26 Aug 2026, 17:51 UTC98 views3 reactionsread 28 August 2026 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን እህተ መላእክት ትባላለች?
እመቤታችን እህተ መላእክት ተብላ ትጠራለች፡፡ ሊቁ አባ ሕርያቆስ
እህተ መላእክት፣ እመ ሰማዕታት፣ ወእግዝዕተ ፃድቃን
እያለ ሲጠራት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ደግሞ
እህተ መላእክት ወእመ ኩሉ ሕዝብ … የመላእክት እህት የህዝቡ ሁሉ እናት
ብለዋታል፡፡ አባ ሕርያቆስም ሆነ አባ ጊዮርጊስ እመቤታችን የሰማዕታት፤ የፃድቃን የህዝቡ ሁሉ እናት ብለው ሲጠሯት እንዲው በራሳቸው ሳይሆን
እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ (ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል)
መዝ.86÷5 የሚለውን ፍፃሜው ለድንግል ማርያም የሆነውን ቃለ ትንቢት በማስታወስና
እነኋት እናትህ
ዮሐ.19÷25 በማለት ጌታችን ድንግልን በዮሐንስ ወኪልነት ከዕ…
❤3
24 Aug 2026, 20:24 UTC139 views6 reactionsread 28 August 2026 ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ አለ፦
በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት
መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡
የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን…
❤6
21 Aug 2026, 14:21 UTC221 views15 reactionsread 28 August 2026 Photo
ለማትኖሩበት ዓለም ደክማችሁ፣
ወደ ምትኖሩበት ዓለም፣ ባዶ እጃችሁን እንዳትሄዱ ተጠንቀቁ።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
❤8🙏4❤🔥3
20 Aug 2026, 17:49 UTC243 views5 reactionsread 28 August 2026 💥የተፈጥሮን ሕግ የለወጡ አምላካዊ ተአምራት
─━━━━━⊱✿⊰━━━━━─
መጽሐፍ ቅዱስ፦ ሰብአዊ አእምሮን ሊያስደንቁ የሚችሉ ፣ አልፎ ተርፎም ለማመን ሊከብዱ የሚችሉ ድንቅ ታሪኮችን የያዘ ፣ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት የሚመሰክር ቅዱስ መጽሐፍ ነው። እነዚህን ታሪኮች በስጋዊ ዓይን ተመልክቶ በምክንያታዊነት ብቻ ለመመርመር ለሚሞክር ሰው ለማመን ሊከብዱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእምነት ዐይን ተመልክቶ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ለሚያምን ሰው ግን የፈጣሪን ሁሉን ቻይነት እና አምላካዊ ኃይል የሚያስረዱ ድንቅ ምስክሮች ናቸው።
✍️ለምሳሌ፦
💥 ኤልያስ በሰረገላ እሳት ተሳፍሮ ብሔረ ሕያዋን አርጓል። (2ኛ ነገሥ 2፥11)
💥 አህያ ጌታዋን መክራለች። (…
❤4👍1
19 Aug 2026, 07:07 UTC308 views8 reactionsread 28 August 2026 ቡሄ፣ ጅራፍ ማስጮህ፣ ችቦ ማብራትና ሙልሙል ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (ቡሄ፣ ጅራፍ ማስጮህ፣ ችቦ ማብራትና ሙልሙል ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡
✞➜ ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ
አንድም ቡሄ፡ ቡ…
❤6🙏2
19 Aug 2026, 06:52 UTC163 views1 reactionsread 28 August 2026 ደብረ ታቦር ማለት ምን ማለት ነው? በዓሉን ለምን እናከብረዋለን?
ክፍል 2
በደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮቱን
የገለጠው እንዴት ነው?
ይህንን ከመገለጡ በምን ምክንያት ነው የሚለውን ማየቱ የተሻለ ነው፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠው በሦስት ምክንያቶች ነው፦
✍ነሐሴ ሰባት ቀን በቂሳርያ ደቀ መዛሙርቱን
ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?
ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ኤርምያስ ነው፣ ኤልያስ ነው፣ ዮሐንስ መጥምቅ ነው፣ ከነቢያት አንዱ ነው፣ ይሉሀል የሚል የተለያየ መልስ ተሰጥቶት
እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?
