16 Jul 2026, 16:59 UTC17 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
“አንድ የቻይና የቀርከሃ ዝርያ አለ … የቀርከሃውን ዘር ከተከልክ በኋላ ለ5 ዓመታት ያህል ምንም አይነት እድገት አታይም - ከትንሽዬ እብጠት መሰል ነገር በቀር !! በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ የቀርከሃው እድገት መሬት ውስጥ ነው፡፡ ቀርከሃው እጅግ ውስብስብ የሆነ ሥሩን ይዘረጋል፡፡
ልክ አምስተኛ አመቱ እንዳበቃ ግን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ 25 ሜትር ይመነደጋል !!!
ሁሌም እንደሚሆነው ያየው ሁሉ አጀብ ይላል፡፡
በሕይወታችን፣ በሙያችን እና በሌላ ሌላውም የሚያጋጥሙን አብዛኞቹ ነገሮችም ልክ እንደዚህ የቻይና ቀርከሃ ናቸው፡፡
ጊዜና ጉልበትህን አፍስሰህ፣ ሰርተህ፣ ለፍተህ … ባጠቃላይ ለእድገትህ አስፈላጊ ነው ያልከውን ሁሉ ነገር አድርገህ ለሳምንታት፣ ለወራት ምናል…
❤1
Signed ሮሐ
13 Jul 2026, 16:06 UTC30 views1 reactionsread 8 August 2026 https://youtu.be/GLyF3EiG50s?si=iLO_qFlYzmvnqhZx
ወገን አንድ ቁምነገር ልንገራችሁ ...?
እዚህ በሚገኘው የ YouTube link ገባ ገባ እያላችሁ ትምህርት ውሰዱ ...videoውንም like comment subscribe አድርጉት ::
#love
#life
#fblifestyle
❤1
Signed ሮሐ
11 Jul 2026, 08:31 UTC33 viewsread 8 August 2026 ንቃት
[ ፍራንዝ ካፍካ ፣ ትርገጓሚት፦ ሙሉ ወርቁ ]
ፈረሴን ከጋጣው እንዲያመጣልኝ አዘዝኩ።አሽከሩ አልረዳኝም፣ እኔ ራሴ ወደ ጋጣው ገባሁና ፣ ኮርቻውን ጭኜ ተፈናጠጥኩ። በርቀት ጥሩምባ ሲነፋ እሰማለሁ፣ ምን ማለት እንደሆነ ጠየኩት። ምንም አያውቅምና ፣ ምንም አልመለሰም።
በሩ ላይ አስቁሞ "ጌታዬ ወደ የት ነው የምትጋልበው?" ሲል ጠየቀኝ
"አላውቅም ከዚህ መራቅ ብቻ ፣ ያለማቋረጥ ከዚህ መራቅ፣ ግቤ ላይ መድረስ የምችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።" አልኩ።
"ግብህን ታውቀዋለህ ማለት ነው?" ጠየቀ።
"አዎ" መለስኩ፣ "ተናገርኩ እኮ ከዚህ መራቅ፣ እሱ ነው ግቤ።"
"ምንም ስንቅ አልያዝክም።"
"ምንም አልፈልግም፤ ጉዞው ከመርዘሙ የተነሳ በመንገድ …
Signed ሮሐ
9 Jul 2026, 07:05 UTC34 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሲራክ እስክንድርን፡ ትኩር ብሎ ሲመለከተው ከቆየ በኋላ «ለመሆኑ ስለምንድነው የምትፅፈው?» ብሎ ጠየቀው ፡፡
«ምን ማለትህ ነው?»
«ድርሰት እወዳለሁ»
ጥሩ ግን ድርሰት፡ ፍቅር ብቻውን በቂ አይደለም፡፡
«ድርሰት ተልዕኮም አላት ፡፡»
«ያንተ ድርሰት ተልዕኮ ምንድነው?»
«በድርሰትህ ምን ለመግለፅ ነው የምትፈልገው ?»
«ሀቅ ፡ውበት ፡በድርሰት ሌላ ምን የሚገለፅ ነገር አለ?»
«የማን ሀቅ፡ የማን ውበት?»
....
( በዓሉ ግርማ ፡ ደራሲው)
#books
#love
#fblifestyle
❤1
Signed ሮሐ
6 Jul 2026, 06:25 UTC34 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
እንቅልፍ ሳትወዱ ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ተግታችሁ ሥራችሁን ፈጽሙ ። እኔ እናንተን ስለአመንኩ እናንተም የምታምኑትን ፣ ገንዘብ የማይወደውን፣ ድኻ የማይበድለውንና የሚረዳችሁን ሰው እያመለከታችሁኝ ከሥራው በመግባት መንግሥታችንን እርዱ
ዳግማዊ_ዐፄ_ምኒልክ
#books
#love
#fblifestyle
❤1
Signed ሮሐ
4 Jul 2026, 15:34 UTC30 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
Welcome 🤗አዳም... !!!እምንወደው አዳም ረታ በአዲስ ልቦለድ!
ከብዙ ናፍቆት ጋር!!!
---
መዝሙረ ሄላም!!!
