22 Jul 2026, 19:56 UTC480 views3 reactionsread 7 August 2026 Video
የሳምንቱ #HRConcept: የውሃ መብት
...
የተ.መ.ድ. የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ኮሚቴ፣ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 15
ሁሉም ሰው ለግሉ እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት በቂ የሆነ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተቀባይነት ያለው፣ በአካል ተደራሽ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ ውሃ የማግኘት መብት አለው።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 90
የሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የንጹሕ ውሃ፣ የመኖሪያ፣ የምግብና የማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=38876
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል…
👍2❤1
4 Jul 2026, 05:40 UTC972 views7 reactionsread 7 August 2026 ትግራይ፡- በትግራይ ክልል ያለውን አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ
...
በክልሉ ወጣቶችን ከፈቃዳቸው ውጪ ወደ ወታደራዊ ሥልጠና የማሰማራትና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የመገደብ ተግባራት ከሰብአዊ መብቶች መርሆዎች እና ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረሱ በመሆናቸው በአፋጣኝ ሊቆሙ ይገባል
🔗 https://ehrc.org/?p=38519
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsforAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
😁4👍2❤1
3 Jul 2026, 09:07 UTC803 views0 reactionsread 7 August 2026 ማብራሪያ፡- በቂ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት
...
በቂ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ምንድነው? በቂ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት በዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ የሕግ ማዕቀፎች የተሰጠው ጥበቃ ምን ይመስላል? በቂ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ዋና ዋና ይዘቶች ምን ምን ናቸው? በቂ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብትን አስመልክቶ የመንግሥት ግዴታዎች ምንድን ናቸው?
🔗 https://ehrc.org/?p=38511
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsforAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
2 Jul 2026, 15:58 UTC670 views1 reactionsread 7 August 2026 ማእከላዊ ኢትዮጵያ፦ በዳኝነት ነጻነትና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ የተካሄደ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በዳኝነት ነጻነት እና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እንዲሁም በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ እና የፍትሕ ዘርፍ ሪፎርም ዙሪያ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፍትሕ አካላት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ዳኞች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ፋጤ ስርሞሎ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እርሴኖ አቡሬን ጨምሮ የተለያዩ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አስተዳዳሪዎች፣ የክልሉ የፍትሕ ዘርፍ ተቋማት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች ባለድር…
👍1
2 Jul 2026, 11:04 UTC583 viewsread 7 August 2026 ዓለም አቀፉን የስደተኞች ቀን አስመልክቶ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (Office of the United Nations High Commissioner for Refugees-UNHCR) ፣ Jesuit Refugee Service (JRS) እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነጻ የሕግ ድጋፍ ማእከል ጋር በመተባበር ዓለም አቀፉን የስደተኞች ቀን “ሁሉም ሰው ደኅንነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ” በሚል መሪ ቃል ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አክብሯል። መርኃ ግብሩ የስደተኞችን ጽናት፣ አስተዋጽዖ እና ስኬቶችን ለማክበር፣ ስለ መብቶቻቸው ግንዛቤን ለማሳደግ፣ እንዲሁም በ…
29 Jun 2026, 11:49 UTC713 viewsread 7 August 2026 Socioeconomic, Psychological, and Health System Challenges of Persons with Podoconiosis and its Human Rights Impacts
...
What is Podoconiosis? What are the human rights impacts of Podoconiosis? What is the situation in Ethiopia?
🔗 https://ehrc.org/?p=38426
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsforAll
You can file a human rights violation complaint by calling our toll-free line at 7307.
27 Jun 2026, 11:21 UTC680 viewsread 7 August 2026 በሴቶች መብቶች ዙሪያ መደበኛ ካልሆኑ የሴቶች አደረጃጀቶች ጋር የተካሄደ የግንዛቤ ማሳደጊያ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሴቶች መብቶች ላይ ለሚሠሩ መደበኛ ያልሆኑ የሴቶች መብቶች አደረጃጀቶች የግንዛቤ ማሳደጊያ ውይይት በሰኔ 11 እና 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አካሂዷል። ውይይቱ መደበኛ ያልሆኑ የሴቶች መብቶች አደረጃጀቶችን ዐቅም በማሳደግ ሥራቸውን ከሰብአዊ መብቶች መርሕ ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲያከናውኑ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በዞንና በወረዳ ያቋቋማቸው የበጎ ፈቃደኛ ኮሚቴ አመራሮች፤ ከአፋር፣ ከአማራ፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከኦሮሚያ፣ ከ…
26 Jun 2026, 18:01 UTC676 views3 reactionsread 7 August 2026 Video
የሳምንቱ #HRConcept: የማሠቃየት ተግባር ተጎጂዎች መብት
...
