12 Jul 2026, 09:46 UTC≈1,150 views21 reactionsread 18 September 2026 «የተሸፈነው ቀዳዳ»
አንድ ትልቅ መርከብ በባሕር ላይ እየተጓዘች ነበር።
አንዳንዶች ወደ መርከቧ ውኃ እየገባ መሆኑን አዩ።
"እንጠግነው፤ ካልሆነ ሁላችንም እንሰምጣለን።" አሉ።
ሌሎች ግን እንዲህ አሉ፦
"መርከባችንን መተቸት አይገባም፤ ችግር የለም።"
እየቆዩ ውኃው ጨመረ፤ መርከቧም እየከበደች ሄደች።
በመጨረሻም ሁሉም አንድ እውነት ተረዱ፤
መርከብን መውደድ ማለት ቀዳዳዋን መደበቅ ሳይሆን፣ መጠገን ነው።
ምክር፦
ሀገርን መውደድ እውነትን መፍራት አይደለም፤ ችግርን አውቆ ለመፍትሔ መሥራት ነው።
✍️ በአንተነህ ፈጠነ
❤20👎1
Signed єskindir
3 Jul 2026, 20:09 UTC≈1,480 views45 reactionsread 18 September 2026 ካነበብኩት እና የወደድኩት ታሪክ ነው ተጋበዙልኝ
💫💫💫💫
.............የጭንቅላት ጨዋታ...........
የሰው ልጅ እንዴት እንደሚያስብ ስታቅ ሰውን ማታለል በጣም ቀላል ነው ተከታዩን ታሪክ ጋበዝኳቹ...
የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ወሳኝ ትምርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ፉጨት ሰማ። ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቀቃቸው ፣ሁሉም ዝም አሉ።
ፕሮፊሰሩ ተረጋግቶ ፣ እስክሪቢቶውን ወደ ኪሱ እየከተተ ፣ የዛሬው ሌክቸር እዚ ላይ ያበቃል፣ አለና ፈገግ ብሎ ነገር ግን መጀመሪያ አንድ ታሪክ እነግራችኋለው አላቸው። ሁሉም በጉጉት መጠበቅ ጀመረ
" ትላንት ቤቴ እንቅልፍ ስላስቸገረኝ ፣ዝም ብዬ ተነስቼ ነዳጅ ሞልቼ በዛውም ልናፈስ …
😁31❤10👍3👌1
Signed єskindir
30 Jun 2026, 16:15 UTC≈1,480 views12 reactionsread 18 September 2026 የሸክላ ሠሪው እና የሸክላ ውጤቶች
በአንድ ወቅት፣ አንድ ወጣት የሸክላ ስራ የሚማር ተማሪ ነበር። ይህ ተማሪ በጣም የተዋጣለት የሸክላ ሠሪ ለመሆን ቢመኝም፣ በየቀኑ የሚሰራቸው የሸክላ ስራዎች እየተሰባበሩ ወይም ቅርጻቸውን እየሳቱ ይቸግረው ነበር። በጣም ተስፋ ቆረጠ።
አንድ ቀን አስተማሪውን እንዲህ አለው፦ "መምህር ሆይ፣ ምን ያህል እንደምጥር ታያለህ፤ ነገር ግን ስራዎቼ ሁሉ እየተበላሹብኝ ነው። ጥረቴ ሁሉ ከንቱ ሆኖ እየቀረ ነው። ምናልባት ለዚህ ስራ አልተፈጠርኩም መሰለኝ።"
መምህሩ በፈገግታ ተመለከተውና እንዲህ አለው፦ "በሸክላው ምድጃ ውስጥ ምን እንደሚፈጠር ታውቃለህ?"
ተማሪው መለሰ፦ "አዎ፣ እሳት አለ። እሳቱ እኮ ነው ስራዬን የሚያቃጥለ…
❤10👍2
Signed єskindir
4 Jun 2026, 11:10 UTC≈1,820 views21 reactionsread 18 September 2026 መምህሩ ደቀመዛሙርቱን ሰብስቦ ስለ ፈጣሪ ፍጹም መልካምነትና ጥበብ ያስተምራቸው ነበር።
...
