25 Feb 2025, 12:45 UTC481 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
ኢዜማ የመንግስት አካላት በሚል በጠራቸው የፀጥታ ኃይሎች በአዲስ አበባ ውስጥ ወጣቶች እየታፈኑ እና የት እንዳሉ ማወቅ አሰቸጋሪ እየሆነ እንደመጣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል‼️
ባለፉት ጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ወጣቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየታፈኑ የት እንደገቡ ሳይታወቅ መሰወራቸውን ከቤተሰቦቻቸው እና ከተለያዩ አካላት ለመገንዘብ ችያለሁ ብሏል ኢዜማ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ዛሬ በሕግ መጠየቅ ያለበት የትኛውም ዜጋ በሕግ ሊጠየቅ የሚገባው ሕጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ ነው በሚል ዛሬ ሰፊ መግለጫ አስነብቧል፡፡
ባለፉት ጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ወጣቶች ኢዜማ የመንግ…
👍4❤2
Signed Never
25 Feb 2025, 12:38 UTC374 viewsread 8 August 2026 Photo
4 ልጆች በአንድ ጊዜ‼️
በዛሬው እለት 18- 06 - 2017 በጂንካ ጠቅላላ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ
* 2 ሴት
* 2 ወንድ
በአጠቃላይ 4 ልጆችን በሰላም የተገላገለች ሲሆን ልጆቹ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሆስፒታሉ ገልጿል።
4 ልጆች በአንድ ጊዜ 🥹
Signed Never
25 Feb 2025, 12:34 UTC360 views0 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባቋቋመው የክልሉ ጊዜያዊ ምክር ቤት ለመሳተፍ መወሰኑን አስታወቀ!
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባቋቋመው ጊዜያዊ ምክር ቤት እንደማይሳተፍ ከአንድ ወር በፊት አስታውቆ የነበረው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ በምክር ቤቱ ለመሳተፍ መወሰኑን አስታወቀ።በመግለጫው ላይ የተገኙት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አሉላ ኃይሉ “ጊዜያዊ ምክር ቤቱን የትግራይን ሁለንተናዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል መታገያ መድረክ ለማድረግ በምክር ቤቱ በመሳተፍ ለመታገል ወስኗል” ብለዋል።
ሳልሳይ ወያነ በጊዜያዊ ምክር ቤቱ ውስጥ “መካተት ያለባቸው ጉዳዮችን በመዘርዘር ሲያመላክት መቆየቱን” የገለጹት የፓርቲው የህገመንግስት እና የህግ ክፍል …
Signed Never
25 Feb 2025, 12:34 UTC288 viewsread 8 August 2026 Photo
በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር የሚያስችል መመሪያ ሊጸድቅ ነው‼️
በኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።
መመሪያው ደረጃውን የጠበቀ አሰራርን የሚከተል ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ማሟላት ያለባቸውን ደረጃዎችም ይወስናል።
በቅርቡም በባለሙያዎችና በባለድርሻ አካላት ማረጋገጫ ከተሰጠው በኋላ መመሪያው ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ42 ሺህ በላይ ምዝገባ ያጠናቀቁ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይገኛሉ። ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ደግሞ ያልተመዘገቡ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው …
Signed Never
25 Feb 2025, 12:31 UTC246 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምሽት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ።
ምሽት 4 ከ30 ሦስት ጨዋታዎች ሲደረጉ ብራይተን ቦርንማውዝን ያስተናግዳል።
አስቶንቪላ ከሜዳው ውጭ ከክሪስታል ፓላስ ሲጫወት ዎልቭስ ከፉልሃም ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
ምሽት 5 ከ15 ላይ ደግሞ ቼልሲ ከሳውዝሃምፕተን ጋር ይጫወታል።
ነገ አራት ጨዋታዎች ሲደረጉ በማግስቱ ሐሙስ ደግሞ ሁለት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል።
❤1
Signed Never
25 Feb 2025, 12:31 UTC225 viewsread 8 August 2026 Photo
በኢትዮጵያውያን እና በኬንያ አሳ አጥማጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት 22 ሰዎች መጥፋታቸው ተነገረ‼️
