13 Feb 2025, 04:34 UTC858 views12 reactionsread 7 August 2026 #ትምህርተ_ፀሎት
የስምኦን ጸሎት
የጌታችን የኢየሱስን መወለድ በብዙ ናፍቆትና ጸሎት ይጠባበቁ ከነበሩት ጥቂት የእግዚአብሔር ሰዎች መካከል አንደኛው ስምኦን ነበር። ስለ እርሱ እንዲህ ተብሎአል፦
“በዚያን ጊዜ ጻድቅና ትጉህ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረ ሰው ነበር። ደግሞም የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፤” ሉቃ 2:25-26
ስምዖን የተሰጠውን ተስፋ በጉጉት እየጠበቀ ሲኖር ሳለ አንድ ቀን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ወደ ቤተመቅደስ ገባ። አስቀድሞ የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት ተስፋ የሰጠው መንፈስ ቅዱስ አሁን ደግሞ የተስፋ…
❤8👍4
Signed Bur'yew
10 Nov 2024, 10:25 UTC≈1,030 views18 reactionsread 7 August 2026 #ትምህርተ-ፀሎት
ሳታቋርጡ ፀልዩ(1ኛ ተስ 5:18)
ሳያቋርጡ መጸለይ ያለ አፍታ እያቀጣጠሉ መጸለይ አይደለም፤ ወይም ልክ እንደመተንፈስ የሚሆንም አይደለም ። ሳናቋርጥ እንደምንበላ፣ ሳናቋርጥም እንደምንተኛ፣ እያሰብንበትና ጊዜ እየሰጠነው ሁልጊዜ እናድርገው ማለት ነው። ጸሎት የከበደነን፣ ያስቸገረንና እገዛ የምንፈልግበትን ነገር ሁሉ ወደ እግዚአብሔር በማቅረብ: የምናርፍበትና ለአምላክነቱ እውቅና የምንሰጥበት መንፈሳዊ ልምምድ ነው። ጸሎት ሌሎችን በማሰብ ፍቅራችንን የምንገልጥበትም ነው።
ወደ ቻናላችን ለመቀላቀልና በፀጋ ለመታነፅ ይኼንን የ Telegram ሊንክ ሁለቴ ብቻ ይንኩ👉 @biruk351
❤11👍6😱1
Signed Bur'yew
5 Nov 2024, 13:00 UTC969 views11 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ትምህርተ_ፀሎት
#ጸሎት_አይቋረጥም። ይህ ሲባል ግን ተግዳሮት አይገጥመውም ወይም አያታግልም ማለት አይደለም። አንድን ሰው ብቻ ለማጥቃት አንድ ትልቅ አገር ሕግ አወጣ፤ ጸሎት ለ30 ቀናት ይቋረጥ ተባለ። "ዳንኤልም ዐዋጁ እንደ ወጣ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፤ መስኮቶቹ በኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ባሉበት በሰገነቱ ቀድሞ ያደርግ እንደ ነበረው በቀን ሦስት ጊዜ ተንበርክኮ ጸለየ፤ አምላኩንም አመሰገነ" (ዳን 6፥10)። ለእርሱ ጸሎት ብቻ ሳይሆን ምስጋናም አይቋረጥም። በገሃድ (#በግልጽ) አምላኩን ማነጋገሩን ቀጠለ። #እግዚአብሔር_ከአዋጁ፣ ከዛቻውና ከአንበሳው በላይ እንደ ሆነ ለማመን አልተቸገረም። ስለዚህም የዘወትር መንፈሳዊ ተግባሩን ቀጠለ። የሚያምነውንና …
🥰6❤3👍2
Signed Bur'yew
11 Oct 2024, 04:27 UTC903 views3 reactionsread 7 August 2026 'ጸሎት የታዛዥነት የአኗኗር ዘይቤ አካል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ነገሮች የሌሉን ስለእነርሱ እግዚአብሔርን ስለማንጠይቅ ነው ይላል (ያዕቆብ 4፡2 ተመልከቱ) እና ትላቁ የጸሎት ሚስጥር እርሱ አስቀድሞ ያዘጋጀልንን እንድጠይቀዉ መፈለጉ ነው። . #እግዚአብሔር_ሉዓላዊ_እና_የሚፈልገውን #ማንኛውንም_ነገር_በየትኛውም_ቦታ፣ #በማንኛውም_ጊዜ_በፈለገው_መንገድ #ማድረግ_የሚችል_እና_የማንንም_ፍቃድ #የማይፈልገው_እንድንጠይቀው_ይፈልጋል።
#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ ጅማ
👉👉 @biruk351
👏2👍1
Signed Bur'yew
