27 Jan 2026, 05:01 UTC609 views16 reactionsread 8 August 2026 ኢየሱስ
በጥፋተኞች እናዝንባቸዋለን ፤ ጌታ ግን ያዝንላቸዋል።ስለጎዱን እናለቅሳለን ፤ ኢየሱስ ግን በጥፋታቸው ስለሚጎዱ ያለቅስላቸዋል።ሰላም ስላሳጡን እናባርራቸዋለን ፤ እርሱ ግን ሰላም ሆኖ ይሰበስባቸዋል።ስለጣሉን እናዝንባቸዋለን ፤ እኛን በመጣል ስለወደቁ ያዝንላቸዋል።መልኩ እዝነት ነው።ኃጢአተኛውን አይገፋም።ሁሌም ደጁ ክፍት ነው።ርኅራኄው አልቆ አያውቅም።ለወደቁት ይራራል።በየማለዳው የምህረቱ ብዛት ምድርን ይሸፍናል።በቸርነቱ ያቆማል።ይደግፋል።ያጸናል።ዳግመኛም ያበረታል።ብርታት የሌላቸው በእርሱ ይበረታሉ።ደካሞችም ይጸናሉ።እጁ ሁሉን ትረዳለች።ክንዱም ታጸናለች።ከወንድም በላይ ይጠጋጋል።ከእስትንፋስ ይልቅም ቅርብ ነው።የተረሱትን ያስታውሳል።ለተጠቁት ሁሉ ያዝናል…
❤16
7 Oct 2025, 05:25 UTC≈1,090 views10 reactionsread 8 August 2026 በሮች ሁሉን ክፍት እንዳልሆኑ መረዳት ያስፈልጋል።ዝግ በሮች መዓት ሲሆኑ ለምን እኔን ከማለት መቀበልን መምረጥ ይገባል።አስቂኙ እና የሞኝ የህይወት መርህ በሮች ሁሉ ክፍት ሆነው እንደሚጠብቁን ማሰብ ነው።ይህ ግን ላይሆን ይችላል።እግዚአብሔርም ሁሉን በሮች ከፍቶ የሚሰጥ ሳይሆን የሚያስፈልገንን ብቻ የሚሰጥ ነው።አንዳንዶች የምትለምኑትን አታውቁም ተብለዋልና።ምን እንደምንለምን አለማወቅ በመልሱ መቅረት እንድናዝን ያደርገናል።በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ስንሆን ግን ሁሉም በር ዝግ ሁሉምም በር ክፍት አይደለም።ተስፋ ስናደርግም በእውቀት ቢሆን ይመረጣል።አምላክ እውነተኛውን መንገድ ሲመራን የተዘጉ በሮችን ቢከፍትም አንዳንዴ ላይሆንም ይችላል።እምነት በነገሮች መቀየር ላ…
❤10
6 Oct 2025, 05:22 UTC859 views6 reactionsread 8 August 2026 ዮሐንስ 14:12
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
❤6
5 Oct 2025, 11:08 UTC789 views6 reactionsread 8 August 2026 የመጨረሻው ድንቅ መገለጥ ኢየሱስ ነው።በዘፍጥረት አንድ ላይ የተፈጠሩት ድንቅ አይደሉም ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ግን እሱ ድንቅ ነው።
❤6
2 Sept 2025, 21:25 UTC≈1,220 views20 reactionsread 8 August 2026 ትልቁ የህይወት ሕግ በከባድ ጉዳዮች ላይ ከብዶ መገኘት ነው።የክብደት መንገዱን ከኢየሱስ የጀመረ ደግሞ ከብዶ ጀምሯልና መቅለል አይቻለውም።
🔥19❤1
25 Aug 2025, 06:17 UTC≈1,010 views9 reactionsread 8 August 2026 በማን ስም እንጠመቅ? (ክፍል 1)
ስለ ጥምቀት በተነሣ ቁጥር በወንጌላዊያንና በሐዋርያት ቤተክርስቲያን አማኞች መካከል የሚደረገው ሙግት ጥምቀት በማን ስም መደረግ አለበት የሚለው ነው።ይህንንም መመርመር እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ለማወቅና ለመያዝ ይጠቅማል።በኢየሱስ ብቻ አማኞች እምነት ጥምቀትን በአብ፣በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማድረግ የተሳሳተ አመለካከት ነው።መጽሐፍ ቅዱሳዊም አይደለም የሚል ሙግት ይቀርብበታል።ስለሆነም በእነርሱ እምነት ጥምቀት በኢየሱስ ስም ብቻ ነውና በሌላው ስም ከተደረገ ስህተት ነው ብለው ያምናሉ።እንደ ክርስቲያን ልንጠይቅ የሚገባው የመጽሐፍ ቅዱስን አስተማሪነት ስለሆነ ይህንን ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ መፈተሽ ያስፈ…
❤8👍1
24 Aug 2025, 10:02 UTC699 views6 reactionsread 8 August 2026 የሕግን ባህሪይ ያልተረዳ የኃጢአትን ባህሪይ አያውቅም።የኃጢአትን ባህሪይ ያልተረዳ ደግሞ የአዳኙን ባህሪይ አይረዳም።
