21 Jun 2026, 04:52 UTC299 views13 reactionsread 6 August 2026 🔴መኖር ጣፍጦ አሁንም መኖርን የሚያስመኝ ብቸኛ ነገር ቢኖር ለእግዚአብሔር መኖር ነው።
የዚህ ምድር ሩጫ ጉልበቱን ያላዛለበት ያለ አይመስለኝም፣የነገሮች መውጣት መውረድ ልቡን ያላወረደበት የለም ።
የተመኘዉን ሊያሳካ ጥሮ ግሮ ግን ሲደርስበት የቀለለበት ማነው? በጠበቀው ልክ በነገሩ ከመደሰት ይልቅ አሁንም ሌላ የተመኘ ማነው? በቃ ይኸው ነው። ለክርስቲያኖች የመኖር ትርጉሙ ኢየሱስን ማሳየት እንጂ የተመኙትን አድርጎ ማለፍ ስላልሆነ ነው ።
🔴ምንም ላይ ብንደርስ በደረስንበት በዛ ነገር እግዚአብሔር የልቡን ፈቃድ እንዲገልጥበት ካልተመቸው ከስረናል።
ሞተን ነፍሳችን አምላኳ ጋር ብትሔድ ደስ አይልም? አስባችሁታል በዘላለም ደስታ ስትኖር 🥰የተሻለው እዛ መሆ…
❤11👍1🔥1
Signed Elsa
1 Jun 2026, 14:13 UTC502 views16 reactionsread 6 August 2026 🔴ምንም ነገር ሊቀር ይችላል ፤ምንም ነገር ሊደክመን ይችላል፤..........ግን በየትኛውም የህይወት መንገድ ውስጥ ሆነን ኢየሱስን መፈለግ የህልውናችን ጉዳይ ነው።(
እሱን መፈለግ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ስለሆነ (ያለእርሱ የማይሞላ ክፍተት ስላለን)
እሱን መፈለግ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን የመሰንበቻ(የዘለአለም) ስለሆነ
እሱን መፈለግ አማራጭ ሳይሆን ለመኖር ግድ ስለሆነ
እሱን መፈለግ ለስጋ ብቻ ሳይሆን የነፍስ ጉዳይ ስለሆነ
ኢየሱስን እንፈልገው🥺
🔴እሱ ደጁን ስለማይዘጋ፣ ደጋግመን እየበደልነውም ደጋግሞ ይቅር እያለ ደጋግሞ የሚያድስ ደግ አባት ስለሆነ።
ዛሬም በምህረቱ ተማምነን አባ ብለን እንድንጮህ፣ ልጄ ብሎ በፍቅር እጁ ሊሸከመን፣ሊያባብለን የ…
❤15🔥1
Signed Elsa Anbes
30 Apr 2026, 13:41 UTC695 views8 reactionsread 6 August 2026 Photo
እንዴት ደስ ይላል በብዙ መንገድ ተፈትነን በምናልፍበት ጊቢ ፤ጥቂቱ ፀጋ በዝቶለት ከጌታው ተጣብቆ ፣ጥቂቱ አለም አሸንፎት ተሰባብሮ ፣ አንዳንዱ ደግሞ ለብ ብሎ ይቀራል። Mintesnot Gizachew ደግሞ ከጊቢ ቆይታው መፅሀፍን አበርክቶልን እያለፈ ነው😊🤗 የምር ነው ደስ ያለኝ እንኳንም ጌታ ረዳህ🙏
በብዙ ውጣ ውረድ እያለፈ #እንዲህ ያለ ፍሬ ለህዝብ ማድረስ የሚችል ትውልድን ማየት የምር ደስ ይላል ።
ውድ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በወንድማችን ምንተስኖት ግዛቸው የተጻፈው "የታረሙ ገጾች" 🎉መጽሐፍ ምረቃ ደረሰ🎉!!
