31 Jul 2026, 12:00 UTC53 views1 reactionsread 2 September 2026 Photo
በወልደጊዮርጊስ ይልቃል ቢተው የሚተዳደረው YBS ማርኬቲንግ እና ረቂቅ ድርጅት ላይ ገንዘብ አስቀምጠው በየወሩ ዳጎስ ያለ ወለድ ሲቀበሉ የነበሩ ደንበኞች ተጭበርብረናል የሚል ጭንቀታቸውን እየገለፁ ነው።
ረቂቅ ድርጅት 200 ሺህ ብር አስገብተው በሁለቱ ወራት ውስጥ 40 ሺሕ ብር የተከፈላቸው አንድ ነዋሪ፣ ለጣቢያችን እንደገለጹት ሶስተኛውን 20 ሺሕ ብር ክፍያ መቀበል አልቻሉም።
ወደባንክ ሄደው የተሰጣቸውን ቼክ ለመመንዘር ሲጠይቁ ገንዘብ የሌለው ደረቅ ቼክ መሆኑን ነግረውናል።
ድርጅቱ ኦዲት ላይ ነኝ በሚል የገንዘብ እንቅስቃሴውን ማቋረጡን እና ቢሮዎቹም መዘጋታቸውን ጣቢያችን ሰምታለች።
በወልደጊዮርጊስ ይልቃል የሚተዳደረው YBS ማርኬቲንግም ኦዲቲ ላይ ነ…
❤1
16 Jul 2026, 18:16 UTC80 viewsread 2 September 2026 Photo
በምሥሉ ላይ በመንግስት ደጋፊነቱ የሚታወቀው ያወዛጋቢው አክቲቪስት ስዩም ተሾመ ነው የተባለ መኪና ይታያል።
የኢትዮጵያ መንግስት በስጦታ መልክ ሰጥቶታል የተባለው ባለቅንጦቱ V8 መኪና በአዲስ አበባ "72" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቆሞ ተመልክተነዋል።
መኪናው በዚህ ወደ አራብሳ ወይም አያት በሚወስደው መስቀለኛ መንገድ መግቢያ ባለ «ወንድማማቾች» የተሰኘ ቁርጥ ቤት ፊት ለፊት ለምን እንደቆመ በግልጽ መረዳት አልቻልንም።
ጣቢያችን ከወራት በፊት መኪናው ለመንግስት ቅርብ ለሆነው ለዚህ አክቲቪስት መሰጠቱን የሚጠቁሙ ፍንጮችን ሰምቶ ነበር።
አሁን ደግሞ በአካል ታይቶ በጣቢያችን ዘጋቢ ፎቶ መነሳቱ መረጃውን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል።
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔ…
14 Jul 2026, 03:20 UTC74 viewsread 2 September 2026 Photo
ከ50 ዓመታት በፊት፣ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መርካቶ አካባቢ አንድ ሕፃን ተወለደ።
ዛሬ ያ ሕፃን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ የማይረሳ አሻራ ያኖረ ድምፃዊ ሆኗል።
የልጁ ስም ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞ (ቴዲ አፍሮ) ነው፤ የታዋቂዎቹ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች የካሳሁን ገርማሞ እና የጥላዬ አራጌ ልጅ!
ቴዲ አፍሮ ከ20 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓለም የራሱን ልዩ ስፍራ በመፍጠር፣ በሚሊዮኖች ዘንድ ፍቅርና ክብር አትርፏል።
በዚህም ምክንያት ብዙ ኢትዮጵያውያን በፍቅር "ሳልሳዊ ቴዎድሮስ" ብለው ይጠሩታል።
🏛️ የመጀመሪያው ቴዎድሮስ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ የተጠቀሰ ንጉሥ ነበር።
⚔️ ሁለተኛው ቴዎድሮስ (ዐፄ ቴዎድሮስ ዳግማዊ) በ1…
13 Jul 2026, 15:28 UTC62 viewsread 2 September 2026 Photo
⚽🏆 ከምንም በላይ እንግሊዝ የዓለም ዋንጫውን እንዳታነሳ የሚመኙት እነማን ናቸው?
