5 Aug 2026, 13:57 UTC38 views6 reactionsread 7 August 2026 አንዳንድ ሰው አለ!
በለጋነት እድሜ ከልብ ውስጥ የቀረ ልጅነት ያበጀው፤
በትዝታ መስመር ሁሌ ሚገናኙት ዘመን ማያስረጀው።
ምን ወልደው ቢስሙ የሌላ ቢሆኑ ሁሌም የሚያልሙት፤
ልክ እንደ ኤርታሌ ሲያዩት የሚያሸብር መንካት ያልታደሉት።
አዳም እንደዋጣት እንደበለስ ፍሬ ከመሀል የቀረ፤
አይለቁት አይተዉት ቀልብን አነሁልሎ መንፈስ ያሸበረ።
በልጅነት ዳብሶ የገላው ትኩሳት ዛሬም ላይ የሚፋጅ፤
ከስሜት ተሳስሮ ሰርክ የሚያብከነክን ህሊናን ተጣማጅ።
አለ አንዳንድ ሰው!
አዙሪትን መሳይ ወደጀመሩበት አዙሮ ሚመልስ፤
ድንግል ፍቅር ይዞ በድንግል ልብ ላይ ጎጆ የሚቀልስ።
እንዲህ እንዲህ ብለው ለሰው የማይነግሩት ውይይት ማይፈታው፤
ለቅፅበት ሲያገኙት ውስጥን የሚነዝር መ…
❤1👍1👏1🔥1😢1🙏1
29 Jul 2026, 08:21 UTC78 views2 reactionsread 7 August 2026 ግራ ገባን እኮ!
አንድ አንዶቹ ቀርበው ወደድኩህ ይሉና ከቤታችን ገብተው፣
የያዙትን ይዘው ከቤቱ ሲወጡ ከልባችን ገብተው፤
እኛ አማኞቹ..
ወደድኩህ እያለ የጠላን መብዛቱ እምነት አሳጥቶን፣
የመጣን መቀበል ስራችን ሆነና መፈለጉን ትተን፤
መተው ይሄዳሉ..
አስታዋሽ ይመጣል ትንሽ ስንከርም ታይተን ልንረሳ፣
መኖሩ ታከተን አንዲቷ ልባችን አስር ግዜ ፈርሳ።
አንድ አንዶቹ ደግሞ..
ተሥፋ ከቆረጥን ጀንበር ከጠለቀች ከርመው እየመጡ፣
ራሳችንን ገለን በቁም ስንራመድ ሊወልዱን ሲያምጡ፣
ማመን እያቃተን..
አምነውንአምነውን ለመኖር ሌት ከቀን ሲለፉ፣
ስራ እየሆንን እኛ እንድንለምድ ጠፍቶአቸው ማረፉ፤
ይረፍድብን እና..
እነሱ ሰልችተው ጓዛችውን ይዘው ጠፍተው የሄዱ ቀን፣
ቤ…
👍2
Signed ሩሀማ የኪዳነምህረት ልጅ
28 Jul 2026, 06:48 UTC125 viewsread 7 August 2026 Photo
ለምን እንደምጠጣ ታውቂያለሽ?
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ለመኖር ያነቃኝ የተስፋዬ ተሸካሚ አንቺነትሽ ሲሰንፍ፤
