10 Aug 2026, 04:04 UTC304 views14 reactionsread 12 August 2026 💫...
...... ግን ምን ያደርጋል ሁሉም የራሱን ስሜት ብቻ ያዳምጣል ስትደስት አብሮህ ይሆናል ሲከፋህ ትቶህ ይሄዳል....ግን ምንም ቢሆን ሁልጊዜም አንተ ለሰዎች መልካም ሁን ፈገግታህን አትንፈጋቸው፡፡ ምናልባት አምላክ ከነሱ የተሻለ ስላንተ የሚጨነቅና የእውነት የሚያስብልህን ጓደኛ ይሰጥህ ይሆናል፡ ሳይሆን በእርግጠኛነት ይሰጥሃል::✨🤗
#መልካም_ቀን 🤌
❤12🙏2
Signed ✞ 𝒴𝒾𝒹𝒾𝒹𝒾𝓎𝒶 ✞
9 Aug 2026, 20:31 UTC370 views10 reactionsread 12 August 2026 ወዳጄ አስታውስ🙂
ምን በእጅህ እንዳለህ ልብ በል፣ የያዝከውን ለማግኘት ላደረከው ጥረት ሁሉ አመስግን፡፡ እንዲሁም በሙሉ ከእጅህ እንዲወጣ አንድ ሰከንድ ብቻ በቂ እንደሆነ አስታውስ፡፡🤌
🙏5🔥3👍2
Signed ✞ 𝒴𝒾𝒹𝒾𝒹𝒾𝓎𝒶 ✞
9 Aug 2026, 14:15 UTC418 views6 reactionsread 12 August 2026 ነገን ኑረን ፥ ዛሬን ሞትን
ትላንትናን እየለፋን ፥
በቀደም 'ለት ተቀበርን
መሞቻና መሰንበቻው ፥
ሳይታወቅ የውል ፍቺው
ቀን ልንጨብጥ በቀናችን ፥
ቀን አስጣለን መኖራችን።
By ፍቅረ-ማርያም ተሾመ
👍5❤1
Signed ◡̈⃝ ቴ ኖ ቶ ር
9 Aug 2026, 08:27 UTC443 views8 reactionsread 12 August 2026 ❤️በሚወድህ ሰው ላይ ክፉ አትስራ
❤️ለሚፈልግህ ሰው ቢዚ ነኝ አትበል
❤️የሚያምንህን ሰው አታታል
❤️ሁሌም የሚያስታውስህን ሰው አትርሳ!!
❤️ቦታ ለሚሰጥህ ሰዉ ጊዜህን አትንፈገዉ!!
#መልካም_ቀን
👍6❤2
Signed ✞ 𝒴𝒾𝒹𝒾𝒹𝒾𝓎𝒶 ✞
ከመጽሐፍት መንደር💠 pinned «#ጥሪ_ወደ_ሞት ፡ ፡ #ክፋል_አንድ ፡ ፡ #በአህመድ_ሁስ(ሻድ) . . ጥሪ ፡ ወደ ፡ ሞት! እዚህ ሁሉም ነገር ደባሪ ነው። ነፍሴን ያቀፋት ስጋዬ ይደብረኛል። ቁሳቁሶቼ በመሉ ደባሪ ናቸው። ሁለት ርምጃዎችን ሰንዝሬ የምደርስበት ቁመቱ ከጉልበቴ በታች ርዝመቱ ደግሞ ወደ ሁለት ሜትር የሚጠጋው የእቃ መደርደሪያዬ እግሮቹ ተንሻፈዋል። የተኛሁበት ፍራሽ ይጎረብጠኛል። የተንተራስኩት ትራስ ጠረኑ እምክ እምክ ይላል።…»
8 Aug 2026, 18:16 UTC472 views15 reactionsread 12 August 2026 እጄን አፌ ላይ አድርጌ የራሴን ትንፋሽ መልሼ አሸተትኩት። ጠረኑ የተበላሸ አሳ አይነት ነው። የውስጤን ሀሳብ ነው ወደ ውጪ በትንፋሽ መልክ ያስወጣሁት። ከዚህም በላይ ቢሸት ግድ አይሰጠኝም። ምክንያቱም እዚህ ከማንም ጋር አላወራም። ትንፋሼ ከማንም አፍንጫ ስር አይደርስም። ቢደርስም ግድ አይሰጠኝም። ይሽተታቸው ካስፈለገ። እኔም የእነሱን ጠረን ሳሸት ኖሬያለሁ።
ለማንም ብዬ የምቀይረው ማንነት የለኝም። የተወለድኩት ራሴን ሆኜ ነው። እርቃኔን። ከልብስም ሆነ ከሀሳብም ንፁህ ሆኜ ተወልጃለሁ። የምኖረውም በራሴ ዓለም ነው። ዛሬ ተመልክቶኝ ነገ ለሚረሳው ገፅታዬ ምንም የምቀባባው ማሳመሪያ አልፈልግም። እንዲሁ ከተቀበሉኝ እሰይ። ካልሆነ ግን ገደል ይግቡ!
በመስኮቴ …
❤13👍2
Signed ◡̈⃝ ቴ ኖ ቶ ር