ከተማሪዎቹ መካከል አንዱ ግን ሁልጊዜ በዓለም ላይ የሚታዩትን መከራዎች፣ ድህነትና በሽታዎች እያየ 'ፈጣሪ ፍጹም መልካም ከሆነ ለምን ክፉ ነገር በምድር ላይ ይፈቀዳል?' የሚል ጥያቄ በውስጡ ያመላልስ ነበርና መምህሩን ጠየቀው።
...
መምህሩ የተማሪውን ለመመለስ አንድ ቀን እንዲህ ያለ ተግባራዊ ትምህርት ሰጠው።
...
ለተማሪው አንድ እጅ ሙሉ በጣም ጣፋጭ የሆኑ የሀገር ውስጥ ከረሜላዎችን እና አንድ እጅ ሙሉ ደግሞ ጥሬና ጠንካራ የሆኑ ባቄላዎችን ሰጠው።
...
ከዚያም ''እስኪ መጀመሪያ ከረሜላዎቹን በአንድ ጊዜ በአፍህ ጎርሰህ ዋጣቸው።' አለው። ተማሪውም ከረሜላዎቹን…
❤21
Signed єskindir
1 Jun 2026, 06:37 UTC≈1,800 views20 reactionsread 18 September 2026 በአንድ ወቅት አንድ ተጓዥ በጫካ ውስጥ ብቻውን እየተጓዘ ሳለ፣ ድንገተኛ የጫካ ነብር ያጋጥመዋል። ነብሩ ሊያጠቃው ወደ ተጓዡ ተወረወረ ።
...
ተጓዡም በሕይወቱ ለመተርፍ ባለው ኃይል ሁሉ ወደ ፊት መሮጥ ይጀምራል። ነገር ግን ብዙም ሳይሮጥ፣ መንገዱ አልቆ በአንድ ትልቅ ገደል ጫፍ ላይ ይደርሳል።
...
ወደ ኋላ ቢመለስ ነብር ሊያጠቃው ተዘጋጅቷል፤ ወደ ፊት ቢራመድ ደግሞ ገደሉ በጣም ጥልቅ በመሆኑ መውደቂያው ሞት ነው። ተጓዡ በጣም ተጨነቀ።
....
በዚያ የጭንቀት ቅጽበት፣ በገደሉ ጫፍ ላይ በቀልጣፋ ሁኔታ የበቀለች የአንድ የዱር ወይን ተክል (የወይን ግንድ) አየ። ሌላ አማራጭ ስላልነበረው፣ ግንዱን አጥብቆ በመያዝ ወደ ገደሉ ቁልቁል ተንጠለጠለ።
.…
❤20
Signed єskindir
31 May 2026, 12:32 UTC≈1,490 views22 reactionsread 18 September 2026 በአንድ ወቅት፣ በታላቅ ወንዝ ዳርቻ በሚገኝ ገዳም ውስጥ የሚኖር 'እግዜር አይተወኝም' የሚል ፅኑ እምነት ያለው አንድ መነኩሴ ነበር። መነኩሴው ጸሎት እንጂ ምንም ዓይነት ጥረትና ሥራ አይወድም ነበር።
....
አንድ ቀን በድንገት ከባድ ዝናብ ዘንቦ ወንዙ ሞላ። የጎርፉ ውሃ የገዳሙን ቅጥር ግቢ እያጥለቀለቀው መጣ። የገዳሙ መነኮሳት በሙሉ ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ተራራው መሸሽ ጀመሩ። እርሱን ግን አብሯቸው እንዲሸሽ ሲለምኑት።
...
"እናንተ እምነት የላችሁም! እዚህ ሆኜ እጸልያለሁ፣ እግዜር በባዶዬ አይተወኝም፣ እርሱ ያድነኛል!" እያለ እዚያ ቆየ።
....
