4 May 2025, 11:07 UTC≈3,090 views79 reactionsread 7 August 2026 ዓመታት እያለፉ ነው። እኛ ደግሞ እንድንኖር በተፈረደብን ህይወትና እኛን ከሚሸሹ ህልሞቻችን መሀል ነን። ህያው የምንሆንባቸው ትዝታዎች አሉን… የነበረውን ናፍቆት ፣ ሳቅ ፣ ሀዘን እያስታወስን አንገት እንነቀንቃለን በፈገግታ፣ በአግራሞት። እና ሁሉንም እናይና እንዲህ እንደመድማለን… በተፃፈልን እጣፈንታና ራሃ መሆንን አምርሮ በሚፈልግ ልብ መሃል ነን ሁልጊዜ።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤64👍10🥰3🔥2
1 May 2025, 18:56 UTC≈3,180 views71 reactionsread 7 August 2026 አንዳንድ ሰው ከአንደበቱ ማር ይዘንብለታል። ሲያገኝህ ለስለስ ባለ ፈገግታ ይገድልሃል። ሆን ብለህ ብትፈልግ እንኳን ድርቅና አታይበትም። ተፈጥሮ ሆኖ ይሁን ተለማምዶት እኔንጃ። … እና እንዲህ አይነት ሰው ሲያገኝህ ካንተ የሆነ ነገር መጠቀም ፈልጎ እንደሆነ እንዳታስብ። ወይም በጣም ወዶኛል፣ ተመችቼዋለሁ ብለህም እንዳትደመድም። በቃ እርሱ በዚህ መልኩ ማስተናገድ ልምዱ ሊሆን ይችላል። ተፈጥሮውም ሊሆን ይችላል።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤57👍13🥰1
26 Apr 2025, 18:29 UTC≈3,380 views65 reactionsread 7 August 2026 የሰዎችን መጥፎ ጎን ብቻ ለማስታወስ ከተቀመጥክ ለማንም ውዴታ አይኖርህም። ፍፁም ንፁህ ፍጡር ስለማይኖር ቅርብ ሰዎችህን እንኳን ባልተለመደ መልኩ በጥቁር ዓይን መመልከት ትጀምራለህ። ከዚያ ቀንህም አያፈካህም፣ ሌሊትህም አያሳርፍህም። አንዳንዴ መጥፎ ጎናቸው ጋር ስትደርስ አይንህን ስበር፣ አይቶ እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍንም ተለማመድ። አንዳንዴ "መርሳት"ን ተደገፈው። አንተም አጠገብህ ያሉትም ሰላም እንዲሆኑ።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
🥰35👍16❤14
26 Apr 2025, 18:25 UTC≈3,150 views38 reactionsread 7 August 2026 "ያሳዝናል! ነገሩ የተወሰኑ ቀናት ይሆንና ያልፋል ብዬ አስቤ ነበር። ግን ህይወቴ ሆነ።" ዴስቶቪስኪ
አንዳንዴ… ብዙም የማንኖርባቸውና መሻገሪያችን የሚመስሉን ነገሮች ራሳቸው መዳረሻችንም ይሆናሉ። ድንገት የተፈጠሩ ናቸው እንልና ዝንተዓለሙን እነርሱ ውስጥ እንኖራለን። ለተወሰኑ ቀናት አስበን እንጀምራቸውና የህይወታችን ክፍል ሆነው ይቆያሉ። የጓደኝነት ህይወት፣ የስራ ዓይነትና ወይም ለሆነ ችግር መፍትሄ ያደረጋችሁትን አስቡ። ብዙዎች ለሆኑ ቀናት መታለፍ የተጀመሩ ናቸው፣ አሁን ግን ህይወት ሆነዋል።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤29👍9
24 Apr 2025, 17:49 UTC≈3,110 views123 reactionsread 7 August 2026 ስናድግ ዝምታም አብሮን ያድጋል። ለሰዎች ከምናወራው በበለጠ ወደውስጥ የምናወራው መብዛት ይጀምራል። ከራሳችን ጋር የምንመላለሰው የውይይት ሀሳቦች መሀል የሚገራርሙ መመሰጦች ውስጥ እንገባለን። የመገለል ፍላጎት ይቆጠጠረናል። ለብቻ የመሆን። ብዙም ቅልቅል አለመውደድ። ጥሩ ስሜት አለው።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤100👍23
14 Mar 2025, 13:49 UTC≈4,000 views120 reactionsread 7 August 2026 ኑህ ልጁን አልመሰለም። ዩሱፍም እንደ ወንድሞቹ አልነበረም። በአንድ ጎጆ ስር እልፍ መልኮች ይኖራሉ። ዥንጉርጉር ቀለሞች። ሙሉ በሙሉ ዘመደ መጥፎ የሆነ ሰው ቢኖር… ከሰውዬው ምግባር ጋር አይገናኝም። መለኪያ ሆኖም አይቀርብም። ምርጥ አባት ምርጥ ልጅ ላይወልድ ይችላል። ምርጥ ወንድምም ወንድሙን በምርጥነት ላያንፀው ይችላል። ነብይ አደምን በልጆቹ መሀከል ስለነበረው መበዳደል ምን ብለህ ትወቅሰዋለህ? ምንም!!
