3 Aug 2026, 10:57 UTC≈1,570 views35 reactionsread 3 September 2026 Photo
ግመሉ ሁልጊዜ ከቤቱ ውጭ ስለሚተኛ ቅዝቃዜ ያሰቃየው ነበር። አንድ ቀን ግን በጣም ቀዝቃዛ ከመሆኑ የተነሳ መንቀሳቀስ ሲከብደው ወደ ድንኳኑ ጭንቅላቱን ሲያስገባ ባለቤቱም አዝኖ ፈቀደለት።
..
ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግመሉ አንገቱን አስገባ ባለቤቱ የውጭውን ስቃይ በማሰብ አሁንም ፈቀደለት። ቀጥሎ... ትከሻውን፣ ቀስ እያለም ሙሉ ሰውነቱን ወደ ድንኳኑ አስገባ። በመጨረሻም ድንኳኑ ቦታ ስለጠጠበው፣ የድንኳኑን ባለቤት ገፍቶ ወደ ውጭ በብርዱ ወረወረው።
...
አላስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች የምንሰጠው "ትንሽ የሚመስል" ፈቃድ ወይም ገደብ የሌለው መብት፣ በኋላ ላይ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውን ከራሳችን ቦታ ያፈናቅለናል። ትንሽ ስህተትን ወይም ጎጂ ልማድን ገና ሲጀምር ካ…
👍33🥰2
24 Jul 2026, 10:47 UTC≈2,170 views32 reactionsread 3 September 2026 Photo
መልዓከ ሞት ወደ አንድ ሰው ቤት ገብቶ "ልወስድህ ነው" ይለዋል። ሰውዬውም ቢደነግጥም እራሱን አረጋግቶ "መጨረሻችን ነውና ወይን እየጠጣን ፌሽታ እናድርግ" ብሎ ጋበዘው። ሞትም በሃሳቡ ተስማማ። ሰውዬው ግን በወይኑ ውስጥ የእንቅልፍ መድኃኒት ቀላቅሎበት ነበር።
...
መልዓከ ሞት ወይኑን ጠጥቶ እንደወደቀ፣ ሰውዬው የሞት ደብተር ላይ ስሙ ቁጥር የመጀመሪያ ላይ ተጽፎ አየ። ስሙን ከላይ አጥፍቶ ከደብተሩ መጨረሻ (ከስር) ላይ ጻፈው። መልዓከ ሞት ሲነቃ "እንዴት ግሩም ወይን ነው ጃል?" አለው።ሰውዬውም "ምንም አይደል" ብሎ መለሰ። ሞትም "ስላስተናገድከኝ ውለታህን ለመመለስ ዛሬ ሥራዬን ከላይ መጀመር ትቼ ከደብተሩ መጨረሻ (ከስር) እጀምራለሁ!" አለው። …
👍22❤10
22 Jul 2026, 19:57 UTC≈2,080 views25 reactionsread 3 September 2026 Photo
ንጉሱ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ቆንጅዬዋ ሚስቱን በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈት እና ሚስቴን አግባት…" ብሎት ፈረሱ ላይ ወጥቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው አቧራማ ንፋስ እንዳለ አየ። ቆም ብሎ ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየሮጠ ሲመጣ አየ።
...
"ምነዉ ምን ሆንክ ?" ብሎ ንጉሱ ጠየቀ። በጣም ከመሮጡ የተነሳ ትንፋሹ እየተቆራረጠ ጓደኛው ሙሳ "የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ" ሲል መለሰ።
....
