10 Aug 2026, 16:11 UTC≈1,530 views25 reactionsread 20 August 2026 File
( የፍልሰታ መዝሙር )
ወፌ ሰንብታ መጣች በፍልሰታ
የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ዘሰንበት ት/ቤት ቤተሰቦች እንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሠን አደረሳችሁ !!
ከእመቤታችን ዕርገትና ትንሣኤ በረከት እንዲያሳትፈን ፤ የእመቤታችንን ጣዕሟን በአንደበታችን ፍቅሯን በልባችን ያሳድርብን።
ፆማችን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጽድቅና የበረከት ፆም ያድርግልን።
የኪጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
❤23🔥2
Signed BHS 👨⚕️
7 Aug 2026, 13:29 UTC≈2,420 views35 reactionsread 20 August 2026 Photo
ትመስሊ ፊደለ ወትወልዲ ወንጌለ ወታገምሪ መስቀለ : (ፊደልን ትመስያለሽ ወንጌልን ትወልጃለሽ መስቀልን ትወስኛለሽ (ትችያለሽ))
ትመስሊ ሰማየ ወትወልዲ ፀሐየ ወታገምሪ አዶናየ : (ሰማይን ትመስያለሽ ፀሐይን ትወልጃለሽ አዶናይን ትወስኛለሽ (ትችያለሽ))
ትመስሊ መሶበ ወትወልዲ ኮከበ ወታፀግቢ ርኁበ : (መሶብን ትመስያለሽ ኮኮባዊ ኅብስትን ትወልጃለሽ ረኃብተኛን ታጠግቢያለሽ)
ትመስሊ መቅደሰ ወትወልዲ ንጉሠ ወታገምሪ መንፈሰ ቅዱስ : (መቅደስን ትመስያለሽ ንጉሥን ትወልጃለሽ መንፈስ ቅዱስንም ትችያለሽ)
ትመስሊ ጽላተ ወትወልዲ ታቦተ ወታገምሪ መለኮተ : (ጽላትን ትመስያለሽ ታቦትን ትወልጃለሽ መለኮትን ትሸከሚያለሽ)
ትመስሊ ደመና ወትወልዲ ኅብስተ መና ወ…
❤26🙏8👍1
Signed BHS 👨⚕️
4 Aug 2026, 05:33 UTC≈3,010 views47 reactionsread 20 August 2026 ++ በሠርጋቸው ዕለት ባል ሚስቱን ምን አላት ?
በሰርጋቸው ዕለት ባል ለሚስቱ እንዲህ አላት፥ የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ። በእኔ እና ባንቺ መሃል ከእንግዲህ ምንም ዓይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም።
የኔ ውድ... በፊት እኔ ትልቅ ልጅ ነበርኩ፣ አሁን ግን በድጋሜ ህፃን እሆናለሁ። ትዝ ይለኛል ህፃን እያለሁ ምግብ በልቼ እንደሆነ ወይም እርቦኝ እንደሆነ የምታውቀኝ እናቴ ነበረች። ጥዋት ከእንቅልፍ የምትቀሰቅሰኝ እናቴ ነበረች። ከቤት ከመውጣቴ በፊት መስተካከል ያለበትን ነገሮች አስተካክላ የምትሸኘኝ እናቴ ነበረች፣ ከእንግዲህ ግን እናቴ አንቺ ነሽ። ከእንግዲህ የኔን ደካማ ጎን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም። ከእንግዲህ ጥማቴን…
❤42👏3🙏2
Signed BHS 👨⚕️
3 Jul 2026, 16:09 UTC≈5,100 views62 reactionsread 20 August 2026 ++ ኪነጥበብ - መነባንብ !!
(ርዕስ - ግቢ-ጉባኤ ትዝ አለኝ)
የፍረሽ ቅበላው ትምህርት መጀመሪያው፡
የከረመው ግቢ አየሩን ስንቀስመው፡
ዌል ካም ሩጫው መልካም ግርግሩ፡
የልዩ ጉባኤው እሑድ መርሃ ግብሩ፡
. . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . .
ነጭ ነጭ ለብሶ ማስታወሻ ይዞ ለጉባኤ መብረር፡
ቀኖናና ዶግማ ሥርዓት ለመማር፡
ደግሞ ተመልሰን ጭምጨማው ችከላው፡
አቤት ተማሪነት ስንቱን አሳለፍነው።
. . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . .
የበዓል ዋዜማው ማኅሌት ቅዳሴው፡
በተማሪ ድባብ ተመስጠን ስንቆመው፡
መዝሙር ምስጋናውን በኅብረት ስናወርድ፡
የበዓል ድግሱን የፍቅሩን ማዕድ፡
ስንጎራረሰው ሁላችን አንድ በአንድ፡
. .…
❤47🥰6🙏6👍3
Signed BHS 👨⚕️
10 May 2026, 08:36 UTC≈6,680 views43 reactionsread 20 August 2026 Photo
እናት ፥ እናትነት 🤱🤰❤
ከስሞች ሁሉ ምርጥ ስም ከሰው ልጅ ከናፍራት ከወጡ ውብ ቃላት አንዱ “እናት” ነው። የጥሪዎች ሁሉ ምርጡ ጥሪም “እማ” የሚለው ቃል በፍቅርና ተስፍ የተሞላ ነው፤ እርሷም የምትጣፍጥ ቃል ከሰው ልጅ ጥልቅ ልብ የወጣች ናት። እናት ሁሉ ነገር ናት፤ በችግር ሰዓት አማካሪያችን ናት፣ በጭንቀት ሰአት ተስፍችን ናት፣ በድካማችን ሰዓት ጥንካሪያችን ናት፣ እሷ እኮ የፍቅር , የእዝነት፣ የርህራሄ፣ ምንጭ ናት።
እናት እንደ መሬት ሁሉን ቻይ ናት። ብትረገጥ ታግሳ ለወግ ማረግ ታበቃለች። ብትነቀፍና ብትተችም ፈገግታዋ አይከስምም። የዘሩባትን መልካም አድርጋ እንደምታበቅል እርሻ ልበ ንፁሁ እንዲሁም መልካም ፍሬ እንደምታፈራ ዛፍ አብራኳ ለምለም …
❤27🙏16
Signed BHS 👨⚕️
10 May 2026, 08:13 UTC≈5,380 views8 reactionsread 20 August 2026 በምሽቱም ቡናው እየተጠጣ ስለውሎአቸው፣ ስለአገርሰፈሩ፣ ስለነገአቸው፣ ስለልጆቻቸው ባጭሩ ስለህይወታቸው አንዱ ሌላውን እየመለሰ ሲጫወቱ ያመሻሉ። ከዛም ያቺ ብርቱ ሴት ምሽቱ እገፋ ሲሄድ ልጆጇን ታስተኛች በኋላ የውሎ ሁሉ ድካሟ ይመጣና በዠኔዲ አልያም በሳር ወይም በገለባ ፍራሽ እሱም ካለ ነው፤ የመኝታ እረፍት ይገላግላትና ጎኗን ታሳርፈዋለች።
ጃል! ይቺ የኑሮ ምስቅልቅል የውጣ ውረድ ሕይወት ፊቷን ያገረጣት፣ ያከሳት፣ ያለዘባት፤ ጥላሸቱም፣ ሊጡም፣ አፈሩም በብጫቂ ቀሚሷ የወዛባት፤ የፊትዋ ፈገግታና ብርሃን ግን ከውስጧ ለእኛ የፈካላት ዘንካታዋ የገጠሯ ብርቱ ሴት የእኔ፣ የአንተ፣ የአንቺ እና የሁላችንም ኢትዮጵያውያን እናት ነች። እናት የሁሉ መሠረት ናት። በእ…
❤8
Signed BHS 👨⚕️
10 May 2026, 08:13 UTC≈5,240 views15 reactionsread 20 August 2026 ++ እናቴ ይህቺ ናት 🤰🤱 !
ፍቅር እንደ እንጀራ ተጎዝጉዞ በሚበላበት የገጠሩ አካባቢዎች ኢትዮጵያዊ ለዛና ወዟን ጠብቃ የበቀለችው እናቴ፤ በጠዋት ማልዳ ወፍ ተንጫጭቶ ሳያበቃ ከመኝታዋ ትነሳና ፊትዋን ተታጥባ ወደምድጃዋ ታመራለች፡፡ ብዙዎቹ እርሷን መሰል አርሶአደር ሴቶች የሚያጠቡት ልጅ አያጡም፡፡ እናም ልጅዋ አግቶ ያደረ ጡትዋን ፍለጋ እየተነጫነጨ፣ እንደማልቀስም እያደረገው ከምድጃው ሳለች የውጥር ይይዛታል፡፡ ማታ አዳፍና ያሳደረችውን እሳት ከማዳፈኛው አመድ ውስጥ ገላልጣ ካወጣች በሁዋላ ከምዳጃዋ ጠፍቶ ከማይጠፋው ኩበት ሰበር አድርጋ ከፍሙ ላይ ትፈረፍርበታለች፡፡ ከፍሙ ላይ ያረፈው ስብርባሪ ኩበት መጨስ ይጀምራል፡፡ ትንሽ ጭራሮ ቢጤ ሰባብራ በሚጨሰው ኩ…
