26 Sept 2026, 13:26 UTC485 views10 reactionsread 28 September 2026 Photo
አንበሳው በዛፉ ስር ተኝቶ እያለ፣ ድንገት አንዲት አይጥ በሰውነቱ ላይ እየሮጠች ስታልፍ ከእቅልፉ አባነነችው። አንበሳው በጣም ተናዶ ይዞ ሊጨፈልቃት ሲል አይጧም "እባክህ የጫካው ንጉሥ ሆይ! ማረኝ፣ ሳላስበው ነው፤ አትጨፈልቀኝ። አንድ ቀን እኔም ይኸን ውለታህን እመልስልሃለሁ" ብላ ለመነችው።
...
አንበሳውም በንግግሯ እየተገረመ "አንቺ ትንሽ ፍጡር እኔን ምን ልትረጂኝ ትችያለሽ?" እያለ አዝኖላት ለቀቃት። ከጥቂት ቀናት በኋላ አንበሳው በአዳኞች በተዘረጋ መረብ ውስጥ ገብቶ ተያዘ።
...
ሊያመልጥ ቢታገልም አልቻለም፤ በቁጣ ያገሳው ድምፁም ጫካውን ሞላው። ድምፁን የሰማችው ያቺ ትንሽ አይጥ በፍጥነት ወደ ቦታው ደረሰች። አንበሳውን በወጥመድ መያዙን …
❤10
26 Sept 2026, 13:01 UTC465 views7 reactionsread 28 September 2026 Photo
"አ-ፍ-ቅ-ሬ-ሻ-ለ-ሁ" የሚሉ ...ፊደሎች ተንዘርዝረው በከንፈሮቼ መሃል ወደ አየሩ ተበተኑ። አልደነገጠችም፤ እንደ ዘመኔ ዘመናይ ኮረዶች ዐይኗን በመገረም ብልጥጥ አላደረገችም፤ ከንፈሯን በመደነቅ ልዩ ክብ አልሰራችበትም።
...
እንዲህ አለችኝ።
"አየህ! ይኸን ስሜት እወደዋለሁ...ደስ ይለኛል...ያምረኛል..ደሞ የሚያፈቅር ልብ አለኝ። የሚያቅፍ እጅ አለኝ። ከንፈሮቼ መሳም ያምራቸዋል። ወጣትነቴ እሳቱ ውስጤ ይነድዳል...ከኔ ሰው ጋር መተኛትም መኖርም እወዳለሁ..እፈልጋለሁ...ጠዋት ስነሳ ፊቱን በፈገግታ የማየው ባል እንዲኖረኝ እንዲሁ...."
...
በጉጉት እየሰማኋት..ደሞ ምንድን ነው ይኸ ሁሉ እላለሁ...
...
"ታውቃለህ....ፈልጌ አጥቼ አውቃለሁ…
❤5🥰2
25 Sept 2026, 07:58 UTC620 views9 reactionsread 28 September 2026 Photo
አረጋዊው በሞት አፈፍ ላይ እያሉ፣ ደቀ መዛሙርት አልጋቸው ዙሪያ ተሰብስበው በሐዘን ያለቅሱ ነበር። ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ "መምህር የሕይወትን ምስጢር ከማረፍዎ በፊት ይንገሩን!" ሲል ተማፀነው።
....
አረጋዊውም በምልክት እንዲቀረቡ አደረጉና በጥቂቱ ፈገግ ብለው እንዲህ አሉ፤ "እባካችሁ ያንን ውጭ ያለው ወፍ ሲዘምር ስሙት።" ደቀ መዛሙርቱ ደንግጠው ጸጥ አሉ።
...