ብዙዎች ፈረንሳይ፣ ጀርመን ወይም አርጀንቲና ብለው ሊገምቱ ይችላሉ። ነገር ግን የእንግሊዝ ምቀኛ😂 አየርላንዳውያን ናቸው።
"እንግሊዝ ዋንጫውን ካነሳች፣ ለሚቀጥሉት 40 ዓመታት ስለዚያ ድል ሲያወሩልን መስማት አንፈልግም!"
ይላሉ።
ይህ አስተያየት ከሁለቱ አገሮች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን የታሪክ፣ የፖለቲካ እና የእግር ኳስ ፉክክር የሚያንፀባርቅ ነው።
እርግጥ ነው፣ ሁሉም አየርላንዳውያን እንዲህ አያስቡም፤ ግን ይህ ቀልድ በስፖርት ውይይቶች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚነሳ ነው።
እርስዎስ ምን ያስባሉ? አስተያየትዎን ያጋሩ! 👇
#WorldCup #England #Ireland …
12 Jul 2026, 18:17 UTC70 viewsread 2 September 2026 Photo
🚨ዐቢይ አሕመድ መሐል ጎጃም ዋሉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደብረ ማርቆስን ጎብኝተው የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን በይፋ መርቀዋል።
የዛሬው የጠቅላይ ሚንስትሩ የደብረማርቆስ ጉዞ ከስድስት ዓመታት በኋላ የተደገመ ነው።
የአውሮፕላን ማረፊያው ምርቃት ለጎጃም ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ መሆኑ ቢገለጽም፣ ከምርቃቱ በላይ ትኩረት የሳበው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ መልእክት ሆኗል።
ዐቢይ በንግግራቸው ውስጥ በአማራ ክልል ያለውን የጸጥታ ችግር፣ የመንገዶች መዘጋጋት፣ የሰላም እጦት እና የብሔር ክፍፍል አደጋ በግልጽ አንስተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ልማት በትዕግሥት፣ በትብብር እና በሰላም ብቻ እንደሚሳካ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ነገር ግን…
7 Jul 2026, 13:59 UTC75 viewsread 2 September 2026 Photo
አስቸኳይ መረጃ፡ በፖለቲካው መድረክ አዲስ መነጋገሪያ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ረፋድ ላይ የመደመር ፍልስፍናን በጽኑ ሲተቹ ከነበሩት ከደሳለኝ ጫኔ ጋር አብሮ ለመስራት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት አስተያየት፣ ደሳለኝ ጫኔ የመደመርን ፍልስፍና በሚገባ መረዳታቸውንና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ከፓርላማው ስብሰባ በኋላም፣ ሁለቱ የምክር ቤት ባላንጣዎች ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በአንድ ላይ መታየታቸው ትኩረት ስቧል።
ይህ መገናኘት በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ አዲስ የትብብር አቅጣጫ ያስከትል ይሆን?
በቀጣይ ቀናት ሁለቱ ወገኖች የሚወስዱት አቅጣጫ በጉጉት ይጠበቃል።
ቀጣዩ የዐቢይ ሚንስትር ደ…
7 Jul 2026, 06:11 UTC59 views1 reactionsread 2 September 2026 Photo
የዘመናችን "ቫስኮ ደጋማ"፤ የክርስቲያኖ ሮናልዶ እንባ እና የኢቤሪያውያን ፍልሚያ
በ15ኛው እና 16ኛው ክፍለ ዘመን፣ የዓለም ካርታ ባልተሟላበት የድቅድቅ ጨለማ ዘመን፤ ስፔን እና ፖርቹጋል ዓለምን ለመቃኘት በውቅያኖሶች ላይ ይኳትኑ ነበር።
ትናንት በዓለም ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ፍልሚያ፣ ያ የጥንት ታሪካዊ ፉክክር በስታዲየም ውስጥ በአዲስ መልክ ተከሰተ።
