29 Jul 2026, 07:55 UTC101 views13 reactionsread 8 August 2026 Photo
ስሙማ ቀሪ ገፅ እየተፃፈ ነው።ከዚህ በፊት ብዙ ጀምሬ ያቋረጥኳቸው ፅሁፎች ሰላሉ እንድበረታ ታግዙኛላችሁ።
ይህን ልብ ወለድ ለመፃፍ ካለኝ ጠባብ ሰዕት ላይ በረጅሙ እየተሻማው ለእናንተ አሪፍ አድርጌ ለመፃፍ እሞክራለሁ።ታዲያ እናንተም ቤቱን ሞቅ ሞቅ እያደረጋችሁት ጠብቁኝ።ለምትወዱት ሁሉ እየላካችሁ ብዙዙ ሁኑልኝ።ቤታችንን አስተዋውቁ።ሰነፍ ነኝ እና ከዘገየው ጠይቁኝ።
እናንተ የአንባቢን ቁጥር ስትጨምሩ እኔ ደግሞ ሰፊውን ግዜ እየሰረቅኩ በቅርቡ ታነቡት ዘንድ እፅፋለሁ።አላህ ካለ የተጀመረ ነገር ያልቃል።እስቲቲ ብዙዙ አንባቢ ይኑረኝ እና ደስ ይበለኝ 🫠
@bintsumi
❤13
Signed ሱሚ-ማማይ
27 Jul 2026, 18:23 UTC77 views12 reactionsread 8 August 2026 ጥያቄ አለኝ ማ
እኔ ልብወለድ ብፅፍ ታነቡልኛላችሁ? ብዙ ግዜ ጀምሬ በራሴ ስንፍና መቀጠል አቅቶኝ አቁሚያለሁ።ልክ እንደሁሌው የፉአድ ሙና ልብወለድ ሳነብ <ፃፊ ፃፊ>ይለኛል።በቅርቡ የፉአድ ሙና ማለፊያን አንብባችሁታል ብዬ አስባለሁ።ካላነበባችሁ ተጣላን።ብቻ እናንተ ካበረታታችሁኝ በድፍረትም ቢሆን ለመፃፍ አስቢያለሁ።እ ልፃፍ?🤔
@bintsumeya
👍10❤2
Signed ሱሚ-ማማይ
24 Jul 2026, 12:50 UTC80 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
(ሱሚ ማማይ)
ጠፍቶኛል ቃል
ውብ አንተን ማወደስ
በቂም አልሆነልኝ
ድርሻህን ለመድረስ
ግና እድሜ አለኝ
ግዜ አለኝ
የምከፍለው ከአንተ
ተፍሲርህ እስኪለይ
መች ልቤ ታከተ!
@bintsumi
❤2
Signed ሱሚ-ማማይ
22 Jul 2026, 12:26 UTC74 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
[ሱሚ ማማይ]
ይረዝምብኝ እና..
የመምጫህ ቀን ዕለት
እንቅልፍ በወሰደኝ እላለሁ
አንተን እስካይበት
ልክ እንደ ታሪክ
በጠረንህ ልንቃ
ከአንተ ጋ አለኝ
የመኖር ፈረቃ።
@bintsumi
🥰2
Signed ሱሚ-ማማይ
14 Jul 2026, 13:15 UTC87 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
ስካር አላት አለም
(ሱሚ ማማይ)
የንዋይ ሞገድ
በገላ ሲነገድ
የመኖር ቀመር
ሲቀላ በወንበር
የመውደድ ደረጃ
ማንነት ሲቀዳ
የክብር መብረጃ
ለቁስ ሲመነዳ
መንገድ ባሉት ጉዞ
ዳና ጠፍቶ ፈዞ
ወዲህ ወዲያ ሲል
መረኑን ሲቀጥል
ዱንያ ገብታ ልቡ
ሰው ታጠፈ ከደንቡ
አካሄድ ሲመዘን
በምድር መዕዘን
ስካር አላት አለም
ከነፍስ የሚቃረን
@bintsumi
❤3👏1
Signed ሱሚ-ማማይ
6 Jul 2026, 14:40 UTC99 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
እኛ ዘንድ ውድ ነሽ
[ሱሚ ማማይ]
እቴዋ
የነቢ አደራ
የአላህ ውብ አዝመራ
የዱንያ ውብ ገላ
የተከበርሽ
በህጉ ከለላ
ዘመን አደባብሽ
አንቺን እየሰራ
ውብ መልክሽ አደፈ
ቆመሽ በሰው ተራ
ሸበተ ታሪክሽ
እድሜ እየተቀማ
በሰው ኮቴ ደጅሽ
ጨቅይቶ ከደማ
ነይ
ወደ እውነትሽ
ነይ
ወደ እምነትሽ
በገላሽ የፈላው
የአለም ህግ አይበጅሽ
ሴትነት ተገልጦ
ዘውድ ከሚነገድ
በአላህ ህግ ክበሪ
ውድ ነሽ እኛ ዘንድ
እጅ እጅ አለ ልብሽ?
