3 Sept 2026, 05:50 UTC36 viewsread 5 September 2026 ተመረቀ፤ በረከትንም ተቀበለ፡፡ ይስሐቅም ሲዳስሰው የአሳውን ልብስ ለብሶ ስለነበር ያዕቆብ እንደሆነ አላወቀውም ነበር፡፡
ያዕቆብም አባቱ ከመረቀው በኋዋላ ወጥቶ ሄደ፡፡ ኤሳውም አደን ከዋለበት ተመልሶ መጣና ለአባቱ አድኖ ያመጣውን አቀረበለት፡፡ ይስሐቅም የኤሳውን ማንነት ካወቀና ያዕቆብም እንደዋሸው ዐወቀ፣ ጥንቱንም ተጠራጥሮ ነበርና በዚህም ጊዜ እጅግ ደነገጠ፡፡ ‹‹ለወንድምህ ጌታ ሁነው፣ እርሱም ይገዛልህ፤ የሚረግምህ የተረገመ ይሁን….›› ብሎ መርቆታልና፡፡
ያዕቆብም ወደ አጎቱ ላባ ዘንድ ተሰዶ 14 ዓመት ለላባ ተገዝቶ ራሄልንና ርብቃን አግብቶ ብዙ ልጆችን ወለደ፡፡ ሀብት ንብረት ካፈራ ከ21 ዓመት በኋላ ወደ አባቱ አገር ተመልሶ ለወንድሙ ብዙ ሀብት እጅ …
Signed 🅰ቢtaጎ
3 Sept 2026, 05:50 UTC51 views1 reactionsread 5 September 2026 ያሰናብተው ዘንድ ላባን ጠየቀው፡፡ ላባም ‹‹ደመወዝህን ንገረኝ›› ሲለው ያዕቆብ ‹‹ዳግመኛ በጎችህን እጠብቃለሁ፣ በጎችህም ሁሉ በፊትህ ይለፉ ከበጎችህ ጸጉራቸው ነጫጭ የሆኑትንና መልኩ ዓይነቱ ዥንጉርጉር የሆነውን ለይተህ ስጠኝ፣ ይህም ደመወዜ ይሁነኝ›› አለው፡፡ ‹‹መልኩ ነጫጭ ያልሆነውና መልኩ ዓይነቱ ዥንጉርጉር ያልሆነው ግን ላንተ ይሁን›› አለው፡፡ ለባም በዚህ ተስማቶ ‹‹እንዳልክ ይሁን›› አለው፡፡ ላባም ነጩን ዥንጉርጉሩን ሁሉ መርጦ ለልጆቹ ሰጣቸውና የሦስት ቀን መንገድ ይዘው ሄዱ፡፡ ያዕቆብም ተመርጠው የቀሩትን የላባን በጎች እየጠበቀ ሳለ እርጥብ የልምጭ በትር፣ ታላቅ የሎሚ በትር ኤርሞን የሚባሉ ሦስት በትሮችን አንሥቶ ሁለቱን ቅርፊታቸውን ልጦ አን…
❤1
Signed 🅰ቢtaጎ
3 Sept 2026, 05:50 UTC82 viewsread 5 September 2026 እርሱም ከአባቱ ከያዕቆብ ሚስቶች ከዘለፋ ልጆችና ከባላ ልጆች ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፡፡ ያዕቆብም በእርጅናው ዘመን ወልዶታልና አብልጦ ይወደው ነበር፡፡ ወንድሞቹም በዚህ ምክንያት ጠሉት፡፡ (ከዚህም በኋላ ዮሴፍ በወንድሞቹ የደረሰበትንና ወደ ግብፅም መውረዱን ያስታውሷል፡፡)
ዮሴፍ በወንድሞቹ ግፍ ደርሶበት ወደ ግብፅ ተሸጦ ከሄደ በኋላ እዚያም ብዙ ፈተና አሳለፈ፡፡ ነገር ግን እግዚአሔር ሞገስ ሆኖት በግብፅ ተሾመ፡፡ የሸጡት ወንድሞቹም በረሀብ ምክንያት ስንዴ ሊለምኑ ወደ ግብፅ ሲወርዱ ዮሴፍን በስልጣን ሆኖ አገኙት፡፡ እርሱም ራሱን ገለጠላቸው፡፡ ያደረጉበትንም ነገራቸው፡፡ የርኃቡም ዘመን ገና 5 ዓመት ይቀረው ነበርና ዮሴፍ ወንድሞቹን ‹‹ስለሸጣችሁኝ…
Signed 🅰ቢtaጎ
3 Sept 2026, 05:50 UTC92 views1 reactionsread 5 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤1
Signed 🅰ቢtaጎ
3 Sept 2026, 05:50 UTC92 viewsread 5 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed 🅰ቢtaጎ
3 Sept 2026, 05:50 UTC93 viewsread 5 September 2026 File
File, posted without a caption
Signed 🅰ቢtaጎ
3 Sept 2026, 05:50 UTC58 views0 reactionsread 5 September 2026 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ነሐሴ 28-የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችንን የአብርሃም፣ የይስሃቅና የያዕቆብ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው፡፡ የሁሉ አባት አብርሃም ፍጥረትን በመመርመር አምላኩን ካገኘ በኋላ እግዚአብሔር ተገልጦለት አንድነቱንና ሦስትነቱን አስረድቶታል፡፡ ከዚህም በኋላ አብርሃም እቤት ሄዶ ቤተ ጣዖቱን አቃጠለው፡፡ በዚህም ጊዜ የጣዖት ቤቱ አጋፋሪ የነበረው የሎጥ አባት የሆነው አራን ወደ እሳቱ በመግባት አብሮ ተቃጥሎ በመሞት ሰማዕተ ጣዖት ሆኗል፡፡ ወንድማቸው በዚህ መልኩ ከሞተ በኋላ ሁለቱ የታራ ልጆች አብራምና ናኮር ሚስት አገቡ፡፡ ታራም ልጁን አብርሃምን ከሚስቱ ከሳራ ጋር የአራንን ልጅ ሎጥን ይዞ በመነሣት ወደ ከነዓ…
Signed 🅰ቢtaጎ