በግቢ ውስጥ በሚገኝ ዛፍ ላይ አንዲት ትንሽ ወፍ በደስታ ትዘምር ነበር። ለጥቂት ደቂቃዎች ሁሉም ያንን ድምፅ በዝምታ አዳመጡ።ከዚያም አስተማሪው ቀስ ብለው ዓይኖቻቸውን ጨፍነው "ያ ነው የሕይወት ምስጢር። ወፏ ለምን እንደምትዘምር ወይም የዘፈኗ ትርጉም ምን እንደሆነ አታስብም፤ ዝም ብላ ትዘ…
❤5👍2🥰2
18 Sept 2026, 10:30 UTC≈1,250 views17 reactionsread 28 September 2026 Photo
በሀገሪቱ ውሻን መብላት እስከ ሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። ታድያ አንድ ቀን አራት ሰዎች ከሚወዱት የቤት ውሻቸው ጋር ለአደን ይወጣሉ። ሆኖም ለቀናት ቢኳትኑም ምንም ግዳይ ባለማግኘታቸው ርሃብ ሊጨርሳቸው ሆነ።
...
ከመካከላቸው አንደኛው "ለምን ውሻውን በልተን አንተርፍም?" የሚል ሃሳብ አቀረበ። ይኸ ሃሳብ ሶስት ሰዎችን ያስማማ ቢሆንም አንደኛው አሻፈረኝ አለ። የተስማሙት ውሻውን በማረድ ጠብሰው በሉ።
...
ታድያ እንደአጋጣሚ ሆኖ ያልበላውም ምንም እንኳ ቢደካክምም ከሞት ተርፎ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ከዚያም አርፎ፣ የሚበላውን በልቶ ካገገመ በኋላ ሶስቱን ሰዎች "ውሻ በልተዋል።" ብሎ ከሰሰ።
...
ይኸን የሰሙ የሸንጎ ዳኞች ሶስቱን ሰዎች አስጠሩ…
❤13👍4
18 Sept 2026, 03:42 UTC≈1,160 views18 reactionsread 28 September 2026 Photo
አንበሳው ትንሿን አይጥ በመንገዱ አግኝቶ ሊጨፈልቃት ሲል አይጧ በከፍተኛ ቁጣ እና ጩኸት አከባቢውን አናወጠችው። አንበሳው በአግራሞት ሲመለከታት "ስማ አንተ አንበሳ ጀግና እና ሃይለኛ እንደሆንክ ነው የምታስበው? አርባ ቀን ስጠኝና ሰዎች በተገኙበት አንተ እና እኔ እንፋለም። ያን ጊዜ ማን እንደሚያሸንፍ ታያለህ።" አለችው።
...
አንበሳው ያልጠበቀው ንግግር በመሆኑ "እንዴት አንቺ እንዲህ ደፈርሽኝ?" አለ። "አርባ ቀን ብቻ። ውርደትህን ትከናነባለህ።" ብላ ኼደች። ሌሎችም እንስሳቶች በአግራሞት አይጧን ተመለከቷት።
...
አንበሳው ወደ ዋሻው ገብቶ ማሰብ ጀመረ። 'በምን ልታሸንፈኝ ትችላለች? እንዴት አርጋ ነው? በመርዝ ነው? በመተት ነው? በምንድን…
❤11👍7
14 Sept 2026, 10:26 UTC≈1,430 views25 reactionsread 28 September 2026 Photo
ሁለት የማይተዋወቁ ሰዎች ጫካ ውስጥ በድንገት ተገናኝተው እየተጓዙ ትንሽ የአልማዝ ሉል ተመለከቱ። ከሁለቱ አንደኛው ከመካፈል ይልቅ ብቻውን ለመውሰድ ተስገበገቦ አፈፍ አድርጎ አነሳ። በዚህ ማሃልድንገት ግን ፊት ለፊታቸው አንድ የተራበ ነብር ተከሰተ።
...
ስግብግቡ ሉሉን ሲወስድ ያኛው ከመቆም ይልቅ፣ በፍጥነት ቁጭ አለና የጫማውን ገመድ ማጥበቅ ጀመረ። ሁለተኛው ሰውዬ በድንጋጤ እያየው፣ "ለመሆኑ የጫማህን ገመድ ብታስር ነብሩን በሩጫ መቅደም የምትችል ይመስልሃል?" አለው።
..
የጫማውን ገመድ የሚያስረው ሰው ቀና ብሎ "አይመስለኝም! እኔ እሱን መቅደም አይጠበቅብኝም፤ ዋናው አንተን መቅደም ነው!"