8 Aug 2026, 18:14 UTC398 views3 reactionsread 12 August 2026 #ጥሪ_ወደ_ሞት
፡
፡
#ክፋል_አንድ
፡
፡
#በአህመድ_ሁስ(ሻድ)
.
.
ጥሪ ፡ ወደ ፡ ሞት!
እዚህ ሁሉም ነገር ደባሪ ነው። ነፍሴን ያቀፋት ስጋዬ ይደብረኛል። ቁሳቁሶቼ በመሉ ደባሪ ናቸው። ሁለት ርምጃዎችን ሰንዝሬ የምደርስበት ቁመቱ ከጉልበቴ በታች ርዝመቱ ደግሞ ወደ ሁለት ሜትር የሚጠጋው የእቃ መደርደሪያዬ እግሮቹ ተንሻፈዋል። የተኛሁበት ፍራሽ ይጎረብጠኛል። የተንተራስኩት ትራስ ጠረኑ እምክ እምክ ይላል። የደረብኩት ብርድ ልብስ ትኩስ ደሙ ያልደረቀለት የከብት ቆዳ ይመስላል። የመስኮቱ መጋረጃ መቆሸሽ የሰው ልጆችን መልክ ይመስላል።
ሁሉም ነገር ደስ አይልም። ዓለም በጠቅላላ ደባሪ ሆናለች። ለእኔ የሚሆን ቦታ የላትም። በመኝታዬ የቀኝ ግድግዳ በኩል በሚገኘ…
❤3
Signed ◡̈⃝ ቴ ኖ ቶ ር
8 Aug 2026, 15:14 UTC411 views7 reactionsread 12 August 2026 ትንሣኤሽን ልየዉ
ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣
በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ።
ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣
ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ።
ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣
ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ።
ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣
አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ።
ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣
ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ።
እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣
ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ።
ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣
በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ።
እንኳን አደረሳችሁ🙏
✍ዔደን ታደሰ
❤6👌1
Signed ◡̈⃝ ቴ ኖ ቶ ር
7 Aug 2026, 17:26 UTC513 views13 reactionsread 12 August 2026 የሰይጣኑ ውድ መሣሪያ
ሰይጣኑ ሥራውን ለማቆም ወስኖ መሣሪያዎቹን በሙሉ ለሌሎች ሰይጣናት በሐራጅ ሊሸጥ ወሰነ። በመሸጫው ውስጥ ቅናት፣ ንዴት፣ ምቀኝነት፣ ውሸት፣ ፍርሃት እና ትዕቢት የመሳሰሉት መሣሪያዎች ተደርድረው እያንዳንዳቸው ዋጋ ተጠቅሶባቸው ነበር። ከአንዱ ጥግ ላይ ደግሞ እጅግ አሮጌ፣ የተወለወለ እና በብዙ አጠቃቀም ምክንያት ያለቀ የሚመስል አንድ ትንሽ መሣሪያ ተቀምጧል። ይህ ትንሽ መሣሪያ ግን ከመደብሩ ውስጥ ካሉት መሣሪያዎች ሁሉ በዋጋ እጅግ ውድ ነበረ።
...
