23 Apr 2022, 17:20 UTC≈15,500 views253 reactionsread 29 September 2026 በፈተና ውስጥ ማለፍ፣ መውደቅና መነሳት የተፈጥሮ ቋሚ ህግ ነው። ሁላችንም እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ አገር የምንፈተንበት፣ የምንወድቅበትና የምንነሳበት ጊዜ አለ። የወደቀ የሚመስለው አይዘን፣ ከፊቱ መነሳት አለና። የተነሳ የሚመስለውም አይመጻደቅ፣ መውደቅ የሚሉት ነገር አለና። መጪው ጊዜ እንደ አገር የገጠመንን ፈተና አልፈን የጋራ መነሳታችንን የምናውጅበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።
ለክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወገኖቼ በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
👍158❤53👎30😁12
14 Apr 2022, 21:07 UTC≈16,300 views103 reactionsread 29 September 2026 ጠ/ሚ አብይ " አማራ ኦሮሞ የሚሉ ጄኔራሎችን አንፈልግም" እንዳሉት ሁሉ፣ "አማራ ኦሮሞ የሚሉ የክልል መሪዎችንም አንፈልግም" ቢሉ፣ ኢትዮጵያ የብሄር ፖለቲካን "ቻው" ብላ ሰላሟን ታገኝ ነበር። በአንድ አገር ውስጥ የፖለቲካ አመራሩ በብሄር እያሰበ፣ መከላከያውን በብሄር አታስብ ማለት ከባድ ነው። የፖለቲካ አመራሩ ከብሄር አስተሳሰብ ከወጣ፣ መከላከያውም በፍጥነት ከዚሁ አስተሳሰብ ይወጣል። መከላከያ ፖለቲካውን ይከተላል እንጅ፣ ፖለቲካ መከላከያውን አይከተልም። እናም አሁን መከላከያ ላይ የተዘራው ዘር ጥሩ ፍሬ እንዲይዝ ከተፈለገ፣ የፖሊቲካ አመራሩ በመላ ከብሄር አስተሳሰብ ይውጣ።
👍58❤37👎4🥰4
12 Apr 2022, 08:10 UTC≈13,700 views51 reactionsread 29 September 2026 በዚህ ወቅት የሚካሄድ "የግፋ በለው" ፖለቲካ፣ አገርንና ራስን አደጋ ላይ ከመጣል ውጭ፣ የሚያስገኘው ትርፍ የለም። በተለይ የኦሮሞና የአማራ ብሄርተኞች በይዋጣልን የፖለቲካ አካሄዳቸው፣ የታሪካዊቷን አገር ምሰሶ እየነቀነቁ እንደሆነ ልብ ያሉት አይመስልም ። ቀደምቶቻቸው ያስረከቧቸውን አገር ካላፈረስናት ብሎ ልፊያ፣ የጤና አይመስለኝም።
ትናንት የመጣንበት መንገድ ለዛሬ አይሆነንም። የዛሬው መንገድ፣ እንቁላል በአናቱ ላይ ተሸክሞ እንደሚራመድ ሰው፣ በጥንቃቄ የሚሄዱበት እንጅ፣ ድንጋይ ተሸክሞ፣ "ቢወድቅም መሬቱ አይጎዳም" ብሎ በግዴለሽነት እንደሚራመድ ሰው የሚጓዙበት አይደለም።
ኢትዮጵያ በውስጥና በውጭ ጠላት ተይዛ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ላይ በምትገኝበት ሰዓ…
👍40❤6🤔4😁1
10 Apr 2022, 19:55 UTC≈10,800 views56 reactionsread 29 September 2026 በዶ/ር አብይ ላይ ካሉኝ ቅሬታዎች አንዱ፣ ምናልባትም ዋናው፣ ሌብነትንና ሌባን ለመከላከል ከወሬ በዘለለ እርምጃ መውሰድ አለመቻሉ ነው። ምናልባት አብዛኛው ሌባ ሆኖበት ተቸግሮ ይሆናል። ወይም ጊዜ እየጠበቀ ይሆናል። ወይም እንደ መለስ ዜናዊ የፖለቲካ ታማኝነትን ለማግኘት ሲል ሌቦችን አይቶ እንዳላየ እያለፋቸውና ሲያፈነግጡ የስርቆት ካርዳቸውን ለመምዘዝ አስቦ ይሆናል ። ወይም የስርቆት መከላከያ መንገዱ ጠፍቶበት ይሆናል። ወይም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ብሎ ንቆት ይሆናል ። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፣ ዶ/ር አብይ ባለፉት አራት ዓመታት ብሄር፣ ሃይማኖት፣ ታማኝነት፣ ምህረት ወዘተ ሳይል ሌብነት ላይ ሰይፉን ቢያነሳ ኖሮ፣ አሁን የሚታዩት ችግሮች ቢያን…
👍48❤8
