2 Jul 2026, 18:14 UTC742 views12 reactionsread 7 August 2026 ሰላም ኤዱ ዜድ እባላለሁ። ይቅርታ ካላስቸገርኩሽ ይቺን ታሪኬን ቻናልሽ ላይ እንድትፖስቺያት ነበረ። የሰዎች ምክር ያስፈልገኛል ብዬ ስላመንኩ ነው። በብዙ ምክንያት እኔ እና እህቴ አንድ ላይ ከቤተሰብ ርቀን ነው የምንኖረው። እኔ ታላቅ ወንድሟ ነኝ እሷ ገና 17 አመቷ ነው 11ኛ ክፍል ናት። ጎበዝ ተማሪ እና ስርአት ያላት ነበረች፤ ግን አሁን እርጉዝ ናት። ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፤ እኔ እህቴ በዚህ ልክ ትሳሳታለች ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር።
ቤተሰቦቻችን ወደ እኔ ሲልኳት "ለእሷም (ከአንተ ጋር) ከተማ መማር ይሻላታል፤ አንተንም ታነጋግርሃለች፣ አደራ ጠብቃት" ብለውኝ ነበር። ግን እሷ በሙሉ ልብ ከማፈቅረው ሰው አርግዣለሁ፣ ከእሱ ጋር መኖር እፈልጋለሁ አለ…
❤5🙊4👍3
Signed edº..
27 Jun 2026, 18:13 UTC≈1,000 views22 reactionsread 7 August 2026 ***
ፍቅር አለ ማይረሳ ፣
ሳቅን የሚቀማ
ሰላም የሚነሳ ፣
ጭስ የማይደብቀው ፣
መጠጥ የማይፍቀው ፣
.
አይንን የሚጋርድ
ጆሮን የሚደፍን ፣
አንችሆየ አምባሰል
ትዝታን ሚዘፍን ፣
ሌላ ማያሰማ
ምክር የማይደንቀው ፣
መልክ ገለመሌ
ውበት የማይሞቀው ፣
.
ፍቅር አለ አዝጋሚ
መቼም የማይጠፋ ፣
ከመጠጥ ከጭስ
ከሁሉ ሚከፋ ፣
.
ፍቅር አለ ፡፡
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
❤19💔2❤🔥1
Signed edº..
7 Jun 2026, 07:43 UTC≈1,230 views31 reactionsread 7 August 2026 Photo
አዲስ ነገር የለም
""""""""""""""""""""""
ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣
ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣
ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣
አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣
መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣
ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣
የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣
ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣
እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣
እንከተላለን ....
በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤
በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣
የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣
ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣
ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣
አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣
ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣
መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀ…
❤20👍5💯5🔥1
Signed edº..
31 May 2026, 10:56 UTC≈1,390 views18 reactionsread 7 August 2026 #አንተን_መውደድ
ፏፏቴ ዳር ቁጭ ብሎ
ዋሽንትን እንደ ማድመጥ፣
ዜማውን ተከትሎ
በደስታ እንደ መስመጥ፣
አይንን ከደን እንዳረጉ
የለሆሳስ ውዝዋዜ፣
ቢደጋገም የማይሰለች
የሚናፈቅ አይነት ጊዜ፣
ከተፈጥሮ ተዋህዶ
ንጹህ ህይወት እንደመልመድ፣
ልክ እንደዛ ሰላም አለው
ደስ ያሰኛል አንተን መውደድ፡፡
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
❤14❤🔥2👍1🤩1
Signed edº..
2 May 2026, 18:30 UTC≈1,820 views28 reactionsread 7 August 2026 #ይሂድ
.
ለመሄድ ቀጠሮ ይዞ
እያንቀላፋ ያለን ሰው፥
አባብለህ አታስቀረዉም
መሄጃዉ ሲደርስ ቀስቅሰው፡፡
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
👍18💯5👏3❤2
Signed edº..
12 Apr 2026, 06:39 UTC≈1,900 views21 reactionsread 7 August 2026 ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል እንኳን አደረሰን🤍🥰
❤17🎉3🙏1
Signed edº..
