14 Oct 2024, 19:27 UTC≈2,440 views1 reactionsread 9 August 2026 ጨረቃ እንዴት ተፈጠረች
የ ዛሬ 4.5 ቢሊየን ዓመት ገደማ:: በወቅቱ የቋጥኞች ክምችት የሆነውና በፀሐይ በቅርብ ርቀት ውስጥ የምትገኘው አዲሲቷ ምድር በፀሐይ ዙሪያ ግራ በተጋባ ሁኔታ ነበር የምትሽከረከረው:: የምትሽከረከርበት ምህዋርም አቅጣጫውን የጠበቀ አልነበረም:: የዛሬ 4.5 ቢሊየን ዓመት ገደማም የማርስ ፕላኔትን የሚያክል መጠን ያለው «thea» በመባል የሚጠራ ግዙፍ ቋጥኝ በጥንቷ የምድር ፅንስ ላይ ወደቀ፡፡ የዚህ ያልተጠበቀና ድንገተኛ ግጭትም እነሆን የጥንቷን ምድር ለሁለት ከፈላት:: ገሚሱ የምድራችን ክፋይ ቋጥኝም በከፍተኛ ፍጥነት ወደሰማይ በረረ፡፡ ሌላውም ባለበት ቀረ፡፡ ወደሰማይ ተከፍሎ የበረረው ቋጥኝም እነሆን የዛሬይቱን ጨረቃ ሊፈጥር ቻለ፡…
❤1
11 Oct 2024, 17:44 UTC≈1,010 views2 reactionsread 9 August 2026 ለግርምት
በመሀከለኛው አፍሪካ ቦሸንጎ የሚባሉ ጎሳዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከጥንት ጀምሮ እንደሚያምኑት ከሆነ ይህ ዩኒቨርስ ከመፈጠሩ በፊት የነበረው ቡምባ የሚባል አምላክ እንደነበርና ቡምባም ከዕለታት በአንድ ቀን ሆዱን በመታመሙ ሊያስታውክ እንደቻለ፡፡ በዚህ ተደጋጋሚ የማስታወክ ሂደት ውስጥ የዩኒቨርስ ክፍሎች ተራ በተራ ከሆዱ እንደወጡና አሁን የምናየው ዩኒቨርስና እኛም ስዎች እውን እንደሆንን ይገልፃሉ::
Share it
✍ Joo
@liele_hlina
❤2
13 Jul 2024, 08:54 UTC≈1,090 views1 reactionsread 9 August 2026 በፈጣሪ ሥራ መግባት?
(ግርምተ ሳይቴክ)
በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ወላጆች የሚወልዱትን ልጅ ጾታ ቀድመው የሚወስኑበት፣ የሚወለደውን ሕፃን የአዕምሮ ልቀት እንዲኖረው ገና ሳይወለድ የሚያረጋግጡበት፣ የጸጉር እና የዓይን ቀለሙን የሚወስኑበት፣ በዘር ሊመጣ የሚችልን በሽታ ወደልጁ እንዳይተላለፍ ማድረግ የሚችሉበት ሳይንስ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል። ከዚህም አልፎ እንስሳት ከተፈጥሮ አሠራራቸው ውጪ ምን ዓይነት ቅርጽና ይዘት እንዲኖራቸው መወሰን የሚቻልበት እና የተለያዩ እንስሳትን በማዳቀል ልዩ እንስሳ የሚፈጠርበት ሁኔታ ይኖራል ተብሎ ይታሰባል።
በ2016 ዓ.ም. አጋማሽ ላይ እንግሊዝ አገር በሚገኘው በዩኒቨርስቲ አፍ ባዝ የተደረገው ሙከራ ደግሞ ያል…
👍1
13 Jul 2024, 05:34 UTC≈1,210 views2 reactionsread 9 August 2026 # የአለም_ህግ
አንድ ገበሬ በጣም የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ወደ እንስሳት ሀኪም ጋር ይዞት
