9 Aug 2022, 05:53 UTC125 viewsread 10 August 2026 የቆራጥ ሰው እጣፋንታ
ቆራጥ መሆን ስትጀምርና ወደ ራስህ ስታተኩር ምድራዊ ጥያቄህ መመለስ ይጀምራል፤ እጣፋንታህ በሰዎች እጅ መሆኑ ያቆማል። ህይወትህን የሚቀይረው ከሰዎች በምታገኘው እርዳታ ወይ ትብብር አይደለም ወይ ሁኔታዎች በሚያመጡት ዕድል አይደለም!
ህይወትህ የሚቀየረው ቆራጥ በመሆንህ አምላክህ በሚያዘጋጀልህ ስጦታ ነው! ለዛ ነው መጠንከር ስትጀምር ሰዎች የሚያከብሩህ፣ ስራው ዕድሉ ገንዘቡ የፍቅር ግንኙነቱ ሁሉ የሚስተካከለው። ወዳጄ መጠንከር እንደጀመርክ አውቃለው ከዛ ግን ወደኋላ ማየት የለም!
@learnmoreof
@Inspire Ethiopia
Signed Têđđÿ
5 Jun 2022, 13:38 UTC132 viewsread 10 August 2026 ከፍርድ ነጻ የሆነ ሳምንት
ከሰው ጉዳይ ላይ የመውጣት ምስጢር
“ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር የሌላው ሰው ጉዳይና ደካማ ጎን ላይ ሳይሆን የራሳችን ጉዳይ ላይ ሊሆን ይገባዋል”
አንድ በጣም የታወቀ የስኬት አሰልጣኝ በመካከለኛ እድሜ ላይ የሚገኙ ስኬት የጠማቸው ነጋዴዎችን ለተወሰኑ ሳምንታት ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡ የሳምንቱ የስልጠና ርእስ ከዋናው ዓላማችን የሚያስወጡንን ተጽእኖዎች ስለማስወገድ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ሳምንት በአንድ አስፈላጊ ርእስ ላይ መመሪያ ከሰጣቸው በኋላ የሳምንቱን የቤት ስራ ይሰጣቸዋል፡፡
በእለቱ ከሰጣቸው ትኩረትን የመሰብሰብ ትምህርቶች መካከል አንድ አስፈላጊ ነጥብ ይገኝበታል፡፡ “አብዛኛውን ጊዜ” አለ ሃሳቡን…
Signed Åbï £@št
16 Oct 2021, 10:33 UTC145 viewsread 10 August 2026 ≈ዶ/ር ምህረት ደበበ
#1. ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!
#2. 'ሼም ነው' የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!
#3. አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን
ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..."
አይባልም።
#4. ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ
ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን
እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።
🚢🚢🚢
#5. ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ
ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያ…
Signed Têđđÿ
3 Jun 2021, 20:27 UTC139 viewsread 10 August 2026 🚹ለራሳችን መንገር የሌለብን 4⃣ ነገሮች🚺
የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለችግሮቹም ራሣችሁን ተጠያቂ ታደርጉ ይሆናል፡፡ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና ከሠዎች በታች ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ ቃላትን መጠቀም የለባችሁም በማለት የሥነ-ልቦና ምሁራን ይመክራሉ፡፡ እነኚህ ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡ ፡ ለራሳችን የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ ጉዳት እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት የሥነ-ልቦና ባለሙያው ማይክ ቡንድራንት በተለይ የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ መንገር የለባችሁም ይላሉ፡፡
1⃣ የማልረባ…
Signed Åbï £@št
10 May 2021, 08:47 UTC86 viewsread 10 August 2026 እናስተውል !!!
አጠጋብችን ሆነው ሳሉ፤ እሩቅ ቦታ የምንፈልጋቸው ስንት ነገሮች አሉን? አንገታችን ላይ ታስረው በየክፍሉ እየበረቀስን ለማግኘት የምንደክምላቸው ፤ብዙ አመት አብረውን ከርመው ሳለ፤ እኛ ግን ገና ይመጣሉ ብለን የምንጠብቃቸው ብዙ ነገሮች አሉን። የሌሉን የሚመስለን፤ በሚስጥር ኪሳችን ውስጥ ተደብቀው ያሉ እጅግ ብዙ ሀብቶች አሉን።
*ዉድ ነገሮች በሙሉ በነፃ ነው የተሰጡን ። ስለዚህ እናመስግን !
