31 Oct 2025, 15:50 UTC≈4,310 views59 reactionsread 7 August 2026 አስተዋይ እቁ እንስት ማለት
➧ከማይመለከታት እና ከማያገባት ነገር ሁሉ እራሷን ያራቀች!
➧ሀቅን በመናገር ላይ ወገንተኝነት የለለባት!
➧ሀራምን ከማየትም ከመስማትም ፈፅማ የራቀች!
➧ንግግር አሳንሳ ምላሷን በዚክር የጠመደች በኸይር ወቅቷን እምታሳልፍ!
➧በታዘዘችበት ቀጥ ያለች ከተከለከለችው ሁሉ ፈፅማ የራቀች!
➧መህረሟ ያልሆኑ ወንዶችን አይኗን እነሱ ላይ ከመትከል የራቀች እነሱን ከማየት አይናን ሰበር ያደረገች!
➧ንግግሯ የተረጋጋ!
➧በሁሉም ነገር የተረጋጋች ለነገር እማቸኩል ተባልኩ ብላ እማትጨነቅ!
➧ጊዜዋን በኸይር በኢልም በሙሀደራ በዚክር በቂርአት እምታሳልፍ!
➧በመጀመሪያ ወደ ዱንያ አለም የመጣችበትን አላማ ጠንቅቃ የምታውቅ መጨረሻዋ…
❤39👍10🥰10
30 Oct 2025, 03:39 UTC≈3,790 views15 reactionsread 7 August 2026 🌴ኢማም አዩብ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
ከፊል ሰዎች ትዕቢተኛ ሲሆኑ በቅንጦት ከፍ ብለው መኖር ይፈልጋሉ።አላህም በተቃራኒው ዝቅ አድርጎ ያዋርዳቸዋል።ከፊል ሰዎች ደግሞ ትሑት ሲሆኑ ተናንሰው ዝቅ ብለው መኖር ይፈልጋሉ። ነገር ግን አላህ ከፍ ያደርጋቸዋልና።
📚[ حلية الأولياء 3 / 10 ]
👍11❤4
29 Oct 2025, 05:32 UTC≈3,840 views16 reactionsread 7 August 2026 ✍አስማ ቢንት ኻሪጃ ልጇ ስታገባ የሰጠቻት ምክሮች
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
ልጄ ሆይ!!!
ከለመድሽውና ካደግሽበት ቤት ወጥተሽ
ወደ ማታውቂው ፍራሽና ወዳለመድሽው የትዳር ጓደኛ
ልትሄጂ ነው ስለዚህ
አንቺ መሬት ሁኚለት እሱ ሰማይ #ይሆንልሻል
አንቺ ፍራሽ ሁኚለት እሱ ምሶሶ ይሆንልሻል
አንቺ ለሱ የሴት ባሪያ ሁኚለት እሱ ላንቺ የወንድ
ባሪያ ይሆንልሻል አንድ ነገር ፈልገሽ ችክ አትበይ ይጠላሻል ከርሱ አትራቂ ይረሳሻል
ወደ አንቺ ቀረብ ሲል አንቺም ወደርሱ ቅረቢ
እሱ በአንቺ ከተቆጣ ንዴቱ እስኪበርድ ራቅ በይ አፍንጫውን ጠብቂለት ካንቺ ጥሩ እንጂ መጥፎን እንዳያሸት መስሚያውን ጠብቂለት ካንቺ ጥሩን እንጂ መጥፎን አይስማ አይኑን ጠብቂለት ካንቺ ጥሩ እንጂ…
❤15👍1
27 Oct 2025, 10:41 UTC≈3,670 views11 reactionsread 7 August 2026 ከመፀፀትህ በፊት ሥራ!
🖋ኢማም አህመድ እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ የሥራ ሀገር ናት፣ መጨረሻይቱም(አኼራ) የምንዳ ሀገር ናት፤ እዚህ ያልሠራ እዚያ ይፀፀታል"።
📕[አዝ–ዙህ አል–ከቢር ሊል-በይሀቂ]
•┈┈┈••●◆❁🌹❁◆●••┈┈┈•
❤7👍4
23 Oct 2025, 04:36 UTC≈3,530 views16 reactionsread 7 August 2026 👉ጥበብን እየተማሩ ፈገግ ይበሉ ‼️
አንድ የእሩቅን አውቃለሁ ብሎ የሚሞግት ሰው ሸይኽ አልባኒን ሊከራከራቸው መጣ ።
ሸይኽ አልባኒ እንዲህ አሉት ፤
ከመከራከራችን በፊት ጥያቄ አለኝ አሉት ፣ ሰውየውም ምንድን ነው ጥያቄህ አላቸው ።
ሸይኽ አልባኒ አንተ የሩቅ አውቃለሁ እያልክ ትሞግታለህ ግን የኔ ጥያቄ ምን እንደሆነ አታውቅም ክርክሩን ጨርሰናል አሉት ። ‼️
👍10❤6
20 Oct 2025, 17:56 UTC≈3,550 views16 reactionsread 7 August 2026 የነገው ቀጠሮ
በደመቀው ሳሎን - በተዋበው ማጀት
ብትቀማጠለው ከልጅ እስከ ማርጀት
ያሻህን ብትነዳ በዝቶ ተሽከርካሪ
አለምን ብታስስ በሰማይ በራሪ
ጉድጓድ ነው ማረፊያህ የነገ ቀጠሮ
አፈር ልብስህ ሊሆን ሱፍህን ቀይሮ
ታገል ወንድሜ ሆይ ሰንቅ ለአኺራ
ፀፀት ያኔ አይጠቅምም ዛሬ ካልተሰራ
❤16
19 Oct 2025, 03:58 UTC≈3,580 views12 reactionsread 7 August 2026 ✨አላህ የሚወደውን ባሪያ ይፈትነዋል✨
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፡-
ችግር ለሙዕሚን ብስራት ነው፦ በችግር ቢፈተን በፍፁም አላህ ስለሚጠላኝ ነው ብሎ ማሰብ የለበትም።ይልቁንም አላህ ለባሪያው ያለውን ውዴታ ማሳያ ምልክት ሊሆን ይችላልና።ምክንያቱም አላህ ባሪያውን በሙሲባ ይፈትነዋል ባሪያውም ከአላህ የሚያገኘውን ሽልማት ተስፋ አድርጎ ከታገሰ የአላህን ውዴታ ያገኛል።ትዕግስት አጥቶ ከተቆጣ አላህም ይቆጣበታልና።
📚شرح رياض الصالحين (م١، ص٢٥٩)
