23 Sept 2024, 19:21 UTC287 views2 reactionsread 7 August 2026 ምሥጢረ ቁርባን
ቁርባን ፤ ማለት፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምኃ፣ መስዋዕት፣ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማለት ነው።
በብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ቁርባን (መስዋዕት) ምሳሌዎች
1. የመልከ ጼዴቅ መስዋዕት ዘፍ 14፥ 18። ዕብ 5 ፥6። ዕብ 6 ፥1። ህብስቱ የሥጋው፤ ወይኑ የደሙ ምሳሌ፤ መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ፤ አብርሐም የምዕመናን።
2. የእስራኤል ፋሲካ። ዘፀ 12፥ 1። ሞት የዲያብሎስ፤ እስራኤል የምዕመናን፤ በጉ ደግሞ የክርስቶስ ምሳሌ።
3. የእስራኤል መና። ዘፀ 16፥ 13። መና የጌታችን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም፤ እስራኤል የምዕመናን፤ ደመና የእመቤታችን
በብሉይ ኪዳን መስዋዕት ቁርባን ያቀረቡና በረከት ያገኙ አባቶች
1. አዳም አባታችን አዳም ባቀረ…
❤1👍1
30 Oct 2022, 08:40 UTC≈3,300 views9 reactionsread 7 August 2026 በቶሎ ይነበብ ልንነቃ ይገባል
ለማንበብ 15 ደቅቃ ብቻ ስጥ ህይወትን ይቀየራል አትሳሳት
share አድርገው
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል
* በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም
*በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ
*ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡
*የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ …
👍8❤1
19 Sept 2022, 18:02 UTC584 viewsread 7 August 2026 File
File, posted without a caption
19 Sept 2022, 17:46 UTC532 views3 reactionsread 7 August 2026 #መቁጠርያ_በቤተክርስቲያን (Prayer Ropes)
በተለያዩ መናፍቃን ዘንድ እንደ ባዕድ ነገር ነው የሚታየው የሚገርመው ለዚህ ንግግራቸው ምክንያት እንኳ ማስቀመጥ አይችሉም። አባቶቻችን መቁጠርያን የሚጠቀሙት በፀሎት ጊዜያት ነው። አብዝተው ለመፀለይ ይጠቀሙበታል። መቁጠርያን ለፀሎት ስለተጠቀሙ መክሰስ አይገባም። ቅዱስ ጳውሎስ በ 1ኛ ተሰ 5፥18 ላይ "ሳታቋርጡ ፀልዩ በሁሉ አመስግኑ..." በማለት እንዳስተማረን አብዝቶ መጸለይ ያስፈልጋል። የጸሎት ተቃዋሚም ጠላት ሰይጣን ነው፡፡ ጌታም "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ" ማቴ 26:41 ብሏል፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም ፀሎትን አብዝተን እንድናደርግ መፅሀፍ ቅዱስ ይመክራልና
#እኛ_ኦርቶዶክ…
👍3
16 Sept 2022, 11:16 UTC434 views1 reactionsread 7 August 2026 👉ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ።
👉 እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ_ዕወቃት።
👉ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።
👉በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ።
👉እነዚህም ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።
👉ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገ…
👍1
5 Sept 2022, 16:49 UTC391 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @ortodoxmezmur
ጥብቅ ማሳሰቢያ
****
ነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም
"""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበበ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""
ሰምኑን የቤተክርስቲያናችን ባልሆኑ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የቤተክርስቲያናችንን አርማ በመጠቀምና የቤተክርስቲያናችን ማኅበራዊ መገናኛዎች በማስመሰል ልዩ ልዩ ዜናዎችን በመሥራት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚሞክሩ ድረ ገጾች እየተሰራጩ መሆኑን ደርሰንበታል።
እነዚሁ ድረ ገጾች ላይም በተለይ የቤተክርስቲያናችን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት መግለጫ በማስመሰል የሚያስተላልፏቸው ዘገባዎች ሐሰተኞች ከመሆናቸውም በላይ በብፁ…
21 Aug 2022, 15:48 UTC431 viewsread 7 August 2026
የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው
ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደው…
18 Aug 2022, 17:47 UTC295 viewsread 7 August 2026 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?
ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል
ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚ…
11 Aug 2022, 19:49 UTC308 views1 reactionsread 7 August 2026 ነገረ ክርስቶስ
ክፍል 1
በመጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)
የእግዚአብሔር ልጅ ለምን ሰው ሆነ ?
"እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ሰው ሆኖ ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል " እንዲሉ በነቢያት አድሮ እንደሚወርድ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንደሚወለድ ትንቢት ያናገረው ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሳይሆን ማዳን ሲቻል ለምን ሰው መሆንን ፈቀደ ? ያልንን እንደሆነ
1ኛ.ለአዳምና ለሄዋን ከልጅ ልጃቸው ተወልዶ እንደሚያድናቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ለመፈፀም ።ይህንንም ሊቁ ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ እንዲህ ይገልጠዋል ( ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው ፣ የፀጋ ገዢነት አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዢ ሊያደርገው…
👍1
26 Jul 2022, 06:34 UTC576 views1 reactionsread 7 August 2026 ሐምሌ 19
ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ
ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው
ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው
ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደ…
👍1
7 Jul 2022, 18:45 UTC302 viewsread 7 August 2026 Video
Video, posted without a caption
6 Jul 2022, 18:57 UTC418 viewsread 7 August 2026 #የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት
(በቀሲስ ህብት የሺጥላ)
#ክፍል_3
#ግብረ_አውናን (Masterbation) #ምንድነው ?
እግዚአብሔር ለምህረትና ለመቅሰፍት ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ግዳጆችን የሚፈፅሙ መላእክት እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም ሰውን በልዩ ልዩ መንገድ እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አጋንንት አሉት ። ከእነርሱም ውስጥ አንዱ #ሰይጣነ_ዝሙት ነው ። ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ የተለያየ ነው ። እንደውም አንዳንዶቹ ፈተናዎቹ የዝሙት አይመስሉም
#ፆር_የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያወቁ ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ የሞላበትን የሰይጣንን ፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው በሕይወ…
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ortodoxian. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.