12 Jun 2026, 14:58 UTC175 views5 reactionsread 8 August 2026 "በህይወትሽ ውስጥ ካገኘሻ ቸው ጥሩ ምክሮች የማትረሺ ው የቱን ነው?" አለኝ ወሬ ለመጀመር ያክል.....
"ሁሉም ሰው ለራሱ ጥቅም ብቻ ነው የሚያስበው ለሰው ብለህ እራስህን አትጉዳ፤ ደስታህን አትጣ!"... አልኩት በሃሳብ እየሄድኩ..
"ደስ የሚል ምክር ነው ግን ማን ነው እንደዛ ያለሽ ?" አለኝ ቀና ብሎ...
"በጣም የወደድኩት... በጣም የጠላሁት ሰው ነው!" የህይወቴን ትልቁን ክህደት ያስተማረኝ ሰው! አልኩት በሃዘን... ወደ ዝምታችን ተመለስን!
ሰውን ማመን እንደሌለብን የሚያስተምሩን በጣም ያመናቸው ሰዎች ናቸው!
❤5
Signed 💎✨️
7 Jun 2026, 10:29 UTC234 views3 reactionsread 8 August 2026 አንዳንዴ መጨረሻዎች እንደ ቡና መራራ ቢሆኑም ያነቁናል! ☕️💡
ታዋቂው ፀሀፊ ማህሙድ ዳርዊሽ እንደተናገረው:
“አንዳንድ መጨረሻዎች እንደ ቡና መራራ ናቸው፤ ነገር ግን ንቁ ሰው ያደርጉናል።”
ይህ ማለት፣ በህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን አንዳንድ ክስተቶች ወይም ግንኙነቶች ሲያበቁ ከባድ እና አሳዛኝ ሊሆኑ ይችላሉ። ልክ እንደ መራራ ቡና መጀመሪያ ላይ ለመዋጥ የሚያስቸግር ቢሆንም፣ ከዛ በኋላ ግን አይናችንን እንድንከፍት፣ ነገሮችን በተለየ መንገድ እንድናይ እና አዲስ ትምህርት እንድንቀስም ይረዱናል።
መራራ መጨረሻዎች ለቀጣይ ጉዟችን ጠቃሚ ትምህርት ሰጥተውን፣ ይበልጥ ጠንካራ እና ንቁ እንድንሆን ያደርጉናል።
.
.
❤3
Signed 💎✨️
6 Jun 2026, 12:51 UTC218 views8 reactionsread 8 August 2026 ......!
ልብ ተስፋ ሲቆርጥ ሆድ መቻል ሲያቅተው
እንጀትም ሲቆረጥ አይንም እምባ ሲያጥረው
አለኝ ያሉት ሲተን
በእጅ ያለ ሲበተን
ያመኑት ሲከዳ
ዘመድ ሲሆን ባዳ
ነገርም ሲከፋ ጨለማም ሲነግስ
ሰው ነኝ ባይ ቢጠፋ
ለችግር የሚደርስ
ፈተና ቢበዛ እንቅፋትም ቢኖር
መሄጃ ቢጠፋ እግርም ቢታሰር
አለም ብትከፋ መግፋት ቢያስደስታት
መች ትቶ ይተዋል የላይኛው አባት!!
🔥7❤1
Signed 💎✨️
5 Jun 2026, 01:58 UTC265 views1 reactionsread 8 August 2026 #ማርቆስ 8÷34
ሁሉም አለው አንድ መስቀል...
ሚስጢር ለሰው ማይነገር፤
ብቻውን አስታሞት የሚቀር፤
በፈገግታ የሚሸፈን፤
በጌጣጌጥ የሚዳፈን፤
በብልጭልጭ የሚታፈን፤
አለው ህቡእ ማንነት፤
ፈጣሪ ብቻ የሚያውቅለት፤
እንባ አፍሶ የማይበርድለት፤
ዛሬና ነገ አንድ የሆኑበት፤
ሰአት የማያቅ .....