9 Sept 2024, 19:50 UTC≈1,230 views7 reactionsread 7 August 2026 #ትምህርተ_ፀሎት
ጸሎት ጽናት ይጠይቃል፤ የሚጸልዩ የሚቀጥሉ እንጂ የሚያቋርጡ መሆን የለባቸውም። "ሳይታክቱ ሁልጊዜ መጸለይ እንዲገባቸው" ጌታ ሲያስተምር የክፉውን ዳኛ ምሳሌ ነገራቸው። እርሱ መበለቲቱ ስላሰለቸችው ብቻ ፈረደላት፤ ለራሱ አስቦ ፍትሕን 'ፈጸመ'። ጌታም ስለ እንከን አልባው የሁሉ ዳኛ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? : ከመጠን በላይስ ችላ ይላቸዋልን?" (ሉቃ 18፥7)። ነገር በከፋበት ጊዜ የፍትሕ ጩኸት አብዝቶ ይሰማል። ጩኸትን ማሻሻል ግን መፍትሔ ያመጣል፤ እግዚአብሔርን ታምኖና አምኖ መጮኽ!: በፀሎት የፀኑ በእምነታቸው የተመሠከረላቸው አባቶች አሉን ፤ ከእነርሱ በፀሎት መፅናትና አ…
❤7
Signed Bur'yew
31 Aug 2024, 14:54 UTC≈1,030 views9 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ትምህርተ_ፀሎት
ጸሎት የመንፈሳዊ ኅልውና መገለጫ ነው፤ ስለዚህ የሚቋረጥ አይደለም። መጸለይ ያቋረጡ ወይም የተዉ ሰዎችም መንፈሳዊ ጤንነታቸው ስለ ተጓደለ አፋጣኝ 'ሕክምና' ያስፈልጋቸዋል። ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው የመጀመሪያ መልእክቱ ላይ "ሳታቋርጡ ጸልዩ" ብሎ አሳሰባቸው (5፥17)። ይህንን ያለው ሐዋርያ የትም ቦታ ቢሆን—እስር ቤትም ጭምር—"ሌሊትና ቀን" ይጸልይ ነበር። ለእርሱ የሁኔታ መክፋት ፣ ተስፋ ማጣት ወይም 'ኵርፊያ' ሆኖ ጸሎት ማቋረጫ አይደለም፤ ይልቁንም አብዝቶ የሚጸልይበት አጋጣሚ እንጂ። ሳያቋርጡ ለመጸለይም ሁልጊዜ በጌታ መታመን ግድ ነው። እርሱን ለመታመን ደግሞ እርሱን መጠጋጋት አማራጭ የለውም። አንዱና ዋነኛው መጠጋጊያም ጸሎት…
❤5👍2🙏2
Signed Bur'yew
30 Aug 2024, 14:13 UTC≈2,110 views7 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ትምህርተ_ፀሎት
ጸሎት ቀላል ቢመስልም ቀላል ግን አይደለም፤ ምክንያቱም ስጋዊ አእምሮ ይሄን ለማድረግ መሰልጠንና መላመድ አለበት ። ብዙ ሐሳብ ማሰብ፣ ማውጣትና ማውረድ የሁልጊዜ ተግባር ነው፤ ከሌሎች—ከሚቀራረቡን ጋራ—ማውራት ባለማቋረጥ የምናደርገው ብቻ ሳይሆን የምንናፍቀውም ነው። ከአምላክ ጋራ ማውራት ሲሆን ግን 'ዳገት' ይሆንብናል—ወደ ሰማይ ማውራት ወደ ሰማይ እንደ መውጣት ይሆንብናል። ስጋ በመንፈስ ላይ ፥ መንፈስም በስጋ ላይ ቢቀወምም : የመንፈስ ቅዱስ በእኛ መኖር የመንፈሳዊ አቅማችን ትልቅ ምስጢር ነው ። አቅም ማጣትም አቅም በመቀበል ይተካል። መንፈስ ቅዱስ የጸሎት አጋዣችን የሆነው ለዚህ ነው፤ "በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመና፣ በማንኛውም ሁኔታ…
❤4👍2👏1
Signed Bur'yew
26 Aug 2024, 11:04 UTC≈1,480 views11 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ትምሕርተ_ፀሎት
#ጸሎት_ይሰማል_ይታያልም፣ "እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል ልመናቸውንም አይንቅም" (መዝ 102፥17) እንደ ተባለ ከመለመናችን በፊት በልባችን ያለውን ማወቁ ማየቱ ነው። ጌታ በርግጥ ያያል፤ ላሳሰበን (#ላብሰለሰለን) ነገር ምላሽ ይሰጣል። በርሱ እየታዩ መደመጥ፣ እየተደመጡም መታየት ትልቅ ዕድል ነው። ትኩረት እንደ ተሰጣቸው የሚያውቁም አምላካቸውን ሁልጊዜ #በጸሎት_ያነጋግራሉ።
ስንፀልይ በራስ መተማመናችን ይጨምራል ፣ ስንፀልይ የመደመጥ #ቃል-ኪዳናችን ድፍረትን ይሰጠናል፣ ስንፀልይ በውስጥ ሰውነታችን ጠንካሮች እንሆናለን የውጩንንም ነገር እንደ ቀሊል እናያለን!
