9 May 2026, 13:44 UTC153 views0 reactionsread 7 August 2026 Photo
እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።”
— 2ኛ ቆሮ 9፥7
ሰላም እንዴት ቆያችሁ ውድ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እንዲሁም ወዳጆቻችን በሙሉ ።እንደሚታወቀው ሁላችንም የቤ/ክ አባላት በምንችለው አቅም ወርሐዊ አስራታችንን በየወሩ እንደምናስገባ ይታወቃል ።በመሆኑም በአሁኑ ወር ለየብቻችን ስናስገባ የቆየነውን አስራታችንን በጋራ በመሆን ገንዘቡን ሰብስበን እንደ ሰንበት ትምህርት ቤት በመጠናቀቅ ላይ ለሚገኘው ለቤተ ክርስቲናችን ህንጻ አንድ ነገር ለማድረግ አስበናል።ስለሆነም ይሄ በጋራ የምንናስገባውን የአስራት አስተዋጽኦ ሁላችንም አባላት እንዳያመልጠን ስልን በሰንበት ት/ቤታችን ስም እና…
Signed ያሬድ
9 May 2026, 05:34 UTC190 views2 reactionsread 7 August 2026 Photo
"... ድንግል ሆይ የነቢያት ትንቢት እና ምሳሌ ፤ የሐዋርያት ሞገሳቸው ፤ የሰማዕታት እናታቸው ፤ የመላእክትም እህታቸው አንቺ ነሽ ፤ በመዓልት እና በሌሊት በበሮችዋ ደጅ የሚጠኑ የጐልማሶችና የደናግል የመነኮሳትም መመኪያቸው አንቺ ነሽ ..."
ቅዳሴ ማርያም ❤
ሰንበት ትምህርት ቤታችን በየአመቱ ከምትዘክራቸው በዓላት አንዱ የእመቤታችን የልደቷ መታሰቢያ ነው።ዘንድሮም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም አባል በሚገኝበት ቅዳሜ ግንቦት 1 ከ10 :00 ጀምሮ በሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ መርሐግብሩ ተዘጋጅቷል ።ስለሆነም ሁላችንም አባላት በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የእመቤታችንን የልደቷን በዓል በጋር እናከብር ዘንድ ተጠርተናል።
መልካም በዓል።
❤2
Signed ያሬድ
30 Apr 2026, 17:34 UTC255 viewsread 7 August 2026 1000531563356 Abraham haile
Signed ያሬድ
30 Apr 2026, 17:34 UTC269 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed ያሬድ
30 Apr 2026, 17:34 UTC193 viewsread 7 August 2026 Photo
ልደትሽ ልደታችን ነው
እንኳን ለልደታ ለማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
ሰንበት ትምህርት ቤታችን በየአመቱ ከምትዘክራቸው በዓላት አንዱ የእመቤታችን የልደቷ መታሰቢያ ነው።ዘንድሮም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም አባል በሚገኝበት ቅዳሜ ግንቦት 1 ከ10 :00 ጀምሮ በሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ መርሐግብሩ ተዘጋጅቷል ።
ይሄ መርሐግብር እንዲሳካ ሁላችንም ባለፈው አመት "እመቤታችን በአማላጅነቷ አሁን ላለንበት አመት ዓመት ብታደርሰን" ብለን የተሳልናቸውን ስዕለቶችን እንድናስገባ ስንል በሰንበት ትምህርት ቤታችን ስም እናሳስባለ።
ድንገት የተሳላችሁት ስዕለት ምን እንደሆነ ለጠፋባችሁ አባላት ከስር በፎቶ እናስቀምጥላችኃለን።
Signed ያሬድ
28 Jan 2026, 18:36 UTC335 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍቷ መታሰቢያ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
ከበረከቷ ያሳትፈን አሜን አሜን
❤5
Signed 11616
ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት pinned «በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ አሜን እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍቷ መታሰቢያ በዓል አደረሳቹ! አደረሰን! አስተርእዮ ማርያም ለምን እናከብራለን?አስተርእዮ ማለት ምን ማለት ነው? አስተርዓየ የቃሉ ፍቺ ታየ ተገለጠ ማለት ሲሆን አስተርእዮ መታየት መገለጥ ማለት ነው።ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል መሰረት ዘመኑ ሲፈጸም ከተወለደበት እለት…»
19 Jan 2026, 15:03 UTC354 viewsread 7 August 2026 ሰላም እንደምን ዋላችሁ ።ዛሬ 11/05/2018ዓ.ም ወንድማችን ታሪኩ ጋር የማጽናኛ መረሐግብራችን ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ ስለሚኖር ሁላችንም አባላት በመርሐግብሩ ላይ እንድትገኙ እንላለን።
Signed ያሬድ
18 Jan 2026, 05:25 UTC363 viewsread 7 August 2026 ሰላም ውድ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ
ዛሬ በ10/5/2018ዓ.ም የመዝሙር ክፍል ምክትል ተጠሪ የሆነው የወንድማችን የታሪኩ አባት አቶ ተሾመ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ።ሰንበት ት/ቤታችንም በደረሰው ሀዘን እጅጉን ያዘነች ሲሆን ለአባታችንም እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ አጠገብ ያስቀምጥልን እያልን ለወንድማችን ለታሪኩም ሆነ ለመላው ቤተሰቦቹም ጭምር መጽናናትን እንመኛል ።ታዲያ አባላት 5:00 ላይ በሚካሄደው የቀብር ስነ ስርዐት ላይ ፣ እንዲሁም ምሽት 11:00 ላይ በቤታቸው በሚኖረው የማጽናናት መርሐግብር ላይ ሁላችንም የሰንበት ት/ቤት አባላት በመገኘት ወንድማችንን እንድናጽናና ስንል እናሳስባለን ።
Signed ያሬድ
17 Jan 2026, 19:11 UTC324 viewsread 7 August 2026 ከተራ
ከተራ በዚህ እለት መዕመናን ሁሉ እስከ ምሽት ሰአት ምንም መብል ሳይቅምሱ ይጾሙ ዘንድ የቀደሙት አባቶች ስራዐትን ሰሩ ።አባቶቻችን ይህነን ስራዐት የሰሩበት መክንያትም የልደትና የጥምቀት ቀን በረቡና በአርብ ቢውል በማክሰኞና በሃሙስ ተጹሞ በሌላው ቀን እንዲያከብሩ አዘዋል።ልደትና ጥምቀት የጌታችን ታላላቅ በአሎቹ ናቸውና ነው።በተጨማሪነትም አባቶች ከሰባቱ አፁአማት እንደ አንዱ በመቁጠርም ሁሌ በየአመቱ የከተራ እለት እንዲጾም አዘዋል።
ከተራ ከበበ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ፍችው ደግሞ ውሃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው።የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ህጉ ከቤተ መቀደስ ወቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የአካባቢው ህዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወ…
Signed 11616
6 Jan 2026, 20:35 UTC299 viewsread 7 August 2026 Photo
እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል አደረሳችሁ አደረሰን
መልካም በአል
5 Jan 2026, 13:33 UTC319 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Showing the 12 most recent of 14 posts we hold for @felegemedia. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.