7 Aug 2026, 04:34 UTC32 views8 reactionsread 9 August 2026 ከክፉዎች ምክር የማይሄድ፣ በኃጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም መቀመጫ የማይቀመጥ ሰው ብፁዕ ነው።
ደስታው በእግዚአብሔር ሕግ ነው፤ ቀንና ሌሊትም በሕጉ ያስባል።
በውኃ ፈሳሾች አጠገብ እንደ ተተከለ ዛፍ ይሆናል፤ ፍሬውን በወቅቱ ይሰጣል፣ ቅጠሉም አይረግፍም፤ የሚያደርገውም ሁሉ ይሳካለታል።
ክፉዎች ግን እንዲህ አይደሉም፤ ነፋስ እንደሚበትነው ገለባ ናቸው።
ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ አይቆሙም፣ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር ውስጥ አይገኙም።
እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃል፤ የክፉዎች መንገድ ግን ይጠፋል። ማዝሙር ዳዊት ምዕራፍ 1
🥰3😍2❤1💯1😘1
Signed ◦•●◉✿Royal ✿◉●•◦
6 Aug 2026, 11:59 UTC517 views10 reactionsread 9 August 2026 Photo
ይቅርታ ይቅርታ 🙏🙏
የፍልሰታ ጾም መጥቶ፣
የምሕረት ደጅ ተከፍቶ፣
የሰላም መንገድ ተጠርጎ፣
የፍቅር ብርሃን በርቶ።
እኔም ቆሜ በትሕትና፣
ከልቤ አንድ ቃል እላለሁ፤🤲
በሐሳብ፣ በቃል ወይም በተግባር ካሳዘንኩህ፣ ይቅርታ እጠይቃለሁ።🙏
ሰው ሆኜ ተሳስቻለሁ፣ በድዬም ይሆናል፣
ያቆሰለ ቃል ተናግሬ፣ ያሳዘነ ተግባር ፈጽሜ።
ዛሬ ግን በዚህ የተቀደሰ ጾም፣
ቂምን ሁሉ ልንተው እሻለሁ።
ይቅርታ የደካማ አይደለም፣
የጠንካራ ልብ ምልክት ነው፤
ይቅር ማለት ሽንፈት አይደለም፣
ፍቅርን የሚያሸንፍ ድል ነው።🤲
የተሰበረው ግንኙነት ይጠገን፣💞
የቀዘቀዘው ፍቅር ይሞቅ፣💖
የራቀው ልብ ይቅረብ፣❤️🩹
የጠፋው ሰላም ይመለስ።🥰
ከልቤ የምለምንህ አንድ ነገር ብቻ ነው፤
በፍቅር ይቅር …
❤4👍2😘2💯1🥰1
Signed ◦•●◉✿Royal ✿◉●•◦
6 Aug 2026, 11:10 UTC152 views11 reactionsread 9 August 2026 Photo
ለውዷ እህቴ – መልካም ልደት
ዛሬ ቀንሽ የተለየ ነው፣
ደስታ የሚያበብበት ቀን ነው።
ፈገግታሽ እንደ ፀሐይ ይብራ፣
ሕይወትሽም በፍቅር ይሙላ።
እህቴ ሆይ፣ አንቺ ለእኔ
የቤቴ ብርሃን፣ የልቤ ሰላም ነሽ።
በችግር ጊዜ የምታበረታታኝ፣
በደስታ ጊዜ አብረሽ የምትስቂኝ ነሽ።
ዛሬ በልደትሽ ቀን፣
ሁሉም ህልምሽ እውን ይሁን፤
መንገድሽ በስኬት ይሞላ፣
ቀኖችሽ በፈገግታ ይድምቁ።
እግዚአብሔር ጤናን፣ ረጅም ዕድሜን፣
ሰላምንና በረከትን ይስጥሽ።
የምትመኚውን ሁሉ ያሳካልሽ፣
ፍቅሩም ሁልጊዜ ይጠብቅሽ።
ዛሬ ልደትሽ ብቻ አይደለም፣
ለቤተሰባችን የደስታ በዓል ነው።
አንቺ ያለሽበት ቦታ ሁሉ ፍቅር ይበዛል፣
አንቺ ያለሽበት ልብ ሁሉ ተስፋ ይሞላል።
መልካም ልደት ውዷ እህቴ!
ፈገ…
❤4🥰2😘2🐳1👍1💯1
Signed ◦•●◉✿Royal ✿◉●•◦
31 Jul 2026, 17:27 UTC308 views12 reactionsread 9 August 2026 Photo
እናቴ ማርያም ሆይ 😔😔
በዚህ በጨለመና በከበደ ዓለም ውስጥ ሆኜ የልቤን ስብራት የምዘረግፍበት ሌላ ማንም ስለሌለኝ ወደ አንቺ ጮህኩ ዓለም ፊቷን አዙራብኛለች የጭንቀት ማዕበልም ሊያሰጥመኝ ከፊቴ ተደቅኗል በዙሪያዬ ያለው ሁሉ በሐዘን ተሞልቷል ነፍሴም በልቅሶ ዝላለች
እመቤቴ ሆይ...
