10 Aug 2026, 16:24 UTC≈1,190 views48 reactionsread 12 August 2026 Photo
በአጭር ጊዜ ለመበልጸግ ወይም የንብረት ባለቤት ለመሆን በመቋመጥ ሒደት ለሚታለል ሰው ብዙም አላዝንም። ጫማ እንኳን ለመግዛት ስናስብ 'አምሮብኛል? ቆንጆ ጫማ ነው?' ብለን የምናማክረው ጓደኛ/እህት/ወንድም አስከትለን እንሔድ የለ?
የረቀቀም ይሁን ፍጥጥ ብሎ የሚታይ የማታለል ድርጊት ሲገጥመን አንድ ሰው እንኳን እንዴት አናማክርም? ገንዘቡ ጫን እያለ ሲሔድ ቢያንስ ሁለት/ሦስት ምራቁን ዋጥ ያደረገ ሰው ማማከር የለብንም? ልምዱ የለንም እንዳንል ከልብስ አቅም ተመካክረን እንደምንገዛ ነው ልምዳችን የሚያሳየው።
''ኢትዮጵያ ያለባትን ዕዳ 'በአዲሱ ሞዴሌ' በጥቂት ዓመታት ውስጥ መክፈል የሚያስችል አቅም እገነባለሁ'' ዓይነት ነገር ተናግሮ ፈገግ ከማለት ያለፈ ት…
👍36❤7😁4👏1
8 Aug 2026, 06:31 UTC≈1,650 views31 reactionsread 12 August 2026 የገንዘብ ሥርዓት የተለወጠበት ሒደት 'ዝግመተ-ለውጥ' ሊባል አይችልም። በተለይ አሁን ያለበት የለውጥ ሒደት በጣም ፈጣን ከመሆኑ የተነሳ የት እንደሚደርስ ማሰብ ራሱ ያዳግታል።
በቀደም Abdulkadir Hajj Nureddin ጋር ስናወራ ''የቢሮ ዕቃዎችን መግዛት ፈልጌ ነበር፤ ነገር ግን ሌላ አጣዳፊ ያልጠበቅኩት ወጪ ስለመጣብኝ ለዚያ ልከፍለው ነው'' አልኩት።
ለካ ይሄም ዕድለኝነት ነው። ገንዘባችን በቂ ቢሆንም ባይሆንም ለምን ጉዳይ እንደምናውለው የማሰብም የማድረግም ነፃነት አለን። ወደፊት ምናልባት ብዙም ባልራቀ ጊዜ ይህ የመገልበጥ ዕድሉ ሰፊ ነው። ገንዘቡ ነው የሚያዘን። ''ይህ ገንዘብ ለቢሮ ዕቃ 'programmed' ተደርጓል፤ ለሌላ አገልግሎት ማ…
❤30👍1
8 Aug 2026, 06:31 UTC≈1,540 viewsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
3 Aug 2026, 10:52 UTC≈2,640 views69 reactionsread 12 August 2026 የሙዚቃን ያህል ወደኋላ ወስዶ ክስተቶችን የሚያስታውስ ነገር ያለ አይመስለኝም። ጥሩ ትውስታም ይሁን መጥፎ (ለምሣሌ ጦርነት) በሙዚቃ ትውስ እንዲል ይሆናል። አብዛኛው ቤተሰቤ ልጆቼን ጨምሮ ሙዚቃ አያዳምጡም ማለት ይቻላል። እንዴት ግድ አይሰጣቸውም እያልኩ እገረማለሁ። አባቴማ ሙዚቃ ሳዳምጥ ካጋጠምኩት ግልምጫው ራሱ እህል ውሃ አያሰኝም። 😁
ከሰሞኑ የተሾመ አሰግድ ''ዘራፌዋ''ን ስሰማው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ highschool ፣ የማትሪክ ዝግጅት፣ ሴቶች በየቀበሌው ስንቅ ሲያዘጋጁ የነበረው ... ትዝ ያላለኝ ነገር የለም።
ዛሬ ዩቲዩብ ላይ randomly ሙዚቃ እያዳመጥኩ:-
አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሐ…
❤54👍12🕊2👎1
30 Jul 2026, 11:29 UTC≈3,210 views28 reactionsread 12 August 2026 እኔ ታክስን የተመለከተው ስልጠናችንን እንዴት በአሪፉ ማከናወን እንዳለብን እያሰብኩ ቢዚ ሆኛለሁ፤ ለካ አዲስ ዓይነት ታክስ (ሲብላላ የከረመ ቢሆንም) ሊጣልብን በዝግጅት ላይ ነነ! 🤔
በዚች አንድ ወር ውስጥ ሁለት አዳዲስ ታክሶች! 🤔 በኋላ እናወጋዋለን።
የታክስ ስልጠና ተሳታፊ ሞልቶ ምዝገባ አጠናቀናል።
ቀድሞ የተሰጠው ''Finance for Non-Finance Managers'' ስልጠና በጣም ተወዳጅነትን በማግኘቱ በመሃል ለሁለት ድርጅቶች ሰጥተናል። ይህንን ስልጠና በርካታ የቢዝነስ ባለቤቶች እና የድርጅት አመራሮች በውስጥ እየጠየቃችሁን ስለሆነ በዚህ ክረምት አንድ ጊዜ ብቻ ተጨማሪ ስልጠና ለማዘጋጀት አስበናል። ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ ትችላላችሁ።
----…
❤25🤮3
27 Jul 2026, 17:47 UTC≈3,320 views66 reactionsread 12 August 2026 11ኛ ክፍል ወደ መጨረሻው ሳለሁ (2ኛ ሴሜስተር ጅማሬ) የኢትዮ-ኤርትራ ጦር^ነት ሙቀቱ እየጨመረ ስለማትሪክ ፈተና ደግሞ ግራ መጋባት እያየለ የመጣበት ነበር። በተለይ የወንድ ተማሪዎች።
አንዱን ቀን ሁለት ቦርጫምና አንድ ከሲታ የመንግሥት ካድሬዎች በኃ/ማርያም ማሞ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዳራሽ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ሰበሰቡን። ስለ ህገ-መንግሥት እና ሌሎች ምንም ያልገቡንን ነገሮች ካብራሩልን በኋላ ስለ ኢትዮ-ኤርትራ ጦር^ነት ገለፃ አደረጉ። ሃሳብ እንድንሰጥ ጠየቁ። እኔ የማስበው የዚያን ቀን ከሰዓት ሚኒ-ሚዲያ ላይ ስለማቀርበው ጽሑፍ። እዚህ የሚወራው ጦር^ነት። ''የኃ/ማ/ማሞ ተማሪዎች ናቸው? አይደሉም?'' ብለን የተጠራጠርናቸው 2…
❤48😢16👏1🔥1
27 Jul 2026, 13:07 UTC≈2,860 views26 reactionsread 12 August 2026 በዚህ ሁሉ ጊዜ አዲስ አበባን የሚያስንቁ ቢያንስ 4 ከተሞች ለምሣሌ የንግድ (ቢዝነስ) ከተማ፣ የቱሪዝም ከተማ፣ የኢንደስትሪ ከተማ እና የመንግሥት መቀመጫ ከተማ ሊኖሩን ሲገባ እኛ ሆዬ ''አዲስ አበባን ምን እናድርጋት? በእገሌ ሥር ትሁን የእንትና አካል ትሁን?'' ... ስታሳዝን?! 😥
ከተፈጠረች 4.5 ቢሊየን ዓመት ያለፋት 'እናትየዋ' መሬት ራሱ ሳትታዘበን አትቀርም። ቢሆን ቢሆን አጠቃላይ የአገሪቱ የአስተዳደር ወሰን አከላለል ነው መ'ቀየር የነበረበት። That's the rub!