መጽሐፉም:-
🗓ሚያዝያ 23 እና 24
📍በአምቢቾ MKC
ከተወደዱ ተጋባዥ አገልጋዮች እና ከተለያዩ ከተሞች ከተጋበዙ የክብር…
❤8
Signed Elsa
17 Apr 2026, 14:32 UTC841 views17 reactionsread 6 August 2026 ስሜታችሁን በተመረጠ የቃላት ፍሰት ገልፆ ለጆሮ በሚመች ቅላፄ ሲያዜመው የልባችሁ ደረሰ??
ነገር ግን ለተሰማችሁ ለዛ የውስጥ ስሜት የማልቀሻ ሰበብ ቢሆን እንጂ፣ የህመማችሁን ስሜት የመፈወስ አቅም በጭራሽ የለውም።
ክርስቲያን ተብዬዎቹ እናንተ የመመለስ ልብ ይስጣቹ 😔
ስሜትን ኮርኩሮ ፣ለምድራዊው አላፊ ነገር በዜማ ሙሾ እንድታወርዱ፣ እያንጎራጎራቹ ለችግሮቻችሁ እዬዬ እንድትሉ ከሚያደርግ ግን መፍትሄውን ከማያሳይ(መፍትሄ ስለሌለው)፣ ከዛ የጩኸት ሰፈር ብትሸሹ ይሻላችኋል ወገኖቼ።
ለምን ችግራችንን የሚያንቆላጳጵሰውን እየተከተልን የችግራችንን መፍትሄ ግን ጆሮ ዳባ እንላለን።
የተሰበረ ልብ ጠጋኝ ኢየሱስ ነው ፣ የውስጥን ህመም ተረድቶ ሊያስለቅስ ሳይሆን …
❤12🥰3👍2
Signed Elsa
31 Jan 2026, 17:43 UTC≈1,410 views24 reactionsread 6 August 2026 ⚠️"መባልን ሳይሆን መሆንን ፍሩ" እያሉ መክረው ዘክረው ሲያሳድጉን ከስርአት ያፈነገጡ ድርጊቶች ከማድረግ እንድንቆጠብ ነበር።
በእግዚአብሔር ፊት ያልተወደደውን አካሄድ አድርገን ራሳችንን ከምናጣ በውሸት "እንዲህና እንዲያ " ናቸው ተብለን ስማችንን ብናጣ ከህይወት እንደማንጎድል ስለገባቸው ነበር።
📌አሁን የኛ ፍርሀት ምንድነው "ሰው ምን ይለኛል? " ወይስ "ሁሉን የሚያየው እግዚአብሔር ምን ይለኛል?"
ልባችን ቀን በቀን የሚመኘው "እንዴት አድርጌ አምላኬን ደስ ላሰኘው?" ነው ወይስ "እንዴት አድርጌ ደስታዬን ልፍጠር?"
ለራሳችን ያመቻቸን መስሎን ራሳችንን ከህይወት መንገድ እያጎደልን ይሆን?
መልካም ስም ከመልካም ምግባር ይመጣል ። ለመልካም ምግባር …
❤18🥰4👍1🔥1
Signed Elsa
26 Jan 2026, 18:46 UTC≈1,250 views20 reactionsread 6 August 2026 እግዚአብሔር አይቀደምም ። ነገሩ ግራ ገብቶን "ለምን" ብለን የምንጠይቃቸው አንዳንድ ሁነቶች ህይወታችን ላይ ሲከሰቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ቢሆንስ ብለን ብናስብ መልካም ነው።
የያዘን ጌታ በየት በኩል እንደሚቀርፀን አናውቅም። ወይም የምናውቀው እሱ ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ወደኋላ አይተን ነው።
ግን ማወቅ ያለብን ነገር በእግዚአብሔር እጅ ላይ እንሁን እንጂ ፣ ብቻ ለርሱ እንገዛ እንጂ፣ ብቻ በፅናት እንቁም እንጂ ከኛ ሀሳብ እጅግ ወደተሻው ያደርሰናል።
እኛ መጥፊያ በመሰለን አስቸጋሪ መንገድ ላይ እርሱ መሻገሪያ ድልድይ ሆኖ ፍፃሜአችንን ያስውበዋል።
"ከዚህኛው ችግር ምን ልታስተምረኝ ነው?" ብለን ብናስተውል እናተርፋለን። ለምን ብለን ከማጉረምረም እሺ …
❤17🙏3
Signed Elsa
22 Jan 2026, 16:31 UTC≈1,250 views18 reactionsread 6 August 2026 ጥሩ አልነበረም ብለን የምንቆጭበት ጊዜ ካለ ከእግዚአብሔር ጋር ሳንሆን ያሳለፍነው መንገድ ሊሆን ይችላል።
እሱ ባለበት ግን አሳዛኝ ነገር ቢከሰት እንኳን ለበጎ እንዲደረግ አውቀን በመንፈሱ ማፅናናት ታክመን እናልፋለን እንጂ አንፀፀትበትም።
ያጠወለገን እግዚአብሔርን አለመስማት ነው፤አዎ ብዙ ምክንያት ልንደረድር እንችላለን ግን ለሁሉም መፍትሔው እሱ ነበር እሱን በማወቅ አድገን ቢሆን በሁሉም ነገር እየመራን እየተከተልነው አድገን አሁን የሆንነውን ባልሆንን ነበር።
የሚያስፈልገን እግዚአብሔር ነው ።
ከባድ ናቸው ከምንላቸው ያለፉት ጊዚያቶች የተሻለ ቀላል ቀን አይመጣም ይልቁን የከበደ እንጂ ነገር ግን በኢየሱስ ተሸሽገን ቀላል ነው ማለት እንችላለን።
💥እግ…