....
አብሮህ በህይወት መንገድ የተገኘ ሁለለ ወዳጅህ…
❤21👍4
14 Sept 2026, 07:37 UTC≈1,350 views11 reactionsread 28 September 2026 Photo
ታታሪ እና ጎበዝ አራሽ ነው፤ ዕድሜው ለትዳር ሲደርስ አባቶች አጭተው አንዲት ቆንጆ ኮረዳ አጋቡት። ታዲያ ሙሽራዋ ውበቷ እንጂ ሙያዋ ያልተጠበቀ ነበር፤ ምግብ ማብሰል ፈፅሞ አታውቅም ፤ በጣምም ደተኛ ናት። በመሆኑም ዘወትር ጠዋት፣ ማታ ለእራት አቀራርባ የምታበላው የበቆሎ ንፍሮ ብቻ ነበር። ሆኖሞ ባሏ ልአልተማረረም። ጠንክሮ ይሰራል፤ ይለፋል፤ ያገኘውን ንፍሮ በልቶና ውኃ ጠጥቶ አምላኩን እያመሰገነ ይተኛል።
...
በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ፣ ባለቤቱ በድንገተኛ ሕመም ተይዛ በሞት ተለየችው። ባልም በሐዘን ተሰበረ፤ "ሚስቴን ከቤቴ ውጭ አልቀብራትም!" ብሎ ለያዥ ለገናዥ አስቸገረ። እንደተመኘውም በቤቱ ውስጥ ቀበራት። እሱም ማቅ ለብሶ፣ ከስቶ ከሰውነት ተራ ወጣ…
❤7👍3👏1
12 Sept 2026, 04:49 UTC≈1,390 views20 reactionsread 28 September 2026 Photo
አንድ ሰው እስከ 40 ዓመቱ ድረስ በጣም ጥሩና በጎ ነገሮችን እየሠራ ኖረ። ከዚያ በኋላ ግን ለ30 ዓመታት ሙሉ በሕይወቱ ተስፋ ቆርጦ በየቀኑ ሲሰክርና ሕይወቱን ሲያባክን ኖረ። በመጨረሻም በ70 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ላይ ግን ታሪክ "ይህ ወንድማችን በተወለደ በ40 ዓመቱ አርፏል።" ብሎ ተነበበ።
...
እውነተኛ ሕይወት ማለት በሥራ፣ በበጎነት፣ በሰላምና በትርጉም የምንኖርበት ዘመን ነው። የቀሩት 30 ዓመታት ግን በስካርና፣ ሃላፊነትን በመሸሽ ያለፉ በመሆናቸው በሕይወት እንደመኖር ሳይሆን እንደ ሞት የሚቆጠሩ ናቸው።
. . .
አንዳንድ ጊዜ እኛም ዕድሜያችንን በቁጥር ብቻ እንቆጥራለን። ነገር ግን ዋናው ጥያቄ "ስንት ዓመት ኖ…
👍12❤7🤔1
11 Sept 2026, 11:44 UTC≈1,460 views35 reactionsread 28 September 2026 Photo
አባት ሆይ!
ስለ ፀሐዩ እናመሰግናለን፣
ስለ ንፋሱ እናመሰግናለን።
ስለሰጠኸን፣
ስላልሰጠኸን፣
ስላለፈው፣
ስላላለፈው፣
ስለሚመጣው፣
ስለምትሰጠን ተስፋ፣
ስለ ወራቶቹና ስለ ቀናቶቹ...እንዲሁም ስለሚመጣው ሁሉ!
አባት ሆይ፣ እናመሰግንሃለን!
🌼 መልካም አዲስ ዓመት የምወዳችሁ ሆይ! 🌼
❤21🙏10👍2🥰2
1 Sept 2026, 05:27 UTC≈2,100 views25 reactionsread 28 September 2026 Photo
አንድ አዳኝ ውብ ወፍ ይይዝና ሊያርዳት ሲዘጋጅ ወፏ "ብትበላኝ አትጠግብም፤ ነገር ግን ካስመለጥከኝ በሕይወትህ የሚጠቅሙህን 3 ትልልቅ ምክሮች አስተምርሃለሁ።" አለችው።
...
