7 Apr 2026, 21:06 UTC395 views2 reactionsread 3 September 2026 Photo
ባየርን ሙኒክ በታሪካዊው ሳንቲያጎ ቤርናቤው ሜዳ ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል። በዚህም ሪያል ማድሪድ በደጋፊዎቹ ፊት ነጥብ ጥሏል።
በሌላ በኩል፣ አርሰናል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በካራባኦ ካፕ በማንችስተር ሲቲ፣ በኤፍኤ ካፕ ደግሞ በሳውዝሃምፕተን ደርሶበት የነበረውን ሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በመቀልበስ፣ በስፖርቲንግ ሊዝበን ላይ አንድ ለባዶ ድልን ተቀዳጅቶ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። ይህ ድል ለአርሰናል ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥርለት ጥርጥር የለውም።
❤2
7 Apr 2026, 18:31 UTC359 views4 reactionsread 3 September 2026 Photo
የዛሬው ምሽት በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አስደሳች ፍልሚያዎች ይስተናገዱበታል!
ታላቁ ባየርን ሙኒክ በሜዳው አሊያንዝ አሬና ሪያል ማድሪድን ይቀበላል። በሌላ በኩል፥
አርሰናል ወደ ሊዝበን ተጉዞ ስፖርቲንግን ይገጥማል። እነዚህ ሁለት ታላላቅ ጨዋታዎች ምሽት አራት ሰዓት ይጀምራሉ። የእርስዎ ግምት ምንድን ነው? አሸናፊዎቹ እነ ማን ይሆናሉ? የሁለቱንም ጨዋታ ውጤት በኮሜንት ላይ ይተንብዩልን!
ስማርት ቤት!
❤4
3 Apr 2026, 10:39 UTC329 views2 reactionsread 3 September 2026 Photo
የአርሰናል የትንሳኤ ጉዞ፦
"ከአሁን በኋላ እያንዳንዱ ጨዋታ ለእኛ እንደ ፍጻሜ ነው" — ሚኬል አርቴታ 🔥
የመድፈኞቹ አለቃ ሚኬል አርቴታ ከዓለም አቀፍ የጨዋታ እረፍት በኋላ የሚጠብቃቸውን ወሳኝ ግጥሚያዎች አስመልክቶ ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፏል። አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት በሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትግል ላይ አሰልጣኙ የሚከተለውን ብለዋል፦
"ከዚህ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እረፍት መልስ፣ ለእኛ እያንዳንዱ ጨዋታ የፍጻሜ ያህል ዋጋ አለው።" ⚔️
አርቴታ አክለውም ቡድኑ ለሚጠብቀው ፈተና ዝግጁ መሆኑን ሲገልጹ፦
"በጣም ተከታትለናል፤ ወደ ውድድሩ ለመመለስም ጓጉተናል። እነዚህ ጨዋታዎች 'የመኖር ወይም የመሞት' ያህል ወሳኝ ፍልሚ…
❤2
30 Mar 2026, 10:33 UTC307 views1 reactionsread 3 September 2026 Photo
የተጫዋቾቹ እረፍት ወይስ የአርሰናል ብልጥነት?
አርሰናል ተጫዋቾቹ በኢንተርናሽናል ብሬክ ከብሔራዊ ቡድን ጥሪ ውጪ እንዲሆኑ እያደረገ ያለው ነገር እንደገና መነጋገሪያ ሆኗል። ይህን በማድረግ፥ ክለቡ ተጫዋቾቹን ከጉዳት ለመከላከልና ለቀጣይ ጨዋታዎች ለማዘጋጀት እየሞከረ ነው ይባላል። በአንዳንድ ወገኖች ደግሞ፥ ይህ ድርጊት የብልጥነት አካል እንደሆነና ተቀባይነት እንደሌለው ይነገራል። እናንተስ ምን ትላላችሁ? የአርሰናል ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ የተጋነነ? አስተያየታችሁን በኮሜንት ላይ አካፍሉን።
❤1
26 Mar 2026, 07:45 UTC315 views1 reactionsread 3 September 2026 Photo
የዛሬ የእግር ኳስ ውሎ
በአለም ዋንጫ ማጣሪያ
ዩክሬን ከስዊድን
ዴንማርክ መቄዶንያ
ፖላንድ ከአልባኒያ
ቼክ ሪፐብሊክ ከአየርላንድ ጋር ይጫወታሉ።
በኔሽንስ ሊግ
ጊብራልታር ከላትቪያ
ማልታ ከሉክሰምበርግ ሲገናኙ፥ በወዳጅነት ጨዋታ ደግሞ ሃያላኑ ብራዚሎች ከፈረንሳይ ጋር ፍልሚያቸውን ያደርጋሉ።
❤1
22 Mar 2026, 06:40 UTC316 views2 reactionsread 3 September 2026 Photo
የካራባኦ ካፕ የዋንጫ ፍጻሜ🔥
ዌምብሌይ ስታዲየም
አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ
የ2026 የካራባኦ ካፕ ፍጻሜ ዛሬ በአርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲ መካከል በታላቁ ዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል። ጨዋታው በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1፡30 ላይ የሚጀምር ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ቡድኖች ለዚህ ዋንጫ ፍጻሜ ተገናኝተዋል።
ምንም እንኳን በሁለቱም ወገኖች ቁልፍ ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት የመሰለፍ ጥርጣሬ ቢኖርባቸውም ይህ ግጥሚያ በ2025/26 የእንግሊዝ እግር ኳስ የውድድር ዘመን ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው እንደሚሆን ይጠበቃል።
ስማርት ቤት!
