27 Nov 2025, 14:58 UTC190 views4 reactionsread 8 August 2026 ገና ቁስልህ ሳይሽር መስቀል ላይ እያለህ፣
የአይሁድ ጭካኔ መከራው ፀንቶብህ፣
እንዲያ እየሰደቡህ እንዲያ እየገረፉህ፣
ምራቅ እየተፉ መራራ እየጋቱህ።
ገና በትኩሱ ከተወጋው ጎንህ ደም መፍሰስ ሳያቆም፣
ከግርፋት ብዛት የቆሰለው ገላህ ድኖ ሳያገግም፣
የአይሁድ ዘለፋ ስድብ ሳያበቃ፣
ገና ሳትቀበር ሞተህ ሳትነሳ፣
ያሳየህን ፍቅር ጌታ ሆይ አይረሳ።
እየጨከኑብክ አንተ ወደድካቸው፣
ልብህ ለእነሱ አዝኖ ባለማወቃቸው፣
አባት ሆይ አባት ሆይ አልክ ይቅር በላቸው።
ምን አይነት ፍቅር ነው ምን አይነት ትህትና፣
ከልብ ይቅር ማለት ህመሙ እየፀና።
✍✍✍ሀይማኖት ብርሃኔ
@haymanotbrhane
@haymanotbrhane
@haymanotbrhane
❤4
23 Nov 2025, 21:34 UTC198 views7 reactionsread 8 August 2026 እውነት ተቀብራ ከመሬት
እልፍ ጥያቄ ከልጅነት 🤔
የቱ ነው እውነት የቱ ሀሰት?🤔
ማነውስ ልክ ማነው ስህተት?🤔
ብዙ ቁጭት ብዙ ትዝብት።
በልጅነት ግራ አጋብቶን የጠየቅነው
ዛሬም አድገን መልስ የሌለው
ጥያቄያችን ትዝብታችን ቅያሚያችን
ለብቻችን የቆሰልነው የልጅነት ጠባሳችን
እንዴት ዳነ ማን ፈውሶ ዛሬ አቆመን?
ሳናጠፋ በማናውቀው በለጋነት የቀጡንን
ክፋት በቀል ከልጅነት ያስተማሩ ያሳዩንን
ከልጅነት ስንጠላቸው የኖርነውን
ሁሉን ትቶ ይቅር ማለት ማን አሳየን?
ያንን ሁሉ ቂም በቀልስ ማን አስረሳን?
ይቅር የሚል የወደቀን የሚያነሳ
የተረሳን የሚያስታውስ የተገፋን የሚያስጠጋ
ቁስላችንን የሚፈውስ ቂም በቀልን የሚያስረሳ፣
ስላለን ነው ሩሩህ አባት ደግ ጌታ፣
ለዚህ…
❤7
9 Nov 2023, 20:15 UTC922 views10 reactionsread 8 August 2026 Photo
https://vm.tiktok.com/ZMjvAbVQV/
❤6👍4
8 Nov 2023, 20:50 UTC818 viewsread 8 August 2026 https://vm.tiktok.com/ZMj7KtNGF/
7 Nov 2023, 17:24 UTC664 views3 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @mikurabfamily
ህዳር 02 ታላቅ የኪነጥበብ ድግስ
በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ
ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ
እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል!
ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የኪነጠበብ ስራች
ተውኔት እና ሞኖሎግ
ግጥም
ወግ
መነባነብ
ዝማሬ
ትምህርተ ወንጌል እና ሌሎች መርሃግብሮች ይቀርባሉ።
በብጹዓን አባቶች መድረኩ ተባርኮ ይከፈታል
በሰንበት ተማሪያን ዝማሬ መርሃግሩ ይጀምራል
በገጣሚ ኤሊያስ ሽታኹን
በገጣሚ ኢዮብ ዘሚካኤል
በገጣሚ ኪብሮም ደግፍ (ኬቢሻ) የግጥም ስራዎች ይቀርባሉ።
በአርቲስት ዋስይሁን በላይ (አዋበ) - ወግ እና ሌሎች የስነጽሁፍ ስራዎች ይቀርባሉ።
በተውኔቱ ጸጋን በታደሉ ተዋንያን ሞኖሎግና ሌሎች የትወና ስራዎች ይቀርባሉ
በሰዓሊ ቅዱስ ኤፍሬም - በመድረ…
👍3
30 Jul 2023, 21:01 UTC697 views5 reactionsread 8 August 2026 አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል፣
ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል፣
ዛሬም ስበደለው ልጄ ነሽ ይለኛል።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አስታዋሽ ያላሳጣኽኝ ቀስቃሽም ያልከለከልከኝ፣
አንቀላፍቼ እንድቀረ አሳልፈህ ያልሰጠኽኝ፣
ዘውትር ከቶ እንድነቃ በደሌን እያስታውስከኝ፣
በራሴ እንዳልመካ ድክመቴን እየነገርከኝ፣
ምን ጥፋቴም ቢበዛ ተስፋ ያልቆረጥክብኝ ፣
በበደሌ ብዛት ያረሳህ ያልጠላህ ያልተቀየምከኝ፣
ተመስገን ተመስገን እንጂ ላንተማ ሌላ ምን አለኝ።
ስሳሳት መንገድን ስቼ እንዳልቀር በዛው ሰምጬ፣
እንድወጣ ከጥልቁ በክንዶችህ ተመርኩዤ፣
ከሰላም መዳፍህ እንዳርፍ በእቅፎችህ ገብቼ፣
ልጅህ ነኝና የምትወደኝ ብበድልህም ምን አጥፍቼ፣
ኮርኮም ታደረግና ታነቃኛለህ ከእንቅልፌ…
❤4👍1
28 Jun 2023, 17:04 UTC645 viewsread 8 August 2026 Photo
ተዋህዶ ውድ እናቴ፣
ያደኩብሽ መሰረቴ፣
ክርስቶስን ያወኩብሽ፣
ይቺህን አለም የናቅኩብሽ፣
የአምላክ እናት እመቤቴን፣
የመስቀል ስር ስጦታዬን፣
የልጅነት ሽልማቴን፣
ከጌታዬ ያገኘሁብሽ፣
ልጅ ተብዬ የከበርኩብሽ።
ተዋህዶ ልዬ ቅኔ አላዋቂ የማይፈታሽ፣
የክርስቶስን ጌትነት አምላክነት የመሰከርሽ፣
ያልታደሉ ያላወቁ ጣዕም ፍቅርሽ ያልገባቸው፣
አለማወቅ አጀግኖ ከንቱ ድፍረት ሸልሟቸው፣
ተዋህዶ አንቺን ንቀው ብርሀንሽን አናንቀው፣
ጨለማ ናት ሲሉሽ ሰማሁ።
እንዴት? ቢባል መልስ የላቸው፣
ጥበብ የለው እውቀታቸው።
ቢያውቁትማ ቢገባቸው፣
ቢታደሉት ቢያድላቸው፣
ይሄ እውነት ባልጠፋቸው።
መስራችሽን ክርስቶስን የምታውቂ፣
ህይወትሽን ክርስቶስን የምትሰብኪ፣
የአምላክ እናት አዛኝ…
13 Jun 2023, 15:50 UTC502 views4 reactionsread 8 August 2026 🙏🙏እንኳንም ተወለድኩ🙏🙏
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
በዚች ከንቱ አለም መኖር ባያጓጓም፣
እንኳንም ተወለድኩ ጊዜው ባያሰኝም፣
የዘላለም ህይወት የዘላም ደስታ ምድር ላይ ባይገኝም፣
ለምን ተፈጠርኩኝ ለምን ተወለድኩኝ ብዬ አላማርርም።😊
በዚች አጭር ዕድሜ ስኖር በዚች ምድር፣
ብዙ ስላየሁኝ ብርቄ አይደለም ምንም።🤷♀
ቀኑ ጨልሞብኝ አዝኜ ስከፋ፣
አበቃልኝ ብዬ አንገቴ ስደፋ፣
አልፎ አይቼዋለሁ ሁነህልኝ ተስፋ።
በሁሉ ስጠላ በሁሉ ስገፋ፣
አለሁልሽ የሚል የልብ ወዳጅ ሳጣ፣
ወዳጅ ሆነህልኝ ወዳጅ ሰጠኽኛል፣
ያን ቀን አሳልፈህ አሳይተኽኛል፣
አመሰግንህ ዘንድ ምን ቃል ይበቃኛል።🙏🙏🙏
ሁሉ እንዳለ ሆኖ እንኳንም ተወለድኩ እንኳንም ፈጠርከኝ፣
ያንተ ፈቃድ ሆኖ እ…
❤4
29 Apr 2023, 15:32 UTC493 views2 reactionsread 8 August 2026 ሲሸቀጥ ሲነገድ ፍቅር ጉልት ዋለ
በራሱ ቀይ ቀለም መስቀል ላይ ተሳለ
ተዘባበቱበት ያን ሁሉ አለንጋ መቻሉ እረሱ
እስኪ ይውረድ አሉ ከመስቀል በራሱ
እስኪ ተአምር አድርግ ይሉታል በአለም
በታናሽ መገረፍ ተአምር አደለም?
