12 Jul 2026, 17:00 UTC453 views3 reactionsread 7 August 2026 እንዴት ነሽ ስላት
ሳቅ ታበዛለች
ትጫወታለች ፤
< አለሁ ! >
ትላለች - እንደሞላላት
ቁስሏን የማላውቅ እዬመሰላት ፤
የዐይኗ መደፍረስ
የገጿ ሽክረት
የአንጀቷ ማረር
የልቧ ቁስለት
ጥልቅ ስቃይዋን እዬነገረኝ ፤
እርሷ ግን ሁሌም አንድ የምትለኝ ፤
- - - - - - - - - አለሁ ደህና ነኝ !
ልዩ ፍጥረት ናት
አይደረሱባትም ፤
ስሟ ሕይወት ነው
ካልተሸከሟት አይረዷትም ፤
በሕመሟ መሳቅ
በቁስሏ ማጌጥ
ታውቅበታለች ፤
ልክ እንደ መሬት
ውኃ'ን ከእሳት ጋር ታቻችላለች ፤
ከራስ ቅራኔ
ከራስ ጋር ሙግት ቢኖርባትም ፤
ከመሳቅ በቀር
በሰው ፊት ማልቀስ አይኾንላትም ፤
ደህና ነኝ ከሚል
ከአንድ ቃል በቀር ——
ሌላ አይወጣትም ፤
እወድዳታለሁ ፤…
❤3
10 Jul 2026, 13:23 UTC462 views4 reactionsread 7 August 2026 #ፖለቲካዊ_ኮንትሮባንድ😂
የሩሲያ ዜጋ ነው። አንድ ልጁን ይዞ ወደ አሜሪካ ሊጓዝ፡ ሞስኮ በሚገኘው የሼሬሜቲቮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የፍተሻ ክፍል ደረሰ። ሻንጣው ተፈተሸ ፡ በውስጡ የሌኒንን ምስል የያዘ ቅርጻ ቅርጽ ነበረው። የአየር መንገዱ የፍተሻ ሰራተኛ፡-
"ምንድን ነው ይሄ ?" በማለት ጥያቄ አቀረበ። መንገደኛው ሩስኪ፥- "ጓድ ጥያቄህን ያቀረብክበት መንገድ ስህተት ነው። «ይህ ማነው?» ብለህ እንጂ «ምንድን ነው ይሄ ?» ብለህ መጠየቅ አልነበረብህም።
ለማንኛውም ይህ ሰው ለዓለም ጭቁን ህዝቦች ሲል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የታገለ የኮሚዩኒስት ስርዓት አርበኛ ነው፡፡ ለአዲሲቷ ሩሲያ ምስረታ ደግሞ ቁልፍ ሚና የነበረው ታላቁ አብዮታዊ መሪያችን ኮም…
❤2👍1🔥1
9 Jul 2026, 16:36 UTC432 views6 reactionsread 7 August 2026 ጥሩ ሴት ሁኚ
ታማኝ ሴት ሁኚ የራስሽ መርህና ክብር ይኑርሽ ክብርሽን ጠብቂ ሐያእ (ጨዋነት) ይኑርሽ
ራስሽን በእውቀት አንጪ ለራስሽ እንክብካቤ አድርጊ በደንብና ጤናማ ተመገቢ
የአእምሮ ሰላምሽን ጠብቂ ሰላትሽን በወቅቱ ስገጂ በአላህ ላይ ሙሉ በሙሉ ተመኪንፁህ ልቦና (ኒያ) ይኑርሽ
የቀረውን ነገር በሙሉ ለአላህ ተይው
❤3👍3
25 Jun 2026, 19:27 UTC750 views5 reactionsread 7 August 2026 ነፃነት
ኦሾ
ሙሉ በሙሉ ነፃ ለመሆን ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ ማግኘት አለብን ምክንያቱም የባርነት ስር መሠረቱ ያለው ባለማወቃችን ውስጥ ነው።