3 Sept 2026, 05:50 UTC34 views1 reactionsread 5 September 2026 አብርሃምም ከሰዶምና ገሞራ ጥፋት በኋላ በምሥራቅ በኩል ወዳለው ሀገር ሄዶ በጌራራ ከተቀመጠ በኋላ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደነገራቸው ሣራ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ አብርሃምም ስሙን ይስሐቅ ብሎ ጠራው፣ በ8ኛውም ቀን ገዘረው፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ልጁን ይስሐቅን ወደ አንድ ተራራ ላይ ወስዶ በዚያ ላይ እንዲሠዋለት ባዘዘው ጊዜ አብርሃም በጠዋት ተነሥቶ አህያውን ጫነ፡፡ ልጁ ይስሐቅንና ሁለቱን ብላቴኖቹንም ወስዶ ለመሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ፈልጦ አሸክሞ ሄደ፡፡ በ3ኛውም ቀን እግዚአብሔር ወዳዘዘው ቦታ በደረሰ ጊዜ ሁለቱን ብላቴች ‹‹እናንተ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፣ እኔና ልጄ ግን ወደ ተራራው ሄደን ሰግደን ተመልሰን እንመጣለን›› አ…
❤1
Signed 🅰ቢtaጎ
1 Sept 2026, 17:23 UTC56 viewsread 5 September 2026 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ነሐሴ 27-ሲኦል ውስጥ ገብተው ይጸልዩ የነበሩት ታላቁ ጻድቅ ተአምረኛው አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ልደታቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ሰማዕታቱ ቅዱስ ብንያሚንና እኅቱ ቅድስት አውዶክስያ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፊቅጦርና እናቱ ቅድስት ሣራ መታሰቢያቸው ነው፡፡
+ ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት 4ኛው የሆነው መልአኩ ቅዱስ ሱርያል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፡፡
+ ነቢዩ ሳሙኤልም በቤተ መቅደስ ሳለ የተጠራበት የመታሰቢያው ዕለት ነው፡፡
+ 12ቱ የአባታችን የያዕቆብ ልጆች መታሰቢያቸው ነው፡፡
+ + + + +
ሰማዕታቱ ቅዱስ ብንያሚንና እኅቱ ቅድስት አውዶክስያ፡- ወላጆቻቸው ደጋግ ክርስቲያኖች…
Signed 🅰ቢtaጎ
1 Sept 2026, 17:23 UTC60 viewsread 5 September 2026 በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ስንነሣ ጥናቶች እንደሚያሳዩትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አንዱ ክፍል (UNODC-united nation’s office on Drug and crime) በጥናቱ ይፋ እንዳደረገው በየዓመቱ 200,00 (ሁለት መቶ ሺህ) ሰዎች አደንዛዥ ዕፅን መጠቀማቸውን ተከትሎ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ በአሜሪካን አገር ብቻ በየቀኑ ከ95 በላይ ሰዎች በአደንዛዥ ዕፅ ምክንያት ይሞታሉ፡፡ አደንዛዥ ዕፅን በክትባት መልክ (injection) ከሚወስዱት ውስጥ አብዛኛዎቹ በደማቸው ውስጥ የHIV ቫይረስ ይገኛል፡፡ በአሜሪካን አገር በአደንዛዥ ዕፅ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በመኪና አደጋ እና በድንገተኛ እሳት አደጋ ምክንያት ከሞቱት ሰዎች ቁ…
Signed 🅰ቢtaጎ
1 Sept 2026, 17:23 UTC91 viewsread 5 September 2026 ጋር መጽሐፎቹን ከግዮን ምንጭ ውስጥ ከተቀበለ በኋላ ‹በግዮን ውኃ ውስጥ ሳይረጥቡ በደረቅ መጽሐፎቼን የጠበቀ እግዚአብሔር ይመስገን› ብሎ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡ ‹ያንጊዜም በውስጥሽ ታላቅ ድኅነት ይደረግብሽ፣ ሕመምተኞች ሁሉ ይዳኑብሽ፣ መካኖች ይውለዱብሽ› ብሎ ግዮንን በቃሉ መረቃት፣ በእጁም ባረካት፡፡ ብፁዕ አባታችንም በዚህች ቦታ ላይ ፈውስ፣ ረድኤት፣ በረከት ይደረግብሽ ብሎ ብዙ ዘመን ቆሞ ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ‹ይህ በረከት፣ ረድኤት፣ ሀብት፣ ፈውስ እንደወደድህ እስከዘለዓለሙ በዚህ ቦታ ይሁንልህ› አለው›› ተብሎ ነው በቅዱስ ገድላቸው ላይ የተጻፈው፡፡
ጻድቁ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ሌላው የሚታወቁበት ‹‹ብሄሞትና ሌዋታን›› የተባሉ እጅግ ግዙፍ…
Signed 🅰ቢtaጎ
1 Sept 2026, 17:23 UTC103 viewsread 5 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed 🅰ቢtaጎ
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @sinksarr. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.