እስኪ ድንቅን አድርግ ይሉታል አይፈሩምና ጡር
ተአምር አደለም መቸንከር በፍጡር?
ልፍስፍስ ነው አሉት አይችልም ማስገረም
እናትን እያዩ መመታት በራሱ ተአምር አይደለም?
ተዘባበቱበት እንደተራቆተ ዋለ በአደባባይ
ምድርን ያለበሰ በደመና ሰማይ
ከንፈር ስንት ገባ? ተጠምቶ ያደረ
ዉሀ ለሁለት ከፍሎ እንዳላሻገረ
ማቀፍ ስንት ገባ? መሳም ስንት ገባ?
ዋጋው ተወደደ ወይስ ቀዘቀዘ
አለምን የያዘ በአለም ተያዘ
ያንን ሁሉ አለንጋ መቻሉን እረሱ
እስኪ…
🙏2
28 Apr 2023, 06:41 UTC421 views5 reactionsread 8 August 2026 ወንድምህን አትናቀው
ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍፁም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰውን አትናቅ።
ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደሆነ አስተውል። እንዴት? ያልከኝ እንደሆነም ይህ የምትንቀው ወንድም የክርስቶስ ሕዋስ ሆኗል። የክርስቶስ ህዋስ ከሆነ ደግሞ እርሱን ናቅከው ማለት ክርስቶስን ናቅከው ማለት ነው።
ወንድምህን የምትንቅ ከሆነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት ፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትና ከርቤ ካጠጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም።
ስለዚህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።
📖ሰማዕትነት አያምልጣችሁ📖
✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ትርጉም…
❤4👍1
24 Apr 2023, 12:43 UTC416 viewsread 8 August 2026 ገና ቁስልህ ሳይሽር መስቀል ላይ እያለህ፣
የአይሁድ ጭካኔ መከራ ፀንቶብህ፣
እንዲያ እየሰደቡህ እንዲያ እየገረፉህ፣
ምራቅ እየተፉ መራራ እየጋቱህ።
ገና በትኩሱ ከተወጋው ጎንህ ደም መፍሰስ ሳያቆም፣
ከግርፋት ብዛት የቆሰለው ገላህ ድኖ ሳያገግም፣
የአይሁድ ዘለፋ ስድብ ሳያበቃ፣
ገና ሳትቀበር ሞተህ ሳትነሳ፣
ያሳየህን ፍቅር ጌታ ሆይ አይረሳ።
እየጨከኑብህ አንተ ወደድካቸው፣
ልብህ እጅግ አዝኖ ባለማወቃቸው፣
አባት ሆይ አባት ሆይ አልክ ይቅር በላቸው።
ምን አይነት ፍቅር ነው ምን አይነት ትህትና፣
ከልብ ይቅር ማለት ህማሙ እየፀና።
ይህው ዛሬም እኛ ተሰቅለህ የሞትክልን፣
ያን ሁሉ መከራ የተቀበልክልን፣
ህግህን አፍረስን ትእዛዝህን ሽረን፣
ለአለም ስንገዛ የሀ…
21 Apr 2023, 13:27 UTC348 views3 reactionsread 8 August 2026 የይሁዳን ሀሳብ አስቀድመህ እያወቅክ፣
መምህር ሆይ ብሎ ለማቀፍ ሲጠጋክ፣
ጌታ ሆይ አቀፍከው ሆነህ እንዳላወክ።
በዕለት ሀሙስ ትህትና ለመሰበክ፣
የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብለህ እያጠብክ፣
ይሁዳን ሳትለይ አብረህ አከበርከው፣
አውቀህ እንዳላወቅክ በትዕግስት ጠበከው።
ከእናንተ መካከል የሚክደኝ አለ አላውቀውም ብሎ፣
ብለህ ስትላቸው ጴጥሮስም ተነስቶ፣
እኔስ አልክድህም ብሎ ቢሞግትህ ሳትከራከርከው፣
እንደማያውቅ ሆነህ ዝም ብለህ አለፍከው።
የሰውን ልጅን ክፋት አስቀድመህ እያወክ፣
ወደምድር ወርደህ ተሰቅለህ ሞትክለት።
ጌታ ሆይ እውቀት እፁብ ነው ድንቅ ነው፣
ማወቅህ ፍቅርህን ከቶም አይቀንስው፣
ሁሉን አዉቀህ ሳለ ግን አትለወጥም፣
ሀጥያተኛ ብለህ ማንንም አትነፍ…
🥰2👍1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @haymanotbrhane. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.