7 Aug 2026, 19:36 UTC541 views1 reactionsread 8 August 2026 🚺✅ምርጥ አስተማሪ ታሪክ! ካልጨረሳችሁት አትጀምሩት
#እናቱን የሚወድ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ ፅሁፍ መልካም ንባብ !
ከባለቤቴ ጋር ትዳር ከመሰረትን 21 ዓመት ሞላን ባለቤቴ አንድ እራሴን እንድፈትሽበት ያደረገኝን ጥያቄ አቀረበችልኝ ሃያ አንድ ዓመት ካንተ ጋር ስኖር አንድም ቀን ከእናትህ ጋር ለመዝናናት ስትወጣ አይቼክ አላውቅም ዛሬ ማታ እናትህን እራት ምሽት ጋብዛትና አዝናናት አለችኝ።
ውዷ ባለቤቴ ባቀረበችልኝ ሃሳብ ከመገረም በላይ መሰጠኝ ተስማማሁኝ እናም ወደ እናቴ ጋር ደወልኩላት እማ ዛሬ ካንቺ ጋር ሽርሽር መውጣት ፈልጋለሁ አልኳት ደነገጠች "ምነው ሰላም አይደል ልጆችሕ ምን ሆኑ ባለቤትህስ ሰላም አይደለች እንዴ ?" በማለት የድንጋጤ ጥያቄዎቿን አ…
❤1
6 Aug 2026, 18:31 UTC≈1,210 views3 reactionsread 8 August 2026 """"ንገሯት ለእናቴ""""
ልጄ ልጄ ስትል ስሜን ስታዎሳ፣
ልሂድ አይኗን ልየው.....
ልጠይቃት ብላ እግሯን ስታነሳ፣
እዳትመጪ በሏት ብትላችሁ እሽ፣
ልጅሽን ለማዬት እግርሽን አታንሽ፣
በቁሟ ሙታለች ብትችይ አታስታውሻት፣
ከነመፈጠሯ ከመኖሯም እርሻት፣
በሏት.....
አደራ ንገሯት አጥብቃችሁ ሞቴን፣
ብትናፍቀኝም.....
ላያታ አልፈልግም እንዲህ ሆኜ እናቴን፣
ወይም እዲህ በሏት ብላለች አትምጪ፣
ልጅሽ ክዳሻለች በቃ እርምሽን አውጪ፣
ወልደሽ አሳድገሽ ልጦርሽ ሲገባ፣
እናቷን ከሀዲ ሆነች የማትረባ፣
በሉልኝ ብታምን፣
አልባሷ ቡትቶ ስራዋ ምናምን፣
ይቅርና ለናቷ ያልሆነች ለነብሷ፣
እርኩስ.... የረከሰች.....
ለሁሉ ከፍ የሚል ወለቂ ቀሚሷ፣
እንኳንስ ሊ…
👍2🥰1
5 Aug 2026, 18:31 UTC≈2,220 views0 reactionsread 8 August 2026 ተላለፍን
አይቼው አይቶኛል
አይቶኝ ተያይተናል
ልቤ በእጥፍ መቷል
ልቡም በእጥፍ መቷል
ልቡ በደረቴ ምቱ ተሠምቶኛል
ቅፅበታዊ እይታ ጀምረን መገርመም
ዞር አልኩኝ ዞር አለ በቃ አልተያየንም
ልባችን መዳፉ ጣቱ ተቆላልፎ
እግራችን በሜዳ በሩቅ ተሠልፎ
መሥመር ለይቶናል አልተገናኘንም
ኑሮ ደልድሎናል አልተተዋወቅንም
ውስጥን በሚገዛ የአብሮነት ጥላ
መተዋወቅ ጠፍቶን የአድነት ከለላ
እየተፋለግን በልብ መሻሻት
አልተገናኝተንም ባሠመርነው ህይወት
የህይወት መንገድ ነው ድንገት ያገናኘን
ይኸው መንገድ ነበር ይባስ የለያየን
ለየቅል መንገድ ነው ጉዞ የጀመርነው
በራሣችን አለም የተለያየነው
በጭራሽ አንገጥምም አብረን እንኳ ብንሄድ
የርሱ እ…
4 Aug 2026, 19:12 UTC≈2,910 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
🌞day#
በቀዝቃዛ ሌሊት - ውድህን አቅፈሃል
በኮከብ ታጅበህ - ከንፈሯን ስመሃል
ጨረቃዋን አይተህ - አለም ነው ብለሃል
ፀሐይ ወጣች ቀረች ምን ያደርግልሃል ?
