“የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤” — ዮሐንስ 10፥4 ይሔን ቃል በጣም ነው የምወደው ❤️ ለምን ካላቹኝ... 🎃እረኛዬ የማያውቀው ነገር በሒወቴላይ አይሆንም ነገሮች መልካም ባይሖን እንኳን ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም ምክንያቱም.. እሱ ከፊቴ የቀደመው ለኔ መልካምና የሚጠቅመኝን ከኔ በላይ ስለሚያውቅ አስቀድሞ መርጦ ይጠብቀኛል ስለዚህ የሚሆነው ነገር ሁሉ አስቀድሞ እረኛዬ ቀምሶትና መርጦልኝ ሰቶኛል..😇 አንድ ነገር ልበላችሁ.. 🎃 የምታልፋበት ሆነ አሁን ያላቹበት ሁኔታ እረኛችሁ አስቀድሞ መርጦላችዋል.. 🎃 ችግሩ ከሚጎዳቹ በላይ የሚጠቅማችሁ ይበዛል.. 🎃 ስለናንተ ከናንተ በላይ ይጠነቀቃልና…
Signed እርቅ የጌታ ባርያ የምድር ጨው የአለም ብርሃን