🔥2
5 Mar 2026, 08:51 UTC354 views2 reactionsread 3 September 2026 Photo
አርሰናል ሲያሸንፍ ማንችስተር ሲቲ አቻ ተለያየ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት አርሰናል ብራይተንን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ በአርሰናል መለያ 300ኛ ጨዋታውን ያረገው ቡካዮ ሳካ የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል፡፡
አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አርሰናል 3ኛ ተከታታይ ጨዋታውን ያሸነፈው አርሰናል ወደ ዋንጫው የሚያደርገውን ግስጋሴ አሳምሯል፡፡
በሌላ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከኖቲንግሀም ፎረስት ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡ ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት የሚያጠብበትን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
በኢትሀድ በተደረገው ጨዋታ አንቶኒዮ ሴሜኒዮ እና ሮድሪ የማንችስተር ሲቲን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ሞ…
❤2
4 Mar 2026, 14:08 UTC267 views3 reactionsread 3 September 2026 Photo
የዛሬ ምሽት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች
ዛሬ የሚደረጉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታ በቪላ ፓርክ በ አስቶን ቪላ እና ቼልሲ መካከል የሚደረገው የአራት ውስጥ የመግባት ፉክክር ሲሆን፣ የሊጉ መሪ አርሰናል ደግሞ ከባድ ፈተና ወደሚጠብቀው ብራይተን ሜዳ ያመራል።
ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኖቲንግሃም ፎረስትን በማስተናገድ የአርሰናልን መሪነት ለመቀማት ጥረት ያደርጋል፤ በሌላ በኩል በለንደን ደርቢ ፉልሃም ከ ዌስትሃም ይፋጠጣሉ።
የምሽቱ መዝጊያ ጨዋታ በሴንት ጄምስ ፓርክ ኒውካስል ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ሲሆን፣ ዩናይትዶች ያለመሸነፍ ጉዟቸዉን ለማስ…
❤3
2 Mar 2026, 10:29 UTC287 views6 reactionsread 3 September 2026 Photo
ዓድዋ የጥቁር ሕዝብ ድል!
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ስማርት ቤት!
🔥6
1 Mar 2026, 08:21 UTC293 views5 reactionsread 3 September 2026 Photo
የኤምሬትስ ታላቅ ፍልሚያ 🔥🔥
🔴 አርሰናል vs ቼልሲ 🔵
የዋንጫ ጉዞ እና የለንደን ደርቢ
የዛሬው የኤምሬትስ ስታዲየም ጨዋታ የፕሪሚየር ሊጉን የዋንጫ ጉዞ የሚወሰን ታላቅ ፍልሚያ ነው። አርሰናል በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ሆኖ ጨዋታውን የሚጀምር ሲሆን፣ በቼልሲ ላይ ካለው የ10 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ታሪክ እና በቅርቡ በካራባኦ ካፕ ካገኘው ድል በመነሳት ከፍተኛ መነሳሳት ላይ ይገኛል።
መድፈኞቹ የ5 ነጥብ ልዩነታቸውን ለማስጠበቅ ሲጫወቱ፣ በሊያም ሮሲኒየር የሚመራው ሰማያዊዎቹ የአርሰናልን የ10 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ለመግታትና በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ያለውን ፉክክር ለማጥበብ ከፍተኛ ዝግጅት አድርገዋል። በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው ጠ…
🔥5
26 Feb 2026, 10:28 UTC318 views6 reactionsread 3 September 2026 Photo
🔵 UCL 2026 የ16ቱ ዕጣ ነገ ይወጣል !
ነገ አርብ የካቲት 20 ከቀኑ 8:00 ሰዓትጀምሮ በስዊዘርላንድ ኒዮን የሚወጣው የሻምፒዮንስ ሊግ ዕጣ እጅግ ተጠባቂ ነው።
በዚህ መርሃ-ግብር የ16ቱ ዙር ብቻ ሳይሆን እስከ ፍፃሜውየሚደረጉ የሩብ እና የግማሽ ፍፃሜ መንገዶችም ጭምር ይለያሉ።በአዲሱ የውድድር ቅርፅ መሰረት ከአንድ ሀገር የወጡ ክለቦች እርስ በእርስ ሊገናኙ ስለሚችሉ እንደ አርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲ ያሉ ታላላቅ ፍልሚያዎችን ልንመለከት የምንችልበት ዕድል ሰፊ ነው።
ሙሉ የዕጣ ማውጣት ሂደቱን በ UEFA.com የቀጥታ ስርጭት መከታተል ይቻላል።
ስማርት ቤት!
🔥5❤1
25 Feb 2026, 12:43 UTC283 views3 reactionsread 3 September 2026 Photo
ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች
02:45 | ጁቬንቱስ ከ ጋላታሰራይ
05:00 | ሪያል ማድሪድ ከ ቤኔፊካ
05:00 | አትላንታ ከ ዶርትሙንድ
05:00 | ፒኤስጂ ከ ሞናኮ
ስማርት ቤትን ይቀላቀሉ👇🏽
Telegram
Facebook
Tik Tok
Instagram
👍3
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @smartbett_et. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.