8 Aug 2026, 21:01 UTC221 views1 reactionsread 9 August 2026 ዙረተ -ምድር
አሁን ባለንበት አለም መሬት ክብ ትሁን
ጠፍጣፋ ግድ ከሚለኝ በላይ እረፍት አልባው የዚህ ምድር ሞገደኛው የዙረት ዑደት ሀሳብ ይገባኛል።ገና ጎህ ቀደደ ሲባል ከኩይሳው እንደሚወጣ ምስጥ የሚተመው ህዝብ ማታም ጀንበር ስታዘቀዝቅ ወደ ጎጆው የሚራኮተው ቀላል የሚባል ቁጥር አይደለም።እንደው ይህንን ዑደት ቋም ብሎ ላስተዋለው እያበራየ ቀን ሙሉ በሰጡት ምህዋር ላይ የሚሽከረከረውን በሬ የሚለየን እምብዛም ነገር የለንም ሁለታችንም በስራው አውድማ ተለጉመን ነው ግብራችንን ምናካሂድ ደግሞ እንዳናምፅ ወርሀዊ ጭዳችንን ከወደ አፍ ያጎርሱናል ሁለታችንም የኛ አይደለም ስራው።
ባለ ማህደረ ገንዘቡ የራሱ ያልሆነን ገንዘብ ሲያበራያ ሲያላውስ ይውላል ለጥ'ቆ…
👍1
6 Aug 2026, 22:33 UTC218 views3 reactionsread 9 August 2026 ዳዊት በኢያድልዎ
ፍትሐ ሞት ፈትሐ ላዕለ ካልኡ
ፍትሐ ሞት በርትዕ ዘፈትሖ አመ በላዕሌሁሰ በጽሐ
ከመ ይሚጥ ፍትሐ ቃለ ጽድቁ ፍጹመ ነስሐ
በደመ ፍጡራን ለርእስ አድልዎስ እንተ ነጽሐ
ይትወከፍ ሞተ በአዳም ዘፈትሐ
እደዊሁ በመስቀል ሰፍሐ
ትርጉም
ዳዊት ባለማዳላት የሞት ፍርድን በሌላው ላይ ፈረደ በአግባብ የፈረደው የሞት ፍርድ ግን በእርሱ ላይ በደረሰ ጊዜ
የእውነቱ ቃል ፍርድን ይመልስ ዘንድ በፍፁም ተጸጸተ በፍጡሮች ደም ለራስ ማድላት እርሱ (ዳዊት) አድፎልና!
ከማድላት ደም የነፃ ክርስቶስ ግን
በአዳም የፈረደበትን ሞት ይቀበል ዘንድ
እጆቹን በመስቀል ላይ ዘረጋ።
(መፅሐፈ ቅኔ)
🥰3
3 Aug 2026, 22:37 UTC234 views5 reactionsread 9 August 2026 File
ጸሎቴ
የዘወትር ጥማት መሻቴ
የምናፍቀው ስእለቴ
በቤትህ የጀመረልኝ እድሜዬ
እንዲያልቅ ሸምግልናዬ
ዛሬ ውላላው ከእግርህ ስር
አሳልፋለው ጊዜ ከአንተ ጋር......ጸሎቴ.
የማያስተውል ሆኜ ተላላ
አደራ እድሜዬ እንዳይበላ.........ጸሎቴ.
አልችኩልብህ ጊዜ አልጣ
ከመሠዊያዬ እንዳልታጣ
እንዲፈራብኝ የመንፈስ ፍሬ
ከአንተ ልጣበቅ ከመምህሬ
እንዳይባክን ይህ እድሜዬ
በግሳንግስ ተታልዬ
ምቀዳብህ ሆነኝ ምንጬ
ልዋል ከእግርህ ተቀምጬ*2
አዝማች
የማያስተውል ሆኜ ተላላ
አደራ እድሜዬ እንዳይበላ.........ጸሎቴ.
የልብህ ሃሳብ እንዲሆን ሃሳቤ
ቃልህን ልያዝ ለአትም በልቤ
ሳሰላስለው ቀኑን ልዋል
…
🥰4❤1
1 Aug 2026, 00:25 UTC166 views11 reactionsread 9 August 2026 ብዙ ብዙ - ልልህ እልና
ግን ለምን? - ልልህ እልና
ዝም እላለሁ - ለልዕልናህ።!