በኢትዮጵያና በኬንያ አሳ አጥማጆች መካከል በተፈጠረ የድንበር ግጭት 22 የሚጠጉ ሰዎች መጥፋታቸው የኬንያ ፖሊስ እና የሃገሪቷ የመንግስት ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ግጭቱ ቅዳሜ አመሻሽ ላይ በሎፔሙካት እና በናቲራ በኦሞ ወንዝ አቅራቢያ በኬንያ እና በኢትዮጵያ ድንበር ላይ መከሰቱን የኬንያ ቱርካና ካውንቲ አስተዳዳሪ ኤርሚያስ ሎሞሩካይ በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የቱርካና ካውንቲ ፖሊስ እሁድ እለት ወደ 22 የሚጠጉ ኬንያውያን አሳ አጥማጆች የደረሱበት አለመታውቁን የገለጸ ሲሆን 15 ጀልባዎችመሰረቃቸውን እና ስድስት የዳሰነች ተወላጅ የ…
Signed Never
25 Feb 2025, 12:29 UTC239 viewsread 8 August 2026 በኮንጎ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ‼️
በሰሜን ምዕራብ ኮንጎ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ዶክተሮች እና የዓለም ጤና ድርጅት በትላንትናው እለት ተናግረዋል ።
የበሽታው ምልክቶች እና ለሞት የሚያደርስበት ጊዜ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ጠባብ ነው የተባለ ሲሆን አብዛኛዎቹን በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሞት ዳርጓቸዋል ይህ በእውነት አሳሳቢ ነው” ሲሉ የግዛቱ የክትትል ማእከል እና የቢኮሮ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሰርጅ ንጋሌባቶ ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናግረዋል ።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው ይህ ምንነቱ ያልታወቀው ወረርሽኝ እ.ኤ.አ ጥር 21 ቀን የጀመረ ሲሆን 419 ጉዳዮች ተመዝግበው እስካሁ…
Signed Never
25 Feb 2025, 12:29 UTC214 viewsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Never
26 Jun 2024, 08:44 UTC516 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት እንዳልሰጠ ገለፀ
ድርጅቱ ዛሬ በኦንላይን ካደረገው ውይይት በመነሳት ባወጣው መግለጫ የአገሪቱን የመረጃ ጥበቃ ህግ መሰረት በማድረግ የደንበኞቹን ነፃነት እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በፍርድ ቤት አማካኝነት ካልታዘዘ በስተቀር ማንኛውንም የደንበኞቹን መረጃ ለሌላ አካል አሳልፎ እንደማይሰጥ ጠቅሷል፡፡
ጨምሮም እስካሁን ድረስ እንዲህ አይነት የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት አካል እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳልደረሰው አስረድቷል፡፡
👍1
Signed Never ️😍
6 May 2024, 16:57 UTC524 viewsread 8 August 2026 Photo
የመንግስት ሰራተኛው በኑሮ ውድነት በእጅጉ እየተፈተነ ነው
የኢትዮጵያ መንግስት ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ያቀረብኩት ጥያቄ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቀርቷል ብሏል።
ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበው ምላሽ አላገኙም ካሏቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ "ሠራተኞች አሁን እየተከፈላቸው ባለው የደመወዝ ክፍያ የኑሮ ዉድነቱን በፍጹም መቋቋም ያልቻሉ በመሆኑ ደመወዝ የገቢ የሥራ …
Signed Never ️😍
28 Apr 2024, 04:58 UTC457 viewsread 8 August 2026 Photo
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው ተባለ
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።
በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይፈተናሉ ብለዋል።
የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገል…
Signed Never ️😍
27 Apr 2024, 09:29 UTC380 viewsread 8 August 2026 Photo
ጊፍት ሪል እስቴት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በአጋርነት የመኖሪያና የንግድ አፖርታማ መንደሮች ግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ ተጣለ
የመጀመሪያ በሆነው እና በመንግስት እና የግል አጋርነት ልማት ፕሮግራም መሠረት 12 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ስምምነት መፈረማቸው ተገልጿል።
በዚህ ፕሮግራም ላይ በመጀመሪያ ዙር ሊገነባ የታቀደው የ4000 ቤቶች ግንባታ የማስጀመር ስነ ስርዓት ላይ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሚያዚያ 19 2016 ዓ.ም በይፋ ተካሂዷል።
የጊፍት ሪል እስቴት የለገሀር የመኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ግንባታ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው ተብሏል።
3540 የመኖሪያ ፣46…
Signed Never ️😍
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @mahberawimedia. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.