16 Oct 2024, 19:01 UTC347 views10 reactionsread 8 August 2026 Photo
እግዚአብሔር ብዙ ነገር ያደርግልናል። ሕይወታችንን የሚጠብቅ ጥንካሬያችንን እና ተስፋችን እርሱ ነው። ከኅጢአት እና ከሞት ያዳነን እርሱ ነው። አምልኮአችን ስላደረገው ነገር፣ ስለ ማንነቱ እና ወደፊትም ሊያደርግ ስለሰጠው ተስፋ ነው። አምልኮ በጥሞና ጊዜያት ወይም በቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ ብቻ የታጠረ አይደለም። አምልኮ እያንዳንዱን የሕይወት ክፍል ያካትታል። ንግግሮቻችንንና የልባችንን ሐሳቦች ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስገዛት አስፈላጊ የሚሆነውም ለዚህ ነው። ከዚያም በግል የአምልኮ የጥሞና ጊዜም ሆነ በጋራ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በምናደርገው አምልኮ፣ በዚህ ምድር ላይ የኖርነው ሕይወት የእግዚአብሔርን መዝሙር ላልሰማው ዓለም ያሰማል።
#bible #biblev…
❤10
15 Oct 2024, 19:02 UTC266 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
”ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።“ ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር በዐሥርቱ ትዕዛዛት መጀመሪያ ላይ የእርሱን ማዕከላዊ እና የመጨረሻ ሐሳብ ነግሮናል። ሌላ ምን ማለት እንችላለን?
#bible #bibleverse #devotional #dailyverse #amharicbible #christian #christian #fyp #explorepage
👍1
14 Oct 2024, 18:02 UTC260 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
ይህን ዓለም አትምሰሉ። ይህንን መታዘዝ አይከብድም? የምናሰበው ነገር ትልቅ መንፈሳዊ ውጊያ የሚካሄድበት ስፍራ እንደሆነ ይህ ክፍል ያስታውሰናል። ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ትክክል ካለመሆን ይበልጣል። ይህ እጅግ አደገኛ ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔርን እውነት እና ቅዱስ ባህሪዎች የሚያጣምሙ መልእክቶችን ይህ ዓለም ስለሚመግበን ነው። በዓለም አሠራር ከመናደድ ይልቅ በአእምሮአችን መታደስ እንለወጥ። ጳውሎስ እንዳደረገው አእምሮን ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ ማድረግ አለብን። ብዙ ጊዜ ዐሥራት ማለት ከገንዘባችን ውስጥ ዐሥር በመቶውን መስጠት ነው ብለን እናስባለን፤ ነገር ግን ከዚህ ይልቅ አስፈላጊው ዐሥራት ዐሥር በመቶ ያልተከፋፈለ ሐሳባችንን ለእግዚአብ…
❤2👍1
13 Oct 2024, 19:02 UTC214 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