ባላም -ባራስ
እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤
ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል።
ዕንባቆም 2፥20
🔥6🥰2👌1👍1🤩1
Signed Be Ki
29 Jul 2026, 20:19 UTC187 views3 reactionsread 9 August 2026 የቀጠለ...
በአንፃሩ÷ ስናመሰግንም ዳር የለንም።መሥመር ለቅቀን በውዳሴ ዳንኪራ ማቀንቀን ይቀለናል።
ርግብግቢቱን ላይ ድንኳን ሠርተው ይቀመጡብኝ ዐይነት መነጠፍ ይታይብናል።
መዳፋችን የበሰለ ቲማቲም እስኪመስል እናጨበጭባለን።
ብዕራችን ለውዳሴ ተወድሯል፣አንደበታችን ለከት የለሽ የመስሎ ዐዳሪነት " ዕጣነ ሞገር" ይቀኛል።
በማበረታታትና በማጐብደድ መካከል ያለው ድንበር ደብዝዞ ይታይብናል።
በአጠቃላይ ሰዎችን ለማመስገን ኾነ ለመንቀፍ ዳርና ዳር እንፈራርጦ መቸንከር ማንንም አልጠቀመም።
ዐድር ባይ ወይም ጨካኝ ወቃሽ መኾን ከንቱ ነው።
ከዝቅተኛ ንቃትም ይኹን ከትክክለኛ ግንዛቤ ጒድለት የተነሣ በኹለቱም ዐይነት ጫፎች ላይ መንጠልጠል የተሳካ ማኀበራዊ ዕድ…
🥰3
Signed Be Ki
28 Jul 2026, 20:36 UTC163 views5 reactionsread 9 August 2026 የአድናቆት ዘነዘና
ኹለቱ ጠርዞች
እንደ ማኀበረ-ሰብ ከተጫኑን ማኅበራዊ ድክመቶች መካከል ጭካኔ-ሒስና ውዳሴ-ከንቱ አሉበት። ስንነቅፍ ፥ ጥንብ ርኩስን ማውጣት ይስመኘናል የነቀዘ ቅርንጫፍ በማስወገድ ሰበብ ግንድ እንጨፈጭፋለን ቅርፊት ለመጣል ችግኝ እንፈጫለን አንድ ዛፍ ለመንቀል ጫካ እንመጥራለን ትኀን ለመግደል ጎጆውን እናቃጥላለን።ያዘመመውን ለማቃናት ከመጣር ተሰባብሮ እንዲለይለት የበለጠ እናስጎነብሰዋለን።
ፈቀቅታን ለመጠየቅ ግፍተራ እናስቀድማለን። ሒሳችን ከጭካኔ አልተላቀቀም።
ለወቀሳችን ሰበብ ከኾነው ጥፋት ይልቅ የአወቃቀሳቸን ኹኔታ ይከፋልና እንዳይነሱ አድርገን እንወረውራቸዋለን።ቀና ማለታቸውን እንዘልሳለን። አልመዝምዘን እንመዘልጋቸዋለን። …
🥰4❤1
Signed Be Ki
28 Jul 2026, 20:29 UTC112 views3 reactionsread 9 August 2026 ሰላም ለእናንተ ይሁን....
ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ " የዱባ ጥጋብ " ከተሰኘው መፅሀፍ የአድናቆት ዘነዘና በሚል አርዕስት ስር የቀረቡ ሀሳቦችን የምናጋራችሁ ይሆናል። እንደሚጠቅማችሁ ተስፋ በማድረግ!
ሀሳብ አስተያየት ማከል ይቻላል🙏
“ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤”
— ፊልጵስዩስ 2፥3
❤3
Signed Be Ki
26 Jul 2026, 11:59 UTC137 views6 reactionsread 9 August 2026 ❝ ሴቶች ከወንዶች እኩል ናቸው ወይም አይደሉም የሚለው ነገር ብዙ ሰውን ያናቆረ ጉዳይ መሆኑ ይገርመኛል። ባህሎች የወንድን የበላይነት ያረጋገጡና ሴቶችን በክፉ ቀንበር ውስጥ ያሰሩ መሆናቸውም ግልፅ ነው። በምዕራቡ ዓለም የተነሳው የሴቶች መብትና እኩልነት ትግል እንቅስቃሴ ደግሞ ይሄንን ለማስተካከል ብዙ አስተዋፅኦ ማድረጉ አይካድም። የሴቶችን ከወንድ እኩል መሆን ለማረጋገጥ የተሄደበት መንገድ ግን ውስጡ ቁጣም ቁጭትም ያዘለ ነው። ወንዶችን የሴቶች ጠላት አድርጎ ከመሣሉም በላይ ሴቷን ከወንድ እኩል መሆኗን እና ወንድ የሆነውንና ያደረገውን ሁሉ ማድረግ መቻሏን ለማረጋገጥ ወደማይሆን ድካምና ውድድር ውስጥ ያስገባ ይመስላል። ይህም የወንድንና የሴትን ልዩነት ያ…
❤2⚡1👏1🔥1🥰1
Signed Yabets
21 Jul 2026, 21:14 UTC144 views4 reactionsread 9 August 2026 Photo
እፍርታሙ ልቤ!
ለስህተቱ ሲል ፥ ሲያስተባብል
በአንዱ ጥሪህ ፥ አልሰማህም ቢል
ጭራሹኑ ብሼ!