በእግዜር መሀላ ልቤን ያጀገነ ኪዳንሽ ሲታጠፍ፤
መሄድሽን አውቆ ሰላሜ ሲሸሸኝ ብቸኝነት ሲተም፤
ጥረት ዋጋ አጥቶየብዙ አመት ፍቅሬ በነበር ሲታተም፤
የሚሆን ቢመስለኝ አልኮልን ተዛመድኩ ቁስለቴን ልታከም።
✍ጫላ መኮንን
ጥበብ ምንጊዜም ትንገስ
ስለቆይታችሁ ክበሩልን።
ለተደራሲያን እያጋራን
https://t.me/chahi_1
27 Jun 2026, 22:59 UTC171 views4 reactionsread 7 August 2026 ያልታደለ ተድላ!
በአንዲት እናት ጓዳ ምኞት ተሰረገ,
የዘላለም ተስፋን ተስፋ ያደረገ።
እንዳይደርሱ የለ ቀኑም ተቃረበ,,
አበባው አፍርቶ እሸት አዘነበ።
ዳሩ ምን ያደርጋል? ማራኪው አበባ ፍሬ መስጠት እንጂ መበላት አልቻለም,
ለኮትኳቹ ተድላን መስጠት አልታደለም።
እናት ሀዘን ወርሷት ልቧ ተሰበረ,
ከሰርገኞች መሀል ልጇ ስለ ቀረ።
ለማን አቤት ትበል ማን ይስማ ጩኸቷን,
ልትሞሽር ጠብቃ ሞት ሲነጥቃት ልጇን!
፲ከአዳራሹ ቆማ ማእረጉን ለማየት ይህችን ቀን ስትናፍቅ,
እንዴት ትረጋጋ በክፋይዋ ፈንታ ሀውልቱ ሲመረቅ?
?
ሩሀማ።
የዛሬዋን የደስታ ቀኑን ለማየት ላልታደለ ለወንድሜ እያደር ማስታወሻ ይሁንልኝ!
አንተ ሰላማዊ ሰው ነፍስህ በሰላም ትረፍ።
❤3😢1
Signed ሩሀማ የኪዳነምህረት ልጅ
27 Jun 2026, 05:18 UTC152 views2 reactionsread 7 August 2026 ሞኝነት -1
አለም እያበቃች እየፈራረሰች
እኛን ግን ምን ገዶን
አፈር አቦካክተን ሰማይ እንሰራለን
ጨለማን ታቅፈን ጨለማ እንሞቃለን
ደሞ እንዳይደብረን
ቲንሽዬ ማሾ፣ ሚጢጢዬ ኩራዝ
ለኮስ !
ጨለማውን አበስ አበስ
መቼም ሞት ነው እንጂ ህይወትን አይለግስ
የሰርግ ድንኳን ውስጥ ሞሾ አይወረድ
ሀዘን ተቀምጦ እስክስ አይረገድ
ኧረ ወግድ
ለበሬ ቢላ እንጂ አይሆነውም ማጭድ ...
✍ዳኒ ዘ ጀማይካ
ጥበብ ምንጊዜም ትንገስ
ስለቆይታችሁ ክበሩልን።
ለተደራሲያን እያጋራን
https://t.me/chahi_1
🔥1😁1
Signed Chala Mekonnin
26 Jun 2026, 12:38 UTC≈1,240 views4 reactionsread 7 August 2026 ስራማ ነበረኝ!!!
??????
እኔን ለማሻገር ብዙ ላሳለፈ፤
ከሰው ተራ ወጥቶ ወዙ ለነጠፈ፤
እሱ ያላየውን እኔ እንዳይለት፤
ህልሙን ለገበረ ለሆነኝ መሰረት፤
ዛሬ ከጄ ውሎ እርጅና ለጣለው፤
እጄን ለሚናፍቅ እድሜ ለተጫነው፤
የምስኪን አባቴን ድካም ያላሰላ፤
የላቡን ውለታ ቀርጥፎ የበላ፤
እንዳልሞት እንዳልሽር ሰርክ የሚያባክነኝ፤
ወጥቶ ለመግባቱስ ስራማ ነበረኝ።
ያኔ ልጅ እያለሁ መደብ ላይ ቁጭ ብዬ፤
በስስት ስቃኛት እንቅልፌን ታግዬ፤
አረቄ ለማውጣት ስትታገል ከእሳት፤
አንዴ እየነደደ አንዳንዴ ሲፈጃት፤
ነገዬን ስትሰራ ማዲያት ሲወርሳት፤
መንገዴን ላቀና ምክሯን ሰምቼ፤
አንግሼ ላኖራት ትልቅ ቤት ሰርቼ፤
በእልህ ታጅቤ ቃል ገብቼ ነበር፤
ጉዳቷን ጎድቼ ችግሯን …
❤3💔1
Signed Chala Mekonnin
24 Jun 2026, 11:23 UTC228 views1 reactionsread 7 August 2026 ዳቦ ለመብላት!
????????