"ምን?" ብሎ ንጉሱ አይቶት በድንጋጤ እና በመገረም አየዉ ቁልፎቹን ከመሞከሩ በፊት ለአራት ቀናት ይቅርና ለ አንድ ሰአት እንኳን አልጠበ…
❤12👍12🔥1
29 Jun 2026, 13:39 UTC≈2,950 views33 reactionsread 3 September 2026 Photo
እባቡ በጢሻ ውስጥ ሲሽሎከሎክ እና ሲታጠፍ ከበስተጀርባው የሚንቀሳቀሰውን የገዛ ጅራቱን የሌላ ጠላት ይመስለውና በደመነፍስ ተመርቶ ጅራቱን መዋጥ ይጀምራል! ወደ ውስጥ በዋጠው ቁጥር ግን የሚሰማው ህመም እየጨመረ ይሄዳል። እባቡ ግን ህመሙን እራሱ የፈጠረው ሳይሆን "ጠላት" እያጠቃው መስሎት በንዴት ይበልጥ በኃይል መዋጡን ይቀጥላል። በመጨረሻም ራሱን ጨርሶ በመዋጥ ሕይወቱ ያልፋል።
...
ይኸ ክስተት (ራስን መብላት) የሚባል ሲሆን፣ በአብዛኛው እባቦች በጣም ሲጨነቁ፣ አካባቢያቸው ሲሞቅ ወይም የእይታ መጋረድ ሲገጥማቸው የሚያደርጉት ስህተት ነው።
...
የማስተዋል ማነስ ጥፋትን ይጋብዛል። አንዳንድ ጊዜ የምናደርገው ነገር ማንነታችንንና የራሳችንን ወ…
👍22❤8🔥3
26 Jun 2026, 10:20 UTC≈2,810 views34 reactionsread 3 September 2026 Photo
አንድ አሳማ ጭቃ ውስጥ ሲንከባለል ቆይቶ ወጣ። መንገድ ላይ ሲጓዝም በአጋጣሚ ከአንድ ግዙፍ ዝሆን ጋር ተገናኙ። ዝሆኑም አሳማውን ሲያየው ወዲያው መንገድ ለቆለት አለፈ።
...
አሳማው በነገሩ ተደስቶ "ጉድ እዩ! ያ ግዙፍ ዝሆን ሳይቀር የሚፈራኝ እኔ ምንኛ ጀግና ነኝ!" እያለ በትዕቢት ይፎክር ጀመር።
...
ይህን የታዘቡ ሌሎች እንስሳት ዝሆኑን ጠጋ ብለው ጠየቁት። "ለመሆኑ አንተን የሚያህል ግዙፍ የተከበረ ፍጡር አሳማ መሰል አነስተኛ እንስሳ መንገድ እንዴት መንገድ ለቀቀለት?"
..
ዝሆኑም "እኔ እኮ አሳማውን ፈርቼው አይደለም፤ ቆሻሻው እንዳይነካኝ ብዬ ነው!" አላቸው።
..
ሰዎች ርቀው የሚሄዱት ስለፈሩ ሳይሆን 'ቆሻሻ' አስተሳሰብና ንግግር እ…
❤20👍14
25 Jun 2026, 12:03 UTC≈2,490 views30 reactionsread 3 September 2026 Photo
ጅቡ አህያውን ሊበላው አሯሯጠው፤ ሊደርስበት ግን ፈጽሞ አልቻለም። ቢል ቢል ቢጫንቀው... ዞር አለና "ይኸ አህያ በጤናው ነው? አብዷል እንዴ?!" አለ ይባላል።
...
በሕይወትህ ውስጥ ብዙ ሰው ሊጥልህ፣ ሊያቆምህና ሊያሸንፍህ ይሮጣል። በጥንካሬህና በጥረትህ እጅ አልሰጥ ስትለው ግን፣ በራስህ ብቃት ያመለጥከው አይመስለውም።
...
የገዛ ድክመቱንና ያንተን ጥንካሬ አምኖ ከመቀበል ይልቅ ስም ሊሰጥህ ይሞክራል፤ "ቡዳ ነው"፣ "አሰርቶ ነው"፣ "ዕድለኛ ነው" እያለ ያማሃል።
..
ዋናው ነገር አንተ ከሚያሯርጥህ "ጅብ" አምልጠህ ግብህ ላይ መድረስህ ብቻ ነው። ጅቡ ማውራቱን አይተውም፤ አንተ ግን መሮጥህን አታቁም!
