15 Dec 2024, 11:47 UTC867 views14 reactionsread 8 August 2026 ምረር...
ከቤት ጀርባ 'ምቆረጥ ምግብ ሲፈለግ
ጠላቶቹም ሲመጡ የሚልላቸው ፈገግ
በሞቀ ውሃ፤ በፈላ ውሃ ሲደግሱለት ሰርግ
ወዶ ይመስልሃል ዱባ የሚሞተው በጠላቶቹ ዘንግ?
ወዶ እንዳይመስልህ የሚያወጣው ድምፀ-ስቃይ
አትጣፍጥ እያልኩት ጣፋጭ እየሆነ ስለሚታይ
እንኳን ሰው ይቅርና በምድር የሚያይ
በረዶም ይበላዋል ተመልክቶት ከሰማይ፤
ይህ ነው እንግዲህ የዱባ ችግሩ ይህ ነው ጥፋቱ
እንደ ቅል መምረር ትቶ እየጣፈጠ መምጣቱ።
ልምከርክ ወዳጄ ልምከርክ አድምጥ
ሰው ላንተ ትልቅ ቦታ እንዲሰጥ
አውርዶህም እንዳይመለከትህ ልክ እንደ አይጥ፤
ትመር እንደሆን ምረር እንደ ቅል
አልመር ስላለ ነው ዱባ የሚቀቀል።
ትመር እንደሆን ብለጥ ከሎሚ
ይህ ትልቅ ምክር ነው ጆሮ ላለው ሰሚ።…
👍11❤2👏1
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
14 Dec 2024, 13:14 UTC≈1,070 views9 reactionsread 8 August 2026 መልሱን ጀባ በሉኝ
።።።።።።።።።።።።።
😭😭😭😭😭😭😭😭😭
መናገር ፈርቼ
ተሸክሜው ኖሬ የመከራን ፍዳ
ግፉ ከጨመረ መስለናቸው ዲዳ
ዛሬ ግን ልጠይቅ ያበጠው ይፈንዳ
በገዛ ሀገሬ ላይ
መናገር ተስኖኝ ብዙ ግፍ ሰንቄ
አፍኘው ከርሜ የእንባ ሳቄን ስቄ
በእጥፉ ባሰ እንጅ አልቀነሰም ጭንቄ
መልስ ባይኖር እንኳ
መልሱን እንካ በሉኝ ያገሬን ጥያቄ
?
ጥያቄ 1
የት ሄደን እንኑር?
ሀገር እንደሌለን ስንሆ'ን ባይተዋር
ጉልበት ያለው ሁሉ ሲሸምተን በብር
ጨዋው ህዝብ እንደበግ ባለካራው ነብር
በሆነባት ሀገ…
😱5🤩2❤1👍1
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
13 Dec 2024, 13:23 UTC655 views6 reactionsread 8 August 2026 ተይው...
አብሬሽ ሆኜ ሳለ፣ በሃሳብ ጠልቄ
'ምን ሆነካል?' እያልሽ አትጠይቂኝ ይህንን ጥያቄ።
ላትረጂኝ፣ ላታደምጪኝ ጊዜ ሰጥተሽ
የጠፋብኝን ላታይው፥ ላትፈልጊው አስተውለሽ
በጥያቄ ብዛት አታድርቂኝ እባክሽ፤
በሆዴ ያለውን ከልቤ የዋሻ ሚስጥር
ብነግርሽ ቀድሜ ያስተጋባ እንደ ነበር
....ብቻ...ብቻ ተይው...
ተይው....በቃ ላትረጂኝ ነገር
በሆዴ ይቀመጥ፤ በሆዴ የዘላለም መቃብር
የልቤ መውደድ
የልቤ ማፍቀር
እጆቼም እቤቱን የመበርበር።
በተዘረጋው አስፋልት፣ ጠቁሮ በተዋበው
ጥርሶቼ እስኪደክሙ፤ ምላሴም እስኪያልበው
ስምሽን ብጠራ ብደጋግመው(፪)
በሌለሽበት ስፍራ መልክሽን ብስለው፤
አዎ.......
መች ይገባሽና የልቤ ፍርሃት?