ሰው አንቅሮ ተፍቶኝ በችግር ብደፈር፤
ነገን መመልከቻ ዛሬዬ ቢሰበር፤
ተስፋ ፊቱ ጠቁሮ ጀርባውን ቢሰጠኝ፤
ሀፍረቴን አስጥሎ ረሀብ ቢያጋልጠኝ፤
መቋቋም ቢከብደኝ የኑሮን ፈተና፤
ውድ አካሌን ልሸጥ ወጣሁ ከጎዳና።
እንጂማ፣ ለቡና ማድመቂያ ሰርክ እንደምትሉት እንደናንተ ሀሜት፤
ተዘንግቶኝ ሳይሆን የሀገር ወግ ባህሉ ታውሬ በስሜት፤
ሴሰኛም ሆኜ አይደል ወይም ደሞ ላበርድ አንዳች የወሲብ ዛር፤
በምሽት ጨረቃ ዜማዬ የሆነው ሾርት ወይስ አዳር?፤
ምን ይሉኝን ትቼ ኩሩ ሴትነቴን ገበያ ያዋልኩት፤
ወንድ ርቦኝ ሳይሆን ዳቦ ለመብላት ነው ዳቦዬን የሸጥኩት።
✍ጫላ መኮንን
ጥበብ ምንጊዜም ትንገስ
ስለቆይታችሁ ክበሩልን።
ለተደራሲያን እያ…
❤1
Signed Chala Mekonnin
21 Jun 2026, 08:02 UTC207 views8 reactionsread 7 August 2026 ስራማ ነበረኝ!!!
እኔን ለማሻገር ብዙ ላሳለፈ፤
ከሰው ተራ ወጥቶ ወዙ ለነጠፈ፤
እሱ ያላየውን እኔ እንዳይለት፤
ህልሙን ለገበረ ለሆነኝ መሰረት፤
ዛሬ ከጄ ውሎ እርጅና ለጣለው፤
እጄን ለሚናፍቅ እድሜ ለተጫነው፤
የምስኪን አባቴን ድካም ያላሰላ፤
የላቡን ውለታ ቀርጥፎ የበላ፤
እንዳልሞት እንዳልሽር ሰርክ የሚያባክነኝ፤
ወጥቶ ለመግባቱስ ስራማ ነበረኝ።
✍ጫላ መኮንን
መልካም የአባቶች ቀን።
ጥበብ ምንጊዜም ትንገስ
ስለቆይታችሁ ክበሩልን።
ለተደራሲያን እያጋራን
https://t.me/chahi_1
❤5👏2👍1
Signed Chala Mekonnin
1 May 2026, 05:02 UTC260 views5 reactionsread 7 August 2026 መኖር ይሻለናል!
???????????????
ሰው ለሰው መሆኑን ትርጉሙን አጥተናል,
እምነት ጉድጓድ ገብቶ ፍትህ ሞቶብናል,
ሀቃችን ተወስዶ በቁም ተቀብረናል,
ታድያ እዚህ መኖር ምንያደርግልናል,
በቃ እኛን እርሱን መሄድ ይሻለናል.
ይህን እያሰቡ እየተሸነፉ,
ሶሻል ሚዲያ ላይ ሞትን እየፃፉ,
ስንቶች ተስፋ ቆርጠው ትተውን አለፉ.
መልካምነት ከስሞ ክፋት ቢጎመራ,
ሂወት ፅልመት ከቧት ለመኖር ቢያስፈራ,
አንሰንፍም ለማየት የብርሀንን ጮራ.
