20 Dec 2025, 19:30 UTC965 viewsread 8 August 2026 ረጀብ መጣልን ♥️
ለታላቁ ወር ረመዳን በሰፊው የምንዘጋጅበት፣ ብዙ ኸይሮችን ያዘለው የተከበረ ወር መጣልን አልሃምዱሊላህ!
አላህ ሱረቱል ተውባ ላይ እንዲህ ይላል:
إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ
«የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ…
Signed Umu Zinirah saduni
23 Sept 2025, 19:45 UTC≈1,380 views0 reactionsread 8 August 2026 ከአላህ ወደ አላህ
አንዳንዴ ህይወት ድክም ታደርጋችኋለች አንዱን አረፍኩ ስትሉ ሌላን እያከታተለ ይፈታትናችኋል።ታዲያ ነገሮች ሲደራረቡ ነገ የተሻለ ይሆናል ብላችሁ ያመናችሁት ያቦታ ላይ አላህን ስታጡት የተዋችሁ አይነት ስሜት ይሰማችኋል።ይህቺ ስሜት አድጋ አላህን በ..ጣም ካመናችሁበት ጥግ ታፈገፍጋላችሁ
﴿وَذَا النّونِ إِذ ذَهَبَ مُغاضِبًا فَظَنَّ أَن لَن نَقدِرَ عَلَيهِ...﴾
እንዳለው አላህ የነብዩላህ ዩኑስ ዐለይሂ ሰላም አይነት ይሆናል ሁኔታችሁ።አላህ ታዲያ የሚወዳችሁ ከሆነ በዚሁ ስሜት አይተዋችሁም።ልክ እንደ ነብዩላህ ዩኑስ አንድ ሳይሆን ድርብርብ ጨለማዎች ውስጥ አስገብቶ ዙሪያችሁ ብዙ ሰዎች ያላችሁ የሰው ሀብ…
Signed Umu Zinirah
17 Sept 2025, 03:32 UTC≈1,130 views2 reactionsread 8 August 2026 እያብላላቿት እደሩ🙌🏼
" አንዳቹ በ እጁ ተክል ይዞ ቂያማ ብትቆም እንኳን ይትከላት " የሚለው ሀዲስ ትዝ አላቹ? (ያኔ የ አረንጓዴ አሻራ ጊዜ ኡስታዝ ያልሆኑ ኡስታዞች abuse ያደረጉት ሀዲስ) የ ሀዲሱ ቃል በቃል አማርኛ ትርጉሙ ትክክል መሆኑን እርግጠኛ አይደለሁም ግን ዋናው ነገር ማስታወሳቹ ነው😂🙄 ብቻ ምን መሰላቹ ሀሳቡ ለምን ይተክለዋል? ቂያማ እየቆመ ነው ፣ ዱንያ እየጠፋች ነው፣ የሰው ዘር ሁሉ አልቋል፣ ተክሉ ለማነ ሊጠቅም ነው የሚተክለው? አንደኛ አያድግም ሁለተኛ ቢያድግም ምድር ላይ የሚቀር ፍጥረት የለም ለምን ይተክለዋል? ለምን መሰላቹ? የሱ ሀላፊነት መትከል ብቻ ስለሆነ ነው።
ሙስሊም የተሰጠው ሀላፊነት የመልፋት ( የ ሰዕይ ) ነ…
👍2
Signed Umu Zinirah
4 Jul 2025, 19:02 UTC≈1,650 views10 reactionsread 8 August 2026 ~ሐጃ ሲኖርህ እጅህን ወደ ላይ በማንሳት ብቻ አይደለም አላህ የሚለመነው፡፡
ለአላህ ብቻ ብለን በምናደርጋቸው መልካም ነገሮችም ጭምር አላህ ይለመናል፡፡
የበደለንን ዐፉ በማለት፣ ለወላጆቻችን መልካም በመዋል፣ ሶደቃ በመስጠት፣ የቲምን በማስታወስ፣ የተቸገረን በመርዳት፣ ሰውን ወደ መልካም ነገር በመጥራት፣ ከመጥፎ ነገር በመከልከል፣ ግራ ለገባው መፍትሄ በመስጠት፣ ቁርኣን በመቅራት፣ ሰዎችን ከጭንቅ በመገላገል፣ ዚክርና ኢስቲግፋር በማብዛት፣ በሰዎች ነፍስ ውስጥ ደስታን በመዝራት፣ ለሌላ ሰው ዱዓ በማድረግ፣ ስለ አላህ ባሮች በመጨነቅ፣ ተውባ በማድረግ እና በመሣሠሉት ደጋግ ሥራዎች ሁሉ ወደ አላህ በመቃረብ አላህ ይለመናል፡፡
ወዳጆቼ! ችግር ሲገጥማችሁ፣ መከራ ሲ…
👍10
Signed Umu Zinirah
3 Jul 2025, 05:38 UTC≈1,640 views9 reactionsread 8 August 2026 Photo
አላህ የተማመኑበትን ባሮቹን አይተውም አይጥልምም!! በአሹራ የሆነው ይሄ ይመስለኛል ኧረ ነውም! የትኛውም በዳይ ሰው የትልቅ ስልጣን ባለቤት ..... የብዙ ጭፍራ ሰራዊት..... የታጠቀ ሀይልና ጉልበት ብኖረው እንኳን.... ደካማና በአላህ የሚያምን የሚመካና የሚተማመን አካልን ፈፅሞ ማሸነፍ አይቻለውም!!