👍19❤10🥰1
25 Jun 2026, 07:11 UTC≈2,320 views26 reactionsread 3 September 2026 Photo
አንድ አባት ወፍ ልጁን እንዲህ እያለ ሲመክረው "ልጄ ፤ ሰው የሚባለው ፍጡር እጅግ ክፉና ተንኮለኛ ነው። ጥሬህን እየለቀምክ በአጠገብህ ሲያልፍ ድንገት 'ዝቅ' ካለ ፈጥነህ ብረር። ምክንያቱም ዝቅ ያለው ድንጋይ አንስቶ ሊወረውርብህ ሊሆን ይችላልና!"
...
የወፉ ጫጩትም በረዥሙ አሰበና እንዲህ ሲል ጠየቀ። "እሺ አባባ፣ ይሁን! ግን ዝቅ ሳይል ድንጋዩን አስቀድሞ ከኪሱ ይዞ ቢመጣስ?" አባትየውም ልጁን እያየ "ልጄ እኔ የነገርኩህ የኔን ዘመን ችግርና መፍትሔ ነው። አንተ ደግሞ ለዚህ ለተራቀቀው ለዘመንህ አዲስ አስተሳሰብና ጥንቃቄ ጨምርበት" አለው።
...
የትናንት መፍትሔ የዛሬን አዳዲስ ፈተናዎች ሙሉ በሙሉ አይፈታም። ዘመን ሲቀየር የክፋትም ሆነ የችግሮች…
👍17❤7👌2
21 Jun 2026, 05:15 UTC≈2,490 views20 reactionsread 3 September 2026 Photo
በአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል ውስጥ አንድ መጽሐፍ የሚያነብ ወጣት አየሁ። ከሌሎቹ ታማሚዎች የተለየ ሆኖ ስላገኘሁት ቀረብ ብዬ "እንዴት እዚህ ልትገባ ቻልክ?" ስል ጠየቅኩት።
...
ልጁም መጽሐፉን ዘጋና እንዲህ ሲል መለሰልኝ። "አባቴ እንደሱ ሀኪም እንድሆን ፈለገ፤ እናቴ እንደ ወንድሟ ነጋዴ እንድሆን ተመኘች። እህቴ ታዋቂ አርቲስት እንድሆን ስትገፋፋኝ፣ አያቴ ደግሞ የሃይማኖት አባት እንድሆን ይጸልይ ነበር። እኔ ግን የራሴ ህልም ነበረኝ። የሁሉንም ፍላጎት ለማርካት ስታገል ግን በመጨረሻ ራሴን አጣሁት። አዕምሮዬ ሲታወክ ግን ሁሉም ተስማምተው እዚህ አስገቡኝ። አሁን ግን በጣም ደስተኛ ነኝ! ምክንያቱም እዚህ ቦታ ማንም 'ይሄንን ሁን' የሚለኝ የለም። እዚህ …
👍13❤7
20 Jun 2026, 18:13 UTC≈2,370 views26 reactionsread 3 September 2026 Photo
ወጣቱ መምህሩን "ስለ ፍቅር እና ጋብቻ ንገረኝ ።" አለው። መምህሩም "ወደ ስንዴ ማሳው ሂድና ረዥሙን ስንዴ ቁረጥ፤ ህጉ ግን ወደ ኋላ መመለስ አትችልም።" አሉት።
....
ወጣቱ ሄዶ ባዶ እጁን ተመለሰ። "ምነው?" አሉት። "በጣም የሚያምር ስንዴ አግኝቼ ነበር፤ ነገር ግን ‘ከዚህ የተሻለ አገኝ ይሆናል’ ብዬ አልፌው ሄድኩ። ወደፊት ስሄድ ግን የተሻለ አላገኘሁም፤ ወደ ኋላ መመለስ ደግሞ አይቻልም።"አላቸው። መምህሩም እንዲህ አሉት። "እንግዲህ ፍቅር ማለት ይህ ነው! ምርጡን ዕድል (ሰው) እያየህ፣ ‘ከዚህ የተሻለ አገኝ ይሆናል’ በሚል ስግብግብነት አልፈኸው ትሄዳለህ። ነገር ግን ጊዜው ካለፈ በኋላ ያጣኸው ነገር ምን ያህል ውድ እንደነበር ይገባሃል።"
.…
👍18❤8
18 Jun 2026, 09:22 UTC≈2,270 views23 reactionsread 3 September 2026 Photo
አንድ ጊዜ የአንድ መንደር ሰዎች ዝናብ እንዲዘንብ ለመጸለይ ወሰኑ። በጸሎቱ ቀን ሁሉም ተሰበሰቡ፤ ነገር ግን ጃንጥላ ይዞ የመጣው አንድ አነስተኛ ልጅ ብቻ ነበር። ይህ እውነተኛ እምነት ነው።
...