አዳኙም ተስማምቶ እጁ ላይ እያለች የመጀመሪያውን ምክር እንድትነግረው ጠየቃት። ወፏም፡ "የማይቻሉና ሊሆኑ የማይችሉ ነገሮችን ጨርሰህ አትመን!" አለችው። ሰውዬውም ጥሩ ምክር ስለመሰለው ለቀቃት። ወፏን የዛፉ ቅርንጫፍ ላይ ሆና ሁለተኛውን ምክር እንዲህ ስትል ነገረችው ፡"ያለፈውን ነገር አትቆጭ፤ የሌለን ነገር አትመኝ!"
...
አዳኙም "ሶስተኛው ምክርስ?" ብሎ ጠየቃት። ወፏም " ሶስተኛውን ከመንገሬ በፊት በሆዴ ውስጥ 300 ግራም አልማዝ ነበረኝ፤ ብታርደኝ ኖሮ ሀብታም ትሆን ነበር…
❤25
31 Aug 2026, 10:28 UTC≈1,850 views27 reactionsread 28 September 2026 Photo
ገበሬውና ሚስቱ እሳት ዳር ተቀምጠዋል።
ባለቤቱ ወሬ ጀመረ "ቀጣይ ዓመት ያችን ጫካ መንጥሬ ፈረስ እገዛለሁ።"
...
ሚስት "እኔ ደግሞ እየጋለብኩ ወደ እናቶቼ ቤት እሄድባታለሁ!"ባል በንዴት አበደ። "ሳታስፈቅጂኝ በእኔ ፈረስ የምትሄጂው አንቺ ማን ነሽ?"
....
እሷም "የአንተ ንብረት የኔም አይደል እንዴ?" አለችው ።ጥሉ እየከረረ ሄደ...ሚስት "ሲጀመር ምን የወንድ ሙያ አለህና ነው ጫካ የምትመነጥረው?" አለች።
...
ባሏም ተነስቶ በጥፊ አጮላት! እሷም አልተቻለችም... በጥፊ መለሰችለት!በመጨረሻም ገና ያልተገዛ ፈረስን ምክንያት አድርገው ተደባደቡ፣ ደምም ፈሰሰ!
...
ብዙ ጊዜ ሰዎች እውነተኛ ችግር ሳይኖርባቸው፣ አልተፈጸመም በሚል ነገር ይጣላሉ…
❤21👍6
18 Aug 2026, 12:11 UTC≈2,560 views36 reactionsread 28 September 2026 Photo
የጅቡ አያት በድንገት አረፈ። ይኸን የሰሙ የአካባቢው አህዮች በጭንቀት ተዋጡ። "ለቅሶ ሳንደርስ ቀርተን 'ሀዘናችን አላሳዘናቸውም' ብለው ሌላ ጊዜ እንዳያጠቁን ግዴታ መሄድ አለብን" ብለው ተስማሙ። ሆኖም ወደ ለቅሶው የሚሄዱበት እጅ መንሻ አሳሰባቸው፤ ጅቦች ከሥጋ ውጭ አይበሉ ነገር!
...
አንዱ አህያ ተነስቶ "እጣ ጥለን ከእኛ አንዱን ለጅቦች እጅ መንሻ እንውሰድ" አለ። እጣው ሲጣል ግን አንዱ ጉልበተኛና ወደረኛ አህያ ላይ ወጣ። አህያውም "ማን ወንድ አባቱ ይነካኛል!" ብሎ ገገመ።
...
በዚህ ጊዜ ሌላ መላ መቱ "ለምን ሁላችንም ከንፈሮቻችንን ቆርጠን አንወስድላቸውም?"
ሀሳቡን ሁሉም ተቀበሉት። ከንፈሮቻቸውን ቆርጠው ይዘው የጅቦቹ ቤት ደረሱ። ጅቦቹ ከን…
❤25🥰7👍4
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @meadetibeb76. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.