ውሃው እየጨመረ መጥቶ መነኩሴው እስከ ወገቡ ድረስ ሰጠመ። በዚህ ጊዜ ፈጣን የረድኤት ታንኳ መጣች።
.…
❤14👍4🥰4
Signed єskindir
16 May 2026, 12:40 UTC≈1,780 views28 reactionsread 18 September 2026 የሁለቱ ጫማ ሻጮች ታሪክ
ከብዙ ዓመታት በፊት አንድ የጫማ አምራች ድርጅት አዳዲስ ገበያዎችን ለመፈለግ ሁለት ሰራተኞቹን ወደ አንድ ራቅ ያለ ደሴት ላከ። ሁለቱም ሰራተኞች ደሴቱ ላይ ደርሰው አካባቢውን መቃኘት ጀመሩ።
የመጀመሪያው ሰራተኛ ደሴቱ ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ በባዶ እግራቸው እንደሚሄዱና ማንም ጫማ እንደማያደርግ አየ። ወዲያውኑ ወደ ድርጅቱ ስልክ ደውሎ እንዲህ አለ፦ "እባካችሁ እዚህ ደሴት ላይ ጫማ እንዳትልኩ! ማንም ሰው ጫማ አያደርግም፣ ስለዚህ አንድም ጫማ መሸጥ አንችልም። በከንቱ አንልፋ።"
ሁለተኛው ሰራተኛ ግን ያየው ነገር በጣም አስደሰተው። እሱም ወዲያውኑ ወደ ድርጅቱ ደውሎ እንዲህ አለ፦ "እባካችሁ በአስቸኳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ጫማዎችን ላኩል…
❤21👍6🥰1
Signed єskindir
13 May 2026, 16:14 UTC≈1,840 views19 reactionsread 18 September 2026 ነፋሱና ፀሐይ
አንድ ቀን ነፋስና ፀሐይ ማን እንደሚበረታ ይከራከሩ ነበር። ነፋስ "እኔ ከጥንካሬዬ የተነሳ ዛፎችን እነቅላለሁ፣ ማዕበል አስነሳለሁ፤ ስለዚህ እኔ በርትቼ እታያለሁ" አለ። ፀሐይም ፈገግ ብላ "ጥንካሬ በጩኸትና በሀይል ብቻ አይደለም" አለችው።
በዚህ መሀል አንድ መንገደኛ ካፖርት ለብሶ በመንገዱ ሲጓዝ አዩ። ሁለቱም ተስማሙ—ከሰውየው ላይ ካፖርቱን ቀድሞ ማስወለቅ የቻለ እሱ አሸናፊ ይሆናል።
ነፋስ መጀመሪያ ተራውን ወሰደ። በሙሉ ኃይሉ ይነፍስ ጀመር። ነፋሱ በበረታ ቁጥር ግን መንገደኛው ቅዝቃዜ ስለተሰማው ካፖርቱን አጥብቆ ወደ ራሱ ያስጠጋው ነበር። ነፋሱ ቢጨነቅ ቢጠበብ የሰውየውን ካፖርት ሊያስወልቀው አልቻለም።
በመጨረሻም ነፋሱ ተስፋ ቆርጦ ተቀመ…
❤8🔥8🙏3
Signed єskindir
11 May 2026, 13:52 UTC≈1,960 views23 reactionsread 18 September 2026 ትልቁ መርከብና ትንሿ መዶሻ
በአንድ ወቅት በአንድ ትልቅ ወደብ ላይ ያለች ግዙፍ መርከብ ሞተሯ ተበላሽቶ ቆመ። የመርከቧ ባለቤቶች ብዙ ባለሙያዎችንና መሃንዲሶችን ቢጠሩም ማንም ሊያስተካክለው አልቻለም። ሞተሩ እጅግ ግዙፍና ውስብስብ ስለነበር ሁሉም ግራ ገባቸው።
በመጨረሻም እድሜያቸው የገፉና በሜካኒክ ስራ ብዙ ዓመታት ያሳለፉ አንድ አዛውንት መጡ። አዛውንቱ መርከቧ ውስጥ ገብተው ከላይ እስከ ታች ሞተሩን በጥንቃቄ መመርመር ጀመሩ። ምንም አልተናገሩም፤ ዝም ብለው ሁሉንም ክፍሎች አዩ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፣ አዛውንቱ ከያዙት ትንሽ ቦርሳ ውስጥ አንዲት ትንሽ መዶሻ አወጡ። ከዚያም በአንዱ የሞተር ክፍል ላይ በቀስታ "ክዋክ" አደረጉት። ወዲያውኑ ግዙፉ ሞተር ድም…
