25 May 2026, 20:29 UTC571 views7 reactionsread 6 August 2026 አታውቂም ልንገርሽ
======+=====
አንቺ እኳን ጨክንሽ ላትመጪ ሔደሻል
በስለቱ ፍቅርሽ ልቤንም ቆርጠሽዋል።
ትመጫለሽ ብዬ ማዶ ማዶ ባይ
አትመጣም ይሉኛል ለመሆን ገላጋይ
እውነት ግን አትመጪም?
ተስዬ ነበረ ከቤተ መቅደሱ
ግዜው ነጎደ አልደረሰኝ መልሱ
አንቺን ስላልሰጠኝ እግዜርን መውቀሱ
በዝምታው ብዛት ለኔ መመለሱ?
ዛሬ ግን ታመምኩኝ መመነን አማረኝ
አንቺን መሳይ አየው እግዜር ሊፈትነኝ
እመጣለሁ በይኝ መጠበቅ አልደክምም
ሄደሽ ቀርተሻል እውነት ግን አመጪም?
"ሺ ቢባል ዘመኑ ፍቅሬ...........
ቀን፦17/09/2018
✍ ምንተስኖት ሱሌይማን
👍4😢3
14 Apr 2026, 10:52 UTC877 views9 reactionsread 6 August 2026 Photo
አይ መክሊት
----+----------
መክሊት ወይስ ገንዘብ
ብቻ መልስልኝ ሳታበዛ ሠበብ?
ገንዘብ ያለም ገዢ
ሁሉን ነገር ከዋኝ
ብትታመም አሳክሞ አዳኝ
ታድያ መክሊት ነው ምትመኝ?
ከችግር በመነሳት ጥያቄዬን መልስልኝ።
ነበርኩ ደራሲ እንዲሁም ገጣሚ
ብታመም አጣው አሳካሚ።
ሕልሞቼን እጆቼ ቢፅፉ
እንጀራን ፍለጋ ስደት ሆነ ትርፉ
ለምን?
ማጣት ስለሆነ ክፉ።
ነዋይ ተናግሮታል በሙዚቃ ግጥም
እኔ ማን ሆኜ በመክሊቴ ላልም
ቅዠት ቢሆንብኝ መክሊቴ ዘወትር
ተሸንፊለሁ በፍራንካ ፍቅር
አወየው ገንዘብ
አወየው ብር።
ገጣሚ፦ ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦06/08/2018
🌚5❤4
8 Dec 2025, 05:42 UTC≈1,300 views2 reactionsread 6 August 2026 Posted without readable text
❤2
Signed Abenezer 🎥
21 Oct 2025, 15:59 UTCviews —0 reactionsread 6 August 2026 Posted without readable text
21 Oct 2025, 15:58 UTC≈1,510 views3 reactionsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👏2🥰1
Posted without readable text
6 Oct 2025, 15:30 UTC≈1,530 views22 reactionsread 6 August 2026 ማረኝ
====
ሰውነኝ ስጋ ለባሽ ሀጥያት ያደለበኝ፤
ባልገድል ባልዘርፍ ሀጥያቴ ባያቀኝ፤
በአምሳልህ ተፈጥሪለው እና ማረኝ።
የበደሉኝን ሁሉ ቂምን የማልሽር፤
ዳቢሎስ ተጠግቶኝ የማይገባኝ ፍቅር፤
ሰው የሚያስጠላኝ ብቻያን የምኖር፤
አንተን ለመጠጋት ሀጥያቴ ሚቀፈኝ፤
አቤቱ አማላኬ ሰው ነኝ እና ማረኝ።
✍ምንተስኖት ሡሌይማን መሐመድ
ቀን፦26/01/2018
❤13👍5🙏2👏1🥰1
29 Jul 2025, 17:55 UTC≈1,970 views12 reactionsread 6 August 2026 ጦርነት ሠለቸን
---------+__
ወጣት ተገደለ
ከገደል ከዱር
እርስ በእርስ እልቂት
በዚች ቅድስት ሀገር
ማንስ ነው ያልሞተ
በሀሳብ፤በባሩድ
የሠው ልጅ ረከሰ
ኑሮ እንኳን ሲወደድ።
✍ምንተስኖት ሱሌይማን
❤6👏2😭2👍1🥰1
21 Jul 2025, 21:57 UTC≈1,920 views11 reactionsread 6 August 2026 ወይ ፍቅር
