስተውል፦ "ሰማዕት"ወይንስ"ሕያው"?
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ!
በታሪክ ውስጥ ብዙ ታላላቅ ሰዎች ለሰው ልጅ ነፃነትና ለእውነት ሲሉ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል። እነዚህን ሰዎች "ሰማዕታት" እንላቸዋለን። የናዝሬቱ ኢየሱስ ግን ከእነዚህ ሁሉ የሚለይበት መሠረታዊ የባሕርይ ልዩነት አለው። ይህን ልዩነት በሦስት ነጥቦች እንመልከት፦
1. የሞት "ተገዥነት" እና "አሸናፊነት" ልዩነት
ሰማዕታት፦ ሞት በላያቸው ላይ ሥልጣን አለው። አንድ ጊዜ ከሞቱ በኋላ ታሪካቸው በመጽሐፍ ይዘከራል እንጂ ዳግም አይነሱም።
ኢየሱስ፦ እርሱ ሞትን የገደለ ብቸኛ ጌታ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ክርስቶስ ከሙታን ተነስቶ ወደፊት እንዳይሞት ሞትም ወደፊት እንዳይገ…
❤3
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
11 Apr 2026, 17:05 UTC65 views3 reactionsread 9 August 2026 ፋሲካ ይሁንላችሁ!
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!
በመጀመሪያው ፋሲካ እስራኤላውያን በግብፅ ምድር በነበሩበት ወቅት፣ በደሙ ምልክት ምክንያት ከሞትና ከባርነት እንደወጡ፤ ዛሬም በቤታችሁ ላይ እነዚህን ሰባት የፋሲካ በረከቶች ይሁንላችሁ
1. የመቅሰፍት ማለፍ በረከት! በግብፅ ላይ የመጣው የሞት መልአክ ደሙ ባለበት ቤት ላይ እንዳለፈ፣ በሕይወታችሁና በቤታችሁ ላይ የመጣው ማንኛውም መቅሰፍት፣ ሕመም እና የኪሳራ ድምፅ ያልፋችሁ! ጌታ በምሕረቱ ይለፋችሁ።
2. የነፃነት በረከት! ለ430 ዓመታት እስራኤላውያንን አስሮ የነበረው የባርነት ሰንሰለት በዚያች የፋሲካ ምሽት እንደተበጠሰ፣ እናንተንም አስሮ የያዛችሁ ማንኛውም የሕይወት ቀንበር ዛሬ …
❤2🔥1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
10 Apr 2026, 21:40 UTC59 views2 reactionsread 9 August 2026 ከእርቃን ሩጫ... እስከ መጀመሪያው ወንጌል! 📖
ሰላም የቴሌግራም ቤተሰቦቼ!
ዛሬ ስለ አንድ ወጣት አስገራሚ ታሪክ እናውራ፤ ስለ ማርቆስ። የእርሱ ሕይወት "አምላክ ሰውን እንዴት ይለውጣል?" ለሚለው ትልቅ መልስ ነው።
📍 ያ አስፈሪ ምሽትና "እርቃን" መሮጥ
ጌታ ኢየሱስ በተያዘበት በዚያ አስፈሪ ምሽት፣ አንድ ወጣት በነጠላ ብቻ ተሸፍኖ ይከተለው ነበር። ጭፍሮቹ ሊይዙት ሲሉ ግን "ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ" (ማርቆስ 14፥51-52)።
ይህ ወጣት ማርቆስ ነበር። በፍርሃት የተሸነፈ፣ ጌታን ጥሎ የሮጠ፣ በሰው ፊት የውርደት ታሪክ የነበረው ተራ ወጣት።
📍 ግን እግዚአብሔር እንዲህ አይተውህም!
ዓለም በማርቆስ "ፈሪና እርቃኑን የሮጠ" ብላ ስትፈርድበት፣ ጌታ ግን …
❤1🔥1
Signed Ⓣⓔⓜⓤ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @visionarytemuali. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.