ነገ ጥሩ ሆኖ እስክናየው ፈክቶ,
ደስታ እስኪሞላን ህልማችን ተሳክቶ,
ተስፋችን በተግባር እስከሚታይ ጎልቶ,
እንታገላለን አንቆምም ከቶ.
መራመድ ቢያቅተን እየተንፏቀቅን,
አንድ እየተነሳን አንድ እየወደቅን,
በትናንት ስህተት …
👏2👍1😱1🙏1
Signed Chala Mekonnin
18 Apr 2026, 14:31 UTC240 views2 reactionsread 7 August 2026 ### እንኳን ሆነ!
እንኳን! ያድያቢሎስ በእባብ ገላ ተሰውሮ ባይገለጥ፤
እፀበለሥ እንድትበላ ለሄዋን ቃል ፍቃድ ባይሠጥ።
ከገነት ቤት ባይባረር አዳም ሀዘን አኮራምቶት፤
ባይፀፀት ባያነባ መበደሉ እውነት ገብቶት።
የአለሙን ክስ ሊሽር ቃል በስጋ ባይወለድ፤
በቅዱሡ ደም ተፍቆ የሞት መዝገብ ባይቀደድ።
ቀራንዮ ባይታየን እውነት ፍቅር ባይሠቀል፤
ኖረን ነበር የፍቅር ቃል ሣንረዳ ሣናሥተውል።
እንኳን በሉ! በለሥ ቀጥፋ ያኔ ሄዋን ባትበድል፤
የአዳም እንባ ከዳዊት ሥር እመቤቴን ባያበቅል።
ድንግል ማርያም አንቺ ለኛ ባትወለጅ ብትቀሪ፤
አይኖረንም ንፁ ፊደል እናትነት አሥተማሪ።
ሥለዚህ, ለወደድንሽ ለወደድሽን ለተዋብነው በውድ ልጅሽ,
የአዳም ስህተት ሸልሞናል ጥኡም ዜ…
❤2
Signed ሩሀማ የኪዳነምህረት ልጅ
14 Apr 2026, 20:08 UTC225 views3 reactionsread 7 August 2026 File
ይህንን ድንቅ ጥበብ ተጋበዙልን።
ጥበብ ምንጊዜም ትንገስ
ስለቆይታችሁ ክበሩልን።
ለተደራሲያን እያጋራን
https://t.me/chahi_1
❤3
Signed Chala Mekonnin
14 Apr 2026, 19:43 UTC216 views5 reactionsread 7 August 2026 የቴዲ አፍሮ "ሙዚቃ ህይወቴ" የተሰኘው ዘፈን የድምፃዊው የጥበብ ፍልስፍና እና ለሙዚቃ ያለው ጥልቅ ፍቅር በግልጽ የሚታይበት ስራ ነው። ይህ ዘፈን ሙዚቃን እንደ ተራ የመዝናኛ መሣሪያ ሳይሆን፣ እንደ ነፍስ ምግብ እና እንደ ህይወት መመሪያ አድርጎ ያቀርበዋል።
ዘፈኑን በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች መተንተን ይቻላል፦
1. ሙዚቃ እንደ ህልውና (Identity)
ቴዲ በዚህ ዘፈን "ሙዚቃ ህይወቴ" ሲል፣ ሙዚቃ ከእለት ተእለት እንቅስቃሴው ውጪ ሊነጠል የማይችል ማንነቱ መሆኑን ይገልጻል። ለእሱ ሙዚቃ ዝም ብሎ ስራ ሳይሆን፣ የሚተነፍሰው አየር እና የአለምን ሚስጥር የሚያይበት መነፅር መሆኑን ይነግረናል።
2. የመንፈስ እርካታ እና ፈውስ
ግጥሞቹ ሙዚቃ በሰው ልጅ…
❤2👍1👏1🔥1
Signed Chala Mekonnin
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @chahi_1. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.