8 Apr 2022, 19:41 UTC≈9,360 views35 reactionsread 29 September 2026 የደርግ መንግስት በቅድሚያ ወያኔን እንምታ ወይስ ሻዕቢያን በሚለው ጥያቄ ዙሪያ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እንደነበር በቅርቡ የታተመው የሌ/ጄ ሐዲስ ተድላ መጽሃፍ በዝርዝር ያስረዳል። ኮ/ል መንግስቱ ወያኔን በመናቅ፣ የሰራዊቱ ሃይል ሁሉ ሻዕቢያ ላይ ማረፍ እንዳለበት ጽኑ አቋም በመያዛቸው፣ ወያኔ እየተጠናከረ መምጣቱን ጄኔራሉ ጽፈዋል። አሁን ደግሞ የብልጽግና መንግስት በኦነግ ሸኔና በወያኔ መካከል ውጥረት ውስጥ መግባቱን እያየን ነው። ኦነግ ሸኔ ተራ ዜጎችን ከመግደልና ማፈናቀል አልፎ፣ ለማዕከላዊ መንግስቱና ለኢትዮጵያ ህልውና ስጋት እየሆነ ነው። የመከላከያ ሃይላችን ያለውን አብዛኛውን ሃይል ማን ላይ ያሳርፈው የሚለው ጥያቄ የወደፊቱን የወያኔን የሸኔን እን…
👍32❤3
7 Apr 2022, 18:50 UTC≈6,440 views29 reactionsread 29 September 2026 የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ የሩስያን ከተመድ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ መባረር በመቃወም ድምጽ ሰጥቷል። የኤርትራ መንግስትም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። የኢትዮጵያ ውሳኔ የተመድን የሰብዓዊ መብት ጉባኤ አሰራር ከመቃወም የመነጨ እንደሆነ አስባለሁ። በሩስያ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ነገ በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ሊደገም እንደሚችል መገመትም አይከብድም። ከዚህ አንጻር ከታየ ኢትዮጵያ ተቃውሞዋን መግለጿ ተገቢ ይመስላል ። ግን አሁን ካለንበት የፖለቲካና የአለማቀፍ ግንኙነት አንጻር ድምጸ ታዕቅቦ ማድረግ አይሻልም ነበር ወይ የሚል ጥያቄ አነሳለሁ። የመንግስትን ምክንያት ለመስማት ቸኩያለሁ። ምዕራባውያን የሚከፍቱብንን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ለመመከትስ ተዘጋጅተናል?
👍15❤7👏4👎3
6 Apr 2022, 09:00 UTC≈6,430 views26 reactionsread 29 September 2026 በዲፕሎማሲው ዓለም የካሮትና ዱላ ምሳሌ በደንብ የሚታወቅ ነው። ባጭሩ፣ ጥሩ ስትስራ "ካሮት" ፣ መጥፎ ትስስር ደግሞ " ዱላ" ይከተልሃል ማለት ነው። አስተሳሰቡ በአገሮች መሃል የአዛዥና ታዛዥ፣ የጌታና የሎሌ፣ ወይም የበላይና የበታች ግንኙነት መኖሩን የሚያሳይ ነው። ጥሩ ባህሪ ስታሳይ የሚሸልምህ፣ መጥፎ ባህሪ ስታሳይ ደግሞ የሚቀጣህ አለቃ ወይም ጌታ እንዳለህ እንድትገነዘብ ያደርግሃል። በሌላ አነጋገር ጌታህ የሚፈልገውን ከፈጸምክ፣ የምትበላው ካሮት፣ እምቢ ካልክ ደግሞ የሚበላህ ዱላ ይከተልሃል ማለት ነው።
የአሜሪካ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ መንግስት የሚሉትን ከፈጸመ HR 6600 የተባለውን ህግ ውድቅ እንደሚያደርጉለት ፣ እምቢ ካለ ግን ህጉን አጽድቀው …
👍25❤1
3 Apr 2022, 08:21 UTC≈6,020 views31 reactionsread 29 September 2026 በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እያደረገለን ላለው ድጋፍ እጅግ እናመሰግናለን። በኢትዮጵያ ያለው ወገናችን የሚልክልን የሞራል ማበረታቻ ደግሞ በቃላት ለመግለጽ የሚቸግር ነው። ይህ ድጋፍ ሸክማችን ያከብደዋል። ሸክሙን የምንሸከምበት ብርታቱን ፈጣሪ ይስጠን። ባላገሩ ቲቪ ላይ አጣናችሁ እያላችሁ ለምትጠይቁን ወገኖች፣ የ ኢ ኤም ኤስ ባልደረቦቼ በተደጋጋሚ እንደገለጹት፣ አንድ እርምጃ ስንሄድ አንድ እንቅፋት ያጋጥመናል፣ እሱን ዘለነው ስናልፍ፣ ሌላ ግንድ ተጋድሞ ይጠብቀናል። አሁን ዘለን ዘለን፣ የመጨረሻውን እቅፋት ላይ የደረስን ይመስለኛል። እናያለን።