በገባዖን ሰማይ - እምነቱን ተጠቅሞ - ፀሐይዋን አስቁሞ
ተዋግቷል ኢያሱ ፤
እስኪ ተሻል ከ'ሱ !
ጭር ባለው ሌሊት
ከምትወዳት ልጅ ጋር በስልት ደንሱ ።
ሰማይና ምድር ለዛሬ ባይነጉም
ዘላለም ነውና የአንዲት ቅፅበት ትርጉም
ይቺን ጨረቃ አስቁም ።
🔥3
3 Aug 2026, 15:09 UTC≈3,980 views4 reactionsread 8 August 2026 ❦ ══•⊰❂ ከታሪክ ማህደር ❂⊱•══ ❦
አይጧ
አይጧ የግድግዳውን ቀዳዳ በመጠቀም የቤቱ ባለቤት በታሸገ ካርቶን እቃ ይዞ ሲገባ ትመለከታለች፡፡ አይጧ “ዛሬ ደግሞ ምን አይነት ምግብ ይዞ መጣ!?” ብላ ተደስታለች፤ ነገር ግን ሰውዬው ለባለቤቱ ሊያሳያት የታሸገውን ካርቶን ሲከፍተው ወጥመድ ነው፡፡
አይጧ ደነገጠች፤ ወዲያውኑ ወደ እርሻው ተመለሰችና ጮክ ብላ “በዚህ እርሻ ውስጥ የምትገኙ እንስሳቶች ሆይ! የአይጥ ወጥመድ እየተጠመደላችሁ ነው፤ ወጥመድ! መጥመድ!!” በማለት ትናዘዛለች፡፡
ይህን ድምፅ በንቃት የሰማችው ☞"ዶሮ"፦
"ካጎነበሰችበት ቀና በማለት “አይጦ" ላንቺ ምን ያህል እንደሚያስጨንቅሽ ይገባኛል፤ ነገር ግ…
❤3🥰1
2 Aug 2026, 14:25 UTC≈5,180 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
ናፈቀኝ
""""""""
ወደሰማዩ ሳይ በደመና ምስል፣
ባይኔ ተከሰተ እርሱን የሚመስል፣
ጉብታውን ስቃኝ ተራራ ዳገቱ፣
ተመሳሰለብኝ ከኮራ ደረቱ፣
ንፋስ የሚገፋው ያየሩ መአዛ፣
እርሱን አስታወሰኝ ናፍቆት እየገዛ፣
እያንዳንዱ ነገር ያሳለፍነው ጌዜ፣
ገደለኝ ትዝታው ሆነብኝ ትካዜ፣
ጩኬ የሰደብኩት ያኔ ሲያበሳጨኝ፣
ትውስ አለኝና ባርባር አለኝ ቆጨኝ፣
መጣብኝ ጫዎታው መጣብኝ ሞገሱ፣
ናፈ'ከኝ ብል እንኳን አይሰማኝም እሱ፣
ናፍቆኛል ጨንቆኛል ግን ባይመለስስ፣
ዝም ልበልና ጎርፍ ዕንባዬን ላፍስስ።
❤4
1 Aug 2026, 15:59 UTC≈6,250 views3 reactionsread 8 August 2026 ያንተ ሞርጫ
እጇ አለንጋ
ቁመተ ሎጋ
አመለ ሸጋ።
አንተ ፋንጋ
ያንተ ምኞት
ተረከዘ ሎሚ
ሂል ተጫሚ
ፀጉረ ዞማ
አይነ ቡናማ
የቀይ ዳማ
ጉንጨ ሮማን
ቅርፇ ያማን
ያንተ ኪንኪ
ቁመተ ኮርኪ
ጥፍረ መጥምጥ
ቦርጭህ ዝርጥጥ
አፋንጫህ ድፍጥጥ
ለምን ብሎ ይከፋሀል
እኔ አንተን በመዉደዴ
የድስት ግጣሜ ማለት አንተ አይደለሀኝ እንዴ?🤔
❤2🥰1
31 Jul 2026, 17:38 UTC≈7,530 views2 reactionsread 8 August 2026 .... በርግጥ በኔ ዘመን .....
እምነት እንደ ጉሊት ሲቸበቸብ ያድራል
ቃል አክባሪ ግትር ተብሎ ይወቀሳል::
እዎ በኔ ዘመን......................