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤86🥰13🔥11👍10
20 Aug 2024, 17:25 UTC≈6,200 views79 reactionsread 7 August 2026 አላህ አያረፍድም። ዩሱፍ ላይ እንዳላረፈደው።
👆👆
"አዳምጡት"
🥰42❤26👍9🔥2
17 Aug 2024, 04:26 UTC≈6,870 views144 reactionsread 7 August 2026 መካሪ ሁሉ ጨዋ አይደለም። በምክሩ ውስጥ አብዝቶ ስለፅድቅና የሚነግርህ ሰው ፃድቅ ነኝ እያለም አይደለም። በተሸወደበትና በወደቀበት ነገር ውስጥ የከፈለውን ዋጋ እየነገረህ ሊሆን ይችላል። ነፍሱን ማሰር በተሳነው ጉዳይ ላይ "ይህ ነው ክፈተቴ አንተ ግን በዚህ በኩል ነፍስህን አሸንፋት" ይሆናል የሀሳቡ ውጥን።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤105👍35🥰4
15 Aug 2024, 14:14 UTC≈6,210 views84 reactionsread 7 August 2026 “ሰዎችን የመንገዱ አጋማሽ ላይ አትተው። መንገዱን በናንተ ምክንያት ብቻ ጀምረውት ሊሆን ይችላል።” የሚል የዐረብኛ ጥቅስ አነበብኩና እውነት ነው አልኩኝ።
በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ስንት እህቶች ከአንዳንድ ወንዶች በተሰጣቸው አጉል የይሆናል ተስፋ መሀል መንገድ ላይ ቀርተዋል? የማያውቁትን መንገድ ጀምረው። በስራ ምክንያት እኛ እናውቀዋለን ብለው መሀል መንገድ ላይ በሚጠፉ ሰዎች ስንት ነጋዴዎች ከሰሩ? ስንት ወጣቶች በጓደኞቻቸው ውትወታ ጀምረውት… መመለስም ማለፍም የተሳናቸው የሱስ አዘቅት ውስጥ ገብተዋል። አይደል? እስኪ ሀሳብ ስጡበት።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤60👍22🔥2
10 Jul 2024, 16:47 UTC≈7,350 views172 reactionsread 7 August 2026 በመጨረሻም ዱንያ ከቤተሰብህ የበለጠ ውድ ነገር ልትሰጥህ አትችልም። ዱንያን በሙሉ ብትዞራት ከነርሱ የበለጠ ዋጋ ያለውን ነገር አታገኝም። ደስታን ከነርሱ ጋርና በነርሱ ውስጥ አብዝተህ ታሸተዋለህ፣ ትኖረዋለህ። ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ።
@Fuadkheyr
@fuadkheyr
❤132👍20🥰14🔥6
8 Jul 2024, 17:00 UTC≈6,350 views105 reactionsread 7 August 2026 ከጊዜ ጋር… የእድሜያችንን እኩሌታ ስናልፍ… ወደ አመሻሽ ላይ እንደድሮው ሁሉንም ነገራችንን ለሰው አንናገርም። መጥፎ የሆኑ ስሜቶቻችንን የመደበቅ ትልቅ ችሎታ ከወዴት እንደመጣ ሳናውቀው ይቆጣጠረናል። እንደጉድ እንችላለን። በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ምንም ያልሆንን ፅኑ መስሎ መታየት እንዴት እንደሆነ እንማራለን። አይገርምም? ወላጆቻችን የራሳቸውን ችግር ሲነግሩን እንኳን በአስተውሎት እናደምጣለን። የኛን ጉዳይ ሳንተነፍስላቸው። እንድናለቅስ የሚያስገድዱን ነገሮች ተፈጥረው እንኳን ፈገግታ ለመላበስ እንውተረተራለን። ፈገግታ የሚያሸነፈው የማይደረመስ የእንባ ግድብ ከየት መጣ? አቤት የአመሻሽ ውበት…
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤84👍14🔥5😭2
6 Jul 2024, 07:55 UTC≈5,970 views126 reactionsread 7 August 2026 "ዱዓዬ እጣፈንታዬን ለመቀየር በቂ አልነበረም ማለት ነው?" የሚሉ ከርታታ ልቦች አሉ። በህይወት ልዩ መልኮች እንቅፋት የተመቱ ልቦች። በህመም፣ በእዳ፣ በትዳር አለመሳካት፣ በሁኔታዎች መዘበራረቅና ግራመጋባት የሚዋኙ ስሜቶችም እንዲሁ። ምን ያህል ጌትዬን ተለማምጠናል? … ከአለሙ ሁሉ እስኪያስቀድመን፣ ከጠያቂዎች ሁሉ እስኪመርጠን። እርሱ የሚለማመጡትን ይወዳል። የሚወደውን ደግሞ ይመርጣል።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
❤96👍15🥰13🔥2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @fuadkheyr. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.