እለት እለት የሚጨንቀው፤
ለሌላ ሰው የማይደንቀው፤
ለርሱ ብቻ የሚዘልቀው፤
እድሜ ልኩን የማይለቀው፤
አንድ መስቀል አንድ መከራ፤
ቦታ የማይመርጥ በሁሉ ስፍራ፤
ሁሉ አለው አንድ መስቀል፤
እንደ ሰንኮፍ ማይነቀል፤…
❤1
Signed 💎✨️
4 Jun 2026, 05:42 UTC159 views4 reactionsread 8 August 2026 የጠቋር ሚስት
ጓደኛዬ አዲስ ሙሽራ ነው። ገና ስድስት ወሩ ነው ካገባ። የሆነ እሁድ ጠዋት ልጠይቃቸው ቤታቸው ስሄድ ይሄን ገንገበት ጓደኛዬን ባለቤቱ “ዳዲ” እያለች ስትጠራው ሰማሁ። ተወልዳ እስክታድግ በአንድ የአምበሳ ቆዳ ጫማ እየዳከረ ያሳደጋትን የአባቷን ስም እንደቀልድ ለስድስት ወር ባሏ መስጠቷ ግርም አለኝ። አጎቴ "ሴትና የቀበሌ ቤት የኔ ነው አይባልም" የሚለው እውነት ሳይሆን አይቀርም።
ቤታቸው የሄድኩት እሁድ ጠኋት ስለነበር “ቸርች ልንሄድ ስንል መጣህ” ብለው አብረን ካልሄድን አሉኝ። ላለመሄድ ብሞክርም ባለቤቱ ቆጣ ብላ “ኖህ! ወደድራፍት ቤት እንሂድ ቢሉህ መች እምቢ ትላለህ? በል ተነስ” አለችኝ።
ይሄ ግምብ ራስ ባሏ ድራፍት እንደምወድ ነግ…
❤2👏1😁1
Signed 💎✨️
4 Jun 2026, 03:11 UTC118 views2 reactionsread 8 August 2026 አለማየው ገላጋይ ውልብታ መፅሀፍ
*"የገጣሚዋ - ገጣሚ"*
ገጣሚዋ አይኗ - ያፍራል _ ሲያፍር ያምራል፣
ጉንጯ ያፍራል _ ሲያፍር ይቀላል _ ሲቀላ ግመጡኝ - ግመጡኝ....... ይላል።
እግሯ ያፍራል - ሲያፍር - ወንበር ሥር - ይደበቃል።
እና ለአይናፋርነቷ እየሳሳሁ _ ለስላሳ ጥያቄ አቀርብላታለሁ።
‹‹እወድሻለሁ››
አይናፋረዋ ገጣሚ _ አፏ ስለሚያፍርባት - ቦርሳዋን ከፍት አድርጋ
ከወረቀቶች መካከል _ አንዱን ታቀብለኛለች።
ግጥም ነው።
እንዲ ይላል
‹‹እወድሻለሁ ማለት _ የልብ አያደርስም
እንቀመጥና _ ንገረኝ ሁሉንም››
*" ከዛ _ ካፌ እንቀመጣለን።
‹‹ሻይ ይሻላል? ወይስ ወተት ትጠጪ?›› ... ስላት
የገጣሚዋ አይናፋ…
👏2
Signed 💎✨️
3 Jun 2026, 14:04 UTC122 views5 reactionsread 8 August 2026 አኩርፈሻል መሰል…
➖➖➖➖➖
(ሰለሞን ሳህለ)
ግራ እጄን አመመኝ…
ከበረዶ በልጦ ይሄው ቀዘቀዘ
መራመድ አቃተው…
ለእርምጃ ሰነፈ ቀኝ እግሬም ተያዘ
የጎረስኩት ሁሉ…
አልጣፍጥህ አለኝ ጣእም ጣሙን አጣ
የመሬት መንቀጥቀጥ…
የሚያስነሳ ንዝረት አናቴ ላይ ወጣ
ሁሉም ፉርሽ ሆነ
ህዝበ አዳም ተቀጣ ህዝበ አዳም ተቆጣ
አኩርፈሻል መሰል…
ካልጋየ ተኝቼ..
የምሰማው ዜማ እንቅልፍ እንዲወስደኝ
የነካውን እንጃ …
ባላሰብኩት ቅጽበት እንቅልፌን ነጠቀኝ
ለሽራፊ ሰከንድ…
ዜማው አልዘመመም ቅኝቱ አልፈረሰም
ልክ እንደ ጥንቱ ነው የጎደለው የለም
የሆነው ሆኖ ግን…
እንዳረጀ ወንበር…
የሚንቋቋ ሆኖ ለኔ ይሰማኛል
በጨቀየ መንገድ…
ፍሬን እንደያዘ የመኪና ጎማ
ድምጹ እንደሚረብሽ
ል…
❤3🔥1🥰1
Signed 💎✨️
3 Jun 2026, 12:41 UTC149 views3 reactionsread 8 August 2026 ወደ እኔ እስክትመጪ
ስንት ቀለም ይንጠፍ ስንት ብዕር ልጨርስ
ስንት ግጥም ልፃፍ ስንት መጽሃፍ ልድረስ
እስክታዪ ናፍቆቴን እስክትመጪ ድረስ
ልብሽ እስኪወስን ስንት ቃላት ልድማ
እስክትወጂኝ ድረስ ስንት ሀረግ ላስማማ
ወደ እኔ እስክትመጪ
ስንት ግዜ ኪሪያላይሶን ስንቴ እግዚኦ ልበል
ሱባኤ ገብቼ ስንት አመት ልከልከል
ወደ እኔ እስክትመጪ
ስንት መስክረም ይጥባ ስንት አደይ ይርገፍ
ስንት ክረምት መጥቶ ስንት በጋ ይለፍ
ስንት ዝናብ ይምታኝ ስንቴ ልደር ዉጪ
መወደዴ አሸንፎሽ ወደ እኔ እስክትመጪ
Prince_zeresenay
❤2😱1
Signed 💎✨️
3 Jun 2026, 12:33 UTC156 views2 reactionsread 8 August 2026 አያቴ አደራ ሰጥታኝ
የሚያልፍ ዝናብ እንዳይመታኝ፤
ለሚቀር
አውርቼ እንዳልቀር ፣
ለሚሞት
ህይወት እንዳልሰጥ ፣
ፀጥ!
