3 Aug 2026, 18:08 UTC383 views5 reactionsread 6 August 2026 ወልዳ የማታረጅ
አብባ ማታፈጅ
ልጆቿን ኮትኩታ
በሰለፎች መንሀጅ
ስንት አሳድጋለች
ፉርቃን ድንቅ ልጆች
ወንዝማ ውሃ ነው
ቢያፈስ ቢያመነጭ
ፉርቃንግን ኸይር ነው
የምታፈልቀው ምንጭ
አይደለም ወዳጅሽ
ጠላትሽም አይክድ
ያበረከትሽውን
ለሱና ለተውሂድ
ይገባሻል ፉርቃን
ፎቅና ግራውንድ
ስትገባ በግፊ
ስትወጣ በሰልፍ
ማንአለ ፉርቃን
ጀመዓዉየሚጎርፍ
ለሡብሂ ሶላት
የማይጥለው እንቅልፍ
ታዲያ ያሏህን ቤት
መስጂድ ለመገንባት
ሁሉም ይረባረብ
ይነሳ ባንድነት
ለነገህ ቤት ስራ
ለቀብርህ አሳልፍ
አሏህ ባገራልህ
በሰጠህ ተሳተፍ
ሞት በድንገት መቶ
ሳ…
👍5
Signed shems muzemil
15 Jul 2026, 11:18 UTC825 views11 reactionsread 6 August 2026 Photo
#እድሜ
ከብሩ ማሽቆልቆል ከዶላሩ መናር
ከሁሉም ተወዷል በብር ቢመነዘር
#ይሀው
እድሜ ልመነዝር ቁጭ ብዬ ሳይ ሳሳይ
ሰላሳ ሊሞላ አለኝ ሁለት ጉዳይ!
ሁሌም ገና ብዬ ራሴን እያየሁት
አዕማሩ ኡመቲ ግማሹን ሸኘሁት!
ሪያል እና ዩሮ ፓወንድ፤ ዶላሩ
ለሐላል ከሆነ እሱም ይሁን ጥሩ
ከሁሉም ከሁሉም
እድሜያቹ ስን'ገባ ይህንን አጣሩ!
✍ሸምስ /2016/
https://t.me/ibnmuzemil/1630
👍11
Signed shems muzemil
12 Jul 2026, 16:22 UTC683 views13 reactionsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍6💯6👏1
Signed shems muzemil
12 Jul 2026, 10:21 UTC754 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
እንደ ናዙ የእግር መንገድ
ነፋሻ ነው የልጅ መውደድ
ትንሽ ሆኖ ግዙፍ ወጀብ
የማይገልፁት አጂብ አጀብ
ከአውሎ ንፋስ የሚገዝፍ
ማይለወጥ፤ማይቀየር የማይነጥፍ
ጀግናና ሁላ ሚያደርግ እነከፍ
ህይወት ያምራል ይህ ሲሸከፍ!
✍ሸምስ
T.me/ibnmuzemil
👍1
Signed shems muzemil
13 Jun 2026, 16:46 UTC≈1,150 views12 reactionsread 6 August 2026 ለአራት ሩብ ጉዳይ!
የአንብያት ሱና የነብዩ ተግባር
ማግባት መዋለድ ነው መጣመር በትዳር
አግቡ ተብለናል ውለዱ ውደዱ
ላጤእየቋመጠ እየጓጓ ላአንዱ
አቅም ጉልበት ላለው ገርቷል ተአዱዱ!
ኡመር ሶስት ሲልህ ሀሀሀ ብለህ ምትሰማ
ህይወት አላማህን በግዜ አስማማ
የትም አያደርስም የፈነዳ ጎማ
እንደኔ እንዳንተው አንድ ያንገዳገደህ
ይህን ነሻጣ አይተህ የሰው ሰው ካመጣህ
ከአሏህ ከሰውም ዘንድ የሰውን ሰው ጎዳህ
ፋራ ፈሪም አትሁን ደፋር መቶ ያለፈ
አንድ ተግባር በልጧል ሺ ከለፈለፈ
ባለአንድ ፈሪዎች አትንበጫበጩ
ኡስታዝም አይቆሙም አራት ካልገጩ
ያንተ ደጋፊ ነኝ ምኖ በርታ በርታ
ሁለቱን አጥብቀህ ባትጨምርም ፈታ!
