29 Aug 2026, 16:20 UTC111 views1 reactionsread 29 August 2026 ሩሲያ ወደ ውጭ የምትልከው ነዳጅ እስከ መስከረም መጨረሻ ታግዶ እንዲቆይ ወሰነች
ሩሲያ የአገር ውስጥ የነዳጅ ገበያን ለማረጋጋት በሚል ወደ ውጭ በምትልከው ነዳጅ ላይ የጣለችው እገዳ እ.አ.አ መስከረም 30 ቀን 2026 ድረስ ማራዘሟን ዛሬ ቅዳሜ ይፋ አደረገች።
የአውሮፓን ህብረት ፕሬዝዳንት በቅርቡ ከሩሲያ የሚገባው ነዳጅ መቅረቱ፣ አህጉሩን ከባድ ዋጋ እያስከፈለው መሆኑን ተናግረው ነበር።
የሩሲያ መንግሥት ይህንን አስመልክቶ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፤ የእገዳ ውሳኔው ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚውለው ዲዝል በተጨማሪ የማሪን ነዳጅ እና የጋዝ ምርቶችን በሙሉ ያካትታል።
ውሳኔውን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያም “እርምጃው የተወሰደው የአገር ውስጥ የነዳጅ ገበያ…
👍1
29 Aug 2026, 15:53 UTC138 views4 reactionsread 29 August 2026 Photo
ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌፕሌይ የዲጂታል ጨዋታ አሸናፊዎች የመኪና ሽልማት አበረከተ
ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌፕሌይ የዲጂታል ጨዋታ አሸናፊዎች ሽልማት የተዘጋጁ ሦስት የቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብር አከናውኗል ።
የቴሌፕሌይ የዲጂታል ዕድል ጨዋታ ከነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተካሄደው የቴሌፕሌይ የሽልማት መርሐ ግብር፣ ዛሬ ዕጣ የወጣባቸውን ሦስት የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽልማት ሳይጨምር እስካሁን ከ32.6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሽልማቶች ለባለእድለኞች መበርከታቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
ይህም የዲጂታል ተደራሽነትን ለማሳደግና የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ …
👍2❤1👏1
29 Aug 2026, 15:07 UTC174 views7 reactionsread 29 August 2026 Photo
የ 46 አመቱ የአንበሳ ባንክ ጥበቃ የ 12 ክፍል ፈተና ማለፊያ ዉጤት አመጡ
👉🏼ባንኩ በዉጤቱ ተደስቶ የተለያዩ ስጦታዎችንም አበርክቶላቸዋል
የአንበሳ ባንክ የጥበቃ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ሰይፈ ተስፋዬ ካሕሳይ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ነጥብ ማግኘታቸዉን ዳጉ ጆርናል ከባንኩ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።
በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ሰለዋ ወረዳ ደላ ከተማ በሚገኘው የአንበሳ ባንክ ቅርንጫፍ ላለፉት ሰባት አመታት በጥበቃ ስራ እየሰሩ የሚገኙ አቶ ሰይፈ በ46 አመታቸው የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቅያ ፈተና ተፈትነው 320.25 ነጥብ በማምጣት ወደ ዩንቨርስቲ ማለፋቸውን ባንኩ ማሳወቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
በዚህም የባንኩ የዳይሬክቶሮች ቦርድ…
👍3❤1👀1👏1💔1
29 Aug 2026, 13:59 UTC203 views4 reactionsread 29 August 2026 Photo
የአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች ክምችት በአሳሳቢ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ‹‹ዎል ስትሪት ጆርናል›› የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘገበ።
በመካከለኛው ምስራቅ ከኢራን ጋር ያለው ግጭት በአውሮፓ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች ክምችት ክፉኛ እየጎዳው መሆኑ ተገልጿል።
በተለይም የ‹ፓክ-3 ፓትሪዮት› ሚሳኤል መከላከያዎች እና የረዥም ርቀት ሚሳኤሎች ክምችት ከወትሮው በበለጠ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተመላክቷል።
በዚህም ግጭት እስካሁን፦ 1 ሺህ 7 መቶ የፓትሪዮት ሚሳኤል መከላከያዎች፣ 2 መቶ የታድ መከላከያዎች፣ እና 150 የባህር ኃይል ስታንዳርድ ሚሳኤሎች አገልግሎት ላይ ውለዋል።
ይህንኑ እጥረት ለማቃለል ሲባልም፤ በርካታ የታድ ስርዓቶች እና ድሮን ተ…