ኑሮዬ ሁሉ እንደ ቃና ዘገሊላ ወይን አልቆብኛል የደስታዬ ምንጭ ደርቋል ተስፋዬም እንደ ጧፍ እየጠፋ ነው የሰው እርዳታ የትም አላደረሰኝም ይልቁንም ብቸኝነቴን አበረታው እንጂ "ሰው የለኝም" ብሎ እንደጮኸው መጻጉዕ እኔም ዛሬ ካንቺ በቀር ማንም የለኝም ብዬ በፊትሽ ተደፍቻለሁ
አደራሽን እመቤቴ
የዓለም ጩኸት ጆሮዬን ሲያደነቁረው የአንቺ የለሰለሰ ድምፅ "አይዞህ" ይበለኝ…
❤5🥰3👍2🎉1💯1
Signed ◦•●◉✿Royal ✿◉●•◦
28 Jul 2026, 14:15 UTC90 views11 reactionsread 9 August 2026 እሷ አይደለችም🥺
ያቻት አትበሉኝ እሷ እንዲ አቶድም
ቁጥብ ደርባባ ናት እዩኝ አታበዛም
ከኔ ሌላ ወንድ ከንፈር አትቀምሰም
እሷ አይደለችም😭
እርግጥ ተክለ ሰውነቶ
ዞማ ፀጉሮ የሰራ አካላቶ
ቁርጥ ብትመሰልም
እኔ ያፈከርኮት የትላት ያ ልባ ዛሬ ከሷ የለም
ለምን አታምኑኝም እሷ አይደለችም
እዲ እየጠበኮት እግዜርን ከድቼ
ፀሃይን ጠልቼ
እኔ እየጠበኮት
በኔማ ጨክና እደዚ አቶንም
እሷ አይደለችም😡
ከደጀ ሰላሙ እሁድ ነው ሲሉኝ የእግዜር ምፅአት
የሚተነበየው ልሳን በሊቃውት
አይኖን ጎጉቼ ነው ቅዳሜን ያልሻርኩት
🥺🥺🥺
እሷ አይደለችም ትላት እኔ ማውቃት
እሷ ትመጣለች ባይሆን እጠብቃት
🤌🥹❤️🩹❤️🩹💃👸
🥰4😍2😘2🐳1👍1💯1
Signed ◦•●◉✿Royal✿◉●•◦
25 Jul 2026, 18:28 UTC91 views7 reactionsread 9 August 2026 0p
😍3❤1👍1💯1🥰1
Signed ◦•●◉✿Royal✿◉●•◦
25 Jul 2026, 18:24 UTC275 views10 reactionsread 9 August 2026 ገብርኤል መልአከ ብርሃን፣
የሰማይ መልእክተኛ ታላቅ ነህ።
የሰላም ዜናን የምታወርድ፣
ለምእመናን ተስፋን የምትሰጥ።
በጽድቅ መንገድ አሳደግን፣
ከክፉ ሁሉ ጠብቀን።
በቀንም በሌሊትም ከእኛ ጋር ሁን፣
በፈጣሪ ፊት ስለ እኛ ለምን።
የሰማይ ክብር ተሸክመህ፣
የፈጣሪን ፈቃድ ታውጃለህ።
የተጨነቁትን ታጽናናለህ፣
የወደቁትን ታነሣለህ።
ልባችንን በእምነት አጽና፣
መንገዳችንን በብርሃን ምራ።
ፍቅርን ሰላምን ስጠን፣
በቸርነትህ ሁልጊዜ አስበን።
ገብርኤል የክብር መልአክ፣
የእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ፣
በምልጃህ አትለየን፣
በጸጋህ አጽናን።
ለአምላክ ክብር ይሁን፣
ለቅዱስ ገብርኤል ምስጋና ይሁን፣
ለዘላለም አሜን።እንኩን አደረሰችሁ 🙏🙏🙏ምልካም በዓል
😍4❤2🙏2👍1🥰1
Signed ◦•●◉✿Royal✿◉●•◦
18 Jul 2026, 10:42 UTC187 views9 reactionsread 9 August 2026 Photo
ተመስገን
መላእክት በፊቱ በፍርሀት የሚቆሙለት
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ከአፋቸው የማይለዩት
ልበ ደንዳኖቹ እርጉማኑ አይሁድ
ፈራጁን ፈጣሪ አቆሙት ለመፍረድ
ለሰማዕታት አክሊል ድልን የሚያቀዳጅ
የእሾህ አክሊል ደፋ ነውና ሰው ወዳጅ
ለኪሩቤል ክብር ግርማን የሚያላብስ
ቀይ ግምጃን ለበሰ ስቃይን ለመቅመስ
ዓለምን የያዙ እጆቹ ተቸነከሩ
አዳምን የፈለጉ እግሮቹ ተሰበሩ
ህይወት እፍ ብሎ በሰጠበት አፉ
ሐሞትን አጠጡት በፊቱ እየተፉ
የብርሀን ፊቱ በጥፊ ተመታ
የዓለም ፈጣሪ የዓለም ሁሉ ጌታ
ዕለተ አርብ ያዘች ሀዘን እና ደስታ