❤15
Signed BHS 👨⚕️
6 May 2026, 04:55 UTC≈5,480 views64 reactionsread 20 August 2026 ++ ዕድሜ መስታወት ነው ብዙ ያስተምራል !!
አንዲት ቆንጆ ናት 18 ዓመቷ ነው። ጎረምሶች ሲያይዋት ዓይናቸው ይመኛታል። ሴቶች በቅናት እንደ ሽንኩርት ይልጧታል። አንድ ቀን እንዲህ ስል ጠየቅኳት። "ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን መስፈርት እንዲያሟላ ትፈልጊያለሽ?" በፍጥነት መለሰችልኝ የተማረ መሆን አለበት፤ ማስተርስ ያለው ይመረጣል። ከተቻለ የግል ቢዝነስ የሚሠራ፤ ኢንቨስተር ቢሆን አሪፍ ነው። ካልሆነ ግን አሪፍ ደሞዝ ሊኖረው ግድ ነው። መኖሪያ ቤቱ G+2 ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ከG+1 በታች ግን አልፈልግም። መኪና በጣም ነው የምወደው። አሪፍ መኪኖች ቢኖሩት ደስ ይላል፥ ካልሆነም ከተጋባን በኋላ እኔ እንዲገዛ አደርገዋለሁ።
ሙድ የገባውና ጨዋታ የሚያውቅ…
❤48🥰10👍3👏3
Signed BHS 👨⚕️
11 Apr 2026, 22:34 UTC≈6,800 views31 reactionsread 20 August 2026 Photo
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ !
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ዓልፋና ኦሜጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ሊይዘው አልቻለምና የተገነዘበትን ልብስ ትቶ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ ተነሳ፤ በተወለደ ጊዜ የእናቱን መኃተመ-ድንግልና እንዳልለወጠ ሁሉ፥ በትንሳኤውም መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በብርሃን መላእክት ታጅቦ እነሆ በክብር ተነሳ።
ዛሬም እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ እኛ ህዝበ ክርስቲያኖችም “ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ” (ትንሳኤህን ለምናምንህ ለእኛ ብርሃንን ላክልን ወደ እኛ) እያልን ስለተገለጸልን ምስጢረ ትንሳኤ እንዘምር።
በመኾኑም የጌታ ትንሣኤ ለእኛ ለክር…
❤23👍5🔥3
Signed BHS 👨⚕️
10 Apr 2026, 08:26 UTC≈6,070 views12 reactionsread 20 August 2026 File
የሰሙነ ሕማማት ትረካ
ርዕስ - ሕማማተ መስቀል
ይኽ የጌታችን ሕማማት ከወንጌል አንጻር የተተረከ ትረካ ነው ። እህታችን ቃለሕይወት ያሰማልን፣ ጸጋውን ያብዛልሽ ።
የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
❤9👍3
Signed BHS 👨⚕️
5 Apr 2026, 05:37 UTC≈7,560 views20 reactionsread 20 August 2026 ++ ሥነጽሑፍ - የዐብይ ጾም ግጥሞች !
( ርዕስ - ሆሳዕና/ ስምንተኛ ሳምንት )
ሆሳዕና በአርያም -
ሆሳዕና በአርያም - - -
ሆሳዕና በአርያም - - - ሆሳዕና በአርያም
የዳዊት ልጅ መድኃኔዓለም፤
በኪሩቤል ግርማ የሚቀመጥ አልፋና ዖሜጋ
በቀስተ ደመና ላይ ዙፋኑን የዘረጋ፤
በእሳት መድረክ ላይ የሚመላለስ
በሱራፌል የሚቀደስ - - - የሚወደስ፤
ሰባት መቅረዝ በፊቱ የሚያበራ
መንጦላይትህ ብርሃን ማደሪያህ የሚያስፈራ፤
በልዩ ልዩ ቅኔ በመለከተ ድምጽ
በመብረቅና ነጎድጓድ የምትገስጽ፤
ዓይኖችህ እንደ እሳት የሚያበሩ
እግሮችህ ንጥረ ነሀስ የመሰሉ፤
የልብስህ ዘርፍ ቤተ-መቅደሱን የሞላ
የኃያላን ኃያል ባለብዙ ሺህ ሠረገላ፤
በማደሪያህ በጸባኦት ባይቻለን አንተን…
❤14🙏6
Signed BHS 👨⚕️
31 Mar 2026, 08:47 UTC≈5,880 views12 reactionsread 20 August 2026 ++ ኪነጥበብ - መንፈሳዊ የትንሳኤ ጭዉዉት !
( ርዕስ - ሃብታም እና ደሃ )
💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀ ስብሐት ለአብ ስብሃት ለወልድ ስብሃት ለመንፈስ ቅዱስ እሰይ አምላኬ ምን ይሳንሃል ለአንተ የአብይ ፆምን በሰላም በፍቅር አሳልፈህ ለብርሃነ ትንሳኤ ያደረስከን እንዉ በትንሳኤዉም በፆም ከበደሉ ከተበዳደሉም ይቅር ለእግዚአብሔር ተባባሉ ይላል እግዚአብሔር አይ የእኔ ጉድ እንደዉ ከጎረቤቶቼ ጋር ሳልስማማ አሁን እሔዳለሁ ምንም ይበሉኝ ልጆች ተኝተዋል እንዴ ቅድስቴ ቅድስት
💐 *ትግስት*👧🏽እማዬ ሰላም አደርሽ እንዴ ቅድስቴ እስካሁን አልተነሳችም እንዴ እኔ እኮ የሌሊት ኪዳን ጨርሼ መጣዉ
💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀እሰይ የእኔ ልጅ ጎብዘሻል እኔም አስቤ ነው …
❤11🙏1
Signed BHS 👨⚕️
Showing the 12 most recent of 22 posts we hold for @sundayschoolstudents. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.