#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ
#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን…
👏8👍3
Signed Bur'yew
24 Aug 2024, 04:11 UTC≈1,780 views6 reactionsread 7 August 2026 ትምህርተ-ፀሎት
“ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን ኀይሉን እንድታውቁ እጸልያለሁ።” ኤፌ 1፥19
#ሃይል 🔥🔥🔥🔥🔥
👉ፍርሃትን ወደ ድፍረት ይቀይራል፣
👉በሽታን ወደ ጤና ይቀይራል፣
👉ደካማን ብርቱ ያደርጋል፣
👉ባሪያን ነጻ ያደርጋል፣
👉ፈሪን ደፋር ያደርጋል፣
👉የማይቻለውን ያስችላል፣
👉ጥላቻን ወደ ፍቅር ያለውጣል፣
👉ሽንፈትን ወደ ድል ይቀይራል፣
👉ድህነትን በብልጽግና ይተካል፣
👉አለማወቅን በእውነት ይሽራል።
🗝ከሁሉ በሚበልጥ አሰራሩ ደግሞ ሃይል ሁኔታው ሳይቀየር የሁኔታውን ውጤት ያጠፋል።
🗝ሃይል በክርስትና ህይወት ውስጥ መሰረታዊ ነገር የሆነው ለዚህ ነው።
ረዘም ላለ ጊዜ በአንዳንድ ሁኔታዎች በመጥፋቴ ምክንያት ተቋርጦ ነበር: አሁን አለው …
🔥3🥰3
Signed Bur'yew
9 Jul 2024, 11:36 UTC≈2,060 views11 reactionsread 7 August 2026 ትምሕርተ-ፀሎት
ማቴዎስ 5:44 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ።
📌 የቀደመችው ቤተክርስቲያን አንዱ ተግባር ጸሎት ነው። እኛም እንደ አማኞች እንድንጸልይ በመልእክቶች ውስጥ ብዙ መመሪያዎችን እናያለን። ማንኛውም አማኝ በጸሎት የዘገየ በአለመታዘዝ ውስጥ እየኖረ ነው እና ለዛውም የአገልግሎትን ስራ ለመስራት እስከምን ድረስ ልንፀልይ ይገባል?!። ስለ ጸሎት ሆን ብለን እናስብ እና ሌሎች አማኞችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ማበረታታት አለብን። ይሁን እንጂ በአለም ላይ የሚጸልዩት ክርስቲያኖች ብቻ እንዳልሆኑ ማወቅ ያስፈልጋል።
📌 በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ሃይማኖቶች ማለት ይቻ…
❤5👏3🔥3
Signed Bur'yew
7 Jul 2024, 14:04 UTC≈2,330 views9 reactionsread 7 August 2026 ትምህርተ-ፀሎት
📌 ጸሎት በአማኙ ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ መንፈሳዊ ልምምድ ነው*። በጸሎት ሥልጣናችንን በክርስቶስ ያገኘነውን መንፈሳዊ ልዕልና በይበልጥ እንጠቀማለን፣ በጸሎት የአገልግሎትን ሥራ ለመሥራት ድፍረትን እናዳብራለን፣ በጸሎት ስለ ሕይወት እና አገልግሎት መመሪያዎችን እንቀበላለን። ስንጸልይ በመንፈስ እርስ በርስ እንተባበራለን: ቋሚ እና ከልብ ለመነጨ የጸሎት ህይወት ካልተሰጠህ በአገልግሎት ስራ ውስጥ ሊኖርህ የማይችላቸው የተፅዕኖ መጠኖች አሉ!: ኢየሱስ የጸሎት ጊዜያት ነበረው እና ሐዋርያትም የጸሎት ጊዜያት ነበሯቸው።
📌 የመንፈስን ሥራ ለመሥራት ትጋትና ስደትን ለመጋፈጥ መጽናት የሚገኘው በጸሎት ነው። ምክንያቱም በጸሎት በውስጣችን ባለው…
❤7👏1🥰1
Signed Bur'yew
5 Jul 2024, 05:53 UTC≈1,830 views10 reactionsread 7 August 2026 ትምህርተ-ፀሎት
✍️✍️“የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች"።”(ያዕቆብ 5፥16)
በእያንዳንዱ አማኙ ውስጥ ገደብ የለሽ ኃያል አለ። ይህ በአማኙ ላይ የተቀመጠው ሃይል መታየትና መገለጥ አለበት። ምንም እንኳን ይህ እጅግ ታላቅ ኃይል በውስጣችን ቢኖረንም፣ ካልተገለጠ ግን ኃይል እንደሌለን እንመስላለን። አንዳንድ አማኞች አቅመ ቢስ እንደሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ ኃያላን እንደሆኑ እንዲያስቡ የሚያደርጋቸው በእኛ ውስጥ ያለው የኃይሉ መግለጫ መንገዶች ላይ ባለን እንቅስቃሴ ነው።
✍️የመጀመሪያው ደረጃ በእኛ ውስጥ ያለውን ኃይል በቅዱሳት መጻሕፍት በመገለጥ እውቀት ማግኘት አለብን። ይህ የመገለጥ እውቀት በግሪክ “#ኤፒግኖሲስ” ይባላል። በውስጣችን …
❤6🔥3👏1
Signed Bur'yew
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @biruk351. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.