ድንገት ስትጠፋብኝ ጓዴ የሚደርስብ…
🤩5👍1
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
11 Dec 2024, 04:02 UTC616 views8 reactionsread 8 August 2026 ከልጅነቱ ጀምሮ እናቱን አያውቃትም። አባቱ ነው እንደ እናትም እንደ አባትም ሆኖ ያሳደገው። ስለ እናቱ አባቱን ደጋግሞ ሲጠይቀው "ግዜ መልስ ይሰጥሀል" ከማለት ውጭ ምንም ብሎት አያውቅም። ሰው ነው እና እድሜው ለፍቅር ሲደርስ ከአንድ መልከ መልካም ኮረዳ ጋር ተዋወቀ። ከልቡ አፈቀራት እርሷም ከልቧ እንደምታፈቅረው ነገረችው አመናትም። ከአንድ አመት የፍቅር ግዜያት በኋላ ያች ውብ እንስት እንቆቅልሽ በሚመስል መልኩ ከፊቱ ተሰወረች። ችግር ገጥሟት ነው ብሎ አሰበ በጣም ጨነቀው። የዛን ግዜ የጭንቅ አማላጇ ማሪያም ትዝ አለችው እና ወደ ቤቷ አመራ። በዱርየ ልቡ እንዲህ ሲል ፀለየ " ማሪያም ሆይ የእውነት ከጭንቅ የምታማልጅ ከሆነ በዚች ሰባት ቀን ውስጥ ከልቧ የም…
😱5❤2👍1
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
7 Dec 2024, 14:56 UTC693 viewsread 8 August 2026 Voice message
Voice message, posted without a caption
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
7 Dec 2024, 06:35 UTC747 views11 reactionsread 8 August 2026 እንታረቅ 🤝
በቀጠርሽኝ ሰዓት
መድረሱ ተስኖኝ ጊዜሽን ስበላሽ
ጊዜኮ ወርቅ ነው ለምን ትይኛለሽ?
ሰዓትሽን ገድፌ
ቀንሽን ሸራርፌ
ቃሌንም አጥፌ
አውቃለሁ የለሁም
በቀጠርሽኝ ስዓት
ተገርፈሻል አዎ
በመጠበቅ ቅጣት
ግን
በፍቅር ተሸንፎ ወድቆ ለሚታገል
ጊዜ ይቅርና ህይወት ይሰጥ አደል
እያልኩኝ በትቢት ቀንሽን ሳቃጥል
ሰዓትሽን ነጥቄ ቀንሽን ስገድል
"የጊዜን ምንነት ነግሬህ ካልገባህ
ያፈቀረን ሰዓት አይተህ ካልተረዳህ
በጊዜ ልርገምህ ግዜ ይፋረድህ"
ብለሽኝ ስትሄጂ
ያንች ስለት ሰምሮ ግዜ ተፋርዶኛል
የነበረኝ ሁሉ
በደቂቃ ግድፈት ከእጄ ሸሽቶኛል
ዛሬ
በ…
👍8🤩2❤1
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
3 Dec 2024, 17:10 UTC646 views9 reactionsread 8 August 2026 ለባለ ጠመኔው
የትውልድ አሻራ የሀገር መሠረት
ዘመን አሻጋሪ የህመም መድሀኒት
የነገ አለኝታ የመበልፀግ ሀውልት
እውቀትን ደራቢ የመኖር ትሩፋት
የስራውን እሩብ ላልተነገረለት
ለሀገር መስራቹ አንዴ ልቀኝለት
"ባለመኖር ኖሮ መኖርን የሰጠ
ሀገር ለማስከበር ክብሩን የረገጠ
እውቀትን ሊገዛ ጉልበቱን የሸጠ"
"በረሀ ላይ ወርዶ
በውሀ ጥም ሲቀጣ
ከሰው በተለየ
ነጭ ላብ ለጠጣ"
"የሚበላ ጠፍቶ ራብ ሲደቁሰው
የጠመኔ ብናኝ ባፉ ለጎረሰው
ሌላው ነገር ቢቀር
እስኪ አንዴ እናስታውሰው"
"ብዙ ኪሎ ሜትር
በጭኝጫ ላይ ሄዶ
በበረሃው ነዳድ
በረ…
👍7❤2
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
3 Dec 2024, 05:07 UTC659 views5 reactionsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍5
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