የማሠቃየት እና ሌሎች የጭካኔ፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነና ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ለማስቀረት የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 14
- እያንዳንዱ አባል ሀገር በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የማሠቃየት ተግባር ሰለባ የሆነ ሰው መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዲሁም በተቻለ መጠን የተሟላ ማገገሚያን ጨምሮ ተፈጻሚነት ያለው ፍትሐዊና በቂ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ አለበት።
- ተጎጂው በደረሰበት የማሠቃየት ተግባር ምክንያት የሞተ እንደሆነ በእርሱ ኃላፊነት እና ድጋፍ ይተዳደሩ የነበሩ ሰዎች ካሳ ሊያገኙ ይገባል።
🔗 https://ehrc.org/?p=38394
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordS…
👍2❤1
25 Jun 2026, 22:08 UTC675 views1 reactionsread 7 August 2026 ኦሮሚያ፦ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ ዙሪያ የተዘጋጀ የውትወታ መድረክ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል፣ በጅማ እና ምሥራቅ ሐረርጌ ዞኖች እንዲሁም በጅማ ከተማ አስተዳደር በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ አተገባበር ላይ ባከናወናቸው የክትትል ሥራዎች፣ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ዙሪያ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የውትወታ መድረክ በጅማ ከተማ አካሂዷል። መድረኩ ኢሰመኮ ባከናወናቸው ክትትሎች የተለዩ መልካም ተሞክሮዎችን፣ ተግዳሮቶችን እና የተፈናቃዮች መብቶች የሚከበሩበትን ሁኔታ ለመገምገም እና ልምድ ልውውጥን ለማጎልበት ያለመ ነው።
በመድረኩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮ…
❤1
24 Jun 2026, 12:37 UTC633 views1 reactionsread 7 August 2026 በሀገር ውስጥ በሴቶች እና በሕፃናት የመነገድ ድርጊትን አስመልክቶ የተካሄደ የምክክር መድረክ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሀገር ውስጥ በሴቶች እና በሕፃናት የመነገድ ድርጊትን ለመግታት በሚወሰዱ ምላሾች ላይ ባከናወነው ክትትል የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበርን አስመልክቶ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል። በመድረኩ ከፌዴራልና ከክልል ተቋማት የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ፣ ከባሕር ዳር፣ ከሐዋሳ እና ከወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከምሥራቅ ሸዋ ዞን የተወጣጡ የፍትሕ ተቋማት፣ አስፈጻሚ አካላት፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል።
በውይይቱ በ…
❤1
20 Jun 2026, 18:44 UTC759 views3 reactionsread 7 August 2026 Video
የሳምንቱ #HRConcept: የአካባቢ ደኅንነት መብት እና ልማት
...
የአፍሪካ የሰዎች እና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 24
ሁሉም ሕዝብ ለእድገቱ አመቺ የሆነ አጠቃላይ ተስማሚነት ያለው አካባቢ የማግኘት መብት አለው።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 44
ሁሉም ሰዎች ንጹሕና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው።
መንግሥት በሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሯቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ እርዳታ ወደሌላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው።
🔗 https://ehrc.org?p=38278
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
…
👍3
19 Jun 2026, 19:12 UTC778 viewsread 7 August 2026 Accessibility of Roads and Buildings for Persons with Disabilities Remains a Pressing Human Rights Concern
...
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) conducted a public hearing in Hawassa City on April 28 and 29, 2026, as part of its ongoing systemic human rights investigation into the accessibility of roads and buildings for persons with disabilities. The hearing focused on barriers affecting accessibility of…
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ethiopiahrc. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.