8 Aug 2026, 14:22 UTC905 views16 reactionsread 3 September 2026 ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)
በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ወጣቶች የአካል ብቃት ፉክክር ሲያደርጉ በቲክቶክ ሳይ ደስ ይለኛል ፤ የሆነ ቦታ ጡንቻቸውን በስሚንቶ በተበጀ ዳምቤል ያጠጠሩ፣ ከወገባቸው በላይ የተራቆቱ ጎረምሶች ወደ ካሜራው አየሾፉ እንዲህ ይላሉ፤ ‘ ኢስቲ ወንድ ናን የሚል ካሌ ኢሂንን ቻሌንጂ ይሞኪር፤ የኛ ጀማ! ማኒንም አይሰማ ! “
ስክሮል ሳደርግ ሌላው ቡድን ከሆነ አካባቢ ብቅ ይላል፤ የቡድኑ መሪ በዳጉሳ ቂጣ ዳጎስ ያለውን ደረቱን እየመታ ‘’ እስቲ ይህንን ደረት አጣብረው፤ ሰባ አመት ብትማስን ምታመጣው ይመስልሀል፤ የልምጥ ልይ ! የኛ ዠማ ! ማንንም አያምጥ፤ ደሞ ሸር ኮቢሊንክ ማረግ እንዳይዘነጋ” የ…
😁13❤3
31 Jul 2026, 08:10 UTC≈1,280 views10 reactionsread 3 September 2026 =የምድረበዳ በረከት =
አንዲት ብርጭቆ ወይን
አንዲት ጤፍ እንጀራ እንዲት አሪፍ ቅኔ
እነዚህ ባሉበት በምድረበዳ ላይ ቁጭ ካልሽ ከጎኔ
ሌላው ምን ይሰራል
ምድረበዳው ሁሉ ዓደይ ለብሶ ያድራል።
በዕውቀቱ ስዩም (የማለዳ ድባብ )
https://t.me/matter_of_facts
❤10
27 Jul 2026, 18:18 UTC≈1,460 views18 reactionsread 3 September 2026 እስቲ ዛሬ ደግሞ ለለውጥ ያክል አለቃ ክንፌ የላኩልኝን ግጥም መሳይ ምክር ልጋብዛችሁ!
(ለለጅ ምክር የአባት መታዘቢያ)
ልዠ ሆይ!
ሙቫይልህን አስቀምጥ
ምክሬን አድምጥ !
ጦርነትን የሚጠምቀው
እድሜውን ብትጠይቀው
የማቱሳላ ገራዥ
የአብርሀም ዣንጥላ ያዥ
በጎሽ ያረሰ
አዳምና ሄዋን ገምጠው የተፉትን በለስ አንስቶ የጎረሰ
የሎጥን ሚስት ሀውልት የላሰ
ሆኖ ታገኘዋለህ ፤
ልዠ ሆይ!
ጦርነትን የሚያውጀው
ያረጀው ነው የጃጀው
ግና ጦርሜዳ ላይ የሚዋጋው
ያንተ ብጤ ነው ለጋው፤
ሜሲ አንደመታት ኩዋስ ወደ መቃብር የሚልለጋው፤
ልዠዋ!
በጀግኖች ዘመን እንኩዋ-“ከመሞት መሰነበት” ይባላል
የሰማእት ሀውልት ሆኖ ተመቆም
ህያው ሆኖ መተኛት ይሻላል
ልዠ ሆይ!
