9 Sept 2026, 05:09 UTC117 views7 reactionsread 9 September 2026 "... [ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ] ወደ ቤተ ክርስቲያኑም ይትከላችኹ፤ ለገዛ አገልግሎቱም ይመዝግባችኹ፤ የጽድቅንም የጦር ዕቃ ያልብሳችኹ፤ የዐዲስ ኪዳንን ሰማያዊ ነገር ይሙላባችኹ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ለዘለዓለም የማይጠፋ የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ይስጣችሁ..."
(የኢየሩሳሌሙ ቅዱስ ቄርሎስ የመንፈስ ልጆቹን እንደ ባረከው)
❤7
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
8 Sept 2026, 07:59 UTC214 views8 reactionsread 9 September 2026 ጌታ ኢየሱስን እወደዋለኹ፤ ደግሞም መዳኔን አውቃለኹ እያለ ወንድሙን ግን የሚጠላ ርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ መጽሐፍ፥ “ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።” (1ዮሐ. 3፥15)
❤7👍1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
7 Sept 2026, 05:25 UTC288 views5 reactionsread 9 September 2026 Photo
"እንደ ቃሉ ከኖርን ጉባኤያቾንን የሚመራው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" ( አቡነ ኤርምያስ)
👍5
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
6 Sept 2026, 15:28 UTC327 views5 reactionsread 9 September 2026 Photo
ቸርነትህ በ'ዛ¡ ምን ትቀልዳለህ?! ዘይት ማን በነጻ እንደ ሰጠ አንተ ትሰ'ጣለህ?! እንዲህማ በጣም ደግ ጻድቅ አተገባበር ኹን እንጂ¡ ጌታ ይገስጽህ!
😁4❤1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
6 Sept 2026, 06:04 UTC344 views4 reactionsread 9 September 2026 "... የእንቅልፍ ጽናት ይኸውም የሞት ምሳሌ እንዳያሰጥማቸው፤ ክቡር ኀያል ስምህን ያመሰግኑ ዘንድ፥ አቤቱ በፍቅርህ አንቃቸው፤ ዐለምን ሁሉ የያዝኽ እግዚአብሔር አምላካችን አንተ ነህ ..."
(ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ)
❤4
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
5 Sept 2026, 14:26 UTC417 views6 reactionsread 9 September 2026 Video
ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶነት የሰው ሥራ የሚመስላቸው ዐያሌ "ካራ ኦርቶዶክሳውያን" አሉ። ነገር ግን ተሐድሶ፥ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሚሰጠው ታላቅ ዕድል ነው። ቤተክርስቲያን ይህን በጎ ዕድል ከተጠቀመችበት፣ ጉብኝትና ኀይል ይኾንላታል፤ ባትጠቀም ግን ጨውነቷን አጥታ "ከመረገጥ በቀር" ላትጠቅም ትችላለች፤ (ማቴ. 5፥13)።
ተሐድሶን አቁመናል፤ ከንግዲህ ዕድል የለውም የሚል "ሽለላ" ከንቱ ነው፤ እንዲህ እያላችኹ ከመራመድ የሚከለክለው አንዳች ምድራዊ ኀይል የለምና፤ እናም ተሐድሶን በአደባባይ መግፋት ዋጋ ያስከፍላል፣ እባካችኹ እልኸኞች አትኹኑ። ጌታ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሰጠውን ዕድል ባለመታዘዝ አታዘግዩ።
የቴሌግራም አድራሻ - https://t.m…
❤4🤮2
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