ጠልቀን ስንመረምረው ነፃነትህን የሚያሳጣህ ነፃነትን ለማግኘት ያለመፈለግህ ነው። ነፃነትህን የሚያሳጣህ ጥገኝ የመሆን ፍላጎት ነው። ራስህን የመሆን ኃላፊነት ላለመሸከም ያለህ ፍላጎት ነው።
ሰው ለራሱ ኃላፊነት ለመውሰድ በፈቀደ ጊዜ በነገራችን ላይ ይህን ማድረግ ሙሉ በሙሉ አስደሳች ነገር አይደለም በውስጡ እሾህና መራር ነገሮች ይገኙበታል። ጣፋጫ ነገር ሁሉ ሚዛናዊ ነገር እኩል በእኩል ተከትለው ይመጣሉ። ጽጌሬዳዎች ያለ እሾህ አይበቅሉም ቀናትን ሌሊትን ተከትለው ክረምቱ አብቅቶም ፀሐይ ትወጣለች። ሕይወት የተቃራኒ ነገሮች …
❤5
23 Jun 2026, 18:03 UTC711 viewsread 7 August 2026 https://youtube.com/shorts/y2fwZTmCxqo?si=XbeuZ7JkGJ95XDWl
6 Jun 2026, 17:06 UTC910 views12 reactionsread 7 August 2026 ዳዊት ኤፍሬም
……ይለበድ ######
አዳምና ሄዋን
አይናቸው ሲከፈት
ቀድሞ የተሰጣቸው
የቀለም ትምህርት
ምራፍ አንድ ላይ
የራቁት ምንነት
በገፅ ሁለት ላይ
በመራቆት ምክንያት
የሚመጣ ሃፍረት
በስተመጨረሻ ማጠቃለያው ላይ እራቁትነትን ሸፍኖ
ሚደብቅ አይነተኛ መንገድ
የሚሉ ነበሩ
ገና ከጅምሩ
ያኔም እሱን አውቀው
ትምህቱ ገብቷቸው
ቅጠሉን ለበሱት
ላስከፊው በሽታ
እጅ ላለመስጠት
ግና የቅጠል ልብስ
ዋጋም እንደሌለው
የገባው ፈጣሪ
የሁላችን ሰሪ
ወዶ አለበሳቸው
ከፀሃይ ከውርጩ
…
❤10👍2
Signed ለ_post
6 Jun 2026, 17:04 UTC677 views1 reactionsread 7 August 2026 #ክባዳም_ትረካዎች
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
የአባቴ የጉንጭ ሥርጉድ ከየት የመጣ ነው? እናቱ ሲሥቁ ብዙ ጊዜ ዐይቻታለሁ።አያቴ ጉንጯ እንደ ገብስ ገንፎ የነጣና የሞላ ነው።አባቱም ቢሆኑ ጉንጫቸው የተለመደ አዘቦታዊ ጉንጭ ነው። አባቴ የጉንጭ ሥርጉዱን ከየት አገኘው?
.
በመሠረቱ የጉንጭ ሥርጉድ የሚገኝ ነገር አይደለም።ሳይንሱ "ጉንጭ ላይ ሥርጉድ የሚፈጠረው ጉንጭን ጉንጭ የሚያደርጉ ጥቃቅን ሴሎች በቁጥር ሲጎድሉ ነው!" ይላል።
.
አባቴ ጉንጩ የሠረጎደው ሴል አንሶት ነው።ከእናቱም ከአባቱም እንዲሁም ከኔ ውዱ ልጁም በሴል ቁጥር ያንሳል። ምስኪኑ አባቴ!
.
ግን አባቴ ከእናቱም ከአባቱም እና ከኔ ውዱ ልጁ የበለጠ የሚማርክ ፈገግታ አለው።ፈገግ ሲል ያየ ማንም ሰው…
❤1
6 Jun 2026, 17:04 UTC614 views3 reactionsread 7 August 2026 የባሰ ቀን ሲመጣ
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
"ያልፋል!" ብዬ ቻልኩ፤
"ያልፋል!" ብዬ ተውኩ፤
"ባያልፍስ?!" በሚል ስጋት
ራሴን ብዙ ቀጣሁ፣
ስብዕናዬን ጥዬ ከሰው ዓለም ወጣሁ!