ሁሉም ሲያኳክልሽ
አንቺን የሚያፀና
እምነት እንዲኖርሽ
ነይ..ወደ አምላክሽ
ቃል አለው በስምሽ
ምሳሌ አለው ለፅናትሽ
ህግ አለው ለክብረትሽ
ቀለም አለው ለውበትሽ
ምርዕፍ አለው ለኩራትሽ
ነብይ አለው ለመልዕክትሽ
ስሙ ማ
ሴትን የወለደ
የተንከባከበ
በ…
❤3
Signed ሱሚ-ማማይ
24 Jun 2026, 18:59 UTC124 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
(ሱሚ ማማይ)
አላውቅም ነበር
የእግርህን እኩል
አላውቅም ነበር
የጉዞህን በኩል
ተለያየን ሳንል
ተለየ መንገዱ
ሳላውቀው ጥግህን
ራቀብኝ ልማዱ
ወዴት?
ከየት?
ምን ብዬ ልራመድ
አንተን አላስጠጋኝ
የትዝታ ገመድ
ዝም ብዬ
ሮጣለሁ
ዝም ብዬ
ሄዳለሁ
አልመዝንም ወዜን
አንተን መፈለግ ነው
የሚነግረኝ ጥጌን
ልቅረብህ?
ልራቅህ?
የለኝም መንገድህ
ወዴት?ለሚለኝ ሰው
አንተ ነው ማሳየው
መልክህ ተቀይሯል?
ወይ ምድር ርቀሀል?
የለኝም ጠቋሚ
አልተገኘም ሰሚ
ከእኔ እየሸሸህ ወይ
እኔን ፈልገህ
አላውቀውም ብቻ
መቼ ትገኛለህ?
አካልህ አልታየም
ሞትህም አልታየም
ብቻ..ስፈልግህ
ከቀደመህ ሞቴ
አደራ ስትሰማ
ዘይረኝ ከቤቴ
ቃል የሰጠሁት
አምላኬ ከሰማኝ
ምድር ካልበቃችን
ጀነት እንገ…
👏3❤1
Signed ሱሚ-ማማይ
20 Jun 2026, 19:13 UTC130 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
(ሱሚ ማማይ)
የሚጋባ
ጉልበት ይዞ
የሚናዘር
ልቡን አዞ
አይታይም
ለሰው አንሶ
ከሸክሙ፣ልቡ ብሶ
ከፈገግታው የሚሰነቅ፣
ከስህተቱ የሚታረቅ፣
ተስፋ አለው
በመኖሩ የሚያኮራ፣
በመጥፋቱ የሚያስፈራ፣
ድርሻ አለው።
ዳናው ሮጦ
መልኩ ፈጦ
ግርማው አብጦ
ምግባር መርጦ
ከሰው መሀል ተለይቶ
የሰው ሞገስ ተቀብቶ
ያን ሰው ፣ምን ኳለው
ከተባለ?
