16 Jul 2026, 19:49 UTC264 viewsread 7 August 2026 Photo
ቃሉን በቃል
261 የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥሮች በሦስት ታዳጊ ወጣቶች በቃል የሚቀርብበት ልዩ ዝግጅት
ሁለት የትንቢት መጽሐፍት: ናሆምና ሐጌ በድምሩ አምስት ምዕራፎች
የመጽሐፍ ቅዱስ ረጅሙ ክፍል: መዝሙር 119 ሙሉውን
በድምሩ 261 ቁጥሮች በሦስት ታዳጊ ወጣቶች በቃል ይቀርባሉ
በዚህ ድንቅ ዝግጅት ላይ እንዲገኙና የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል። ሌሎችንም ይጋብዙ
ቀን፦ ሐምሌ 18፣ 2018 ዓም.
ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ
አድራሻ፦ ወመዘክር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ
Signed Biniyam Abura
21 Jul 2025, 15:26 UTC≈1,320 viewsread 7 August 2026 Photo
ዐዲስ መጽሐፍ!
ከአንገት በላይ ሕክምና ሙያው የምናውቀው ዶ/ር ዓለማየሁ እሸት .. የሕክምና ትምህርት ቤት ሕይወት በተለይም በጎንደር ሕክምናና ጤና ሳይንስ ግቢ መማር ምን እንደሚመስል ሊያሳየን፤ በዛ ወከባ ውስጥ እያለፉ ራስን ፈልጎ ማግኘት፣ በፍለጋ ውስጥ ለብዙዎች መትረፍ መቻልን ከግቢ የፍቅር ሕይወት ጋር አሠናስሎ በልቦለድ ደግሞ ብቅ ብሏል።
በዩኒቨርስቲ ሕይወት ላለፉ፣ ዩኒቨርስቲ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ለሚፈልጉ፣ ዘላለማዊ ደስታቸው በጊዜያዊ ደስታ ለተሸፈነባቸው፣ በጎነትን ለናፈቁ የተዘጋጀ ገጸ በረከት እነሆ!
የመፅሀፍ ምረቃው
ቅዳሜ 10 ሰዓት
አራት ኪሎ፣
ኢክላስ ሕንጻ
በዋልያ አሳታሚ መመረቂያ አዳራሽ
Signed Biniyam Abura
18 Feb 2025, 03:31 UTC≈1,870 viewsread 7 August 2026 Photo
Where are you readers🧐🧐🧐?
Give your book the perfect place to rest 😴😴😴
Price 750
Contact: 0909789313
Telegram: @Kirubel11
Signed Biniyam Abura
12 Feb 2025, 14:24 UTC≈1,780 viewsread 7 August 2026 Photo
✒️ መጽሐፍ የማስፈረም እና የትውውቅ መርሐግብር
📅 ቅዳሜ የካቲት 8
⌚ ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 5:30 ድረስ
🏠 በዋልያ መጻሕፍት መደብር - ኢክላስ ሕንጻ
👐 Open mic session አለን።
"ዓይነ ርግብ"ን በቅድመ ክፍያ የገዛችሁ ወዳጆቻችን፣ በአካል በመገኘት የተፈረመበትን መጽሐፍ እንድትወስዱ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።
Signed Biniyam Abura
18 Nov 2024, 14:18 UTC≈1,900 viewsread 7 August 2026 Photo
በአንድ ዓይነት ሙያ ውስጥ በሕይወትህ እንዴት ገብተህበት እንደምትሣተፍ አታውቀውም፡፡ ዜና ዘግቤ አላውቅም:: ጋዜጣ ላይ በመጻፍ ሃሳቤን እንድዘራ በበዓሉ ግርማ ታጨሁ:: በኋላ ነው “እ! ለካስ ጀምሬዋለሁ የምትለው፡፡ በአንድ ወቅት በትምህርት ሚኒስቴር በስኮላርሺፕ ክፍል እየሰራሁ እያለ አንዱን ቀን በአሉ ግርማ “እዚህ ዝም ብለህ ከቢሮክራሲ ሥራ ጋር ጊዜህን አታባክን፡፡ አሁን በስኮላርሺፕ ለምትሠራው ሥራ አገሪቱ በርካታ ሰዎች አሉዋት፡፡ ለአንተ ተፈጥሮ የእኛ ሙያ ነው የሚስማማህ” አለኝ፡፡
