30 Jun 2026, 18:08 UTC398 views4 reactionsread 7 August 2026 ምን ፍሬ አፈራን???
ልጆች! እስኪ ይፍቀዱልኝና አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ፡፡ ብዙውን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ትመላለሳላችሁ፡፡ መልካም ነው፡፡ ግን ምን ለውጥ አመጣችሁ? ምን ፍሬ አፈራችሁ? ታገለግላላችሁን? ታዲያ ከአገልሎታችሁ ምን ረብ ነገር አገኛችሁ ? ጥቅምን ካገኛችሁ በእውነት ምልልሳችሁ የብልህ ሰው ምልልስ ነው ማለት ነው፡፡
ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ወንጌላውያን እንዲህ እያስተማሩን ሳለ የማንለወጥ ከኾን ግን የእስከ አሁን ምልልሳችን የአይሁድ ምልልስ ነበር ማለት ነው፡፡ አይሁዳውያን ሕገ ኦሪትን የተሰጠቻቸው ኃጢአታቸውን በእርሷ መስታወትነት ዐይተው ንስሐ እንዲገቡባት ነበር፡፡ እነርሱ ግን የንስሐ ፍሬ ሳይፈሩባት እንዲያው ይመኩባት ነበር፡፡ ስለኾነም ለ…
🤯3😁1
26 Jun 2026, 10:50 UTC386 views3 reactionsread 7 August 2026 "ተስፋ ማለት 'ቢሆንስ' ብሎ መመኘት ሳይሆን፣ የሚታየው ዓለም ቢፈርስ እንኳን በማይታየው አምላክ ላይ ለመደገፍ የሚወሰን ጽኑ ውሳኔ ነው። ተስፋ አትቁረጥ፤ እግዚአብሔር አንተ በማታያቸው ነገሮች ላይ አሁን እየሠራ ነውና። መዘግየቱ መከልከል አይደለም።"
(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)
❤3
22 May 2026, 13:23 UTC614 views2 reactionsread 7 August 2026 የውጤታማ የንባብ አይነቶች/የጊዜ አጠቃቀም ስልት ..... በመምህር ገብረመድኅን እንየው
https://youtube.com/watch?v=Qfoc7zX-60s&si=IZM6VBGGSVHNa2g8
👍2
18 May 2026, 13:38 UTC570 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @felege_yohanis
የማይጠጣ ሰው ከሚጠጣ ሰው ይደነቃል
መጠንን አውቆ መጠጣት አይከለከልም ።
ይህ ማለት ሁሉም ይጠጣ ተብሎ ታዟል ማለት አይደለም ።
እንዲያውም የማይጠጣ ሰው ከሚጠጣ ሰው ይደነቃል ።
በማዕረግ ይቀመጡ ከተባለ ምንኩስና ከጋብቻ እንደሚከብር ጨርሶ የማይጠጣ ሰው በልክ ከሚጠጣ ሰው የከበረ ነው።
ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም ሩካቤ ዘግናኝ ኃጢአት እንደሆነ ሁሉ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ከመጠን በላይ አብዝቶ ጠጥቶ መስከር የከፋ ኃጢአት ነው ።
ሰካራሞች የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም 1ቆሮ 6:10
የቡሌ ሆራ ፈ/ዮ መ/መ/ቅ/ዮሐንስ ወልደታ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ
👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም አድራሻ ⤵️ ⤵️ ⤵️ ⬇️
https://t.me/fel…
18 May 2026, 12:40 UTC437 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @felege_yohanisPhoto
https://t.me/felege_yohanis
8 May 2026, 09:30 UTC552 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @felege_yohanis
#ግንቦት ልደታ
#ክፍል_፫
#የእመቤታችን_የልደት_በዓል_አከባበር
💠አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡
💠ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡
💠ስለሆነም አዳም 5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡
💠የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ (ዘፍ. 3፡20)
💠ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም …
❤1
14 Sept 2025, 18:57 UTC≈1,880 views12 reactionsread 7 August 2026 🕊
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 † መጽሐፈ ስንክሳር † 🕊
----------------------------------------------------
አበው እንዲህ ይላሉ ፦ "እናትህን ሳትስማት ፣ አባትህን ሳትሰናበተው ፣ ወንድሞችህና እኅቶችህ የሚሉትን ሳትሰማ ወደ ሥራ አትሠማራ።"