ዛሬ አለፈና. . .
ነገ ደረሰና. . .
"ይኼም ያልፋል!" ለማለት ብበቃም፤
ካሳደረኝ እንቅልፍ ደርሼ ብነቃም፣
ባላፈኝ ማግስቴ፣መንፈሴ አልረካም!
.
ያለፈው ምን አለው?
መጪው ምን ጎደለው?
የዛሬው እንባዬ አሁን እያሣቀኝ፣
ያለፈ ሥቃይ ነው፤ዛሬም 'ሚናፍቀኝ!
.
👇👇👇👇
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
👍3
3 Jun 2026, 16:41 UTC654 views2 reactionsread 7 August 2026 https://youtube.com/shorts/Ebc4XtLU2n8?si=Auisj4r3baOwvFHz
❤2
1 Jun 2026, 13:32 UTC774 views4 reactionsread 7 August 2026 የማይወዳደር እኩያ የሚያጣ
ከልቤ ግርጌ ስር አንዳች ስሜት ወጣ
ተሰማኝ ወደድኩህ ያንተን ጣዕም ለየሁኝ
ቆዳዬ ቀመሰህ ምላሴን ከዳሁኝ
ከየትኛው አካሌ ፍቅርህ የወደቀው
የሚያርበተብተኝ ጥፍሬን የሚነዝረው
አካልስ አለ ወይ የሚታይ ሚቀመስ
ሴትነት ገላዬን ነክቶ ሚያጎለምስ
ንገረኝ አንተዬ ከደጅ እንዳያድር ዳስም ልጣልለት
እንዲህ ያለ ፍቅር አያድርም ከኔ ቤት
በአዳፋዬ ባያድፍ ንፁህ ጥሩ ፍቅርህ
ከቆሸሸ ገላ ከዚህ በድን ይሽሽ
እንዲህ ያለ ልመና ሚዛን አያነሳም
የፍቅር ባህሪ ዙፋንን አይሻም
የት ጋር ነው የሚሰማኝ ምኔን ነው የያዝከው
የት ጋር ነው ያገኘኸኝ ምኔን ነው ያጣኸው
ብቻ ከልቤ ስር ስሜቴ ይፈልቃል
…
❤3👍1
31 May 2026, 15:38 UTC702 views3 reactionsread 7 August 2026 https://youtube.com/shorts/M4MdN435WGo?si=1jM__Qixc6E2XNl8
❤3
29 May 2026, 19:52 UTC≈1,440 views6 reactionsread 7 August 2026 #በሃገሩ_ባዳ !
ዩኒቨርሲቲ የላኩት ልጄ... ሃገሩን አምኜ፥
ምንም አይቸገርም.. ወገኑ ነው ብዬ...
"ተደበደበ!" አሉኝ እንዲያው እንደዋዛ!
"ሊሞትብሽ ነው፡፡" የሚል - መርዶ አርጂ በዛ።
...............................................
ምነው ሆዴም ባባ... አንጀቴ ሳሳብኝ
ያጠባሁት ጡቴን ክፉ ጦር ወጋብኝ፥
የምሰማው ነገር ገዳይ መርዝ ሆነብኝ፤
ፍርሃት ... ፍርሃት አለኝ..
ሊማር እንደወጣ - ልጄ እንዳይቀርብኝ፤
…………………………………………………………….
በላቤ ነው ያደገው - በጭስ ውስጥ አልቅሼ - ባነባሁት እንባ
እንጀራ ጋግሬ - ቆጮውን ጠፍጥፌ - ጡቶቼን ሳጠባ፥
ነበር መፅናኛዬ - የአይኔ ማረፊያ
አይኑ እስኪቀላ - በኩራ…
👍6
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @hollypoem. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.