አንድ ገዢ ሰይጣን ጠጋ ብሎ "ይህ ትንሽ መሣሪያ ለምን እንዲህ ውድ ሆነ?"ሲል ጠየቀው። "ሰይጣኑም ይህ መሣሪያ ‘ተስፋ መቁረጥ’ ይባላል! ሌሎቹ መሣሪያዎቼ በሙሉ የአንድን ሰው አእምሮ …
❤13
Signed ◡̈⃝ ቴ ኖ ቶ ር
7 Aug 2026, 11:30 UTC618 views8 reactionsread 12 August 2026 ጌታህ ስንት ያወጣል???✍️
ያ እንቁ..ያ ሽቶ ፣
ከእግሩ ስር ሲጣል
የይሁዳ ጥያቄ ፣
ይሄ ስንት ያወጣል??
ፐ !!...
ስንት ድሃ የታረዘ
መጠለያው የነቀዘ
በሞላበት በዚህች ዓለም
እግር ሽቶ ልክ አይደለም።
ፐ !! በሉ ለይሁዳ
ደግነት ለዳዳ።
* * * *
ከሰፊሮስና ከእንቁ ተንከራ
እኩል ተንጠባርራ
አንድ ዲናር ንራ
ትርምስ ባደለች ፣
በዚህች በውድ ዓለም
ሶስት መቶ ዲናርን
መስበር ልክ አይደለም!።
.
.
እውነት አለው አይደል?
.
…
❤7🔥1
Signed ◡̈⃝ ቴ ኖ ቶ ር
6 Aug 2026, 21:27 UTC568 views11 reactionsread 12 August 2026 💫💥
....ስለምትጓዙበት መንገድ፣ ስላላችሁ ነገር እርግጠኛ ሁኑ አጥብቃችሁም ያዙት መርምሩትም ኋላ ላይ በማይረባ ድንጋይ ጊዚያችሁን እንዳባከናችሁ ሲገባቹ በእጃቹ የነበረው እንቁ እንደነበር ከረፈደ እንዳትረዱ ተጠንቀቁ!! 💫✨
🔥9❤2
5 Aug 2026, 11:38 UTC763 views14 reactionsread 12 August 2026 አንዳንድ ጊዜ፣ ዝም ማለት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው። በሕይወት ሩጫ ውስጥ፣ ብዙ ጊዜ ወደፊት ለመራመድ፣ ውሳኔዎችን ለማድረግ እና በእያንዳንዱ ቅጽበት አዲስ ነገር ለማሳካት እየሞከርን ነው፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሰላምና ጸጥታ በጣም ኃይለኛ መልሶች ናቸው። ጸጥ ማለት አቅጣጫችንን ለማሰላሰል፣ ትንፋሻችንን ለመያዝ እና ልባችንንና አእምሯችንን ለማደስ እድል ይሰጠናል። ዝምታና ጸጥታ የድክመት ምልክቶች ሳይሆኑ የጥበብ ምልክቶች መሆናቸውን አስታውሱ። ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ ምንም አለማድረግ በጣም ጠንካራው እርምጃ ነው።💫
🔥11👍2👌1
Signed ✞ 𝒴𝒾𝒹𝒾𝒹𝒾𝓎𝒶 ✞
Showing the 12 most recent of 30 posts we hold for @manbabemulusewyaderegal. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.