==+===
ፀሀይ ገባቸች ብርሀን ተባረረ
ይነጋል ይመሻል እየተቀያየረ
ልቤ ከእኔ ወጥቶ ከሷ ቤት አደረ።
ወይ ፍቅር
አምላከ ዓብ ልቤን አይቶ
አንቺን ሠጠኝ ጌታ ፀሎቴም ሠምቶ።
አለም በጥበብ ቃል ፍቅሬን ብትገለጠው
አካሌ በምድር አንቺን ነው ሚመስለው።
ወይ ፍቅር
በቅዠት ያስዋኛል ሠፊውን ውቂኖስ
የጎሠቆለ ጎጆዬን በፍቅሯ ስታድስ
ምድር ጨልማብኝ የሚታየኝ ጠፍቶ
በፈገግታሽ ብርሀን ታቶኛልና ነግቶ።
አዎ ሳቂልኝ ሳቅሽ የኔ ገዳይ
ግን ፀለይኩኝ ሌላው እንደኔ አንዳያይ።
ዓይኖትሽ ክብል ክብልል ሲሉ ሲስተዋሉ
አፍዝዘው ከመንገድ አድርቀው ያስቀራሉ።
እምወድሽ የጎደለው ጎኔ
ፍቅርሽ በርቶቶብኝ ታምሚለሁ እኔ
በቶሎ ነይልኝ አትራቂ ከጎኔ።
✍ምንተስኖት ሡሌየ…
❤10👏1
30 Jun 2025, 20:20 UTC≈1,820 views10 reactionsread 6 August 2026 ስለ ውበቷ ላድንቅ
----__----------
ዓይና ሲንከባለል ልብን ይነጥቃል
ሀር መሳ ፀጉራ የሠው ቀልብ ይስባል
የጥርሷ ፈገግታ አይኖችን ያጠፋል
የከንፈሯ ውበት ብሉኝ ብሉኝ ይላል።
እንኳን የአዳም ዘር በውበት ሚል ዕልም
ውበቷ ሴቱንም ሚስደምም
ስለውበቷ ላወራ ቃላት ቢያጥርብኝ
የጠዋት ፀሀዬ ለኔ ብሪልኝ።
✍ምንተስኖት ሡሌይማን መሐመድ
ቀን፦23/10/2017
ከ ምሽቱ 5:20
❤8👏1🔥1
30 Jun 2025, 16:28 UTC≈1,620 views9 reactionsread 6 August 2026 አበደ ተባልኩኝ
------++___
ወፊቷ ባትበርም መልክቴን ልታደርስ
አንቺን በመናፈቅ እንዲው ብመላለስ
አበደ ተባልኩኝ በፍቅርሽ ከነፈ
አንቺን ባያገኝሽ ፎቶሽን ታቀፈ።
የኔ
እሠይ ልበድ ሰውን ዝም በይ
ግና ናፈቀሽኛል ብቅ በይ
ከርቀትም ቢሆን አይንሽን እዳይ
ሰዎች አፌዙብኝ ብዙ ወሬ አወሩ
አንቺን በማፍቀሬ ተቃጥለው አደሩ።
አው አብጃለው በፍቅርሽ ወድቄ
ሚሰበስብ ጠፍቶ ጨርቄና ሜቄ
አው ናፍቀሽኛል በጣም በክፉኛ
አንቺን አልማለው እንቅልፍም አልተኛ።
አው ወድሻለው ከልብ ካንጀቴ
አብጃለው እና ነይ መዳኒቴ።
✍ምንተስኖት ሱሌይማን መሐመድ
ቀን፦23/10/2017
ከ ምሽቱ 1:25
❤7🔥1🥰1
29 Jun 2025, 19:36 UTC≈1,460 views8 reactionsread 6 August 2026 አንቺ ነሽ
----+----
ፈጣሪ ከሰጠኝ ከሴቶች ለይቶ
ከጎደለው ጎኔ አንቺን አበጅቶ
የኔ ጠይም የኔ ቸኮሌት
ከምንም ከምንም መውደዴን ወደድኩት።
አው ተማረኩ በፍቅር ከንፌ
እሷ ትራመድ እኔ ተነጥፌ።
የኔ አለም የአብራኬ ክፋይ
የበረከት ፈለግ ሲሳይ
ፈጣሪ የሠጠኝ ከጎኔ ለይ
እኔ ወድሻለው ከማንም በላይ።
ሰክና እደ አቦል ብና
በሳቋ እኔን ስታዝናና
የተፈጠርኩ መሠለኝ በዐለም እንደገና።
አፍሽ ጣፋጭ ሳቅሽ ገዳይ
ናፍቆትሽ ድርብ ስቃይ
ማሬ አጥቷል ገላጋይ
ልምጣ ወይ ነይ እንድንተያይ።
የኔ አለም የኔ ውብ ሴት
ዘላለም ፍኪልኝ እነደ መብራት።
✍ምንተስኖት ሱሌይማን መሐመድ
ቀን፦22/10/2017
ከምሽቱ 4:35
🥰3❤2👏2🔥1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @getami_mintesnot. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.