❤20👍3🙏3
26 Jul 2026, 10:03 UTC≈3,580 views29 reactionsread 12 August 2026 Photo
ለክረምት ንባብ❗️ ለእርሶም ልጅዎችዎም❗️
=========
መ-ገንዘብ መጽሓፍ ቅድመ ሕትመት ዋጋ
- የታዳጊዎች 825 ብር
- የአዋቂዎች 900 ብር
- ሁለቱን የምትፈልጉ 1,725 ብር
ዋጋው በመላ ኢትዮጵያ በፖስታ ቤት ማድረሻን ይጨምራል::
CBE
1000632718245
IZZELISLAM ABDULKADIR
ስክሪንሹት, ስም, ስልክ, አድራሻ (ለምሳሌ ቡታጅራ, ሰመራ, እንጅባራ, ሳሪስ, ጨርቆስ) በዚህ ቴሌግራም
👇👇
https://t.me/MeGenzeb
ቴሌግራሙ ውስጥ ከዚህ ውጪ መልእክትም ሆነ ጥያቄ ባለመጠየቅ ተባበሩን።
ብሏችኋል የመጽሐፎቹ ደራሲ አብዱልቃዲር ኑረዲን!
👍18❤11
23 Jul 2026, 07:56 UTC≈3,250 views130 reactionsread 12 August 2026 'ለሰው ልጅ መሠረታዊ ነገሮች 3 ናቸው' ተብለን የተማርነው 1ኛ ክፍል ነው። ምግብ፣ መጠለያ እና ልብስ። 'መራባት' ም መሠረታዊ ነገር ስለሆነ አራተኛ ሆኖ ይገባል። መንቀሳቀሻ አምስተኛ መሠረታዊ ነገር ነው። ሁሉም basic needs ናቸው።
በኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት፦
1ኛ. ምግብ ላይ በደንብ አድርጎ ታክስ ተጭኗል።
2ኛ. አልባሳት ታክስ ተጭኖባቸዋል።
3ኛ. መጠለያ ታክስ ተጭኖበታል።
4ኛ. መንቀሳቀሻ (መኪና) - የተለያዩ ተዘዋዋሪ ክፍያዎች እንዳሉበት ሆኖ ከሰሞኑ አዲስ ታክስ ይጫንበታል። በቀጣይ በቅሎና ፈረስ ታክስ ይከፈልባቸው መባሉ አይቀርም።
አሁን የቀረው አንዱ ነው። ''የመራባት ታክስ''! ለምን በወለድናቸው ልጆች ቁጥር ታክስ አንከፍልም? ? …
❤56😁48🙈11👍10🤷5
21 Jul 2026, 08:04 UTC≈4,450 views118 reactionsread 12 August 2026 ምግብ በጣም ውድ ከሆነባቸው የአፍሪካ ከተሞች በ4ኛ አንዳንዴም በ5ኛ ደረጃ አናት ላይ ትገኛለች፤ የ'ኛዋ አዲስ አበባ።
ኩዋላ ለምፑር (ማሌዥያ) በኖርኩባቸው ወራት አንድ ነገር አስተውዬ ነበር። ብዙ ቤተሰብ ያላት የኔ ጓደኛ የነበረች ሱዳናዊት ቤት ለመከራየት ተቸግራ አየሁ። ምክንያቱም እዚያ አገር ያሉ ቤቶች በጣም ሰፊ ቢሆኑም እንኳን ኩሽናዎቻቸው በጣም ትንንሽ ናቸው። የለውም ማለት ይቀላል። ይህም የሆነው ምግብ እና መጠጥ እጅግ በብዙ ዓይነት እና ጣዕም እዚህም እዚያም እንደልብ በርካሽ ዋጋ ስለሚገኝ ነው። እናም የኩሽናው አስፈላጊነት ምግብ ከማሞቅ ወይም ፍሪጅ ከማስቀመጥ የዘለለ ብዙ ሚና የለውም። እኛ ደግሞ (ሱዳናዊቷ ጓደኛዬን ጨምሮ) ጠባብ ኩሽና የሚ…
❤83👍35
21 Jul 2026, 08:04 UTC≈3,450 viewsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
20 Jul 2026, 14:05 UTC≈3,330 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤2
Showing the 12 most recent of 23 posts we hold for @hawla_Ahmed. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.