❤15👏1🔥1🙏1
Signed Elsa Anbes
20 Jan 2026, 15:35 UTC≈1,120 views15 reactionsread 6 August 2026 በራሳችን አቅም መታገል የደከመን ስንቶቻችን ነን? እስኪ ለሱ እንተውለትና እርሱ ይዋጋልን፤
ግድየለም ኢየሱስን አስቀድመን እንሞክረው ፤የርሱ ድካም ከኛ ብርታት ይሻላል፤ብቻውን ከሮጠ ከግዚአብሔር ጋር የቆመ ይሻላልና እርሱ ላይ እናተኩር🙏
@sle_hiwot @sle_hiwot
@sle_hiwot @sle_hiwot
❤9🥰3🙏3
Signed Elsa Anbes
19 Jan 2026, 10:26 UTC≈1,150 views10 reactionsread 6 August 2026 ልብ በኑሮ በሂደት ውስጥ በአንድም በሌላም ጫና ቀድሞ ከቆመበት መሰረቱ ለቆ ሊቀየር ይችላል።
ታዲያ እግዚአብሔር ረድቶት ቶሎ መፍትሔ ፍለጋ ወደ አምላኩ ተጠግቶ ያልታከመ ሰው ልቡ ይበልጥ ልክ ወዳልሆነ መንገድ እየሄደ ያ ልክ ያልሆነው መንገድ ማንነቱ ወደመሆን ያድጋል።
ለዛ ማንነቱ ጠበቃ ሊሆንለትም ይችላል ለምሳሌ:-"ከዚህና ከዚያ አንፃር ባህሪዬ እንዲህ ተለወጠ ፣ካሳለፍኳቸው ችግሮች የተነሳ እንዲህ ሆንኩ ይላል ወይም በክፉ ሰዎች ምክንያት ተቀየርኩ "ብሎ ለሰሚዎች አሳማኝ ምክንያት ሊያስቀምጥ ይችላል።
ከዛ የሰው ልጅ ቀድሞ የነበረውን መልካም ልማድና ማንነት በቀስታ እንዳጣው ይሰማዋል። እንደቀድሞው መሆንን እየናፈቀ ግን ልቡ ተቀይሮበት ይቸገራል።
…
❤9👍1
Signed Elsa Anbes
13 Jan 2026, 18:22 UTC≈1,060 views19 reactionsread 6 August 2026 ላላየነው ነገ "እንዲህና እንዲያ ቢሳካልኝ ብለን" ለዚህ ጥቂቱ የምድር ኑሮአችን እንተጋለን።
ተማሪ የሆነ ሙያ ሲማር እንቅልፉን አጥቶ ቁጭ ብሎ ያነባል(ዛሬ የሚተጋው ነገ ላይ ይጠቅመኛል በሚል ተስፋ ነው)
ሰራተኛ ስራውን በየቀኑ ይሰራል (በወሩ መጨረሻ ደሞዝ እንደሚከፈለው ተስፋ ስላለው)
ልጅ የወለደ ወላጅ ልጁን ዋጋ ከፍሎ ጠብቆና ተንከባክቦ ያሳድጋል(ሲያድግ በሁሉም መንገድ እንዲሳካለት ስለሚፈልግ)
ይሄ ሁሉ የምድራዊ ተስፋ ነፍስ ከስጋ ሲለይ የሚያከትም ነው።
ታዲያ ይሄ ሁሉ ሩጫ ሲያበቃ ዘላለሙ እንዲሳካ ዛሬ ላይ ምን እያደረግን ነው?
ለዘላለማዊ ቤቴ ብለን በየቀኑ ምን ያክል እንተጋለን የሚለው ሲታሰብ ከምድራዊው የበለጠ ፣ወይ ያነሰ፣ ወይ ጭራሽ…
❤13🔥3🥰3
Signed Elsa
10 Jan 2026, 20:04 UTC≈1,000 views26 reactionsread 6 August 2026 ብቸኝነት እንዳይሰማን ማድረግ የሚችል የሰው አይነት የለም።.........መንፈስ ቅዱስ ግን ይችላል🥰🙏
@sle_hiwot @sle_hiwot
@sle_hiwot @sle_hiwot
🥰17❤9
Signed Elsa
10 Jan 2026, 05:05 UTC≈1,450 views22 reactionsread 6 August 2026 🖌ያለመወደድ ስሜት እንዳይሰማን ነፍሱን የሰጠ ወዳጅ መጥቶልናል።......ሲደክመን ወደርሱ ሸሽተን እንደበቅ፤ ደህንነታችን ግድ ብሎት ነፍሱን የሰጠ ወዳጅ አለን። እርሱ ይጠግነናል😊
ብቸኝነት ተሰምቶን ውስጣችን ባዶ እንደሆነ ሲሰማን ከጌታ ውጪ የውስጣችን ህመም ሊገባው የሚችል የለምና መንፈስ ቅዱስ እንዲያፅናናን በድካማችንም ጌታ ሆይ ብለን እንጩህ፤
ሲከፋው ማውራት እንኳን አቅቶት በጌታ ፊት እምባ የሚቀድመው ሰው ቢኖር ጌታ የለቅሶውን ድምፅ ሰምቶ በዝምታ ውስጥ ለሚጨነቀው ነፍስ ይደርሳል፤ልቡን በሰላሙ ይሞላል፤ከከበበው ሁሉ መከራ ያድነዋል።
መጽሐፈ ኢዮብ 5:8-9 (AMH)
⁸ እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፥ ነገሬንም ወደ እግዚአብሔር አቀርብ ነበ…
❤18🙏3👍1
Signed Elsa
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @sle_hiwot. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.