በሀያ…
👏10❤6😁2
25 Jul 2026, 13:09 UTC≈1,320 views7 reactionsread 3 September 2026 ምክሩ
(በእውቀቱ ስዪም)
የሆነ ጊዜ ላይ ምኡዝ ሰፈሩ በሚገኘው ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ በማኪያቶ ነፍሱን በማስደሰት ላይ ነበር፤ ካጠገቡ ሶስት ወጠምሻዎች አንዱን ጠረጴዛ ከበው ሻይ ቡና ይባባላሉ ፤ አንደኛው ሰውየ የባጥ የፎቁን ያወራል፤ አፉን በከፈተ ቁጥር ከውስጡ ከፍተኛ ጠረን እየተመዘዘ ይወጣና የእናት አገራችንን ንጹህ አየር ይበክለዋል፤
ምኡዝ የሰውየው ጉዋደኞቹ በጠረኑ ተመርዘው አለመሞታቸው አስደነቀው፤ ማሽተት የተሳናቸው ሰዎች መኖራቸውን አወቀ ፤ የኒህ ሰዎች አፍንጫ ዋና ጥቅም ፊታቸውን ለሁለት መግመስ እንደሆነ ገባው፤ ከራሱ ጋራ ትንሽ ሲሙዋገት ከቆየ በሁዋላ “ወንድሜ አንዴ ብቻህን ላናግርህ “አለውና ወደ ጉዋሮ ወሰደው፤
…
❤6😁1
25 Jul 2026, 06:55 UTC≈1,030 views12 reactionsread 3 September 2026 ወጣቶች ነበርን
በእውቀቱ ስዩም
ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ
ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ
ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ
ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤
ወጣቶች ነበርን
ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን
ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን
ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤
በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን
ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤
ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ
ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ
ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን
የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን
ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ
ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ
የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ
ምትቀበለን ፣ እየመሰለን
ከቁመታችን፤ በላይ የዘለልን፤
ወጣቶች ነበርን
ዛሬ እንደዋዛ
ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን፤
htt…
❤11🤔1
20 Jul 2026, 12:34 UTC≈1,350 views21 reactionsread 3 September 2026 የጋራ ድል
(በእውቀቱ ስዩም)
የስፔን ደጋፊ ብሆን ምን ያስገርማል? ስፔን በስነፅሁፍ አክብራ የጋበዘችኝ አገር ናት፤ ስፔን ሁለተኛ አገሬ ናት ብል ኩሸት አይሆንም፤
ስፔን እንድታሸንፍ ፈልጊያለሁ፤ ያም ሆኖ፣ ከጉዋደኛየ ከካሳ ጋራ አር-ጄንቲና ታሸንፋለች ብየ በአራት ሺ ብር ተወዳደርሁ፤ ስፔን ካሸነፈች እፈነጥዛለሁ፤ አርጄንቲና ካሸነፈች ደግሞ ላብ ያልገነፈለበት ፣ እንቅልፍ ያልተሰዋበት አራት ሺ ብር አካውንቴን ያጠበድላል ብየ አሰብኩ፤ በሁለቱም በኩል አሸናፊው ነኝ የሚል መላ መጣልኝ፤
በመጨረሻ እንዳያችሁት ስፔን፣ በረኛ ሳይሆን በር የሆነውን የአርጀንቲናን ግብጠባቂ ጣጥሳ አገባች፤ ዋንጫውን ጨበጠችው፤ደስ አለኝ፤ግን ደስታየ…
😁16❤5
11 Jul 2026, 19:10 UTC≈1,700 views38 reactionsread 3 September 2026 ኦሮማን
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠና…
😁17👍6🤣6❤5👎2👏2
8 Jul 2026, 10:56 UTC≈1,650 views24 reactionsread 3 September 2026 በረንዳ
(በእውቀቱ ስዩም)
ባለፈው ከያሬድ ሹመቴ እና ከምኡዝ ጋራ የሆነ ምግብ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ምሳ ስንበላ አንድ ጎስቆል ያሉ አዛውንት መጡና “ልጆቸ ርቦኛል “አሉን
ምኡዝ ፣ “ካለ ይስጥዎት” አላቸውና መብላቱን ቀጠለ፤
ያሬድ ምኡዝን ክፉኛ ገላመጠውና’ ‘ አባቴ ቁጭ በሉና ከኛ ጋር ይብሉ” ብሎ ጋበዛቸው፤
እኔ አዛውንቱ እንዲበሉ ፈልጊያለሁ፤ ግን አብሮ መብላቱን ልቀበለው አልቻልኩም፤
ስለዚህ “በልተን ሲበቃን የተረፈውን እንሰጣቸዋለን” የሚል ለጽድቅ የማያበቃ ለኩነኔም የማይዳርግ ሀሳብ አቀረብኩ፤
ያሬድ ግን አመረረ “ሂዱና ታጥበዎ ይምጡ አባቴ” አላቸው፤
ምኡዝ በንዴት ጨሰ፤ “ለምን ሜቄዶኒያ ቁጥር 2 ብለህ አትከፍ…
😁11❤9🤣4
8 Jul 2026, 06:20 UTC≈1,350 views16 reactionsread 3 September 2026 (ተስፋዬ ሀይለማርያም)
ባሻዬ! ምክር ቤታችን የሥራ ዘመኑን ጨረሰ አሉ? ምክር ቤቱ በ5 ዓመቱ ውስጥ የዶክተር ደሳለኝ ጫኔን የፀጉር ዕድገት ያህል እንኳን ሳያድግ ተሰናበተ።
በአንድ አገር ውስጥ የሚገኙ የምክር ቤት አባላት ስብሰባ ላይ አንዱ የምክር ቤት አባል እጁን አውጥቶ እንዲህ አለ፣
" የተከበሩ አፈ ጉባዔ፣ ከዚህ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ግማሾቹ ደደቦች ናቸው"
"የተከበሩ የምክር ቤት አባል፣ ንግግሮ ትክክል አይደለም። ከአንድ የምክር ቤት አባል አይጠበቅም። እባክዎን ንግግሮን አስተካክለው ይናገሩ!"