ይሄዳል። ሀኪሙም ፈረሱ ጉረኖ ድረስ በመሄድ በሚገባ መረመረው።
ለገበሬውም - "ተላላፊ በሽታ ስላለበት ለሶስት ቀን መድሀኒት እንስጠውና ካልተሻለው
ወደሌሎቹ ፈረሶች እንዳይዛመት እንገለዋለን" ብሎት ሄደ።
ይሄንን ሲያወሩ ፍየል ተደብቃ ሰምታቸው ኖሯል ለፈረሱ እያለቀሰች ያወሩትን ነገረችውና
"እንደምንም ብለህ ተነስ! ያለበዛ ይገሉሀል" እያለች ተንሰቀሰቀች። የመጀመርያው
ቀንሀኪሙ መጥቶ መድሀኒቱን ሰጥቶት ወጣ።
ወድያው ፍየል ለምለም ሳርና አተላ ይዛለት መጣች ና "እንደምንም ተነስ!" ብላ
ተማፀነችው።
በሁለተኛውም ቀን ሀኪሙ ሲመጣ ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም መድሀኒቱ…
❤1👍1
11 Jul 2024, 04:44 UTC≈2,540 views3 reactionsread 9 August 2026 የምታስረዳውን ነገር እንዲረዱህ አድርገህ አስረዳ!!!
በአንድ መንደር የሚኖር ንጉስ ነበር። አንድ ቀን በህልሙ ጥርሶቹ ሁሉ ሲረግፉ ያያል። በዚህ ጊዜ ህልም የሚፈታለት ሰው ያስጠራና ህልሙን ይናገራል ህልም ፈቺውም በመገረም..."ይህን ህልም ያየኸው አንተ ነህ?
እርግጠኛ ነህ ሲል ይጠይቀዋል።
ንጉሱም አዎ እኔ ነኝ ይለዋል። "ቤተሰቦችህ በሙሉ በፊት ለፊትህ አይንህ እያየ ይሞታሉ" ብሎ ይነግረዋል በዚህ ጊዜ ንጉሱ ተቆጣ..."ይሄን ቀባጣሪ እስር ቤት ወርውሩልኝ"
ሲል አዘዘ። ትዕዛዙም ተግባራዊ ሆነ።
ሌላ ህልም ፈቺ የመጀመሪያው አይነት
በመሆኑ ንጉሱ ተበሳጨ እሱንም ወደ እስር ላከው ፡፡
ሶስተኛ ህልም ፈቺ ተጠራ እንደተለመደው ህልሙን ተናገረ "ንጉስ ሆይ…
👍2❤1
2 Jul 2024, 11:07 UTC386 views1 reactionsread 9 August 2026 Photo
" ...ለእኔ ብዙ ትልቅ ቦታ አትስጡኝ ፤ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ።
እኔኮ በሽተኛ ነኝ ሲጀምር ብዙ ጊዜ ተኝቼ ነው የምውለው ፤ ስራ ያቆምኩ ሰው ነኝ እኔ እንደውም የህብረተሰብ ሸክም መሆን ያለብኝ ሰው ነኝ እውነት ለመናገር።
እንደ እኔ አይነት ሰው ዝም ብላችሁ ብታስቡት እንኳን እንደዚህ ለማድረግ ይቅርና እራሴንም ለመቻል ወይ አግብቶ ወልዶ ለመኖር ሰው ለመርዳት ቀርቶ ለመለመን እንኳን አንድ ሰው ጤነኛ መሆን አለበት ፤ ለመለመን ወጣ ብሎ አንድ ቦታ መቀመጥ አለበት እኔ መቀመጥም አልችልም።
ለመኖር እራሱ የማይገባኝ ሰው ነኝ ፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው ያለሁት ፤ እውነቴን ነው የምነግራችሁ ቀልዴን አይደለም። አንድ ሰው ለመለመን መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሰው መ…
❤1
29 Jun 2024, 06:08 UTC189 views3 reactionsread 9 August 2026 መብል ቤት
(በእውቀቱ ስዩም)
የበቀደም የሆነ አሳ ቤት ገብቼ አሳ ክትፎ አዘዝሁ፤
ትንሽ ቆይቶ አስተናጋጁ በጎድጓዳ ሰሀን የሆነ ነገር አምጥቶ ጠረጴዛየ ላይ ጎለተው፤
“ዠለስ! እኔኮ ያዘዝሁት ያሳ ክትፎ ነው”
“ ታድያ ይሄ ምንድነው?” አለ አስተናጋጁ፤
“ ይሄማ የአሳ መረቅ የተርከፈከፈበት የሽንኩርት ክትፎ ነው ”
አስተናጋጁ ዞሮ ሊራመድ ሲቃጣ፤ “ማኔጀሩን ጥራልኝ” አልኩት፤
“ማኔጀሩን ለማስጠራት አምሳ ብር ያስጨምራል ”
ሲል መለሰ፤
በመጨረሻ ማኔጀሩ ተጠርቶ ሲመጣ፥ ምግቡን በማሻሻል ፋንታ አጥብቆ ወቀሰኝ፤