በሳቄ መኻል ፥ እያረሳሳሁ
ለሙቀቴ ስል ፥ ሠርክ እየሳሳሁ
ይኸው አለሁኝ ፥ እየወደኩ እየተነሳሁ።
:
አንተ ግን ጌታ ፥ አንተ ግን ደጉ
እጅህ የማይስት ፥ ባደራረጉ
የ'ግሬን ፍጥነቱን ፥ እየታገስከው
የእድሜዬን ቁጥር ፥ እየተጫንከው
ስታስነክሰኝ ያንተን ልትሰራ
እንድሆንልህ ፥ ልበ ሰባራ
ዙር ስንገጥም ፥ ስንት ሌት አየን ፥ ስንት ቀን በራ፤
:
እኔ እንደሆንኩኝ ...
በዘወርከኝ ልክ ፡ እንደ ጠመኔ ፡ እያሰጠርከኝ
የነፍሴ ረቢ ፡ እልፍ ገጽ ፈጅተህ ፡ እየመከርከኝ
ለስንቱስ ገባው ፡ እኔ ስሳሳት ፡ አንተ እየማርከኝ
ባላም 'ባራስ
🥰2❤1🔥1
Signed Be Ki
20 Jul 2026, 20:33 UTC129 views3 reactionsread 9 August 2026 የይሁዳ ፀፀት
በአይሁድ ዘንድ አንድ ሽያጭ ከተካሄደ በኃላ
ሻጩ በአንድ አመት ውስጥ ሐሳቡን ከቀየረ ሽያጩን ማስቀረት ይችላል። ከዚህ የተነሳ ትላልቅ ንብረት የገዙ ሰዎች ሻጩ ሐሳቡን ቀይሮ ሽያጩ እንዳይሰረዝ ከሻጩ ይደበቁ ነበር።
ለዚህ ችግር ዝነኛው የአይሁድ መምህር ሀሌል አንድ መፍትሔ አበጅቶ ነበር:: ገዢው የሚደበቅ ከሆነ ሻጩ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዶ ገንዘቡን ካስቀመጠ ሽያጩ ይሰረዛል ።
👉 ይሁዳ ምናልባት ገንዘቡን በቤተ መቅደስ የበተነው ኢየሱስ እንዲለቀቀ እስቦ ይሆን?
(Joachim Jeremias ,Jerusalem in the time of Jesus )
❤2👍1
Signed Be Ki
4 Jul 2026, 21:10 UTC174 views4 reactionsread 9 August 2026 ሀ ሁ ክርስትና …..
(የዶ/ር ደረጀ ከበደ ዝማሬ ) በውብ ግጥም ተሰናስኖ የቀረበ...
ባል ሚስቱን ሲያከብር በውጪና በቤት
በተግባር ሲያልቃት እንደቤቱ እመቤት
ከአባቱ ሲያበልጣት ከእናቱ ሲመርጣት
ከመላው ህዋሱ መውደዱን ሲሰጣት
ክርስትና ሀ ሁው
ያ ነው የገባው ሰው
ከሊቀ ካህኑ ጠዲቅ የደረሰው
የዘሩን ፍሬዎች አምሳያ በረከት
ከዳዴያቸው ይዞ እስከ በሳልነት
በፈሪሃ እግዚአብሄር በመለኮት ፊደል
ልጆቹን ለማነጽ የማይከለከል
አዛውንት አክባሪ የኔ ቢጤን አጉራሽ
ወንድ ሴት ልጆቹን ለቁምነገር አድራሽ
ጥልፍልፎሽ የለው የእምነታችን ልኩ
ላጡ ቆርሶ ማጉረስ ቸርነት ነው ጥጉ
የበረደው ሞልቶ ደጅ አዳሪ ወገን
ቡልኮ እንጣልበት ካለበት ፈልገን
ያ ነው አማኝነት የኢ…
❤3👍1
Signed Be Ki
9 Jun 2026, 20:00 UTC184 views2 reactionsread 9 August 2026 "የልባችንን ሀሳብ ፣የዐይናችን ትኩረት፣ የነፍሳችን ረሀብና የኑሮ ምኞታችንን ወደ ሰማይ ማየት ካላስለመድን፤ አንገቻችንን ወደ ምድር በማቀርቀር የህይወት አቋማችን ይጉብጣል፤ ሳቃችን የውሸት ሆኖ ደስታችን ይሰረቃል። ከእናታችን ማህፀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ እስከሽበታችን በዚህ ዓለም የኑሮ ዘይቤ ላይ ብቻ ከተንጠለጠልን አወይ ምስኪንነታችን፤ ጥቂቱን ቀዳዳ ደፈንን ብለን ስንፈነጥዝ የሚመጣው ቀዳዳ በእጥፍ ተቀዶ ሲጠብቀን ስንደፍን ሲቀደድ፣ አዲሱ ሲያረጅ ፣ ያረጀውን ስንጠግን፣ የጠገነውን ስንለውጥ ወዘት መቸም መኖር ደግ ይኸው ዛሬም አለን። በዚህ የፉክክርና የውድድር ዓለም ውስጥ ከማን አንሰህ(ሽ) ነው ለሚለን የምድር ቱልቱላ ለመስማት እህህ ብለን ጆሮአችንን ከ…
❤1🔥1
Signed Yabets
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @eyesovwisdom. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.