7 Aug 2026, 14:04 UTC152 views1 reactionsread 8 August 2026 ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሓ ወኑዛዜ
ኀበ ይረስእዎ ለላህ ወኢየሐልይዎ ለትካዜ
ማርያም ህሉት ውስተ ልበ አምላክ እምቅድመ ጊዜ
ትፍሥሕተሰ ተፈሣሕኩ በፍልሰትኪ ይእዜ
ገጸ ዚአኪ እሬኢ ማዕዜ ።
ሰላም ለሥጋሽ መፍለስ ወደ መረጋጋት እና ደስታ
ኀዘንን እና ትካዜን ከማያስታውሱበት ቦታ
ዘመን ቈጠራ ሳይታወቅ ዓለም ሳታምር ለምታ
ማርያም በልበ አምላክ ታስበሽ የኖርሽ በጌታ።
መደሰትንስ ተደስቻለኹ በፍልሰትሽ ቀን በእልልታ
"ፊትሽን መች ዐየው ይኾን?" እላለኹ ጧት ማታ።
መልክዐ ፍልሰታ (ትርጒም፥ ኤፍሬም የኔሰው )
https://www.youtube.com/live/r2SNyQ2ge_U?si=cjER6FN6M0ZZhiOz
❤1
Signed ይስሐቅ አ
7 Aug 2026, 07:34 UTC183 views1 reactionsread 8 August 2026 https://www.youtube.com/live/rGQ-qp64Lfc?si=scslcTErzfLvfJ3x
❤1
Signed ይስሐቅ አ
6 Aug 2026, 15:48 UTC257 views0 reactionsread 8 August 2026 በጾመ ፍልሰታ እናቶች በሚያምር ዜማ እመቤታችንን የሚያመሰግኑበት ስንኝ:-
"ወፌ ሰንብታ ሰንብታ፣
መጣች ለፍልሰታ፣
አገርሽ የት ነው?