"እናትህን ሳትስማት" ማለት ወደ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ሔደህ ደጇን ሳትሳለም ማለት ነው። "አባትህን ሳትሰናበተው" ማለት ደግሞ የዘወትር ጠባቂህ እግዚአብሔርን በቤተክርስቲያን ተገኝተህ "ቸር አውለኝ" ሳትለው ማለት ነው። "ወንድም እኅቶችህ የሚሉትን ሳትሰማ" ማለትም ጻድቃን ሰማዕታት የሠሩትን ትሩፋት ሳታዳምጥ ማለት ነው። ይህን ሁሉ ሳታደርግ ወደ ሥራ አትሒድ…
❤12
2 Aug 2025, 08:19 UTC≈1,590 views4 reactionsread 7 August 2026 ተወዳጆች ሆይ ከዛሬ ጀምረን አዲስ ሕይወትን እንጀምር።
አሕዛብ ምን ያህል በረከት እንደራቃቸው እናሳያቸው፡፡ በእኛ ዘንድ መልካምነትን ካዩ መንግሥተ ሰማያትን በእኛ ውስጥ ያይዋታል፡፡ አዎ! ጨዋ ስንሆን፣ ከክፋት፣ ከክፉ ምኞት፣ ከቅናትና ከጠበኝነት ርቀን ሲመለከቱን፡- “እነዚህ ክርስቲያኖች ገና እዚህ ምድር እያሉ መላእክትን ከመሰሉ ወደዚያኛው ዓለም ሲሸጋገሩ ምን ሊመስሉ ነው? በእን ግድነት ዘመናቸው እንዲህ ብርሃን ከለበሱ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ሲሄዱማ እንዴት ሊሆኑ ነው?” ይላሉ፡፡ በእኛ ምክንያት እነርሱ ይለወጣሉ፤ የእግዚአብሔር ቃልም ከእኛ የተነሣ ይከብራል (2ተሰ.3፥1)፤ ወንጌል ከሐዋርያት ዘመን በላይ ይፋጠናል፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት አሥራ ሁለት …
❤4
30 Jul 2025, 12:18 UTC≈1,270 views5 reactionsread 7 August 2026 ❖ የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን፤ ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን፤ ዕለት ዕለት ኃጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም፤ መቼ ይሆን የምንነቃው?
✍️"ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው"
📖ዘፍ 3፥20
❖ ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው? ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል የሚኖርበትን ቤት በቆሸሸ ቁጥር የማያጸዳው ማነው? ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን በንስሐ መወልወያ የምናጸዳው መቼ ነው?
❖ ልጆቼ ንስሐ ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ፤ ወዳጄ ሆይ! ማፈር የሚገባህ ኃጢአት ስትሰራ እን…
❤5
29 Jul 2025, 18:40 UTC≈1,060 views3 reactionsread 7 August 2026 Posted without readable text
❤3
22 Jul 2025, 15:51 UTC≈1,370 views4 reactionsread 7 August 2026 አጉል ልማዶችን ተዉ
አጉል ልማዶችን ከሥር ጀምሮ ወላጆች ያስጥሉናል። ቀጥሎ መምህራን ያስተዉናል። መጻሕፍትም እንደ ሸለፈት የሆነውን ፣ ውበትና ጤንነትን የሚጎዳውን ክፉ ልማድ እንድንተው ያግዙናል። የሰው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ ለማወቅና ለንስሐ ጊዜው አይረፍድበትም። አጉል ልማድ ባለማወቅ ምክንያት ፣ ሥነ ሥርዓትን ባለመማር ፣ ልቅ በሆነ ባሕል ውስጥ በማደግ ፣ ሥልጣኔ በሚመስል ዘላንነት በመያዝ ሊመጣ ይችላል። አጉል ልማዶች እጅግ ብዙ ሲሆኑ ሁሉንም መንቀስ አይቻለንም። አጉል ልማዶች ትንሽ የሚመስሉ ትልቅ ጥፋት የሚያስከትሉ ናቸው። አጉል ልማድ ውስጥ ካለን ከሰዎች ጋር እንጋጫለን። ሰዎች ባይጋጩንም ለእኛ ያላቸው ክብር ይቀንሳል። አንዳንድ ሰዎች ሊነግ…
❤4
17 Jul 2025, 20:01 UTC≈1,520 views9 reactionsread 7 August 2026 ምንታዌነት
ምንታዌነት ሁለት ማንነት ነው
ይሄው ክርስቲያንም ዓለማዊም መሆን ነው
ጠዋት ተነስቶ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳል ክርስቲያን ነው ከሰአት በመጠት ቤት ይውላል ስመሽ ይጨፍራል ዓለማዊ ነው
ይዘምራል ክርስቲያን ነው ይዘፍናል ዓለማዊ ነው
በቤተክርስቲያን ሲሆን ቅዱስ ከዛ ወጥቶ ሲሄድ ቅድስና የለም ....
ሁለቱንም እንዳይከፋቸው የሃይማኖትም የዓለምም ነው
ግማሽ ጎኑ ታቦት ነው ግማሽ ጎኑ ጣኦት ነው ።
ሃይማኖት አለው ግን ከሃይማኖቱና ምንፍቅና መሀል እና ከሃይማኖቱና ዓለም መካከል ያለ ልዩነት አያውቅም በሁሉም ይነዳል።
መጽሐፍ ግን እንዲህ ይላል
“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ…
👍7❤2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @dnhayilemikael. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.