6 Aug 2026, 02:31 UTC791 views11 reactionsread 6 August 2026 ታዋቂው የእናታችን ኸዲጃ [ረዲየላሁ ዐንሃ] ንግግር ታላቅ የፍቅር እና የታማኝነት ትምህርት አለው።…
የአላህ ነቢይ [ﷺ] የመጀመሪያውን ወሕይ ከተቀበሉ በኋላ በፍርሃት ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ እናታችን ኸዲጃ [ረዲየላሁ ዐንሃ] እንዲህ በማለት አጽናናቻቸው፦
«كَلَّا وَاللَّهِ لَا يُخْزِيكَ اللَّهُ أَبَدًا...»
«በፍጹም አይሆንም! በአላህ እምላለሁ፣ አላህ ፈጽሞ አያዋርድህም፤ ዝምድናን ታፀናለህ፣ እንግዳን ታከብራለህ፣ ችግረኞችን ትረዳለህ፣ በእውነተኛ መንገድ ላይ በሚደርሱ ድንገተኛ መከራዎች ላይም ሰዎችን ታግዛለህ።»…
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
እነዚህ በጎ ሥራዎች ብዙ ወጪና ሀብት ይጠይቃሉ። ይህን ሁሉ ለማከናወን ነቢዩ [ﷺ]…
❤10🥰1
3 Aug 2026, 05:29 UTC387 views29 reactionsread 6 August 2026 «ዓኢሻ ሆይ! የተኛሽ መስሎኝ ልቀሰቅስሽ አልወደድኩም።»…
የአላህ መልክተኛ [ﷺ]
:
ይህ የሚያሳየው ነቢዩ [ﷺ] ከሰዎች ሁሉ የበለጠ ክብርና ማዕረግ ቢኖራቸውም፣ ከማንም በላይ የቤተሰባቸውም ሆነ የሰዎች ታዛዥነት ቢገባቸውም፣ ከእዝነታቸው የተነሳ ቤተሰባቸውን ከእንቅልፍ እንዳይረብሹ በጣም ይጠነቀቁ እንደነበር ነው።
ስለዚህም በቤት ውስጥ በዝምታና በረጋ መንገድ ይንቀሳቀሳሉ፤ ድምፃቸውን አያሰሙም፣ አይጮኹም። የረሕማኑ እዝነት!… 💚
اللهم صل وسلم على نبينا محمد ﷺ
❤29
29 Jul 2026, 19:17 UTC≈2,100 views8 reactionsread 6 August 2026 🌹 የረሕማን ስጦታ 🌹
ጊዜው ተፈቃሪው [ﷺ] የተወለዱበት ወርሃ ረቢዐል-አወል እንደመሆኑ በነቢያችን ሙሐመድ ﷺ ሲራ፣ በሱናቸው እና በስነ-ምግባራቸው ጊዜያችንን እናድምቅ።
«የረሕማን ስጦታ» የተሰኘችው ቻናል ስለ አላህ መልእክተኛ [ﷺ] ብቻ የምታሰራጭ የቴሌግራም ቻናል ናት።
📖 ሲራ
🌿 ሱና
❤️ ሸማኢል
✨ የተመረጡ ፋይዳዎች ይቀርቡባታል።
ወዳጆቼ ሊንኩን ከፍተው ይቀላቀሉን፤ ለሌሎችም ያጋሩ።
🔗 https://t.me/mercy_to_the_worlds
❤8
29 Jul 2026, 18:56 UTC≈1,850 views8 reactionsread 6 August 2026 ከማሊክ ኢብኑ አል-ሑወይሪስ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ተዘግቧል፦
«በዕድሜ የምንቀራረብ ወጣቶች ሆነን የአላህ መልእክተኛ [ﷺ] ዘንድ መጣን። ከእርሳቸውም ጋር ሀያ ሌሊት ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ﷺ] እጅግ አዛኝና ለስላሳ ልብ ያላቸው ነበሩ። ቤተሰቦቻችንን እንደናፈቅን ተረዱ፤ በቀዬዎቻችን ስለተውናቸው ቤተሰቦቻችንም ጠየቁን። እኛም ነገርናቸው። ከዚያም፦ 'ወደ ቤተሰቦቻችሁ ተመለሱ፤ እነርሱ ጋር ቆዩ፤ አስተምሯቸውም…' አሉን።»…
:
ዒልም መልካም ነው። የልብ ብርሃን፣ የመንገድ ቀንዲል፣ የጀነት ድልድይ ነው። ነገርግን እንደምታየው ነቢያዊው የዒልም አሰጣጥ እዝነት የተመላ ስለሆነ የተማሪውን ስሜትና ቀልብ የጠበቀ ነበር። «ለዓለማትም እዝነት አድርገን እን…
❤8
29 Jul 2026, 11:18 UTC≈1,670 views21 reactionsread 6 August 2026 ከእናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፦
«በአካሄድ፣ በሥነ-ምግባርና በጠባይ ከፋጢማ [ረዲየላሁ ዐንሃ] የበለጠ የአላህ መልእክተኛን [ﷺ] የሚመስል ሰው አላየሁም። ፋጢማ ነቢዩ [ﷺ] ዘንድ ሲገቡ እርሳቸው ይነሱላት ነበር፣ እጇንም ይይዙና ይስሙት ነበር፤ ከዚያም በተቀመጡበት ስፍራ ላይ ያስቀምጧት ነበር። እርሳቸው [ﷺ] እርሷ ዘንድ በገቡ ጊዜም ከተቀመጠችበት ትነሳላቸው ነበር፣ እጃቸውን ትይዝና ትስማቸው ነበር፤ ከዚያም በመቀመጫ ስፍራዋ ላይ ታስቀምጣቸው ነበር።»
ይህን ሐዲስ አቡዳዉድ እና ሌሎችም ዘግበውታል።
❤21
23 Jul 2026, 19:45 UTC≈2,260 views16 reactionsread 6 August 2026 የተወዳጁ ﷺ በዱዓ፣ በሶላት እና በሌሎች ዒባዳዎች ላይ የነበራቸው ሁኔታ ከነቢይነታቸው ግልጽ ማስረጃዎች መካከል አንዱ ነው።