የሚያልፈው አፌን ሳይከፍተው
ዝግ ዝም እንድል እንድተው፤
አያቴ አደራ ብላኝ
ተባይ ቃል አፌን ቢበላኝ ፣
መተንፈስ ሁሉ እስኪያቅተኝ
ምላሴ ሲተናነቀኝ
ምላሼ ሲተናንቀኝ ፣
ታግዬ ስንቱን ዝም አልኩት
አይቼ ስንቱን አለፍኩት።
ዙሪያዬ የነገር እቁብ
ቆጥረዋት ምላሴን ከቁብ ፣
ጣል ቢሉኝ ቃል ካንደበቴ
አደራ ይዞኝ ያ'ያቴ ፣
አቋም አቅሜን ደብቄ
ስንቱን ያለፍኩት ታምቄ ፣
ምስኪን...
ራሴን ባለማወቄ!
የሚያልፈው ዝናብ ሳይመታኝ
ለማለፍ ዙሪያዬን ስቃኝ ፣
ባየሁት ቃሌ እየቃጣ
ስውጠው ፈርቼ ጣጣ ፣
ሳምቀው ኖሬ ሳፍነው
ምስኪን...
ለካስ እኔው ነኝ…
👏1🔥1
Signed 💎✨️
3 Jun 2026, 11:41 UTC134 views4 reactionsread 8 August 2026 "እንጋባ" ሲል ጠየቃት አሳምነው ። አልተቀበለችውም አስማሩ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው። ተስማሙ
ቤት እየመጣ ይጠይቃታል። ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ። አወግተው ይለያያሉ። የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም። አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ መጣ። እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ። ስለ ሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ።
አስምሩ አሰምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት። ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም ጃኬቱን አውልቆ ሄደ። አስምሩ እሱንም አጥባ አኖረችው
ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!" አወለቀው።
አስማሩ አጥባ አኖረችው ካፕርቱን ጥሎ ሄደ ፣አጥ…
❤2🔥1🤔1
Signed 💎
2 Jun 2026, 10:35 UTC130 views2 reactionsread 8 August 2026 (ከላይ የቀጠለ)
----
‹‹ሆዴ ውስጥ የሚንተከተክ ሚጢጢ እሳተ ገሞራ አለ ልበል ?›› አለች ለራሷ…
ነደደች። ሆዷን በእጇ ደግፋ አልጋዋ ላይ ጋደም አለች።
ትራስ ደረበች። ተደገፈች።
ግን አልተመቻትም።
ስልኳን ሳብ አደረገች። ደወለች።
ሶስት ጊዜ ጠራ።
«ሉላዬ? በደህና ነው የእኔ ቆንጆ?» የሚል በእንቅልፍና ደስታ የተጠመቀ ድምጽ ሰማች።
«ሄኒዬ… ደወለልኝ እኮ» አለች ጨለማው ላይ አፍጥጣ፣ ድምጽዋ እየተሰባበረ።
«ልታገባ መሆኗን ሲሰማ በዚህ ሰአት ለእኔ ደወለልኝ። ሊያለቃቅስብኝ»
«አይዞሽ የእኔ ቆንጆ» ብሎ መለሰላት በፍጥነት።
አቀባብሎ ሲጠብቃት የቆየ ምላሽ ይመስላል።
ማነው የደወለው ብሎ አልጠየቃትም። መጠየቅ አያስፈልገውም።
እሷ ሳሚን በምስጢ…
❤1🔥1
Signed 💎
2 Jun 2026, 10:35 UTC108 viewsread 8 August 2026 አባሮሽ…
ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነበር የደወለው።
ሉላ ገና ስልኩን ሳታነሳው መጥፎ ነገር መሆኑን ቀልቧ ነግሯታል። ሰው በውድቅት ሌሊት የሚደውለው ወይ ለመርዶ፣ ወይ ለመርዶ የቀረበ ዜና ይዞ ነው።
«ሄሎ» ከማለቷ፣ «ሉላዬ… ያንን ብሽቅ ልታገባው እኮ ነው» አላት።
ያለ እንቅልፍ ከተኛችበት ቀና አለችና አልጋዋ መሃል ተቀመጠች። በመኝታ ክፍሏ ግድግዳ ጥግ ካለው የኢንተርኔት ራውተር ጭል ጭል የምትል አረንጓዴ መብራት በስተቀር ክፍሉ ጨለማ ነበር።
«ውይ…» አለች በነገራት ነገር የደነገጠች ለመምሰል እየሞከረች። ምሽቱን ሙሉ የኢንስታግራም ፎቶዎቿን እያፈራረቀች ስታያቸው ነበር። ከውብ የቀለበት ፎቶዎቿ ስር «ላንተ ያለኝ ፍቅር ልዩ ነው» ብላ የጻፈችውንም አን…
Signed 💎
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @e_n_k_u_0. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.