በአሹራ ከጠላት መሸሽ መሸነፍ አለመሆኑን ተምረናል! ። በአሹራ ከጥልቅና ሰፊ ባህር ፊት ቁሞ ከኃላ የሚከተል የታጠቀ ጠንካራ ጦር ኑሮ እንኳን..... በአላህ መተማመን መደገፍና መመካት ምን የሚያምር መደገፊያና መመኪያ መሆኑን አውቀናል!! 🥰
ከዚህ ሁሉ ቦሀላ ደግሞ ለባሪያው ድልን የሚያጎናፅፈው ጌታ የማይሆነውን እንዲሆን አድርጎ…
👍5🥰4
Signed Umu Zinirah
1 Jul 2025, 14:06 UTC822 viewsread 8 August 2026 Photo
🔊🔊 ታላቅ የስልጠና ፕሮግራም
🗣 ሀሙስ ሰኔ 26/2017
▶️ የልጅ አስተዳደግ ስልጠና
ለእናቶች
🔟 ( አስር) መርሆች ለአሳዳጊዋች
🕌 አድራሽ -
ቀራኒዮ በሁዜፍ መስጂድ
⏰ 3:00 - 6:00
ማሳስቢያ፡- ስልጠናው የሚሰጠው በታዋቄው እስታዝ አብድረህማን ሼህ መሀመድ
Signed Umu Zinirah
29 Jun 2025, 18:27 UTC846 viewsread 8 August 2026 እንደዚህ የቁርዐን አያ ልቤን የሚያረጋጋልኝ የለም።
🌸{ لا تَدۡرِی لَعَلَّ ٱللَّهَ یُحۡدِثُ بَعۡدَ ذَ ٰلِكَ أَمۡرࣰا }🌸
የኛ የአዋቂነት ልክ ባለፉት ነገራቶች እንጂ ከአመታት ቡሗላ ወይም ከቀናት ፣ እረ እንደውም ከደቂቃዎች ቡሗላ ምን እንደሚፈጠር አናቅም። even ባለፉት ነገራቶች ስንል ራሱ ምክንያታቸውን ማናቃቸው መከሰታቸውን ብቻ የምናወራባቸው ነገራቶች ብዙ ናቸው።
ግን አላህ ደግሞ ይሄ ነገር አክትሞለታል ስንል እንደ አዲስ ሲያደራጀው እናያለን። እንዳልነበረ እና እንዳልተፈጠረ አድርጎ ክስተቶችን በጥሩ ነገር ሲቀይርም ብዙ ግዜ አስተውለናል።
ቆመው ቀሩ የተባሉት ሲያገቡ
መውለድ አይችሉም የተባሉት ፣ መንታ ሲያሳቅ…
Signed Umu Zinirah
5 Jun 2025, 15:10 UTC≈1,400 views4 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @MuradTadesseFile
ዱዓ ለሚፈልግ…
👍4
Signed Umu Ubeydulah
4 Jun 2025, 15:22 UTC≈1,370 views5 reactionsread 8 August 2026 🙌
አረፋህ ሊመን አረፈህ🥰
ነገ ቤት የማፅጃ ወይ መጋረጃ የማውረጃ ቀን አይደለም። የኢድ ሸመታም ሆነ የመዝናኛ እንዲሁ!
ነገ አላህ የሰማይ ባለሟሎች ላይ በአረፋ ሰዎች የሚኩራራበት፤ የሰው ልጆች ከእሳት በገፍ ነፃ የሚባሉበት ከሁሉ በላይ ዱአዎች በሙሉ ተቀባይነት የሚያገኙበት እለት ነው።
ለይለቱል ቀድር ባትታወቅ የውሙ አረፋ ትታወቃለች። በለይለቱል ቀድር መላእክት ቢወርዱ በአረፋ አላህ (እሱን በሚመጥን አወራረድ) የሚወርድበት ነው!