ነቢይ ባይሆኑ ኖሮ –አላህ ልቅናና ክብሩን ባይሰጣቸው ኖሮ– በእነዚህ ዒባዳዎች ተጠምደው የሚታትሩት በሰዎች ለመታየት፣ ሰዎችን ወደ ራሳቸው ለመሳብ እና ለማስመሰል ብቻ በሆነ ነበር። በዚህ መጠን መትጋት፣ መልፋት፣ መጽናት እና ቀንና ሌሊታቸውን በሙሉ የሚቆጣጠር ተጋድሎ አያሳዩም ነበር። በቤታቸው ሲሆኑ የሚያደርጉት በሰዎች ፊት በግልጽ ከሚያሳዩት የሚያንስ በሆነ ነበር።
ነገር ግን የነቢዩ ﷺ ሁኔታ ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ነበር። በቤታቸው ውስጥ የነበራቸው ዒባዳ በሰዎች ፊት ከሚያደርጉት፣ በብዛትና በርዝመት ይበልጥ ነበር።
'የዓይናቸው ደ…
❤16
22 Jul 2026, 03:31 UTC651 views13 reactionsread 6 August 2026 «የነቢዩ ﷺ መላ ሁኔታ ከሁሉም በላይ የተሟላና ፍጹም ነበር። ጌታቸውን በማምለክ ላይ ፈጽሞ አይሰለቹም ነበር፤ የዒባዳው ብዛት በክቡር ሰውነታቸው ላይ ድካም ቢያመጣም እንኳ አይሰንፉም። ከእርሳቸው በሶሒሕ ሰነድ የተዘገበ ሐዲስ እንዲህ ይላል፦
«የዓይኔ ማረፊያና ደስታዬ በሶላት ውስጥ ተደርጓል።»
📚 ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒ [ረሒመሁላህ]
❤13
17 Jul 2026, 08:13 UTC848 views10 reactionsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤6😢4
12 Jul 2026, 09:29 UTC≈1,060 views5 reactionsread 6 August 2026 Video
Video, posted without a caption
❤5
18 Jun 2026, 19:37 UTC≈3,130 views14 reactionsread 6 August 2026 ሂጅራ...
ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ብቻ አይደለም፤ ከድክመት ወደ ጥንካሬ፣ ከጭቆና ወደ ክብር፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከፍጡር ወደ ፈጣሪ መመለስ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከመካ ሲወጡ ከፍርሃት አልሸሹም፤ ይልቁንስ ሂጅራ እንዲያደርጉ የወረደላቸውን የአላህ ትዕዛዝ ተቀብለው፣ በጌታቸው ተስፋ ተሞልተው፣ በመጻዒ ድሉ እርግጠኛ ሆነው ወጡ።…
ለዚህ እውነታ ማሳያ አለኝ።…
በጋራው ውስጥ ሳሉ ጠላቶቻቸው ደጃፉ ላይ ቆመው ነበር፤ ባልደረባቸው አቡበክርም [ረዲየላሁ ዐንሁ] በጭንቀት ተሞሉ። «…አንዳቸው እግራቸውን ለማየት ቢያቀረቅሩ ያዩናል።» በማለት ተሳቀቁ። እርሳቸው ግን እንዲህ በማለት ወዳጃቸውን አጽናኑ: ‐
«አትዘን፤ አላህ ከእኛ ጋር ነው!»
ይህ …
❤14
18 Jun 2026, 14:48 UTC856 views18 reactionsread 6 August 2026 «ምንም አናውቅም ነበር፤ አላህ ሙሐመድን [ﷺ] ላከልን። ከዚያም እርሳቸው ሲሰሩ ያየነውን እንሰራ ነበር።» ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር
❤17🥰1
3 Jun 2026, 19:23 UTC≈1,360 views17 reactionsread 6 August 2026 ከነቢዩ ﷺ ቃላት መካከል ልቦናዬ አብዝቶ የሚወደው፣ በጥማት የተንገበገበ ሰው ውሃ ሲያገኝ በስስት እንደሚጨልጠው መንፈሴን የሚያረካው፣ የዓይኔ እንባ ቢደርቅ እንኳ የእንባ ዶፍ የሚያራጨኝ፣ ነፍሴ በፍጹም ጥበቃ ውስጥ እንዳለች እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ፣ እምነትቴ እንዳይናድ የሚያጠናክርልኝ፣ የማይሸሽ መከታ እንዳለኝ እንዲሰማኝ የምታደርገኝ አንዲት ቃል አለች።…
:
እርሱም ተወዳጁ ﷺ ለእመቤታችን አስማእ ቢንት ዑመይስ [ረድየላሁ ዐንሃ] የተናገሩት ቃል ነው።
ባለቤቷ ሰይዲና ጃዕፈር ኢብን አቢ ጧሊብ [ረድየላሁ ዐንሁ] ከተሰዉ በኋላ ልጆቿ በድህነትና በችግር ውስጥ እንዳይወድቁ ስትፈራ፣ ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሏት፦
«በእነርሱ ላይ ድህነትን ትፈሪያለሽ? እኔ በዱንያም …
❤12🤔3👍2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @mercy_to_the_worlds. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.