“ ምነው በውቄ? ትልቅ ሰው አይደለህም እንዴ? አገሪቱ የተወሳሰበ ችግር ላይ ናት፤ የህዝብ ድምጽ ትሆናለህ ብለን ስናስብ አ…
👍2❤1
27 Jun 2024, 10:49 UTC190 viewsread 9 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
27 Jun 2024, 10:49 UTC383 views1 reactionsread 9 August 2026 የኢትዮጵያ ሙዚቃ አፍሮዳይት
እጅጋየሁ ሽባባዉ (ጂጂ)
በ1974 ጥቅምት 13 በጎጃም ቻግኒ ልዩ ስሙ ሰገዲ ሚካኤል የታሪክ ድምጽ፣ የድል ዜማ፣ የሰዉነት ልክ ጥበብ፣ ከመንዙማ፣ ከአሚናዎች፣ ከጉባኤ ቃና የተፈለቀቁ ዜማዎች እመቤት ፣ እንደ መልከ ጣዲቅ ካህን ውበቷ ከዘመን ዘመን... ፣ እንደከለዳውያን ጥበብ የረቀቀች... እንደ ሌዋውያን ቅድስና የሙዚቃ ታቦተ ፂዮን ተሸካሚ... የሙዚቃ ቀማሚዋ ጉራያ... የውበት ጠበብቷ ኢሽታር.. ስሟ ከግብሯ የገጠመዉ እጅግአየሁ ተወለደች ።
አስር ወንድምና እህቶቿ መሐሐል አምስተተኛ ልጅ እንደሆነች የምትናገረው እጅጋየሁ ምንም በቂ ሃብት ካላቸዉ ቤተሰቦች እንደመገኘቷ አፈር ሳይነካት ማደግ ብትችልም ለተፈጥሮ ከነበራ…
😁1
24 Jun 2024, 04:41 UTC≈2,360 views2 reactionsread 9 August 2026 Id፣ Ego፣ Superego!
•
፩) Id (ደመ-ነፍስ)
፨ ምግብ፣ ውኃ፣ ጤና፣ ሙቀት፣ ወሲብ…ወዘተ የስነ ሕይወታዊ ፍላጎቶች ማዕከል ነው።
፨ አብሮን የተወለደ በመሆኑ ምንግዜም ደስታን፣ እርካታን ይሻል።
፨ ጊዜና ሁኔታ ስለማይገዱት ተጨባጭ እውነታን አይለይም።
፨ ምክንያት፣ ግብረ ገብነት አይገዛውም።
፨ እንደ ራስ ወዳዱ ብላቴና ደስታውን ብቻ ያስቀድማል።
፨ ማመዛዘን የጎደለው በመሆኑ እውነታን ያማከለ አይደለም።
•••
፪) Ego (እውነታ መር)
፨ የፍላጎትና የእውነታ አስታራቂ ነው።
፨ ንቁ በመሆኑ ከእውነታ ጋር ነው የሚተዋወቀው።
፨ የላቀ ምቾት እንድንጎናፀፍ ድርጊያዎቹን በጊዜና በሁኔታ ያከናውናል።
፨ የሁልጊዜ ስራው ኢድን ማገልገል ነው።
•…
👍2
21 Jun 2024, 14:49 UTC≈1,330 viewsread 9 August 2026 ለፈገግታ
(በእውቀቱ ስዩም)
በቀደም እኛ ሰፈር እሚገኘው መሬት አስተዳደር ቢሮ ጎራ ብየ ጎራው አልሁ ፤
ከአስተዳዳሪው ጠረጴዛ ላይ፥ ሜትር፥ ችካልና በሶስት ጎድጓዳ ሳህኖች የተቀመጠ ናሙና አፈር ተደርድሮ ይታያል፤
“ምን እንርዳዎ ?” አለኝ አስተዳዳሪው፤
“ የሆነች ቀለል ያለች አምስት ሺ ካሬ መሬት ፈልጌ ነበር “
“የገበሬ መሬት ነው የፈለጉት?”
“ የወዛደርም ቢሆን አይደብረኝም፤”
“ አዝናለሁ ፤ ለጊዜው የሚሸጥ መሬት የለንም’
’
“ እኔም የሚሸጥ ሳይሆን የሚሰጥ መሬት ነው የምፈልገው “
“ምንስ ስለሆንክ ነው ላንተ መሬት የሚሰጥህ ?”
ሰውየው ካንቱ ወደ አንተ የተሸጋገረበት ፍጥነት አስደነቀኝ ፤
‘ እስካሁን ለናት አገሬ ካደረ…
16 Jun 2024, 04:49 UTC212 viewsread 9 August 2026 Photo
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
@liele_hlina
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @liele_hlina. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.