የእግዚአብሔርን ሕዝብ ክብር በሚያጎድፍ መልኩ እስራኤላውያን በጨካኝ ጠላት እጅ ውስጥ ሲወድቁ እግዚአብሔር ተስፋ ይሰጣቸዋል። የደረሰባቸው ውድቀት በእግዚአብሔር ላይ በማመፃቸው እና በኅጢአታቸው ምክንያት ቢሆንም የእግዚአብሔር ቅጣት ግን የሚጎዳ ብቻ ሳይሆን የሚያድንም ጭምር ነበር። በውድቀታቸው ውስጥ እንኳ ሆነው እግዚአብሔር ብልጽግና፣ ተስፋንና የወደፊት ሕይወትን ቃል ይገባላቸዋል። ሃኪም የተሰበረ አጥንትን ለመጠገን ሕመም እንደሚፈጥርብን ሁሉ፣ የእግዚአብሔር ተግሣጽ ዓላማ የሌለው ሳይሆን የሚያድን በመጨረሻም ሕይወትን የሚሰጥ ነው።
#bible #bibleverse #devotional #dailyverse #amharic #fyp #explorepage
❤2
11 Oct 2024, 19:02 UTC178 viewsread 8 August 2026 Photo
የልባችንን ምስጢር ለሰው ማካፈል እጅግ ይከብዳል። ድክመቶቻችንን፣ ውርደቶቻችንን እና ኅጢአቶቻችንን መደበቅ እንፈልጋለን። በልባችን ውስጥ ያለውን ምስጢራችንን ማንም ቢያውቅ ራሳችንን እንደምናዋርድ እናስባለን። ማንም አይቀበለንም ብለን እንፈራለን። ነገር ግን የተደበቀ ኅጢአት ሊደበቅ የሚችለው ከሰው ብቻ ነው። ከአባታችን ከእግዚአብሔር ግን አይደበቅም። የተደበቀ ኅጢአት በልባችን ውስጥ ነቅዞ በእኛ እና በሚምረው፣ ደግሞም እንድናሸንፍ በሚረዳው በእግዚአብሔር መካከል ዕንቅፋት ይሆናል። እግዚአብሔር መጠጊያችን ሊሆን እንደሚፈልግ በማወቅ ልባችንን በፊቱ እናፍስስ።
#bible #bibleverse #devotional #dailyverse #amharic #ethiopia #…
10 Oct 2024, 19:01 UTC167 viewsread 8 August 2026 Photo
“ሰው ሐሳብ ያቀርባል፤ ሰማይ ይፈጽማል” ብዙዎቻችን ምክር ለመስጠትና ትልልቅ ዕቅዶችን ለማውጣት እንቸኩላለን። ጠቢቡ እንደሚነግረን ጥበብ የሚመጣው ለረጅም ጊዜ ተግሣጽን ስንቀበልና ምክርን ስንሰማ ነው። ዕቅዶቻችሁን ከመፈጸማችሁ በፊት በጌታ ፊት ትንሽ ብታቆዩአቸው የተሻለ ነው። የአዲስ ኪዳን የጥበብ ጸሐፊ የሆነው ያዕቆብ ሳንጠራጠር እግዚአብሔርን ጥበብን እንዲሰጠን ከለመንን እንደሚሰጠን ያስታውሰናል። ይህ እኔን የሚያጽናናኝ እውነት ነው። ነገር ግን ጥበብን ለማግኘት ስንጸልይ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የጌታን እውነት ለመስማት እና ጥበብ ስትመጣ ደግሞ ለማስተዋል ትዕግስት እንዲኖረን አብረን እንጸልይ!
#bible #bibleverse #devotional #…
9 Oct 2024, 19:02 UTC158 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
ብዙ ሰዎች እነርሱን እንድንከተልና ትዕዛዞቻቸውን እንድንከተል ይፈልጋሉ። በዘመናት ውስጥ ታማኝነቱንና ፍቅሩ ያስመሰከረ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ከኅያልነቱ የተነሣ ሊፈራ ይገባል። እግዚአብሔርን መፍራት “የቤተ ክርስቲያን ነገር” ሳይሆን በሙሴ ታሪክ ላይ እንደምናስታውሰው “የሕይወት ዘመን ሁሉ” ልምምድ ነው። ትዕዛዛቱን ልንታዘዝ እና ልንጠብቅ ይገባል። በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ልናገለግለው እና በእርሱ ልንደገፍ ይፈልጋል። ፍርሀት በጉባኤ መሃል ያለ ዝምታ ሳይሆን ለእርሱ ክብር የምናደርገው ድርጊት ነው!