Share አድርጉት ለሌሎችም
👇
@Learnmoreof
Signed Têđđÿ
5 May 2021, 17:40 UTC92 viewsread 10 August 2026 ሲፈቀር የሚባል...
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
"ፈገግ ስትዪ...
ጥርስሽ ምስራቅ ሆነኝ ፣ የፀሐይ መውጫ በር
ከሳቅሽ ሰማይ ላይ ...
ንጋቴን አያለሁ ፣ ተሰቅላ እንደጀንበር።
አንቺ ስትስቂ...
የጨረቃ ገላ ፣ እስኪያልቅ ይሸረፋል
"ሙሉ"
"ግማሽ"
"ሩብ"
እያለ ይጠፋል
ኮከብ እንደ ቅጠል ፣ እግሬ ስር ይረግፋል።"
ብዬሽም አልነበር?
..................................
"ስታኮርፊ ደሞ
ነፍስሽ ምእራብ ነች ፣ መውጫ ለጨለማ
ከኩርፊያሽ ሰማይ ላይ...
ምሽቴን አያለሁ ፣ ንጋቴን ስቀማ።
አንቺ ስታኮርፊ...
ሳቅሽ ሚያደርቃቸው ፣
"ኮከብ ነን" ባይ ሁላ ፣ ይድናል ከመርገፍ
ጨረቃም ሙሉ ነች...
ዳግም ስትስቂ አይታ ፣ ገላዋ እስኪሸረፍ
እስከዚ…
Signed Têđđÿ
2 May 2021, 16:25 UTC64 viewsread 10 August 2026 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም
እንደ ተናገረ ተነስቶአልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ:: ማቴዎስ ወንጌል (፪፰፥፮)
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ። መልካም በዓል 🙏
Signed Têđđÿ
20 Mar 2021, 13:25 UTC96 viewsread 10 August 2026 በአንድ ወቅት አንዲት ወጣት ወደ እናቷ በመሄድ ኑሮ እንደከበዳትና ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ ላይ እንዳለች ነገረቻት፡፡ “አንዱ ችግሬ አበሳጭቶኝ ሳልጨርስ ሌላ ይተካል፣ በእርሱኛው ደግሞ ውስጤ ተጎድቶ ገና ሳላገግም ሌላ ይጨመርብኛል” በማለት ከፍቅር ሕይወቷ ጀምሮ እስከ ሌሎች አስቸጋሪ ገጠመኞቿ ስሜታዊ በሆነ መልኩ አንድ በአንድ ገለጠችላት፡፡
በጥበቧ የምትታወቀው እናት፣ ወደ ልጇ ጠጋ በማለት ዳበስ አድርጋት ፍቅሯን ከገለጠችላት በኋላ አሁን ለጊዜው ተረጋግታ ስራ እንድታግዛት ጠየቀቻት፡፡ ልጅ ፈቃደኝነቷን ከገለጸች በኋላ እናት ምንም ጊዜ ሳታባክን አንድን ነገር እነድታደርግ ለልጇ አዘዘቻት፡፡
“ሶሰት ድስቶችን ውኃ በመሙላት በምድጃው ላይ ጣጂ” አለቻት፣ እናት፡…
Signed Têđđÿ
4 Feb 2021, 05:41 UTC79 viewsread 10 August 2026 የቃል ፈተና ላይ ለማለፍ ማድረግ ያለብን 23 ነጥቦች
በዚህ አድስ ዓመት ከዩንቨርስቲ የተመረቁ ሁሉ በቶሎ ስራ ለመጀመር ጥንቃቄ ልናደርግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እነሆ....