#books
#love
#fblifestyle
❤1
Signed ሮሐ
2 Jul 2026, 12:24 UTC35 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ጋብሮቮ ወደ ሩቅ መንደር ሄዶ ሲመለስ ብርቱካን ይዞ መጣ፡፡ የመንደሩ ሰዎች “ብርቱካን ስጠን”፣ “ስጠን” እያሉ አስቸገሩት፡፡
ጋብሮቮው እንዲህ አላቸው ፡- “የሰፈሬ ህዝብ ሆይ! የእኔን በጣት የምትቆጠር ብርቱካን ከምትለምኑ ለምን ከዋናው ቦታ ሄዳችሁ እንደ እኔ ፋንታችሁን አትወስዱም?”
…. የሰፈሩ ሰዎችም፤ “ዋናው ቦታ ወዴት ነው?” አሉት፡፡
ጋብሮቮውም፤ “ማዶ ያለው መንደር ብርቱካን በነፃ እየታደለ‘ኮ ነው!”
“አትጠራጠሩ ይልቅ ቶሎ ብላችሁ ሩጡ፡፡ በገፍ እየተሰጠ ነው!”
ህዝቡ ጋብሮቮው ያለውን በማመን ወደተባለው መንደር መሮጥ ጀመሩ፡፡ መንገድ ላይ ያሉ ሌሎች ሰዎች የሚሮጡትን ሰዎች ይጠይቋቸዋል፡፡ “ወዴት ነው የምትሮጡ…
❤1
Signed ሮሐ
27 Jun 2026, 18:08 UTC46 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።
የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
❤1
Signed ሮሐ
24 Jun 2026, 12:57 UTC48 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
የሰው ልጆች የሚተዳደሩት በውሸት አንቀልባ ታዝለው ነው። ውሸት ሂዱ ከእኔ ራቁ ብትላቸው መግቢያ ቀዳዳ የላቸውም። በውሸት ውስጥ ስናልፍ ከነነፍሷ በድመት መንጋጋ ውስጥ እንደገባች አይጥ አይነት ህይወት እንኖራለን። በድመቷ ጥርሶች ተቆንጥጣ የተንጠለጠለችው አይጥ እስከምትሰለቀጥ ድረስ በህይወት መኖሯን እንደፀጋ ትቆጥራለች። መላመጥና መውዋጧ ግን አይቀርም። በውሸት እቅፍ ውስጥ መደላደልም እንዲህ ነው። እቅፏ አባብሎ እስከሚያፍነን የመተንፈሻ እድል የተሰጠን ይመስለናል። የባከኑ ሰከንዶች ያክል እንኖራለን።
በተቃራኒው እውነት ምንጊዜም ገፊ ሀይል ናት። እንደወርቅ በእሳቱ ሳትፈትሸን የራሷ አታደርገንም። በግዛቷ ላይ ከሰፈርን በኋላም መፈናፈኛ የለንም። የማርያም መ…
❤1
Signed ሮሐ
23 Jun 2026, 18:15 UTC52 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
ለ ... እናንተው ....!
ዓይነ ስውሩ መንገድ ዳር ተቀምምጦ ከእግሩ ስር ባርኔጣውን አስቀምጧል፤ አጠገቡ ደግሞ «እኔ ዓይነ ስውር ነኝ፣ እባካችሁ እርዱኝ» የሚል ፅሁፍ ያለበት ካርቶን አስቀምጧል።
...
በመንገዱ የሚያልፉት ሰዎች ግን ዞር ብለው እንኳ አያዩትም ነበር። ባርኔጣው ውስጥ ጥቂት ሳንቲሞች ብቻ ነበሩ። ድንገት አንድ ሰው ወደ ዓይነ ስውሩ ጠጋ ብሎ ካርቶኑን አነሳውና ከጀርባው ላይ አዲስ ጽሑፍ ጽፎለት መንገዱን ቀጠለ።
..
ከዚያ በኋላ በዚያ የሚያልፉት ሰዎች ሁሉ መቆም ጀመሩ። ሁሉም ሰው ባርኔጣው ውስጥ ገንዘብ ይጥልለታል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ባርኔጣው በገንዘብ ተሞላ።
...
ከሰዓታት በኋላ ያ ሰው ሊጠይቀው ተመለሰ። ዓይነ ስውሩም የእግሩን ኮ…
❤1🥰1
Signed ሮሐ
23 Jun 2026, 15:26 UTC29 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
" ማናቸዉም ኢትዮጵያዊ ትክክል
መብት እንዲኖረዉና የተወደደ ህዝባችን
ሁሉ የአንድ ትልቅ ቤተሰብ ተወላጆች ሁነዉ
በወንድም አማችነት እኩል እንዲኖሩ ዘወትር
የተከተልነዉ ዓለማ ነዉ "
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
#books
#love
#fblifestyle
❤2
Signed ሮሐ
23 Jun 2026, 14:26 UTC28 viewsread 8 August 2026 Photo
ተይው -እንተወው !
..
የዘመን ቃፊሩን ማለፍ አልቻልንና ፤
ይህ ዓለም ጥበቱ አልመጠነንና ፤
ተይው እንተወው..
ውጥኑ ግብ ይሁን ጅማሬው ፍፃሜ ፤
ቅፅበቷ ሙሉ ዕድሜሽ ወቅቷ ዘላለሜ !
© ደበበ ሰይፉ 📖
#books
#love
#fblifestyle
Signed ሮሐ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @mayimiran. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.