#bible #bibleverse #dailyverse #devotional #amharic #ክርስቲያን #fyp #explorepage
❤1
8 Oct 2024, 18:01 UTC135 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2 “ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራንን የእርሱን በጎነት ለመንገር” ምስክሮች ለመሆን በዚህ ምድር ላይ እንዳለን ያስታውሰናል። የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ አይተናል። የበረከቱ ተቀባዮች ነን። የሚመጣውንም ታላቅ ድነት የምንጠባበቅ ሕዝቦች ነን። ታዲያ እንዴት ዝም እንላለን? እንዴትስ ጨለምተኛ እና ተስፋ የሚቆርጥ ሰው መሆን እንችላለን? መቃብሩን ባዶ ያደረገው፣ ኢየሱስን ከሙታን አስነሥቶ ሕያው እና ከፍ ያለ ጌታ ያደረገው አምላካችን እግዚአብሔር ነው። እርሱ ሊያድነን የሚችልበት አቅም አለው። እርሱ አዳኛችን ነው።
#bible #bibleverse #devotional #dailyverse #amharic #ethiopia #fyp #explorep…
❤1
7 Oct 2024, 19:01 UTC137 viewsread 8 August 2026 Photo
ሱስ ማለት “ነፍሳችንን እንድትረካ ለእግዚአብሔር ሊኖረን የሚገባውን ረሃብ ለሌላ ምንጭ ስናውለው ነው።” መዝሙር 63 ይህ እውነት መሆኑን ያስታውሰናል። በውስጣችን እግዚአብሔርን የመፈለግ ዝንባሌ አለ። እግዚአብሔር ከእኛ ሩቅ አይደለም። በእኛም ሊታወቅ ይፈልጋል (የሐዋርያት ሥራ 17ን ይመልከቱ)። ነገር ግን ነፍሳችን እግዚአብሔርን ስትጠማ ለእርካታ ወደ እርሱ ብዙ ጊዜ አንሄድም፤ እርሱን አጥብቀን እንፈልገው። የነፍሳችንንም እርካታ በእርሱ ውስጥ እናግኝ።
#bible #bibleverse #dailyverse #devotional #amharic #jesus #fyp #explorepage
6 Oct 2024, 19:01 UTC134 viewsread 8 August 2026 Photo
ተራሮችን ስንመለከት ትንሽ እንደሆንን ይሰማናል። እንዲህ የሚሰማን ከእኛ በትልቀት ስለሚበልጡን ብቻ ሳይሆን፣ ከእኛ በፊት ምን ያህል ጊዜ እንደነበሩ ስለምናስብ ነው። ነገር ግን ጌታ ተራሮች ከመፈጠራቸው በፊት ነበረ፤ እነርሱም ከቀለጡ፣ ካለፉም በኋላ ይኖራል። እርሱ ዘላለማዊ የደኅንነት ዐምባ ነው። ለዘላለም የሚኖር እርሱ ነው።
#bible #bibleverse #dailyverse #devotional #amharic #fyp #explorepage
5 Oct 2024, 19:01 UTC127 viewsread 8 August 2026 Photo
እግዚአብሔር በእውነት ለሚሹት ሁልጊዜ ቅርብ ነው። ዋናው ችግር እኛ ከእርሱ እንርቃለን፤ ለእርሱ ያለንን ፍላጎት እናጣለን፤ ከመገኘቱም እንወጣለን። ስለዚህ እንፈልገው። እርሱ ብቻ በእውነት እንደሚያድን አውቀን ጸጋውንና ረድኤቱን እንቀበል።
#bible #bibleverse #devotional #dailyverse #seekgod #fyp #explorepage
4 Oct 2024, 19:01 UTC125 viewsread 8 August 2026 Photo
ዛሬ ላይ የምትሠራው ነገር የለህም? ነገ ስለሚያጋጥሟችሁ ችግሮች ስትጨነቁ ዛሬ ላይ ያሉትን አስፈላጊ እና አንገብጋቢ ነገሮች ሳታስተውሉ ተዘናግታችሁ አታውቁም? ነገ ላይ ስለሚኖሩ አማራጮች እያሰባችሁ ዛሬ ላይ ያገኛችሁት ዕድል አምልጧችሁ አታውቁም? መቀየር ስለማትችሏቸው ነገሮች መጨነቅ ጊዜ ማባከን አይደለምን? ታድያ ለምንድን ነው ስለ ነገ፣ ስለ ቀጣይ ሳምንት፣ ስለ ወደፊት የምንጨነቀው? ዛሬን ከእግዚአብሔር ጋር እንጓዝ፤ ስለ ነገም በታማኝነቱ ላይ እንደገፍ።
#bible #bibleverse #dailyverse #devotional #ጥቅስ #amharic #ethiopia #fyp #explorepage
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @kedusbible. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.