በዚህ ትልቅ መድረክ ላይ ደግሞ የዘመናችን ታላቅ "አሳሽ" ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶስ ሳንቶስ አቬይሮ ቆሞ ነበር።
ልክ እንደ ቫስኮ ደጋማ፣ ሮናልዶም የእግር ኳስ አህጉራትን ሁሉ አቋርጦ፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ክብረ ወሰኖች ሰብሮ፣ የፖርቹጋልን ባንዲራ በዓለም ከፍ አድርጎ አውለብልቧል።
በከፍተኛ ትንቅንቅ…
🔥1
6 Jul 2026, 21:26 UTC59 views1 reactionsread 2 September 2026 Photo
ስፔን በጭማሪ ሰዓት ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅላለች።
ጨዋታው እንደተጠበቀው ከፍተኛ ፉክክር የታየበት አልነበረም፤ ይልቁንም በአብዛኛው አሰልቺ እና የፈጠራ ችሎታ የታየባቸው የግብ እድሎች የተገደቡበት ነበር።
ቢቢሲ ጨዋታውን ስልታዊ ቢሆንም የደጋፊዎችን ስሜት የሚገዛ አስደሳች ቅጽበት ያልነበረው ሲል ገልፆታል።ኢኤስፒኤን በበኩሉ ፖርቹጋል በተለይም ሮናልዶ በጨዋታው ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ተቸግረው እንደነበር እና ውጤቱ የሁለቱን ቡድኖች ደካማ የፈጠራ ችሎታ ያሳያል ሲል ትችቱን ሰንዝሯል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየት የሚሰጡ ተመልካቾችም ጨዋታውን የሰዓት ብክነት የነበረበት አሰልቺ ግጥሚያ ሲሉ ወቅሰውታ…
🔥1
6 Jul 2026, 19:24 UTC62 views2 reactionsread 2 September 2026 Photo
ኢትዮጵያዊው ደራሲ ሰርቅ ዳ. «ቆንጆዎቹ» በተሰኘው የጥቁርን ሕዝብ ትግል የሚያቀነቅን ፓን አፍሪካኒስት ልቦለዱ ውስጥ«...ራሡን የማይከላከል ቁንጅና የቀትር ፀሐይ ሲወጣ ይረግፋል፤» ይላል።
እንደዚች ኢትዮጵያዊት ያለ ቁንጅና ግን ራሡን ከደሃነት የተከላከለ፣የቀትር ፀሐይ ያሸነፈ፣ባለድል ቁንጅና ነው።
ምሥክር ከበደ በተሰኙ ሰው የተነሱ ናቸው ተብለው በፌስቡክ የተጋሩት የዚች ጥቁር ኢትዮጵያዊት ምሥሎች የብዙ የአገሯን ልጆች ቀልብ ስበዋል።
እናንተ የልጅቱን ውበት ስታዩ ምን ተሰማችሁ?
«ውበቷ
ውበቷ
የዚች ልጅ ውበቷ...»
አላችሁ?
ፃፉልን😀
https://t.me/ethio_best1
❤1🔥1
5 Jul 2026, 18:13 UTC75 views1 reactionsread 2 September 2026 Photo
ራሔል ዮሐንስ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ በወርቃማ ቀለም ስሟን የጻፈላት፣ በባሕልና በትዝታ ዜማዎቿ የብዙዎችን ልብ የገዛች ድንቅ እንስት የኪነ-ጥበብ ሰው ነበረች።
ከካዛንቺስ እስከ ዓለም አቀፍ መድረኮች የዘለቀው የሕይወት ጉዞዋ፣ በትግልና በስኬት የታጀበ የጥበብ መንገድ ነበር።
እንደ “አንቺ ባለድሪ”፣ “ምኒልክ”፣ “አራዳ” እና “ትዝታ” ባሉ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎቿ የኢትዮጵያን ታሪክና የባሕል እሴት በውበት ስትዘምር የኖረችው ራሔል፣ በድምፃዊነቷ ብቻ ሳይሆን በዜማ ደራሲነቷም የኪነ-ጥበብ ስጦታዋን አሳይታለች።
በተለይም የምኒልክን ቤተ መንግሥት ግርማ ሞገስና የጠጁን መዓዛ በዜማዋ ስትስል፣ አድማጭ በዚያ የፍቅርና የሰላም ዘመን ላይ እንዲንሸራሸር ታደርግ …
🥰1
Channel photo updated
Channel name was changed to «ethio best»
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ethio_best1. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.