ባላቸው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መስክሯል፡፡
➤ በፍጡር ቃል የተመሰከረውን
በባሕርይ አባቱ ለማስመስከር
➤ ከነቢያ…
❤1
18 Aug 2026, 19:04 UTC139 views4 reactionsread 28 August 2026 👆የቀጠለ 👇
ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስ ስለ ዕለተ ሰንበት ሲናገር
ቅድስት ሆይ በየሳምንቱ ወደኛ ነዪ በአንቺ ደስ ይለን ዘንድ ለዘለዓለሙ
ሳምንት ማለት ሰባት ቀን ነው ከዚህ የተነሣ ሉቃስ በስምንተኛው ቀን ያለው በሰባተኛው ሲል ነው፡፡
✍በሌላ መልኩ ማቴዎስ በሰባተኛው ቀን ሲል ሉቃስ በስምንተኛው ቀን ማለቱ የወጡበትንና የተመለሱበትን ቆጥሮ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ መጽሐፍ የጎደለውን ሞልቶ የሞላውን አትርፎ መናገር ልማዱ ነው ይህንም በሚከተሉት ማየት እንችላለን፡፡
ሰሎሞን
ወነበርኩ ውስተ ከርሰ ዕምየ አሠርተ አውርሀ ርጉኦ በደም፣ (በእናቴ ማኅፀን በደም ረግቼ አሥር ወር ነበርኩ) ጥበ.7፥2
ብሏል ይህን ያክል ረጅም ቀን የመጨመር ልማድ ያለው መጽሐፍ በስምንተ…
❤3🙏1
18 Aug 2026, 18:54 UTC172 views3 reactionsread 28 August 2026 ደብረ ታቦር ማለት ምን ማለት ነው? በዓሉን ለምን እናከብረዋለን?
ክፍል 1
✍ ደብረ ታቦር፦ በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት (ታላላቅ) በዓላት አንዱ በዓለ ደብረ ታቦር ነው፣ ከዐበይት በዓላት የተመደበበትም ምክንያት በደብረ ታቦር የተገለጸው ምሥጢር ድንቅ በመሆኑ ነው፣ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ አንድ አንድ ጊዜ ለሁሉም፣ አንድ አንድ ጊዜ ደግሞ በከፊል ምሥጢራትን ገልጾላቸዋል፡፡
ከእነዚህም ምሥጢራት የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፦
➜ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን በቤተ አልዓዛርና በቤተ ኢያኤሮስ፣
➜ ምሥጢረ ቊርባንን እንዲሁ በአልዓዛር ቤት፣
➜ ነገረ ምጽ…
🙏3
18 Aug 2026, 09:44 UTC197 views7 reactionsread 28 August 2026 በሀዘን በችግር በልዩ ልዩ ክስተቶች ውስጥ ስትሆኑ
ይህን የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል አስታውሱ
“ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።”
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13
✥••┈┈••●◉ ስለ እምነቴ ◉●••┈┈••✥
❤4🥰2🙏1
17 Aug 2026, 12:35 UTC280 views9 reactionsread 28 August 2026 ካህናት አባቶች ለምን በእጃቸው ያሳልሙናል?
የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል? ይላሉ፣ ነገር ግን ሚስጢሩ እንደሚከተለው ነው።
የካህኑ እጅ እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው፣ በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው፣ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል፣ እኛም የተቀደሰውን የጌታ ሥጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለምን የቅዳሴው በረከትና፣ የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን
"ድንቅ መለኮታዊ ምስጢር " ማለት ይሄ ነው።
✞➜ አ…
❤6👏1🥰1🙏1
15 Aug 2026, 06:47 UTC293 views6 reactionsread 28 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤6
15 Aug 2026, 05:42 UTC290 views6 reactionsread 28 August 2026 ጥያቄያችን የማይጠቅመንና የምንጠፋበት መሆኑ አውቆ ቢከለክለንም አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ እንደሆነ አምነን ማመስገን ይኖርብናል፡፡
ከሱባኤ በኋላ ትኩረት ማድረግ ያለብን በሱባኤ ጊዜ እንጸልየው የነበረውን ዓይነት ጸሎት በመኖሪያ ቤታችን ለመልመድ መጣር ይጠበቅብናል፣ ምክንያቱም ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን መጠበቅ ያለብን በሱባኤ ወቅት ብቻ አይደለምና ሁሌም ልንተገብረው ይገባል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ ወለወላድቱ ድንግል ማርያም፣ ወለመስቀሉ ክቡር
✥••┈┈••●◉ ስለ እምነቴ ◉●••┈••✥
❤5🙏1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @menfesawitimert. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.