1. የኢንተርቪው ሰዓት ሳይጀመር በጣም በጊዜ አለመገኘት (ድካም፣ የርሃብ ስሜት እና መሰልቸትን ስለሚፈጥር)
2. ለስራው እክል ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ መልሶችን አለመመለስ ወይንም ጥያቄዎችን ግልጽልፅ እንዲደረግላችሁ መጠየቅ ይንፕርባችኋል።
3. CV (የሂወት ታሪካቹ) ላይ የፃፋቹትን አለመርሳት
4. ስላላቹ ዕውቀት ወይም ስለምትችሉት ነገር አለመዋሸት (ሁል ጊዜ ኢንተርቪው የሚያደርጋቹ ሰው ስለምትመልሷቸው መልሶች በቂ እውቀት እንዳለው መቀበል ይኖርባችኋል)
5. በቂ የአለባበስ ዝ…
Signed Têđđÿ
25 Jan 2021, 03:56 UTC70 viewsread 10 August 2026 ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ!
• መማር ከባድ ነው፣ ሳይማሩ መኖርም ከባድ ነው - ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ!
• ራስን ከአቻዎች ግፊት መጠበቅ ከባድ ነው፣ በአቻዎች ግፊት ምክንያት ጤና-ቢስ ሕይወት ውስጥ መግባትም ከባድ ነው - ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ!
• ማፍቅር ከባድ ነው፣ አለማፍቀርም ከባድ ነው - ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ!
• በፍጹም ከማይፈልገኝ ጓደኛ መለየት ከባድ ነው፣ ይህንን ጓደኛ ሲለማመጡ መኖርም ከባድ ነው - ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ!
• የትዳር ኑሮ ከባድ ነው፣ መፋታትም ከባድ ነው - ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ!
• በጤናማ አመጋገብና በስፖርት ራስን መጠበቅ ከባድ ነው፣ እንደፈለጉ በመመገብና ስፖርት ባለመስራት የመኖርም ውጤት ከባድ ነ…
Signed Têđđÿ
28 Oct 2020, 04:45 UTC112 viewsread 10 August 2026 አንተ ካልወሰንክ ሌላ ሰው ይወስንልሃል!
የአሜሪካ 40ኛው ፕሬዘዳንት ሆኖ ያገለገለው ሮናለድ ሬገን (Ronald Reagan) ውሳኔ የማስተላለፍን አስፈላጊነት ገና በልጅነቱ እንደተማረ ይናገራል፡፡ ገና በልጅነቱ አንድ ጊዜ አክስቱ አዲስ ጫማ ልታሰራለት ወደ ጫማ ሰሪ ቤት ወሰደችው፡፡ ጫማ ሰሪው እግሩን ከለካው በኋላ “እንዲሰራልህ የምትፈልገው ጫማ ቅርጹ ከእግር ጣቶች ጋር ክብ እንዲሆን ነው ወይስ አራት ማዕዘን እንዲሆን ነው የምትወደው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሮናልድ ሬገን መወሰን አቅቶት ሲወላውል ጫማ ሰሪው፣ “ችግር የለውም ትንሽ ቀናት አስብበትና ትነግረኛለህ” አለው፡፡
ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጫማ ሰሪው ሬገንን መንገድ ላይ አገኘውና፣ “የጫማውን ቅርጽ ጉዳይ …
Signed Têđđÿ
26 Oct 2020, 12:30 UTC96 viewsread 10 August 2026 አስተውል ወዳጄ
●・○・●・○・
➱ አንዳንዴ
☞ አንዳንዴ ነገሮችን በትዕግስት በዝምታ ስታልፋቸው "ያ" ሰው በድጋሜ አንተ ጋ ስህተት ለመስራት ሲጣድፍ ታየዋለህ። ያኔ አንተ ጥንካሬህን አሳየው።
•••
☞ አንዳንዴ ከትልቅ ሰው ጋ ስትውል ትልቅ ትሆናለህ።ስለዚህ መልካምነትን ለመላበስ ስትል ከትልቅና ከመልካም ሰው ጋ ዋል።
•••
☞ አንዳንዴ ትልቅ ሰው በትንሽ ሰው ሲሞት ታየዋለህ። ስለዚህ አዋዋልህን አሳምር ለአንተ ለቤተሰብህና ለሀገርህ ስትል።
•••
☞ አንዳንዴ መፅሐፍ ልታነብ ስትገልጠው ለጊዜው ታነበዋለህ እንጂ ሙሉውን ከአዕምሮህ ጋ አታገኘውም። "ያ" ሰውም ልክ እንደ መፅሐፍ ነው።
•••
☞ አንዳንዴ መልካምነትን ተላብሰህ መልካም ስትሰራ "ያ" ሰው ለታ…
Signed Têđđÿ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @learnmoreof. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.