❤11👍1
15 Oct 2025, 08:48 UTC≈3,780 views15 reactionsread 7 August 2026 አለባበስሽ እዳ ነው ወይስ ዒባዳህ?
🔅አላህ ያዘዛትን አለባበስ ትታ የፋሽንና የባህል አለባበስ በመልበስ ኢስላም እንድትሸፍነው ያዘዛትን የሰውነት ክፍል ገልጣ፣ ወይም ለስሙ ያክል ብቻ ስስና ጠባብ ልብስ ተጠቅማ ከቤት የምትወጣ ሴት በሄደችበት ሁሉ ወንጀለኛ ስትሆንና መላዕክትም ሲረግሟት፤ አላህ ﷻ እና መልእክተኛው ﷺ
ያዘዟትን ዓይነት ሙሉ ሒጃብ አድርጋ ምትንቀሳቀስ ሴት የትም፣ ምንም ላይ ሆና ዒባዳህ (ሰላት) ላይ እንዳለች ነው የሚቆጠረው (ትክክለኛ ሒጃብ በማድረጓ ሁሌም/ የትም ሆና አጅር ታገኛለች)።
ይህም ትክክለኛና የተሟላ ሒጅብ አላህን ﷻ የሚያስደስት ሥራና ልክ እንደ ሰላት፣ ጾምና ሐጅ ትልቅ ወደ አላህ የሚያቃርብ ዒባዳህ በመሆኑ ነው።
🔅ተገላልጦ…
❤9👌4👍2
11 Oct 2025, 05:26 UTC≈3,590 views17 reactionsread 7 August 2026 ✨አላህ የሚወደውን ባሪያ ይፈትነዋል✨
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፡-
ችግር ለሙዕሚን ብስራት ነው፦ በችግር ቢፈተን በፍፁም አላህ ስለሚጠላኝ ነው ብሎ ማሰብ የለበትም።ይልቁንም አላህ ለባሪያው ያለውን ውዴታ ማሳያ ምልክት ሊሆን ይችላልና።ምክንያቱም አላህ ባሪያውን በሙሲባ ይፈትነዋል ባሪያውም ከአላህ የሚያገኘውን ሽልማት ተስፋ አድርጎ ከታገሰ የአላህን ውዴታ ያገኛል።ትዕግስት አጥቶ ከተቆጣ አላህም ይቆጣበታልና።
📚شرح رياض الصالحين (م١، ص٢٥٩)
❤15👍2
6 Oct 2025, 05:49 UTC≈3,900 views17 reactionsread 7 August 2026 ✍ዛሬ ምን ሰራሁ?
ዛሬ ምን ሰራሁ ብለን ራሳችንን ጠይቀን እናውቃለን? በእያንዳንዱ ቀን ራሳችንን መገምገም አለብን ሁሌ አዲስ ቀን ሲሰጠን ለኛ ትልቅ እድል ነው። በተሰጠን ቀን ስናስበው ደስ የሚለን አንድ መልካም ነገር አለን?
عن عمر بن الخطاب - رضي الله عنه - أنه
قال : " حاسبوا أنفسكم قبل أن تحاسبوا ، وزنوا أعمالكم قبل أن توزنوا
👉ኡመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየላሁአንሁ እንዲህ ይላሉ፦ አሏህ ፊት ከመተሳሰባችሁ በፊት ራሳችሁን ተሳሰቡ፣ እርሱ ፊት ከመመዘናችሁም በፊት እራሳችሁን መዝኑ::
🍀🍀🌿🌱
❤17
30 Sept 2025, 06:23 UTC≈4,000 views18 reactionsread 7 August 2026 ከሰለፎች አንደበት
~
ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ "እስቲ ዱንያን ግለፅልን?" ተብለው ተጠየቁ።
* ''ላስረዝም ወይስ ላሳጥር? " አሉ።
- "አይ አሳጥር" አሏቸው።
* "ሐላሏ ሒሳብ አለበት። ሐራሟ እሳት አለበት" አሉ።
[አዙህድ፣ ኢብኑ አቢ ዱንያ፡ 17]
ወዳጄ! ከሐራም ተቆጠብ። በሐላል ሪዝቅህ ደግሞ አላህ ግዴታ ያደረገብህን ግዴታ ተወጣ። ባልተገባ ቦታ አታውጣው። ገንዘብ ለማይጠቅምበት ቀን ለነገ ስንቅ የሚሆንህ ኸይር ስራ ላይ ተካፈልበት።
❤17🥰1
24 Sept 2025, 15:50 UTC≈4,070 views32 reactionsread 7 August 2026 ሴት ልጅ በህይወቷ ሁሉ የምታገኘው
ትልቁ ምስክርነት ጥሩ ሚስት እንደሆነች
ባሏ ሲመሰክርላት «እና «የጥሩ ልጆች »
«እናት ነች ስትባል » ነው።
👍17❤15
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @neshida_tube. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.