“እሺ እውነትክን ነው” አልኩና መልቀቂያ እንዲሰጠኝ ላለሁበት ትምህርት ሚኒስቴር ማመልከቻዬን ጻፍኩ፡፡ እዚህ ላይ
አንድ Interesting ነገር ልጨምርልህ፡፡ የትምህር…
Signed Biniyam Abura
17 Nov 2024, 05:33 UTC≈1,340 viewsread 7 August 2026 Photo
የገቢ ንግድን ለመቀነስና የወጪ-ንግድን ለማበረታታት መወሰድ ያለባቸው ፖሊሲዎች የዋጋ ንረትን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ በአጠቃላይ የገቢ ዕቃ ከቀነሰ ወይም የወጪ ዕቃ ከጨመረ በተያያዥ ወይ ገቢ ይጨምራል ወይ ፍጀታ ይቀንሳል፤ ይሀም አጠቃላዩ የመዋዕለ-ንዋይ መጠን አይቀንስም ብለን ታሳቢ ካደረግን ነው:: ነገር ግን የገቢ ዕቃዎች ውድ በሆኑ የአገር ውስጥ ዕቃዎች ስለሚተኩና አዲሱ የወጪ ንግድም በድጎማ የሚመረት በመሆኑ የሚመረተው ምርት ዋጋው ከሚያፈራው ገቢ በታች ስለሆነ፣ የዋጋ ንረቱ ጫና ከገቢ-ዕቃ ቅነሳው በላይ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ደግሞ በስተመጨረሻ በበጀት ጭማሪ መልክ (በድጎማና የወጪ-ንግድ ማበረታቻ መልክ) የመንግስት በጀት ላይ ይታያል፡፡
ከውጪ የሚገቡትን…
Signed Biniyam Abura
14 Nov 2024, 15:08 UTC≈1,200 viewsread 7 August 2026 Photo
እኮኢዝም፡ በብዙ የሃሳብ ልውውጦችና ጉሥዐተልብ (discourse) ጋጋታዎች ላይ “እኮ የተባለ ቃል ደጋግሜ እሰማለሁ:: የዚህ ቃል ትርጉሙ ለብቻው ምን እንደሆነ ባላውቅም በጆሮዬ ሲገባ ግን አፌን ዳባ ዳባ ይለኛል፡፡ ያልወለዱት ልጅ “አባባ' ሲልዎ ወይም “እማማ' ሲልዎ ዐይነት:: አይጥመኝም ማለቴ ነው:: እስኪሰለቸኝ ሰምቼው ምንም ትርፍ ትርጉም ሊያመጣ ስላልቻለ፣ ወይም፣ ብዙ ጊዜ የምሰማው ረቂቅ የመሰለ ውይይት ላይ የሆነ መደዴ ሃሳብ የደካማነት ጠባሳውን ሊጋርድ እንደ ካባ የሚለብሰው ቃል ስለሆነ ይሆናል፡፡ በ “እኮ” የታጀቡ አንዳንድ ሂሳዊ ስልቶች እውነታን እናስጨብጣለን ብለው ይነቃነቁና ሳይሳካላቸው በሄዱበት ወጥተው ይቀራሉ፣ ተመልሰው ከመጡም ፈንጠዝያ …
Signed Biniyam Abura
14 Oct 2024, 14:41 UTC≈1,100 viewsread 7 August 2026 የተስፋዬ ቤት - ከማዕበል ማዶ
ከቢኒያም አቡራ
ቅይጥ ወይስ የተስፋዬ ቤት
የጋሽ ተስፋዬ ማሞ “ከማዕበል ማዶ” የተሰኘው መጽሐፍ፥ በስፍን ቅንብብ ለመታጠር ያልፈቀደ “አመጸኛ ጅረት” ነው። አሃዱ ብለን፥ "የአንድ ዕብድ ቀን ውሎ" ጋር ስንፋጠጥ፥ “ይሄ ነገር በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ግለ ሕይወት ታሪክ (auto-fiction) ነው እንዴ?” ያሰኘናል።
ጥቂት ፈቀቅ እንዳልን ግን ጥንቅቅ ያለ የግለ ሕይወት ታሪክ (autobiography) ቅርጽ ይመጣል። በራሱ ላይ ትኩረት ከመስጠቱ እና በራሱ ብዕር ከመተረኩ ባሻገር፥ በየዘመናቱ የደረሰበትን አስተሳሰብን እንደ ብር ጻሕል ዘርግቶ፥ ሥነ-ልቦናዊና ፍልስፍናዊ ቀለማትን እንደ ወርቅ እንኮይ ያቀርባቸዋልና፥ “…