ዮሐንስ ቡንያን
🔥5❤1
17 Aug 2025, 15:40 UTC896 views18 reactionsread 8 August 2026 እግዚአብሔር የአዳምን እርቃን ለመሸፈን የገፈፈው ቆዳ ከሞተ እንስሳ እንደሆነው የተስፋው ሙላት ሲገለጥም የሞተው ኢየሱስም ለተቀበሉት ሁሉ እርቃናቸውን የሸፈነ ልብስ ሆኗል።
❤18
14 Aug 2025, 19:20 UTC954 views7 reactionsread 8 August 2026 ``የአካሉ ጥላዎች''
ስድሳ ስድስት መጻሕፍትን የያዘው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን በተባሉ በሁለት ዐበይት ኪዳናት ይከፈላል።እነዚህ ኪዳናትም ሁለቱም ስለ ክርስቶስ ሲናገሩ የየራሳቸው የትረካ ዘይቤም አላቸው።ብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ ተስፋን ሲናገር አዲስ ኪዳን ደግሞ የተስፋውን መፈጸም ያበሥራል።በዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሆነው ይህንን ተስፋ በንግግራቸውም ሆነ በኑሯቸው የሚናገሩ ሰዎች ነበሩ።እነርሱም ለሚገለጠው አካል ጥላ የሆኑ የአካሉ ጥላዎች ናቸው።እነዚህም በኑሯቸውና በንግግራቸው ከክርስቶስ ጋር ያላቸው ግንኙነት የተስፋ ቃል ተናጋሪነታቸውን ያሳያል።ስለሆነም ``የአካሉ ጥላዎች'' በሚል ርዕስ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ በተከታታይነት እንማራለ…
❤7
12 Aug 2025, 10:39 UTC825 views10 reactionsread 8 August 2026 #አንደኛ_ሳይሆን_ምርጫ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደቀመዛሙርቱን ከወቀሰበት ምክንያቶች አንዱ #እምነት ነው።የእምነት እጦት የተሰጣቸውን እንዳያውቁና እንዳይጠቀሙበት አድርጓቸው ነበር።እምነት ቢኖራቸው ሊንዱት የሚችሉትን ትልቅ ተራራ እያሳያቸው እነርሱ ግን ሊያምኑት አልቻሉም ነበር።አለማመን ክርስቶስ እንዳይሠራ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ነው።አንዳንድ ጉዳዮች ያልተሳኩልን ምናልባትም ከእምነት ማጣታችን ሊሆን ይችላል።እግዚአብሔር ሲታመኑት የሚወድ አምላክ ነው።አንድ ወቅት ወደ ገደል እየተንሸራተተ ያለ አንድ ሰው አንዲት ቅርንጫፍ ይዞ ወደታችና ወደላይ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ይቆያል።ከዚያም እግዚአብሔር እንዲረዳው ይለምናል።እግዚአብሔርም …
❤10
5 Aug 2025, 04:55 UTC791 views17 reactionsread 8 August 2026 እርካታ ማጣት እየታገላችሁ ያላችሁ ወገኖች ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ። ዓለም የምታሰቃየው በመጀመሪያ የሚወዳትን ነው ። ወዳጅን የሚያውቀውን ፣ ወዳጅነትን የሚያከብረውን እግዚአብሔርን ተጠጉ ። “ሰይጣን ለወዳጁ አይሆንም” ሲባል ትሰማላችሁ ። በሰዎች ፊት ለማልቀስ ትልቅነታችሁ እንቅፋት ሆኖባችኋል ። ሳይታዘብ ድካማችሁን ለሚሰማው ጌታ በእንባ አዋዩት ። የእርሱ ገበያ መልካም ነው ። የማይገኝበት በረከት የለም ። የሚገርመው በክፍያ ያጣችሁትን ሰላም ከእርሱ ዘንድ በጸጋ ትቀበላላችሁ ።
❤17
4 Aug 2025, 18:02 UTC824 views17 reactionsread 8 August 2026 ሰላም ቅዱሳን በዚህ ቻናል ሲቀርቡ የነበሩ ትምህርቶች ተቋርጠው እንደቆዩ ይታወቃል።ከሰሞኑ የተቋረጡትንም ሆነ አዳዲስ ትምህርቶችን ማቅረብ እንጀምራለን።
ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!
👍16❤1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @naynan1123. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.