2 Aug 2026, 15:32 UTC71 views3 reactionsread 7 August 2026 "ጌታ ሆይ፣ ለድሆች፣ ለመበለቲቱ እና ለድሀ አደጎች ለማልቀስ ርኅሩኆች አይኖች ስትፈልግ ዓይኖቼ ያንተ ይሁኑ። የተቸገሩት ለመድረስ የተዘረጋ እጅ ስትፈልግ እኔ እጅህ ልሁን። በጨለማ እና ባለማስተዋል ውስጥ የጠፉትን ብርሃን ልታበራላቸው ስትፈልግ የምታቀጣጥለው ነበልባል ልሁን። ሰውነቴ በልብህ ሃሳብ ይንቀሳቀስ። እኔ ያለሁት ለዚህ ነውና! "
በ"በረከት ኢያሱ" https://t.me/one_died_for_all
❤3
Signed Aman ebo
20 Jul 2026, 08:59 UTC206 views4 reactionsread 7 August 2026 በዚህች ሕይወት የሚበቃን በቃን ስንል ብቻ ነው። የበቃኝ ኑሮ መረጋጋትን ፣ የጸሎት ሕይወትን ፣ ያለንን ማካፈልን ፣ ደስታን ይሰጣል ከመጎምጀትም ይጠብቃል።
https://t.me/one_died_for_all
❤2👍2
Signed Aman ebo
19 Jul 2026, 07:23 UTC209 views1 reactionsread 7 August 2026 “የምንኖረውና የምንንቀሳቀሰው፣ ያለነውም በእርሱ[በእግዚአብሔር] ነውና።’”
(ሐዋ. 17፥28)
https://t.me/one_died_for_all
❤1
Signed Aman ebo
17 Jul 2026, 07:21 UTC244 views6 reactionsread 7 August 2026 "እግዚአብሔር መጀመሪያ የጠራን (primarily calling) ወደ ራሱ እንጂ ወደ አገልግሎት አይደለም፤ ስለዚህም የመንፈሳዊነት መለኪያው አማኙ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ጠንካራ ሕብረት እንጂ የመድረኮቹ ስኬት ሊኾን አይችልም።"
https://t.me/one_died_for_all
❤6
Signed Aman ebo
16 Jul 2026, 09:54 UTC292 views3 reactionsread 7 August 2026 "አሥር ጊዜ "ኢየሱስ እወደሃለሁ" ማለት መዘመር፣ መነፍረቅ፣ መንፈራፈር ቀላል ነው።... ኢየሱስ አብላኝ አይልህ አጠጣኝ፣ ቤትህ አሳድረኝ አይል ብር አበድረኝ፣ አሳክመኝ አይልህ ደግፈኝ... ልብ ካለህ ዙሪያህን ያለውን ሰው ውደድ፣ ምክንያቱም ጎንህ የቆመ ሰው ከአፍ ያለፈ ብዙ ነገር ያስፈልገዋል...እጅህ ከምላስህ ካልረዘመ ምን ጥቅም!"
#Alex Abreham
https://t.me/one_died_for_all
❤3
Signed Aman ebo
15 Jul 2026, 09:38 UTC231 views5 reactionsread 7 August 2026 “ንስር ራሱን ሲያድስ ክንፎቹን እንደሚነቃቅል፣ ያንተን ክብር የጋረደውን የኀጢአት እርጅናዬን ነቃቅለህ "ለጽድቅ እርጅናው የተሻረለት ጎልማሳ አድርገኝ"።”
https://t.me/one_died_for_all
❤5
Signed Aman ebo
14 Jul 2026, 07:31 UTC502 views10 reactionsread 7 August 2026 አገልግሎት የቦታ ምርጫ ሳይሆን፣ የልብ ጥሪ ነው። በየትኛውም ቦታ ላይ ሆነን፣ በየትኛውም ፈተና ውስጥ ብንተጋ፤ እያከናወንን ያለነው ተራ ሥራ ሳይሆን የዘላለምም ንጉስ የሆነውን የክርስቶስን አካል የማነጽ ታላቅ ተልዕኮ ነው።
የምንፈጽመው አገልግሎት እንደ መሥዋዕት ነው፤ የምንገነባው የክርስቶስ አካል ነውና። ድካማችን የእርሱ ክብር፣ ትዕግስታችን የእርሱ ምስክር ነው። ከሰዎች እይታ በራቅንበት፣ በተረሳንበት ወይም በታክትንበት ቦታ ሁሉ፤ የእውነት ምስክሮች ሆነን ስንቆም፣ የምንነካው የጌታን የከበረ አካል ነው። ይህ አደራ ታላቅ፣ ይህ ጥሪ የተቀደሰ፣ ይህ አገልግሎት ደግሞ የዘላለም ክብር ነው።
https://telegram.me/one_died_for_all
❤10
Signed Aman ebo
13 Jul 2026, 13:58 UTC249 views3 reactionsread 7 August 2026 አዳዲስ ነፍሳትን ከመፈለግ ችላ ብላ፤ ተልእኮን ማዕከል ከማድረግ ተዘልላ የተቀመጠችን ቤተ ክርስቲያን ያህል አሳዛኝ ነገር በዚህ ምድር የለም!
#ዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ
https://t.me/one_died_for_all
❤2💯1
Signed Aman ebo
7 Jul 2026, 13:52 UTC326 views6 reactionsread 7 August 2026 ማገልገል "በጣም ቀላል" ነው፤ በፍጹም ቅድስና ማገልገል ግን የትጉሐንና በወንጌል ጉዳይ ለጨከኑ ብቻ ነው!
https://t.me/one_died_for_all
❤5🔥1
Signed Aman ebo
5 Jul 2026, 12:56 UTC331 views3 reactionsread 7 August 2026 ‘ዕጣ ፈንታ’ እና ‘ዕድል’ ጣዖታት ናቸው።
አብዛኛው የሰው ልጅ ሕይወቱን የሚመራው በሁለት የሐሰት አማልክት ነው፦ ‘ዕድል’ እና ‘ዕጣ ፈንታ’። እነዚህ ቃላት በየቀኑ የምንሰማቸው ቢሆኑም፣ በመንፈሳዊ መነጽር ሲታዩ ግን የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ሥልጣን የሚገዳደሩ እና ክብሩን የሚቀሙ ጣዖታት ናቸው።
https://t.me/one_died_for_all
❤3
Signed Aman ebo
4 Jul 2026, 15:45 UTC323 views5 reactionsread 7 August 2026 እራሳችሁን ለማንም ለማብራራት አትሞክሩ፤
ምክንያቱም የሚወዳችሁ ሰዎች ስለእናንተ ምንም ማብራርያ አይፈልግምና። በውስጣቸው አንዳች ጥላቻ ያደረባቸው ግን ምንም ያህል ብታብራሩላቸው፤ አይገባቸውም!
https://t.me/one_died_for_all
❤3💯1🙏1
Signed Aman ebo
3 Jul 2026, 13:57 UTC328 views4 reactionsread 7 August 2026 “ፍቅር እውነተኛነቱ የሚታወቀው
ለበደል ይቅርታ ፣ ለችግር ጽናት ሲኖረው ነው።”
https://t.me/one_died_for_all
❤4
Signed Aman ebo
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @one_died_for_all. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.