ነገ አላህ በጊዜ ፀጋ ላጣቀማችሁ አንድ to do list ላካፍላችሁ
ጠዋት
ከፈጅር በፊት ከለይሉ ጥቂቱን መስገድ፣ ስሁር መመገብ እና ኢስቲግፋር ማብዛት!
ከሰላት በኋላ ቀጥታ ተክቢራ መጀመር ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ ቁርአ…
👍5
Signed Umu zinirah
1 Jun 2025, 13:56 UTC966 views8 reactionsread 8 August 2026 እሷ አላህ ላይ እንዳላት መተማመንና ፍላጎቱን መቀበሏ እግሯን ዘርግታ ጌታዋ ሚያረግላትን መጠባበቅ ትችል ነበር።ግና የአላህን ውሳኔ ከመቀበል፣በሱ ላይ ከመተማመን ቡሃላ ሰበብ ማድረሷ ግድ መሆኑ ገብቷታል።
ለዛም ነው ረሃብ ባጣበቀው አንጀቷ፣የበረሃው ንዳድ አቅም እያሳጣት፣የተራበ ህፃኗን መሬት አስተኝታ ከሰፋ መርዋ ባለ በሌለ አቅሟ ለሰባት ግዜ የተሯሯጠችው።እስከ ጥግ ሙከራዋን ካየም ቡሃላ ነው ጌታዋ ዘምዘምን የሰጣት።
የእኛም የትዕግስታችን ፍሬ ዘምዘማችን ከመምጣቱ በፊት አድካሚ ሩጫ ግድ ይለናል።ፈተናችን አቅማችንን እያዳከመው፣ተስፋ ለመቁረጥ ጥግ እያደረሰን የጌታችንን ታላቅነት እያሰብን፣የቻልነውን ያህል ሰበብ ለማድረስ መሯሯጥ ይጠበቅብናል።
ውሳኔውን …
🥰6👍2
Signed Umu zinirah
30 May 2025, 10:53 UTC878 views4 reactionsread 8 August 2026 ነፍሳችን ደክሟል .....ውስጣችን ዝሏል .... ወንጀላችን በዝቶ ጀርባችን ጎብጧል !😥 ቀናት በቀናት በተተካኩ ቁጥር አመታት በተደራረቡበት ልክ እኛም ከፍ ከማለት ይልቅ ዝቅ እያልነው አለን!😥🥺 በርግጥ አላህ አዛኝ ነው ...... !🥰 የምንቀሳቀሰው በእዝነቱ ነው ከፍ የምንለውም በቻይነቱ ! ረመዷንን ወስዶ ሸዋልን ተካልን ከዛ ስንሻገር በተወዳጆቹና ምርጦቹ የዱንያ ቀናት ላይ አስገኘን !* ይህ የአላህ ችሮታ ነው ...... በተቻለ ወደአላህ ለመቅረብ ደፋ ቀና ማለት አለብን ቀኑ በረካው ተነስቷል እሄው ዛሬ 3ተኛውን ቀን እያገባደድን ነው ! አረፋ ላይ ለመቆም እስከምትጠራን እዚሁ በያለንበት ለበይክ እንልሀለን🤲 ወንጀሎቻችንን ወዳንተ እንናዘዛለን ..…
🔥4
Signed Umu zinirah
28 May 2025, 13:37 UTC975 views4 reactionsread 8 August 2026 ዙል_ሒጃ 1
ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ ምርጦቹ
ከግብፅ ምድር የተገኘች አንዲት ባሪያ ጌታዋ ሊያልቃት ሲሻ በበደል ይገዛት ከነበረ ንጉስ ቤት አላህን ወደሚፈራ የነብይ ቤት አሸጋግሯታል። በባርነት ቀንበር ውስጥ ሳለች የአሳዳሪዋ ማህፀን ልጅ ባለማፍራቱ ባሏ እሷን እንዲያገባ ታደርጋለች። ከባርነት ቀንበር ወደ ነብይ ሚስትነት የተሸጋገረችው ሀጀራ!
የዱንያ ሀሏ ሞላ ሲሉ መጉደል ነውና የነብይ ሚስት ሆና ተልቃ ነብይ የወለደችው ሀጀራ ጌታዋ ለሌላ ፈተና አጫትና ምድረበዳ በረሀ ላይ ከልጇ ጋር እንድትጣል አዘዘ። ኢብራሂም ዐለይሂ ሠላም የታዘዙትን ሊፈፅሙ በዝምታ ወደ በረሀ ወስደው ትተዋቸው ሊመለሱ ሲሉ አላህ አዟቸው መሆኑን ጠየቀችና አዎ የሚል ምላሽ ስታገኝ ልቧ ተረጋጋ…
👍4
Signed Umu zinirah
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @hamzaibnudinoislamicmedia. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.