5 Sept 2026, 08:05 UTC433 views7 reactionsread 9 September 2026 Photo
የማኅበረ አኀው የክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ ስለ ቤተክርስቲያኒቱም ዓላማና ስለ ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ በሚገባ ይረዱ።
እግዚአብሔር በጸጋው ኀይል አብዝቶ ቤተክርስቲያንን ይጎብኝ፤ አሜን።
https://www.mahibereahaw.org.et/
❤6😁1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
4 Sept 2026, 14:02 UTC424 views16 reactionsread 9 September 2026 Photo
ቃለ ሕይወትን ቃለ ሕይወት ያሰማልን ብለናል፤ "ጭካኔዋም" ይበል ያሰኛል። በሥነ ምግባር "በቁመቱ ልክ መውደቁን" የታማውን ሰው ለጊዜው ማገድዋ ትልቅ መልእክት አለው። የወደቀ ጨርሶ እንዳይወድቅ፣ እንዲነሳ እንጸልያለን።
❤10👍3🔥2🥰1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
4 Sept 2026, 05:33 UTC491 views6 reactionsread 9 September 2026 Photo
በሠለጠነው ዓለም "ዓለማዊ ሥልጣን" ያለው አንድ መሪ፣ እንኳን "በድምጽ ቅጂ በተረጋገጠ" እና በተገለጠ የሙ'ስና ቅሌት ተጠርጥሮ አይደለም፣ "የሙስና ውልብታ ሐሜት" ከታማ እንኳ፣ በገዛ ፈቃዱ ሥልጣኑን ይለቅቃል።
የኛ "የአፍሪካውያን" መሪዎች ግን እንኳንና ምድራዊ ባለሥልጣናቱ፣ የሃይማኖት መሪዎቹ እንኳ "ካፈርኩ አይመልሰኝ" በሚለው መርሕ "ትንሽ እንኳ" ማፈር አያውቁበትም። ይህ በምስሉ የሚሞገሰው ሰው ከካውንስሉ መሪዎች አንዱ ነው፤ ካውንስሉ ደግሞ ከመጀመሪያ ፅንሰቱ ጀምሮ የፖተለከ ነው። ውልደቱ "ዓለማዊ" እንጂ መንፈሳዊነት የማይ'ታይበት የነበረው ካውንስል፣ ፍሬው ከማን ወገን እንደ ኾነ በሚገባ እየተገለጠ ነው።
ነው'ር ካል'ታፈረ፤ ልብ እንደ ፈርዖን…
❤5🥰1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
3 Sept 2026, 17:13 UTC444 views9 reactionsread 9 September 2026 Video
"ለጌታዬ ለእግዚአብሔር ስላደረገልኝ ምን እከፍለዋለኹ
ምሥጋና ነው እንጂ(2x) ሌላ ምን እላለሁ።"
❤8🥰1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
3 Sept 2026, 04:16 UTC466 views3 reactionsread 9 September 2026 “በበሩ አደባባይ የሚገሥጸውን ጠሉ፥ እውነትም የሚናገረውን ተጸየፉ።” (አሞ. 5፥10)
❤2🥰1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
1 Sept 2026, 17:58 UTC574 views11 reactionsread 9 September 2026 Video
እንኳንና ድንግል ማርያምን ማናቸውንም የእግዚአብሔር መልክና አምሳል ያለበትን ሰው መሳደብ፣ መናቅና ማዋረድ ጨርሶ ኀጢአት ነው። አንድ ሰው ግን እግዚአብሔርን ወይም ቅዱሳንን ስለ ተሳደበ፣ ምላሱ ይቆረጥ፤ አፍንጫው ይፎነን ከማለት በዘለለ፣ ይህን ያደረገ አ'ሳፋሪ ንጉሥ ከሞት ተነስቶ እንዲመጣ መመኘት አጋን'ንታዊ ዐሳብ ነው።
እኛ የክርስቶስ ወገን ነንና የሚረግሙንን እንመርቃለን፤ ለሚያሳድዱን እንጸልያለን፤ የሚጠሉንንም እንወዳለን። ክርስቶስ ለሰቀሉት አይሁድ እንደ ማለደ እኛም ዛሬም፣ ክርስቶስን፤ መንግሥቱንና የመንግሥቱን ሠራተኞች የሚጠሉትን እንወዳቸዋለን፤ እንማልድላቸዋለን።
እንዲጠፉና አንዳች 'መቅሰፍት' እንዲያገኛቸው አንመኝም። ይህ ዮርዳኖስ የተባለው …
👍5❤3👏2🥰1
Signed "ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @ebenezertek. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.