ኤፍራታ፣
አሳድሪኝ ማታ፣
በክንፍሽ ጥላ ጋርደሸ
ከልጅሽ ስፍራ ወስደሽ፣
እንዳልቆምብሽ በግራ፣
እንዳያሰቃየኝ መከራ፣
ወፌ ነፍሴን አደራ
ወፌ ነፍሴን አደራ(2)"።
"ወዴት አለፈች ከመንደር፣
የእንቦሳው እናት ያች ጊደር፣
በእግዜር አሳዩኝ መንገዱዋን፣
እንድከተላት በኀዘን፣
እሳት አዝላ ወዴት ባከነች ከገሊላ፣
ባረፍሽበት ከዛፍ ጥላ፣
ሽፍቶች ከበቡሽ በዚያ ቆላ፣
ዓይኖችሽ ፈርተው ስለ እነሱ፣
እንባ ክረምትን አፈሰሱ፣
የኔ የኔ የባሪያሽ ይጥፋ ሁለት ዐይኔ፣
ባንቺ ፈንታ ግብጽ በስደት ልንገላታ፣
ዓለም ይጭነቀኝ ይጥበበኝ፣
እንደ …
Signed ይስሐቅ አ
6 Aug 2026, 15:48 UTC232 viewsread 8 August 2026 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ!!
Signed ይስሐቅ አ
3 Aug 2026, 12:12 UTC399 viewsread 8 August 2026 ሞተ ዘኢይመውት ፣ ሞተ ከመ ይስአሮ ለሞት ፣ ሞተ ከመ ያሕይዎሙ ለሙታን ።
የማይሞተው ሞተ ፤ ሞት የተባለ የሞት አበጋዝ ዲያብሎስን ከሥልጣኑ አዋርዶ ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ ፤ ሙታነ ሥጋን በተአምራት ሙታነ ነፍስን በትምህርት ያድናቸው ዘንድ የማይሞተው ሞተ ።
ቅዳሴ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በሞቱ ሞታችንን ደምስሶ ሕይወትን የሰጠን የሕይወት ባለቤት አምላከ ሰላም መድኃኔ ዓለም ለሀገራችን ሰላምን ለሕዝባችን ፍቅር አንድነትን ያውርድልን ።
Signed ይስሐቅ አ
2 Aug 2026, 19:33 UTC409 views4 reactionsread 8 August 2026 👉አርጤክስስ በሶስት ወርቅ የገዛት የዕንቍ ጽዋዕ ነበረች
(ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘቀዳሚት )
በዚህ ክፍለ ምንባብ ሊቃውንቱ እመቤታችንን በሸክላ በብርሌ በውድ ብርጭቆ መስለዋታል
ልሕኵት ንጽሕት ክብረ ኵሉ ዓለም። ድንግል ማርያም ሆይለሰው ሁሉ ክብር የምትሆኝ ንጽሕት ሸከላ።አንቺ ነሽ
ሐተታ ማለት በሊቃውንቱ አነጋገር ማብራሪያ ወይም በምስጢር መራቀቅ መመራመር ማለት ነው
በዚህ ክፍለ ምንባብ ልሕኵት ንጽህት የሚለውን ቃል ተጠቅመው ብሉይ የኤልሳዕን የንጉሡ አርጤክስስ ታሪክ አምጥተው ሲያመሰጥሩት እናያለን
👉ልሕኵት ንጽሕን ሞብርሌ፤ መርጠብ ብርጭቆ ብለው ተርጉመውታል
ዝምብሎ አይደለም አንጀት አርስ ምክንያት አላቸው
እንደሚከተለው ገልጸውታል
ሞ…
❤4
Signed ይስሐቅ አ
31 Jul 2026, 09:23 UTC454 views1 reactionsread 8 August 2026 ❤ ፀምር ዘጌዴዎን❤
❤እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌዴዎን በአውድማ ላይ በዘረጋት ብዝት ግምጃ ትመሰላለች (መሳ ፮÷፴፮)
✍ይኸውም የምድያም ሰዎች እስራኤልን በጠላትነት እጅጉን ባጠቋቸው ጊዜ፣መልአከ እግዚአብሔር ለጌዴዎን ተገልጾለት አንተ ጽኑ ኀይል ሰው እግዚአብሔር ካነት ጋር ነው አለው፣
ጌታም ሂድ እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን እንሆ ልኬሃለው አለው፣
እሱም መልሶ ለዚህ ምልክት አሳየኝ፣መሰዋዕት ልሠዋ ብሎ ሄደ መሥዋዕት ሠውቶ ሥጋውን በሌማት መረቁን በምንቸት ውስጥ አድርጎ አቀረበ፣ደንጊያውን ጸፍጽፎ እንጨቱን ረብርቦ በላዩ ላይ አደረገው፣ መልአኩም በዘንግ ቢነካው ተቃጥሏል፣ይኸውም ምሳሌ ነው፦
❤ እሳት=የመቅሠፍተ እግዚአብሔር
❤ሥጋው=የአሕዛ…
❤1
Signed ይስሐቅ አ
27 Jul 2026, 05:37 UTC525 views2 reactionsread 8 August 2026 https://www.youtube.com/live/7UxVbMZ6EIE?si=iXnY7W5lI8viw7Jx
❤2
Signed ይስሐቅ አ
26 Jul 2026, 10:19 UTC513 viewsread 8 August 2026 https://www.youtube.com/live/7UxVbMZ6EIE?si=BmGVhod42x018LVe
Signed ይስሐቅ አ
25 Jul 2026, 23:45 UTC530 views3 reactionsread 8 August 2026 [ሐምሌ 19 የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ዶሮዳስ ታደሰ
❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።
❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕ…
❤3
Signed ይስሐቅ አ
25 Jul 2026, 02:06 UTC642 views4 reactionsread 8 August 2026 ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ገብርኤል ሐምሌ ፲፱
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ:
አንቃዕዲዎ ሰማየ:
ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ:
ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ:
እጼውዓከ እግዚእየ:
ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር:
እጼውዓከ እግዚእየ:
ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር:
እጼውዓከ እግዚእየ:
ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።
ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል:
ሞገሰ…
❤4
Signed ይስሐቅ አ
23 Jul 2026, 05:00 UTC531 views2 reactionsread 8 August 2026 ሥርዓተ ዋዜማ ዘሐምሌ ገብርኤል "ሐምሌ ፲፱"
ዋዜማ
እስመ ተለዓለ ዕበየ ስብሐቲከ መልዕልተ ሰማያት:
እምአፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐተ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን:
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላህም ወኢብድብድ በሰብእ:
ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን:
በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ ወኢአባረ እክል:
ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ:
ወልደ አንጌቤናይት።
በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
ሰአል ለነ ሕፃን ቅዱሱ ለእግዚአብሔር:
ሰአል ለነ ሕፃን።
እግዚአብሔር ነግሠ
ሕጻን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምጻ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።
ይትባረክ
ሕጻን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ወስምዖሙ አጥፍኡ ኃይለ እሳት:
ወቦኡ…
❤2
Signed ይስሐቅ አ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @mariam6846. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.