ጓዳ አለው ለስሜቱ
ትግል አለው ለብሶቱ
ሚስጥር አለው ከአምላኩ
አይሰለችም በታሪኩ
በስግደቱ ወድቋል ሸክሙ
ሚስባህ ሲዞር ረጥቧል ስሙ
በሰደቃ ሞልቷል ሲሩ
በዚያራ ድኗል ግብሩ
ለሰው ሲሆን አዛኝ ልኩ
በሀጃው ላይ ኖረ አምላኩ
የደበቀው ግልፅ አላቀው
የጓደው ጠረን በሳሎኑ አነገሰው
ሰደቃ ነው የእሱ ርስቱ
ያ ሰው ፣
ዋዜማ ነው ሁሌ …
❤3
Signed ሱሚ-ማማይ
16 Jun 2026, 18:11 UTC108 viewsread 8 August 2026 በመፅሀፍት ዙርያ እንድንሰበሰብ የተከፈተ Branch 2 channel 😀 ተቀላቀሉ ደሞም መርቁልኝ እ? 💞
Signed ሱሚ-ማማይ
16 Jun 2026, 18:09 UTC110 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @Beytulhikmaa
ይሄ ቻናል ዝክረ በይቱል ሂክማ ሲሆን።ለእኔ ደግሞ የህልሜ ደረጃ ነው።እዚህ ቻናል ላይ ሰለመፅሀፎቶች ይወሳል።የማውቀው ኢምንት ቢሆንም ለእናንተ ለማካፈል በምሄድበት ጉዞ እውቀቴ እንዲጨምር፣ህልሜ እንዲሰምር ያግዘኛል እና በጋራ በሀሳብ እንደምንተጋገዝ አምናለሁ።ውዶቼ እናንብብ አይደል? 💞
https://t.me/Beytulhikmaa
❤2
Signed ሱሚ-ማማይ
15 Jun 2026, 20:56 UTC114 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
ወፊቷ ብረሪ
(ሱሚ ማማይ)
ተነሳች ከደጇ
ቆጠረች መውረጃ
አዘቦት ደግሳ
ቀለመች መልመጃ
ለመኖር ከእራሷ
መኖሯ እንዲወሳ
የህልሟን ጋዜጣ
ገለጠች መላልሳ፣
ፃፈች የእሷን ዜና
ታምና ለመረጃ
ነገዋን ስትስል
ያለ መጋረጃ
በነገ መድረኳ
አቋቋም ልትለካ
ሳትጠራ ወታ
ስትል ሰበር ሰካ
ለሚያያት ቢያስቅም
ሀሜት ብትሰንቅም
ህልሟን ስታባርር
ከመሬት ስታብር
አንድ ቀን አላት
ከፍ ብላ ልትበርር።
@bintsumi
🥰5👍1
Signed ሱሚ-ማማይ
11 Jun 2026, 17:43 UTC102 views2 reactionsread 8 August 2026 አንቺዋ 💤
[ሱሚ ማማይ]
መዋብ፣ማማር ፣መዘነት የእለት ልምዷ ነው።ለቅሶ ስትሄድ እራሱ ለእሷ ባይመስላትም በሰዋች አይን ሰርግ የተጠራች ትመስላለች።ምክኒያቱም ደህና እንዳልሆነች? እንደተጨነቀች ማስረዳት ደክሟታል? ችላ ብታስረዳ ፈራጅ እንጂ ጠበቃ አታገኝም።ለገለባ ሰዋች ማታለያ አላት።እንደዚህ አይነት ሰዋች ውጫዊ ገፅታ ብቻ ነው ጣራቸው።በውጫዊ ገፅ-ንባብ ለመፍረድ ሲቸኩሉ መውደቅን ሁላ አይፈሩም።ታዲያ ደህንነቷን ቀርቦ ላልተመራመረ፣ለመረዳት ፈቅዶ መጠየቅ ላልጀመረ ሰው ማብራራት ከንቱ ልፋት ሲሆን ማስመሰል ደሞ ማምለጫ ዘዴ ነው።ግን ህልሟን ስታስብ መንቃት ባለመቻሏ ለይ ሀዘን አላት።ነገ ያለችው ስትደርስበት ሌላ ነገ እየሆነ ተስፋዋ ተሸርሽሮ በእድል ማመን …
❤2
Signed ሱሚ-ማማይ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @bintsumi. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.