አንድ ዓመት ሕፃንን ወደ ላይ ወርወር ስታደረገው በፍርሃት ፈንታ ይስቃል፤ ምክንያቱም አባቱ (ወላጁ) መልሶ እንደሚያቅፈውና እንደማይጥለው ሙሉ በሙሉ ያውቃል። ይህ መተማመን ነው።
...
በየሌሊቱ ለመተኛት ወደ አልጋችን ስናመራ፣ በማግስቱ ጠዋት በሕይወት ለመንቃታችን ምንም አይነት የፅሁፍ ዋስትና የለንም፤ ነገር ግን የማለዳውን ፀሀይ ለማየት በማሰብ ነገን በብዙ እቅዶች እናስባለን። ይህ ተስፋ ነው።
...
ዛሬም፣ ነገም በህይወታችን እምነት፣ መተማመን እና ተስ…
❤16👍5🔥2
16 Jun 2026, 14:55 UTC≈2,280 views19 reactionsread 3 September 2026 Photo
አንድ ፈላስፋ ከሙላ ናስሩዲን ጋር ሊከራከር ቀጠሮ ይይዛል። በቀጠሮው ቀን ናስሩዲንን ቢጠብቅ ናስሩዲን ሳይመጣ ይቀራል።ፈላስፋውም በንዴት ወደ ናስሩዲን ቤት ሄዶ በሩ ላይ የማይረባ ደደብ ብሎ ጽፎ ይሄዳል።
ናስሩዲን ሲመለስ ጽሑፉን አይቶ ወደ ፈላስፋው ቤት ሄዶ፣ 'ቀጠሯችንን ረስቼ ነበር፤ ስምህን በሬ ላይ አይቼ ነው ያስታወስኩት' አለው።
...
ከእውነት ፍለጋ ይልቅ በክርክር ማሸነፍ የሚጠመድ ሰው ከንቱ ድካም ውስጥ ይወድቃል። ጥበበኛ ሰው ሌሎችን ከማሸነፍ በፊት ራሱን ለማወቅ ይጥራል።
😁9👍6❤4
16 Jun 2026, 08:53 UTC≈2,120 views12 reactionsread 3 September 2026 Photo
አንድ አባት ልጁን ሁልጊዜ ሲመክረው ጠንካራ እና ጀግና እንዲሆንለት በማሰብ ፣ መስመርህን የሚያልፍ ሰው ሁሉ አትታገስ፣ በሀይልም ቢሆን ክብርህን አስጠብቅ፤ ምታው!" እያለ አሳደገው።
...
ልጁ ችግርን በሃይል ብቻ መፍታት እንደሚቻል አምኖ አደገ። አንድ ቀን ግን አባት በሆነ ነገር ተናዶ ልጁን ክፉኛ ተቆጣው። በዚህ ጊዜ ልጁ አባቱን እንደ ወላጅ ሳይሆን "እንዳስቸገረው ሰው" ድንጋይ አነሳና አባቱን መትቶ ገደለው።
...
ልጁ ለፍርድ ቀረበ። ዳኛው በቁጣ "እንዴት የገዛ አባትህን ትገድላለህ?" ሲሉ ጠየቁት።
ልጁ "ክቡር ዳኛ፣ አባቴ ‘የሚያስቸግርህን ሁሉ በለው’ እያለ ነው ያሳደገኝ። በዚያች ሰዓት አባቴ በጣም አስቸግሮኝ ነበር፤ ታዲያ ከመምታት በቀ…
👍11❤1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @mirtyefkrtarikoch. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.