❤15🔥5👍3
Signed єskindir
5 May 2026, 16:08 UTC≈2,050 views16 reactionsread 18 September 2026 የዝምታ ዋጋ
በአንድ ገዳም ውስጥ የሚኖሩ መነኩሴ ነበሩ። እኚህ መነኩሴ በአንድ ነገር ይታወቃሉ፤ ማንም ሰው መጥቶ ጥፋተኛ ነው ብሎ የሚከሳቸውን ሰው ሁሉ "ልክ ነህ" ወይም "እሺ" ብለው ብቻ በዝምታ ያልፋሉ።
አንድ ቀን በዚያ አካባቢ የሚኖር አንድ ሀብታም ሰው ወደ መነኩሴው መጣና በንዴት መጮህ ጀመረ። "አንተ መነኩሴ! ሰዎቹ ሁሉ ቅዱስ ነህ ይሉሃል፤ እኔ ግን አንተ ሌባና ውሸታም እንደሆንክ አውቃለሁ! ገንዘቤን የሰረቅከው አንተ ነህ!" እያለ ስም ማጥፋት ጀመረ።
መነኩሴው ግን እንደለመዱት አይናቸውን ሰበር አድርገው "እሺ" ብቻ አሉት። ሰውየው በዝምታቸው ይበልጥ ተናዶ እየተሳደበ ሄደ። በዚያ የነበሩ ደቀ መዛሙርቱ ግን ተገረሙ። "መምህር ሆይ! ይህ ሰው እንዲ…
❤16
Signed єskindir
5 May 2026, 11:47 UTC≈1,920 views27 reactionsread 18 September 2026 የንስሩና የንጉሡ ታሪክ
ከብዙ ዓመታት በፊት አንድ ንጉሥ ነበረ። ይህ ንጉሥ በጣም የሚወደውና ሁሌም አብሮት የሚሄድ የሰለጠነ ንስር ነበረው። አንድ ቀን ንጉሡ አደን ወጥቶ ሲመለስ በጣም ተጠማ። የሚጠጣው ውሃ ፍለጋ አካባቢውን ሲቃኝ፣ ከአንድ ገደል ላይ ጠብ ጠብ የሚል ጥቂት ውሃ አገኘ።
ንጉሡም ኩባያውን አውጥቶ ያችን ጠብ የምትለውን ውሃ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ ቆይቶ ኩባያዋን ሞላ። ሊጠጣ ወደ አፉ ሲያስጠጋት፣ ያ ንስር ድንገት በረረና ክንፉን አውዝውዞ ውሃውን አፈሰሰው። ንጉሡ ተገረመ፣ ግን እንደገና በትዕግስት ኩባያውን ሞላ። ሁለተኛም ሊጠጣ ሲል፣ ንስሩ በድጋሚ በረረና ውሃውን አፈሰሰው።
ንጉሡ በዚህ ጊዜ በጣም ተቆጣ። "እንዴት ውሃ አስጠማኸኝ!" ብሎ ለሶስተኛ…
❤25👍2
Signed єskindir
18 Mar 2026, 19:13 UTC≈2,780 views46 reactionsread 18 September 2026 በድሮ ዘመን አንድ ንጉስ ከበድ ያለ ድንጋይ ብዙ ሰው በሚመላለስበት እና ወደ ቤተመንግሥቱ በሚያስኬደው መንገድ ላይ አስቀምጦ፤ ማን እንደሚያነሳው ለማየት በድብቅ ቦታ ሆኖ መከታተል ይጀምራል።
አንዳንድ የንጉሡ ባለሟሎች እና ቤተመንግሥቱ አካባቢ የማይጠፉ ሀብታም ነጋዴዎች እንዴት መንገዱ ላይ ድንጋዩ እንደተቀመጠና እንዴት ንጉሱ እንዳላስነሱት ገርሟቸው፤ እያጉረመረሙ እያዪት ሳያነሱት አለፉ።
ከዚያም አንድ ድሀ ገበሬ አትክልት ተሸክሞ ሲያልፍ፤ ድንጋዩ በመንገድ ሲያገኘው የአትክልት ሸክሙ አውርዶ፤ ድንጋዩን ለማንሳት መታገል ይጀምራል። እንደምንም ድንጋዩን ሲያንከባልለው፥ ከድንጋዩ ስር ብዙ ወርቅና " ድንጋዩን ያነሳ፤ ወርቁን ይውሰድ!" የሚል የንጉሱ ፊርማ ያረ…
❤43👍3
Signed єskindir
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @asgrami_tarikoche. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.