"እሺ የተከበሩ አፈ ጉባዔ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ንግግሬንም አስተካክዬ እናገራለሁ። ከዚህ ምክር ቤት አባላት ውሰጥ ግማሾቹ ደደቦች አይደሉም "…
😁8❤5🤣2👍1
29 Jun 2026, 18:37 UTC≈1,810 views31 reactionsread 3 September 2026 አልፎሂያጅ ትዝታ
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰሞኑ የምርቃት ሰሞን ስለሆነ ነው መሰል የግቢ ትዝታ ተቀሰቀሰብኝ፤
ከማይረሱኝ የዶርማችን ተማሪዎች አንዱ ሚኪያስ ነበር፤ ረጅምና ጎበጥ ያለ ነው፤ ለምንም ነገር ትግስት አልነበረውም፤ ለምሳሌ ካፌ ወረፋ መጠበቅ አይሆንለትም ፤ በጊዜው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ምግባቸውን በወረፋ አንዲያነሱ አይገደዱም ነበር፤ ሚኪ በጥቁር ገበያ የገዛውን ጥቁር መነጥር ገድግዶ ፣ በበትር ወለሉን እየዳበሰ ሰልፉን ጥሶ ይገባና ምሳውን ይረከባል ፤
መጀመርያ አጭበርባሪነቱን እያየሁ፣ ምን አይነት ይሉኝታ ቢስ ሰው ነው እያልሁ አስበሳጭበት ነበር፤ እየቆየሁ ግን እኔም የወረፋ ሰልፍ እየሰለቸኝ መጣ፤ ከጥቂት ቆይታ በሁዋላ…
❤15🤣14👍2
22 Jun 2026, 13:15 UTC≈1,800 views8 reactionsread 3 September 2026 ቅንጦትን ስሻ
(በእውቀቱ ስዩም)
ለነገ አይልም ፣ ከላይ ሲያዳላ
ላንደኛው ቴስታ፣ ለሌላው ቴስላ፤
እኔም በፈቃድ፣ ዝተት ለብሼ
በፎቆች መሀል፤ ድንኩዋን ቀልሼ
ቃርሚያ ፈጭቸ፤ ኩርማን ጋግሬ
ጎመን አስግሬ
እንጀራ አጥምጄ
በቃኝ ማለትን ፣ተለማምጄ
ስኖር፣ ከሌላው፣ አያዳላልኝ
ቅንጦትን ስሻ፣ አንቺን ላከልኝ::
https://t.me/matter_of_facts
❤4😁4
18 Jun 2026, 15:04 UTC≈2,140 views20 reactionsread 3 September 2026 ሁኔታው
(በእውቀቱ ስዩም)
ድሮ ልጅ እያለን ‘ንግድ የጀመርኩት አንቁላል በመሸጥ ነው’ የሚሉ ባለሀብቶች በጎረቤት ቲቪ ይታዩ ነበር፤ አሁን ጎልምሸ ሳስበው ‘ እኮ አንዴት?’ እያልሁ ራሴን እጠይቃለሁ፤ ይሸጡት የነበረው እንቁላል ምናልባት የድራጎን እንቁላል ይሆን ?
የዘንድሮ ኑሮ ሰውን ሁሉ ባለ አምስት ኮከብ ስስታም አድርጎታል፤ ባለፈው ስድስት ኪሎ ካምፓስ ግቢ ውስጥ ጥገኝነት አግኝተው ከሚኖሩ ከሲታ ውሾች አንዱ የህግ ዲፓርትመንት አካባቢ የበቀለውን ሳር ሲቀማምስ አየሁት፤ የምሬን ነው፤ ከጥቂት አመታት በሁዋላ ያዲስአበባ ውሾች ባጠቃላይ ከበጎች ጋር ሳር መሻማት ይጀምራሉ፤ የዝግመተ-ለውጥ አሰራር አንዲህ ነው፤
መዲናይቱ ውስጥ ያሉ…
❤11😁8👏1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @matter_of_facts. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.