29 Jun 2026, 08:05 UTC851 views11 reactionsread 5 September 2026 የውድቀቴን መንገድ
ሸርሽራ በመውደድ
ያቀናችኝ ንግስት ... የሰጠችኝ ክብር
አቤት አቤት ሲያምር
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
መኖር እንድጠላ መንፈሴን አድክሞ
ማጣት አንቆኝ ሲዞር ክንዱን አፈርጥሞ
የምሆነው ጠፍቶኝ
ተንበርክኬ ሳዝን ሳትለኝ ደካማ
ቀና አረገችኝ ቀንበሬን ተሸክማ!
እምቅ የእንባ ጠል
ጉንጬን ሲንጠለጠል
ኅዘን በደቆሰው ልስልስ ስስ አንጀቷ
ዕንባዬን ያበሰው
አቤት ሲያምር ጣቷ
{ልክ እንዳንቺ ማርያም}
እኔነት እስካጣ ፍቅር ሸሽቶኝ በሮ
ብቸኝነት ሚስማር ሲያደማኝ ቸንክሮ
የማረገው ጠፍቶኝ
ሞቴን እየናፈቅኩ ሳዘጋጅ መስቀሌን
ትንፋሽ ለገሰችኝ ዳብሳ ሰንበር ቁስሌን
የጅራፍ ሹል ትርትራት
የልቤ ስውር ስብራት
አድቅቆ ሲጥለኝ ... እንዲሆን ለነፍሷ
…
❤11
Signed bek
27 Jun 2026, 10:08 UTC862 viewsread 5 September 2026 https://t.me/ke_kaloche1
Signed bek
23 Oct 2025, 09:29 UTC≈2,820 views29 reactionsread 5 September 2026 አለቀለት ያሉት
(በእውቀቱ ስዩም)
ከጅረት አጠገብ ፥ቆሞ የኖረ ዛፍ
መብረቅ ገነደሰው
አሁን ድልድይ ሁኖ፥ ያሸጋግራል ሰው ::
“አለቀለት” ያሉት፤ ተልኮው መች አልቆ
ቆሞ የጠቀመ፥ መላ አያጣም ወድቆ፤
@ethiopianye
❤23👍6
20 Oct 2025, 07:03 UTC≈2,510 views12 reactionsread 5 September 2026 Forwarded from @fariishubb
ናፍቆቴ
እናቴ አንቺ የኔ ኩራት
እናቴ....
የፍቅር ማሰሮ
እናቴ ልበልሽ የናፍቆት እሮሮ
ትዝይለኛል ያኔ
ጠረንሽ ሲገባ ባፍንጫየ ዘልቆ
አሁን ይሸተኛል ከጎኔ እርቆ
እናቴ ልበልሽ
መጠሪያ ባይኖርሽ
ናፍቆትሽ ይበቃል ከጉያሽ መዋሉ
እኔን ይጎደኛል ፈገግታሽ መጉደሉ
ትዝ ይለኛል ሳቅሽ
ጭንቀት ተሸክሞ ሀዘን ተጫጭኖት
ያላወኩት ነገር በሀሳብ አፍኖት
ትዝ ይለኛል አይንሽ
በስስት እያየኝ ሳይነቀል ላፍታ
ሰቅሎ ሲክበኝ ከላዩ ከፍታ
የኔ የኔ ብየ ዜማ አላወጣው
ለምን እንዳትይኝ
አንዴ ልበልሽ እኔ ወድሻለው
አዚህ ተቀምጨ ሳቅሽን አሸታለው
ጠረንሽ ልዩ ነው
አስከዛሬ ስኖር ሁኘ በምድር ላይ
ካንቺ የምትበልጥ አሎጣችም ፀሀይ
እውነት ከምሬ ነው
ጨረቃ ብትወጣ ብርሀን ብትሰጠ…
❤11👏1
20 Oct 2025, 07:02 UTC≈1,880 views13 reactionsread 5 September 2026 Forwarded from @fariishubbPhoto
አግብተሻል ወይስ አላገባሽም አግብተሽ ከሆነም ደግ ካልሆነም ይጠቅምሻልና እነዚህን ሶስት ነጥቦች መቸም ቢሆን አትዘንጊያቸው፦
1,ስለባልሽ ችግር መቼም ቢሆን ለባልሽ ቤተሰቦች አታማክሪ...ባብዛኛው እነሱ ከርሱ ጎን እንጂ ካንቺ ጎን አይቆሙም።
2,ባልሽ የሚረብሽሽ፣ የማያስደስትሽ፣ የሚበድልሽ ከሆነ ለቤተሰቦችሽ መቼም እንዳትነግሪያቸው...ምክንያቱም አንቺ ረስተሽው ህይወትሽን ስትቀጥይ እነሱ ይቅር አይሉትም።
3,የቤትሽን እና የትዳርሽን ጉዳይ በፍጡም ለሴት ጓደኛሽ አትንገሪ...አንቺ ትተሽው ስትሄጅ እርሷ እንደ ጤፍ ትዘራልሻለች
Amharic_audio_book
❤9👍4
8 Oct 2025, 18:30 UTC≈1,760 views7 reactionsread 5 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍7
5 Oct 2025, 12:12 UTC≈1,820 views20 reactionsread 5 September 2026 እድሜ ይስጣት ለእሷ
ሆኜ ቀርቻለሁ የህመም ጎተራ
እረስቶኛል ዘመድ
ከወጣሁ ቆየሁኝ ከሰውነት ተራ
ያለማንገራገር ሞተች ቢሉኝ እንኳን
ከንፍሮ ልዘግን እገባለሁ ድንኳን
ስራዋን ለማያውቅ ነገሬ ቢመርም
አርባዋን በልቼ...