አሰናብቱኝ እኔን …
👍12
Signed shems muzemil
11 Jun 2026, 04:49 UTC≈2,670 views15 reactionsread 6 August 2026 ✍……
....የባከነ ዘመን....
የዘመን ቁልቁለት
በዘመን ተሟሽቶ፣
ወደ ምስራቅ ስሮጥ
ወደ ምዕራብ መሽቶ፣
ያዝኩት ባልኩት ቁጥር
አንድ እርምጃ ሸሽቶ፣
ሲገፋኝ ስገፋው
ሲሸሽ ስከተለው፣
ሰዶ በማሳደድ
ቀኔን ዘመን በላው።
✍️ አቡ ሙዓዝ አል ቡታጀሪይ
👍14👏1
Signed shems muzemil
28 May 2026, 04:10 UTC≈1,360 views12 reactionsread 6 August 2026 Video
Video, posted without a caption
👍11💯1
Signed الراجية عفو ربها
27 May 2026, 18:27 UTC≈1,140 views9 reactionsread 6 August 2026 Video
يليتني كنت معهم كي أفوز إذا
فازوا وحازوا الرحمن رضوانا
في ساحة الحرم الميمون أمنيتي
أنا أسأل الله إحسانا وغفرانا
ለበይክ የሚለው ቃል በምኞት የሚያከንፍ፣
ቀልብ ስልብ አርጎ ውስጥ ሚያንሰፈስፍ፣
አለው ልዩ ስሜት በተስፋ ሚያንሳፍፍ።
ሸምስ
t.me/ibnmuzemil
👍9
Signed shems muzemil
27 May 2026, 11:32 UTC≈1,110 views9 reactionsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍9
Signed shems muzemil
25 May 2026, 06:55 UTC≈1,110 views10 reactionsread 6 August 2026 🕋ልመን አልተሳካም?!
ትላንት በቻልከው ዛሬ ምትረታ
ህይወት ዥንጉርጉር ናት ባለ ሁለት አይነታ
ብርሃን፤ጨለማ ጤናና በሽታ
ቻልኩት ባሉት መቻል መቻልህ ሚገታ
ይች ህይወት ናታ!
ክብልል አስኮብልሎ
ወዳጅ ሚያገናኝ ከወዳጅ ነጥሎ
ምርኩዝ በዝነጣ ሚያስፈልግ አስጥሎ
መበልፀግ መደህየት አለመቻል ችሎ
ለማይሞላ ምኞት ለሸህዋ አዘንብሎ!
ላይዳን ታክሞ፤
የዱኒያን ስኳር ኦቨር ዶዝ ተቅሞ
ሲያውቁ መመረዝ ለመማቀቅ ታሞ
አንድ ግዜ ከፊት ሌላ ግዜ ድፍት
እንደዚህ ናት ህይወት!
ሲያውቁ መጀሃል ሲይዙ መደህየት
አቤት አስቀያሚ አቤት መልከ ጥፉ
እኛ ዘግይተናል የደላቹ እለፉ!
በቃኝ! ማለት ማታውቅ ህይወት ናት እከካም
ውዝሬን በውዝሬ ላይ ለአመት ልሸከም…
👍10
Signed shems muzemil
17 May 2026, 14:55 UTC≈1,290 views20 reactionsread 6 August 2026 ነገ ሰኞ
እና
ዙልሂጃ አንድ
👍20
Signed shems muzemil
11 May 2026, 04:34 UTC≈1,820 views31 reactionsread 6 August 2026 ╭─••──═••═─••─╮
✒️ኡሚዬ ይቅርታ!🖌
╰─••──═••═─••─╯
ላሳመምኩሽ ህመም ስትወልጂ ላማጥሽው
እኔን በማሳደግ ብዙ ለደከምሽው
ያኔ ላስቸገርኩሽ ልጅነት ሸውዶኝ
ድካም ልፋትሽን እንዳላየው ጋርዶኝ
ይቅርታ እልሻለሁ ደግሜ ደግሜ
እኔን በማሳደግ ለጨረሽው እድሜ
ይቅርታ ጠይቄሽ ጠብቃለሁ ምላሽ
እኔን በማሳደግ ለጠቆረው ገላሽ
ያኔ ያሳዘንኩሽ የነጠኩሽ ደስታ
አሁን ነው የገባኝ ኡሚዬ ይቅርታ!
//የተወሰደ//
👍31
Signed shems muzemil
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ibnmuzemil. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.