Signed Biniyam Abura
14 Oct 2024, 14:41 UTC≈1,380 viewsread 7 August 2026 ሁለተኛ፡-
መካከለኛው የፊልም ዘመን በኢትዮጵያ እና የተከታታይ ድራማ አጀማመር በኢትዮጵያ ላይ የነበረ የአሠራር መንገድ፣ ተግዳሮት እና ዕድሎች ማጥናት ለሚሻ ሰው ትልቅ ፋይዳን የሚሰጥ መጽሐፍ ነው። ስለ መንትያ፥ የንዋይ ሰለቦች፥ ትዝታ፥ ፊርማ፥ ምርጫ፥ ይቅርታ፥ አጋጣሚ፥ መላ ... የተሰኙ ሥራዎቹን ከቅድመ-ቀረጻ እስከ ድኅረ-ቀረጻ የነበረውን በማተቱ በኩል የኢትዮጵያ የፊልም፣ የድራማ ታሪኮችን ለሚሰንድ የጥናት ባለሙያ አንዱ ዋቢ የሚሆን ቅምጥ ጽሑፍ ማዘጋጀቱ ትልቅ አበርክቶት ነው። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ለወደፊቱ ታሪኩን ሲሰንድ ኹነኛ ማጣቀሻ የሚኾን መጽሐፍም ነው።
ሦስተኛ፡-
የጋሽ ተስፋዬ የማስታወቂያ ሥራ አጀማመሩ፣ አካሄዱ እና ዕድ…
Signed Biniyam Abura
14 Oct 2024, 14:41 UTC≈1,080 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Biniyam Abura
2 Oct 2024, 14:01 UTC≈1,590 viewsread 7 August 2026 Photo
አንድ ወደ ፍቅር ጉዞ መጽሐፍን በ500 ብር በመግዛት የሊዱን ሕይወት እንታደግ 🙏
ተማሪ ሊዲያ ሥዩም፣ በውስጠኛው የአእምሮዋ ክፍል ውስጥ የደም ሥር መወሳሰብ በፈጠረው መድማት ሳቢያ እንደ ስትሮክ እየሆነባት ትገኛለች። ለሕክምናም ከ2 ሚልየን ብር በላይ ያስፈልጋታል። እኔ የአቅሜን 50 መጻሕፍትን በ500 ብር አበርክቻለሁ። ከታች ባስቀመጥኩላችሁ የቤተሰቦቿ አካውንት 500 ብር በማስገባት ከቢኒያም አቡራ ዘንድ 1 መጽሐፍ ይውሰዱ።
እባካችሁ 🙏🙏🙏
ንግድ ባንክ - 1000027428162 - ሥዩም ዘውዴ - (አባቷ)
አዋሽ ባንክ - 01336511809500 - አቤኔዘር ሥዩም (ወንድም )
አቢሲኒያ ባንክ - 44516721- አቤኔዘር ሥዩም (ወንድም )
ስልክ:…
Signed Biniyam Abura
25 Sept 2024, 16:35 UTC≈1,320 viewsread 7 August 2026 Photo
የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት ጎበዝ ተማሪ የነበረችው ሊዲያ ሥዩም፣ ተመርቃ ለቤተሰቦቿ መከታ የመሆን ሕልሟ ላይ brainsteam cavernoma የተሰኘ የጭንቅላት ሕመም ጋሬጣ ሆኖባት፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ትገኛለች።
ይህች ምስኪን ልጅ በውስጠኛው የአእምሮ ክፍል ውስጥ የደም ሥር መወሳሰብ በፈጠረው መድማት ሳቢያ እንደ ስትሮክ እየሆነባት ትገኛለች።
ሕመሙ በሀገር ውስጥ ሕክምና ሊገታ ስላልተቻለ በሀገረ ሕንድ ሄዳ እንድትታከም የጥቁር አንበሳ ቦርድ ወስኗል። ለአጠቃላይ ወጪም እስከ ሁለት ነጥብ ሦስት ሚልየን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን በጸሎታችሁ እንድታስቡ እንዲሁም ከታች በተጠቀሰው አካውንት የአቅማችሁን በማበርከት ከጎናችን እንድትሆኑ ሲሉ ቤተሰቦቿ…
Signed Biniyam Abura
Showing the 12 most recent of 12 posts we hold for @binibook. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.