“ለአመቱ ያድርሰን!" ማለቴ አይቀርም
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ያልተመሰረተ!
✍️ ሚኪ
@ethiopianye
❤17👍3
24 Sept 2025, 05:23 UTC≈2,010 views15 reactionsread 5 September 2026 እንዴት ነው ነገሩ?
#ኑረዲን_ኢሳ
እንዴት ነው ነገሩ?
ብንሄድ ብንሄድ ጎዳናው አያልቅም ፣
ሽቅብ ብናንጋጥጥ ጀንበር አትጠልቅም ፣
ጊዜ ቆሟል መሰል አይነቃነቅም ፣
ጋሪያችን ይሮጣል እኛ አንንፏቀቅም ።
እንዴት ነው ነገሩ?
ዒሻራ 📚
27 - 1 - 95 ዓ.ም
@ethiopianye
❤10👍5
20 Sept 2025, 16:22 UTC≈2,060 views8 reactionsread 5 September 2026 File
✍️@ediwub
@ethiopianye
❤8
16 Sept 2025, 10:44 UTC≈2,130 views21 reactionsread 5 September 2026 Photo
አንዱ ለአገሩ ፤
አንዱ ለ'ርስቱ ፤
አንዱ ለልጁ ፤
አንዱ ለሚስቱ ፤
ጥይት ወልውሎ ፤ ጎራዴ ስሎ ፤
በዱር በገደል ይከታከታል ፤
ሲሻው ይገድላል ፤
ሲሻው ይሞታል ።
እኔ ግን ወዲህ . . .
ወይ አገር የለኝ ፤
ወይ ርስት የለኝ ፤
ወይ ልጅ አልወለድኩ ፤ ሚስት አላደለኝ ፤
ጎራዴ ሳልስል ፤ ጥይት ሳልገዛ ፤ በተኛሁበት ሀሳብ ገደለኝ ።
#ቴውድሮስ_ካሳ
@ethiopianye
🥰13❤4😁4
16 Sept 2025, 07:42 UTC≈1,590 views3 reactionsread 5 September 2026 ሁለት ልጃገረዶች
(©አዳም ረታ)
ከ'ከሰማይ የወረደ ፍርፍር '
ቅዳሜ ቅዳሜ ማታ በዙረቴ የማልደርስበት የከተማችን ክፍል የለም ። ሳምንት ወይ አስራ አምስት ቀን ሙሉ ከቤት ሳልወጣ እቆይና እመሽግና አንድ ቅዳሜ መርጬ ከወጣሁ ግን የምመለሰው ተበለሻሽቼ ነው ። በደንቤ ሳምንት ሁለት ሳምንት ሙሉ ከቤት አልወጣም ....... ከእሁድ እስከ ዓርብ ። ብዙ ጊዜ ቅዳሜ ግን ከምሽቱ አስራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እግሮቼ የማያርፉበት የከተማዋ ክፍል የለም። ከፒያሳ በሜክሲኮ አደባባይ አድርጎ ቄራ። በፒያሳ በሐብተጊዮርጊስ ድልድይ አድርጎ በመርካቶ በሰባተኛ እስከ ልደታ። እንደ አውሬ ነው የሚያደርገኝ። በዚያን ዕለት የማውቀውን ማንንም ሰው መገናኘት አልፈልግም ። በሕይወቴ …
❤3
12 Sept 2025, 19:10 UTC≈1,600 views11 reactionsread 5 September 2026 መፍትሔ
በር መስኮት ዘግተህ ፣
ቀዳዳዎች ደፍነህ ፣
የለኮስከው ሻማ "በራ !" ፣ "ጠፋ!" ካለ ፤
ጠርጥር !
ቤት ያፈራው ንፋስ ከጎጆህ እንዳለ ?
©በረከት በላይነህ
@ethiopianye
🔥9❤1👏1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ethiopianye. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.