ህዝብን ይዞ የሚረታ የለምና ድጋፋችሁ አይለየን።
እናመሰግናለን ።
👍24❤5👎1👏1
2 Apr 2022, 21:06 UTC≈5,800 views44 reactionsread 29 September 2026 በዚህ ወቅትም ይሁን በማንኛውም ጊዜ፣ ኢትዮጵያ ልትጣላት ቀርቶ ልታስቀይማት እንኳ የማይገባ አገር ብትኖር፣ ኤርትራ ናት። ኤርትራ የሰሜን እዝ በተመታ ጊዜ ከዋለችው ውለታ በተጨማሪ ሱዳንና ግብጽ አብረው ሊያጠቁን በተነሱበት ጊዜ፣ ከጎናችን ተሰልፋ እውነተኛ ወዳጅነቷን አሳይታናለች። የኤርትራ መንግስት የቱንም ያክል ዋጋ ያስከፍለው፣ ያመነበትን ነገር ያለምንም ማወላወል ያስፈጽማል፤ የሚነበብ፣ የሚገመትና የሚታመን የውጭ ፖሊሲ ያራምዳል።
ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እጣ ፋንታቸው አንድ ስለሆነ ተከባብረውና ተደጋግፈው መጓዝ ምርጫቸው ሳይሆን ግዴታቸው ነው። ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ፣ ኢትዮጵያም በኤርትራ ላይ ቅሬታ ቢኖራቸው፣ ጎረቤት ሳይሰማ ቁጭ ብለው ተነጋግረው መፍ…
👍32❤12
1 Apr 2022, 21:17 UTC≈4,770 views45 reactionsread 29 September 2026 በኢትዮጵያ ውስጥ አሉን ከምንላቸው አንድ ሁለትገለልተኛ ተቋማት ውስጥ ግንባር ቀደሙ፣ በዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ) ነው። ኮሚሽኑ የምንጃር ሽንኮራውን ጉዳይ በፍጥነት አጣርቶ እስኪነግረን ድረስ ፍርድ ከመስጠት መታቀቡ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍትት ያግዛል።
በሺ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምንገኝ እኔንና እኔን የመሳሰሉ ሰዎች፣ የምንሰጠው አስተያየት፣ ግጭቱ እንዳይባባስ፣ የተጎዱት እንዲረዱና ፖለቲካዊ መፍትሄዎች እንዲመጡ ከማሳሰብ ያለፈ ባይሆኑ ይመረጣል። አማራም ይሙት ኦሮሞ የሞተው ኢትዮጵያዊ ወገንችን ነው። ሃዘኑ የሁላችንም ነው። የአንድ ኢትዮጵያዊ ሞት ሁላችንንም ካላመመን፣ ኢትዮጵያዊነታችን የከንፈር እ…
👍25❤18😢2
26 Mar 2022, 23:00 UTC≈5,760 views52 reactionsread 29 September 2026 ብልጽግና ያካሄዳቸውን ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከታተልኳቸው። በመላ አገሪቱ ያለው ህዝብ ተማሯል- በሰላም እጦት፣ በኑሮ ውድነት፣ በሌብነት፣ በስራ እጦት፣ በአገልግሎት እጦት ወዘተ። ፖርቲው ስልጣን በያዘ በ4 ዓመታት ውስጥ ወይም በተመረጠ ሰባት ወራት ውስጥ ህዝቡ በዚህ ደረጃ ከተማረረ፣ እጅግ አሳሳቢ የሆነ ችግር አለ ማለት ነው። ብልጽግና የሰላም እጦቱንና የኑሮ ውድነቱን ችግር ከህወሃትና ከሸኔ ጦርነት እንዲሁም ከኮቪድና ዓለማቀፍ ፖለቲካው ጋር እያያያዘ ምክንያት ለመስጠት ቢሞክር እንኳ፣ ከስርቆትና ከብልሹ የአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሳበትን ችግር፣ ምንም ምክንያት ቢያቀርብ፣ ህዝብን በበቂ ሁኔታ ማሳመን የሚችል አይመስለኝም።
ህዝቡ ምሬቱን ገልጿ…
👍44❤8
25 Mar 2022, 18:05 UTC≈5,560 views30 reactionsread 29 September 2026 ትክክለኛው የኢሳት ኢንተርናሽናል የዩቱብ ቻናል https://www.youtube.com/channel/UCCJbY4YdJIUk7Lygrkg5IRA
❤14👍8👎6🥰2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @fasilyenealem2022. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.