❤1👍1👏1🔥1
29 Aug 2026, 12:34 UTC237 views5 reactionsread 29 August 2026 Photo
የአሜሪካው ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ሊያደርጉ ነው‼️
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አዲስ አበባ ሊያቀኑ እንደሆነ ተገለጸ።
ረዳት ሚኒስትሩ ባለፈው ግንቦት ወር ኃላፊነቱን ከተረከቡ ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የአሁኑ የመጀመሪያቸው ሲሆን፣ ጉብኝቱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጥረት እያደረገች ባለችበት ወቅት የተመቻቸ ነው።
ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኤክስ (X) ገጹ ላይ ባወጣው መ…
👍3❤1👏1
29 Aug 2026, 12:11 UTC229 views6 reactionsread 29 August 2026 Photo
አጋቾችንና ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️
በደብረ ብርሃን ከተማ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የፀጥታ መዋቅር ህገወጥ ተግባራትን በመከታተል አጋቾችንና ዘራፊዎችን ከነ ማስረጃዎቻቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገለጸ።
ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት አንድ ልጅ በማገት 5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን፣ ከልጅ ቤተሰብ ጋር በመደራደር 3 ሚሊዮን ብር መቀበላቸው ታውቋል።
የክፍለ ከተማው የፀጥታ መዋቅር በወቅቱ የተገኘውን መረጃ ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ መረጃ በማሰባሰብና ክትትል በማድረግ ቆይቶ፣ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ማስረጃዎቻቸው በቁጥጥር ስር አውሏል።
በእርምጃውም በርካታ የጦር መሳሪያዎች፣ የሞባይል ስልኮች፣የተለያዩ የባንክ አካውንት ደብተሮችና የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥሬ ገንዘ…
👍3❤2👀1
29 Aug 2026, 11:49 UTC215 views6 reactionsread 29 August 2026 Photo
በትምህርት ዘርፋ ተፅእኖን አሳድረዋል በተባሉ ርእሰ መምህራኖች ላይ እርምጃ ተወሰደ
የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ የተማሪዎችን ዉጤት ለማሻሻል እና የማለፍ ምጣኔን ለማሳደግ ለዘርፉ ማናቆ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥናት አድርጎ የመፍትሄ እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል ።
መምሪያዉ ባደረገዉ ጥናት መሠረት የመምህራን የአቅም ማነስ ፣የተነሳሽነት ችግር ፣የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ድክመት እና ሙሉ ጊዜን በትምህርት ቤት አለማዋል ለምሳሌም በግብርና ፣ንግድና ሌሎች ተጨማሪ ሰራዎች ላይ ማዋላቸዉ ለዘርፉ ችግር ሆኖ መቆየቱን የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹክራላ አወል ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል ።
በዚህም የተነሳ ለትምህርት መስጠት …
❤3👍1🔥1🤨1
29 Aug 2026, 11:39 UTC207 views5 reactionsread 29 August 2026 Photo
"እግዚአብሔር ይመስገን አለሁ" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ
ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከመገናኛ ብዙኃን ራቅ ማለታቸውን ተከትሎ የተለያዩ የሐሰት ዜናዎች ሲሰራጭ ሰንብቷል። በዛሬው እለት ብልጽግና ፓርቲ በይፋዊ የቲክቶክ ገጹ ለሰሞንኛው አጀንዳ መልስ የሚመስል ቪዲዮ ለቋል። በቪዲው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ! "አለሁ እግዚአብሔር ይመስገን" በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል።(አንድ አፍታ )
ነሀሴ 23 2018 ቅዳሜ
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችን
SHERE JOINT 👇👇👌
https://t.me/tekusemerega
https://t.me/tekusemerega
❤2👎1👏1💔1
29 Aug 2026, 11:31 UTC208 views3 reactionsread 29 August 2026 Photo
መቀሌ‼
የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ሰላምን በመናፈቅና የጦርነት ስጋት የፈጠረባቸውን ከባድ ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ገልጸዋል።የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለፁት:-
📌 ህዝቡ ከቀደመው ጦርነት ጥሎበት ያለፈው ቁስል ሳይሽር፣ ዳግም የጦርነት ስጋትና የድሮን ጥቃት ድባብ በመደቀኑ በከፍተኛ ስጋት፣ ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ ይገኛል።
📌 የወንጀል መጨመር የደህንነት ዋስትናን ጥያቄ ውስጥ የከተተው ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ከተማዋን ለቀው በመውጣታቸው የከተማዋ የተነቃቃ ድባብ ረግቧል።
📌 በነዳጅ እጥረት ምክንያት የሸቀጦች ዋጋ ከ30 እስከ 40 በመቶ ጨምሯል (ምሳሌ፦ የምግብ ዘይት እስከ 2500 ብር ደርሷል)።
📌 ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ዝውውር በመገደባቸው (በ…
❤1👍1💔1
29 Aug 2026, 11:30 UTC213 views5 reactionsread 29 August 2026 Photo
ተሸንፎም ድርጅቶች ለማስታወቂያ በሩን በሰልፍ እያንኳኩለት ያለው ሴዶ ማርሻል::
በቅርቡ በተደረገው የኤምኤምኤ (MMA) ፍልሚያ በመጀመሪያው ዙር በጆኒ የተሸነፈው ሴዶ ማርሻል፣ ከተሸነፈ በኋላ ያየው ነገር ግን ከድል በላይ የሆነ ድንቅ እድል ሆኖለታል!
ብዙ ጊዜ በተዋጊዎች ዓለም ውድድር መሸነፍ ከስፖንሰሮችና ማስታወቂያዎች መራቅን እያመጣ፣
በሴዶ ላይ ግን የሆነው ተአምር ነው! ሴዶ በተሸነፈ ማግስት ብቻ ከ4 በላይ ትልልቅ ማስታወቂያዎችን የሰራ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ድርጅቶች ማስታወቂያቸውን በእሱ ለማስራት በረጅም ተራ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተሰምቷል!
"መሸነፍ የውድቀት መጨረሻ ሳይሆን ለአዲስ መንገድ በር ከፋች ነው" የሚሉትን ወገኖች እውነት …
👍2❤1💔1🤔1
29 Aug 2026, 06:36 UTC261 views8 reactionsread 29 August 2026 Photo
32 ኤርትራውያንና 3 የሰዎች አዘዋዋሪዎች በአርባምንጭ ተያዙ።
በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 32 የኤርትራ ዜጎች ሁለት ተቀባይና አንድ አሽከርካሪ ከነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
ኤርትራዊያኑ መነሻቸውን ከመሃል ሀገር በማድረግ በአርባምንጭ ኮንሶ ጂንካ በኩል ወደ ኬንያ ለመሸጋገር ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የገለጹት ኮማንደር ክበበው፣ ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማና በፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅታዊ ክትትል በሲቀላ ክ/ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ሲያትል አልጋ ቤት ግራውንድ ስር ባለ አዳራሽ ፍራሾችን በመጣል ከተሸሸጉበት መያዛቸውን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ 11 ወንዶች፣ 1…
❤4👍2💔1🤔1
29 Aug 2026, 06:05 UTC259 views7 reactionsread 29 August 2026 Photo
በንግድ እና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራቹ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተጠንቀቁ ።
በ3 የሻይ ሲኒ ደረሰኝ ምክንያት 300 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።
በአዲሱ የታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ደረሰኝ አለመስጠት ንብረትዎን ሊያሳጣዎት ይችላል!
አንድ ሰራተኛዎ ቸልተኛ ሆና 100 ብር ለሚያወጣ 'ሻይ' ደረሰኝ ባትቆርጥ... ቅጣቱ 100 ብር ሳይሆን 100 ሺህ ብር ነው ተብሏል።
ይባስ ብሎ ደግሞ... ሰራተኛዋ ለ3 ደንበኞች ደረሰኝ ካልሰጠች፣ ለድርጅቱ ባለቤት የ300 ሺህ ብር መብረቅ የመሰለ ቅጣት ይወርድበታል።
ይህ ቅጣት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 125 ንኡስ ቁጥር 2 መሰረት በባለስልጣኑ ሊነሳ ወይም 'ይቅር' ሊባል አይችልም!
መፍትሄው መክፈል ብቻ ነው…
❤4👍1💔1🤔1
Showing the 12 most recent of 12 posts we hold for @tekusemerega. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.