29 Nov 2024, 17:21 UTC668 views5 reactionsread 8 August 2026 እመቤቴ ገና በማህፀን ሳለሁ የጠበቅሽኝ😍
ከማህፀን ወደ አለም ያስወለድሽ ያሳደግሽኝ🥰
በደረቴ እንድድህ በእግሮቼ እንድቆም የደገፍሽኝ 🥰
ያራመድሽኝ ልቤ መሄደ ከፈለው ያደረስሽኝ 🥰
ያስተማርሽኝ ከጥፋቱ ከቅዝፈቱ ያስማርሽኝ🥰
እባክሽን ወላዲቴ🥰
ከዚህ ዘመን ከቅዝፋቱ አሳልፊኝ።
የጌታ የአመላኬ የክርስቶስ እናቱ
ሚደረስልሽ ኪዳነ ዘነግ ዘዘወትር ቅዱስ ቤቱ 🥰
የጣን መውጫው አንች እኮ ነሽ እናታችን ማህሌቱ🥰
እድንብሽ የመረጠሽ አዳኛችን😍
የጭንቅ እለት የምትደርሽ አማላጇ እናታችን🥰
ማሪያም ብለን ስንጠራሽ ድረሽልን ለሁላችን።
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
🙏 አሜን 🙏
በማሩ ቀረአለም
❤5
Signed Maru
26 Nov 2024, 16:00 UTC723 views13 reactionsread 8 August 2026 ይኸውልሽ አለሜ---
ፍቅርህን በግጥም ንገረኝ ስትይኝ
ላዋድድ ብሞክር ሀረግ እና ስንኝ
ምን ብየ ልጀምር ቃላቶች አጠሩኝ
ምን ብየ ልጀምር?
ከሀዲስ አለማየሁ ቃላትን ተውሼ?
ከኤልያስ ሽታሁን ቅኔን ተንተርሼ?
ከበውቀቱ ስዩም ወጎችን ጠቅሼ?
ምን ብየ ልጀምር?
ያረጁ ቃላትን በምናብ ሰብስቤ?
የሮምዮን ፍቅር በገሀዱ ስቤ?
በፊልም ያየሁትን ቃላት ደራርቤ?
ምን ብየ ልጀምር?
ቃል አጠረኝ የምር
ከመፅሀፍ አለም ቃላት ብለቃቅም
ከስመጥር ፃፊ ስንኞች ብሰርቅም
ከፊልም ከቲያትር ፊደላት ብቃርም
የልቤን መግለጫ ነጠፈብኝ አቅም
አቦ ፍች በቃ
ከአፈቀረ ወዳጅ ቃል አይጠየቅም
✍ዝምተኛው ፀሀፊ
@bela…
👍13
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
23 Nov 2024, 12:22 UTC684 views7 reactionsread 8 August 2026 ሀሳብህን ተናግረህ ሰዎችን ለማስረዳት
ከአንደበትህ ምንጭ ቃልት ሲጠፉብህ
አትልፋ ወዳጀ
ዝም ብትል ይሻልለል እንደአማረብህ
ወይ ብትጮ ይሻላል አብደሀል እንዲሉህ
መቸም በዚች አለም
አብደሀል ከተባልህ
ቃልህ ቢበላሽም ማንም አይፈረድብህ።
😎በማሩ ቀረአለም
👍7
Signed Maru
23 Nov 2024, 05:21 UTC692 views9 reactionsread 8 August 2026 ምኞቴን ተቀበይ🫂
እንች🫵🫵
ልረሳሽ ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
እኔም መሳቅ ጀመርሁ
አለምም ካላንች ይታየኝ ጀመረ
ልረሳሽ ነው መሰል
ይኸው ቃልሽን ሽሬ
አትጠጣ ያልሽኝን
ጠላ ካረቄ ጋር ቀላቅየ ጠጣሁ
እርሷ የት ነች ሲሉኝ
አለች ማለት ትቼ ነበረች
የሚል ቃል ካፌ ላይ አወጣሁ
ልረሳሽ ነው መሰል
ባላምንበት እንኳ
ካንች መለየቱን ችየ ተቀበልኩት
መሽቀርቀሬን ትቼ
ከሷ ውጭ ብየ ራሴንም ጣልኩት
ልረሳሽ ነው መሰል
ያኔ የማለ ልብ ሊረሳሽ አስቧል
የጣቴ ቀለበት ተጨማዶ ጠቧል
ልረሳሽ ነው መሰል
ልረሳሽ ነው መሰል
ወይ ደግሞ ልትመጭ
ጥርሴ ስቆ ታየ
ይኸው ካንች ውጭ
ከመጣሽ ነይልኝ👨🏾
✍ዝ…
🤔7👍2
Signed ዝምተኛው ፀሀፊ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @poem_by_poem. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.