4 Apr 2026, 19:36 UTC≈2,350 views19 reactionsread 7 August 2026 #ብቻ_ይሳቅ
መውዜርም አትስጡት
ጎራዴም አትስጡት
አይጠቅመውም ለሱ፣
ለመግደል ለመግደል
ለመቅጣት ከሆነ
ይበቃዋል ጥርሱ፣
ጉልበት የማይጠይቅ
ልዩነው ፈገግታው
ላየው ቀልብ ይገፋል፣
ለጠላው አይደለም
ለወዳጁም ሳይቀር
ሳቁ ይጋረፋል!
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
❤9👍6🥰3👏1
Signed edº..
1 Apr 2026, 06:34 UTC≈2,020 views26 reactionsread 7 August 2026 #እሷና_እሱ
እሷ ኩሩ ናት ቅምጥል፣
አንድ ጌዜ ለብሳ የምጥል፣
እሱ ሚስኪን ነው ቆጥቋጣ፣
እሷን አግብቶ ተቀጣ።
.
ለአመት የመደበው ብር
በቀናት እየተፈጀ፣
አቅታው የገዛ ሚስቱ
ያለድሜው በጊዜ አረጀ!
#ኤዶምገነት_ፃፈች
@arifgtmbcha
😁13❤7🤣4👏1🥰1
Signed edº..
29 Mar 2026, 05:18 UTC≈1,990 views24 reactionsread 7 August 2026 #አምላኬ
.
ሆነልኝ ደስታና ሀሴት
ሞላልኝ የኔ ሸለቆ፣
እያልኩኝ ባንተ ውለታ
ይህ እርጉም ልቤ ተደንቆ፣
ላመሰግንህ ቀናስል
የደስታ ለቅሶ አልቅሼ፣
በሰጠኸኝ ልክ ያረኩት
አስጎነበሰኝ ምላሼ።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
🙏15❤7👍1👏1
Signed edº..
18 Mar 2026, 11:41 UTC≈2,160 views29 reactionsread 7 August 2026 Photo
#እዴሜዬ..?
በአንተ እሩጫ
በእኔ አረማመድ፣
እንዴት እንዝለቅ
ይሄንን መንገድ..?
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
❤13😁9🎉3🥰2👎1🤓1
Signed edº..
9 Mar 2026, 14:54 UTC≈1,910 views36 reactionsread 7 August 2026 #የኔ_እናት_እንዲህ_ናት
.
የማጠልቅ ፀሀይ ፣
የማጠቁር ሰማይ፣
የማትደርቅ አበባ፣
የማትረግፍ ወለባ፣
.
ሁልጊዜ ደስታ፣
ዘወትር ጫዎታ፣
አትታይ ተከፍታ፣
አትታወቅ ፈርታ፣
.
አዛኝ ሰው አክባሪ፣
ላድማጯ መካሪ፣
የማትሰምጥ መርከብ፣
የማትጠፋ ኮከብ፣
የማትጠር ንጋት፣
እናቴ እንዲህ ናት።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
❤23🕊9👏2⚡1💯1
Signed edº..
2 Mar 2026, 06:19 UTC≈1,730 views24 reactionsread 7 August 2026 🫡አድዋ....
አሀዱ ጅማሬ ጥቁራን ሲነሱ፣
እንደ አሸን ፈልተው ሀገሬን ሲያለብሱ፣
ሞት ፅዋን ሲቀምሱ፣
ፍቅርን ሲዘምሩ ሲያነቡ ቀይ እንባ፣
ክተት በነጋሪት ዝመት በጥሩንባ፣
አድዋ....
ያንድነት ድል ዋልታ፣
ዘደብረ ሀበሻ ማተብ የማይፈታ፣
እምነተቢስ መቶ አረም እንዳይዘራ፣
ክብሩ ከሸፈበት በእነ ጣይቱ ጥበብ
በእነ እምዬ ስራ፣
ከፋይ አከፋፋይ ሽንፈት የቀመሰ፣
በናቀው ምድር ላይ ደሙን አፈሰሰ፣
አድዋ....
የባላገር እልፍኝ የደመ ሙቅ ጓዳ፣
የቁርጥ ቀን ዎሰን ሰይፉን የከነዳ፣
ክብሩ የገነነ በነጭ የታፈረ፣
ሀቅ ያስመሰከረ....
በዝክረ ታቦቱ ውልደት የጀመረ፣
ያ ጥበብ ያ ቀለም ያ ስዕል አድዋ፣
በራቀው ሰማይ ስር ትውልድን የሰዋ፣
እልፎች ያለፉበት ታ…
❤11🔥10👏2👍1
Signed edº..
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @arifgtmbcha. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.