በጌታ መከራ እስራችን ተፈታ
አቤቱ ጌታ ሆይ በተወጋው ጎንህ
ማረን ይቅር በለን በአማኑኤል ስምህ
ከቁጣህ ሰውረን ከመቅሰፍት አድነን
ይ…
👍2😘2❤1💯1🥰1😍1🙏1
Signed ◦•●◉✿Royal✿◉●•◦
16 Jul 2026, 06:52 UTC117 views12 reactionsread 9 August 2026 Photo
ተመስገን የኔ ጌታ በዕድሜ ላይ ዕድሜ ለጨመርክልኝ መውደቄን አይተህ ላልተውከኝ ያየህብኝን ያላሳየህብኝ ደሞ በደሌን የረሳህልኝ. . .ሀብታም ካደረከኝ አንተን የማመሰግንበት አንደበት አትንፈገኝ ደሀም ካደረከኝ አንተን የማማርርበት አንደበት አትስጠኝ ለሆነውም ለሚሆነውም ክብርህ ከፍ ከፍ ያለ ይሁን::አሜንንን ✝️🥳አመሰግናለሁ የኔ ጌታ 🙏🙏🙏
❤4🥰3😘2👍1💯1🕊1
Signed ◦•●◉✿Royal✿◉●•◦
13 Jul 2026, 17:53 UTC101 views13 reactionsread 9 August 2026 እህቴ
እህቴ ሆይ፣ የልቤ ሙዚቃ፣
የፈገግታዬ መነሻ፣
በሕይወቴ ጉዞ ሁሉ
ከጎኔ የቆምሽ ብርታቴ ነሽ።
ፈገግታሽ እንደ ጸሐይ ይደምቃል፣
ቃልሽ እንደ ዝናብ ልቤን ያረጋጋል።
ሲከብደኝ ተስፋ ትሆኚኛለሽ፣
ስደሰት ደስታዬን ታበዛለሽ።
የደስታ ቀኖቼን አብረሽኝ አሳመርሽ፣
የእንባ ጊዜዬን በፍቅርሽ አደረቅሽ።
ያለሽበት ቤት ፍቅር ይሞላል፣
ያለሽበት ሕይወት ተስፋ ይበቅላል።
እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ይስጥሽ፣
መንገድሽን በብርሃን ይምራልሽ።
ህልምሽ ሁሉ ይሳካ፣
ደስታሽም ፈጽሞ አይጥፋ።
እህቴ ሆይ፣
ቃላት ፍቅሬን ሊገልጹ ባይችሉም፣
ልቤ ሁልጊዜ ይመሰክራል፤
አንቺ የሕይወቴ ውድ ስጦታ ነሽ፣
ለዘላለምም እወድሻለ
@Samisha199
@Samisha19…
😍4❤2💯2🙏2🔥1🥰1😘1
Signed ◦•●◉✿Royal✿◉●•◦
10 Jul 2026, 03:53 UTC166 views11 reactionsread 9 August 2026 Photo
መልካም ልደት 🎂heran🫀ምኞት ከ ሮያል 😍😍😍 03/11/2018
ሄራንዬ የኔ ትንሽዬ አንቺ የዋህና ቅን ሴት እንኳንም ወለዱሽ 😍::አንደበት ስንፍና ሲበዛም ልጉም ሆነ እንጂ በየቀኑ ሳወራሽና ደምፅሽን ስሰማ የማየውን ብርሀን በቃል እየሞሸርኩ ብነግርሽ መልካም ነበር ::😘
ንፁ ልባም ሴት ነሽ ፍፁም ቁጥብ🤔!ወጣትነትሽን በአግባቡ ያከበርሽ ነሽ እናቴ በቃ ደስ የሚል ሴትነት አለሽ ::
ልመርቅሽ ነው እጅሽን ዘርግተሽ አሜንንን በይ 🤲🤲
*ከዘመንሽ ቀን አይቅደምሽ 😄 *መሰበርያሽና መጠገኝሽ ክርስቶስ ይሁን🙏
*አግኝተሽ አትጪ 😍
* ከሰዉ አፍ አያውልሽ 😄
* ቤትሽ ሰላም ይሙላ 🫶
* በጉልበትሽ ስሪበት በልብሽ የነፍስ ሰው ይክረ…
❤6😘2👍1💯1🤩1
Signed ◦•●◉✿Royal✿◉●•◦
8 Jul 2026, 16:23 UTC95 views9 reactionsread 9 August 2026 Forwarded from @yealem_gud
ሴቶቹ በዙና ቤቱ አነሳቸው
ወደጓሮ ወስደው በዳስ ቢያረጓቸው😂
ዳስ ማለት መጠልያ ነው 😎
👍3😍2❤1💯1🥰1😁1
Signed 🕷🕸༎꯭ࠫ𓆩 ⃝⃪⃕❜𝆺꯭𝅥ŠĨĻĚŃȚ BØÝ𝆺꯭𝅥༎ࠫ, ✨🕷🕸
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @link19956. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.