ፍቅር ከጭን ዳሌ ውሉን ያሳሰረ
የገበያው ዘዴ ሳይለዩ መግዛትን ብሂል የሰበረ::
በፍቅር ቅኝት ስም ሴሰኝነት ነግሶ
የነፍስ ፍቃዷ ተድሶ
በየ ጥጋ ጥጉ አስክሮ ሚያዳራ
ሺህ ጭኖችን ታቅፎ ሺህ ነፍስ የሚያሳጣ
የዘመናት ዋጋ.......
ወጣትነት ልኩ.........
መዝናናት ታቅፎ ውስጡ እዥ ያዘለ
በፈረሰ ደስታ ጠማማ ምሰሶ ታቅፎ የዋለ::
የእድሜ ጣሪያ ልስን
በእኔ ከሞትኩ ሰርዶ
በሺ አይኖር ወርዶ
በውሽት ቅብ ውበት ከላይ የተዋበ
አራዳ የሚያስብል አንዳንድ ስግጥና እለ::
❤1🥰1
30 Jul 2026, 15:47 UTC≈8,600 views7 reactionsread 8 August 2026 Photo
አዲስ ነገር የለም
""""""""""""""""""""""
ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣
ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣
ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣
አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣
መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣
ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣
የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣
ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣
እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣
እንከተላለን ....
በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤
በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣
የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣
ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣
ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣
አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣
ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣
መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀ…
❤7
29 Jul 2026, 15:02 UTC≈7,250 viewsread 8 August 2026 File
File, posted without a caption
28 Jul 2026, 14:28 UTC≈8,890 views5 reactionsread 8 August 2026 #የጸሎት_ለውጥ°°°
ለፍተህ ጥረህ ብላ
የሚል ትዕዛዝህን ህግህ ተከትዬ፤
እጠባበቃለሁ
የማጥመጃ መረብ ከባህሩ ጥዬ፤
እንግዲያው ፈጣሪ
የኔ አቅም ይህቺ ነች፤
ገመድ አጠላልፎ
ባህር ላይ ከመጣል በላይ ያልዘለለች፤
በል ጸሎቴን ስማ...
በጣልኩት መረብ ላይ የዓሳ ዘር ይሙላ፤
ወገኔ ይደሰት እስኪጠግብ ይብላ፤
..
ብዬህ ነበር
..
አሁን ግን...
የጣልኩትን መረብ መልሼ ሰበሰብኩ፤
ጠግቤ ለማደር ሌላ መንገድ አሰብኩ፤
ምክንያቱም..
እኔ መረብ ጥዬ
ዓሣ ስጠኝ እያልኩ እየተማፀንኩኝ፤
ከመረብ ጠብቀኝ
ብሎ የፀለየውን ዓሣውን አሰብኩኝ፤
...
የባህሩ ዓሣ
እንዲህ ሲለምንህ እኔ እሱን ባጠምደው፤
ያንተን ጠባቂነት ነውና ማወርደው፤
ስለዚህ አምላኬ…
አዲሱን ልመና ፀሎቴን …
❤4👏1
24 Jul 2026, 14:17 UTC≈10,700 views3 reactionsread 8 August 2026 እመነኝ ወዳጄ
ከዘንድሮ ፍቅርህ ያየችው ከሚያምራት
የትላንቷ ሚሚ
የቃቃነት ሚስትህ ሲበዛ ታማኝ ናት
ትዳር መያዝ ካሻህ
እሷኑ ፈልገህ እቤትህ አስገባት፡፡
😁2🥰1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @nev_give. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.