7 Aug 2026, 08:05 UTC95 views3 reactionsread 24 August 2026 ፍልሰታ ምን ማለት ነው?
ፍልሰታ ማለት ‹ፈለሰ – ተሰደደ› ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››
'ፍልሰታ ለማርያም' የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡
እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አ…
❤3
7 Aug 2026, 08:04 UTC75 views1 reactionsread 24 August 2026 ክፍል ፪
ሱባኤ ለመግባት መደረግ ያለበት ዝግጅት
ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት ኣስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት ኣስፈላጊ ነው፡፡
ቅድመ ዝግጅት
ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/ በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኣንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት ኣለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት …
❤1
5 Aug 2026, 20:17 UTC83 viewsread 24 August 2026 ክፍል ፩
🍁🌿✨🍁🌿✨🍁🌿✨🍁🌿✨🍁🌿✨
ሱባዔና ሥርዓቱ
🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩🤩
ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ
ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡
ሱባዔ ምንድን ነው?
ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው…
4 Aug 2026, 19:30 UTC93 viewsread 24 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
18 Jul 2026, 06:42 UTC160 views2 reactionsread 24 August 2026 ምክረ አበው
🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐
'ስለ ሌላው ሰው ከመፍረድህ በፊት፣ በእርሱ ጫማ ውስጥ ገብተህ ለመራመድ ሞክር። ያኔ መፍረድ ትተህ መጸለይ ትጀምራለህ።"
አባ ሙሴ ጸሊም
🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐
"እግዚአብሔር አንተን ሲፈጥርር ዓለም አላሰፈለጋትም ነበር እርሱ ግን አስፈልገኸዋል አሁንም አንተ ባትፈልገው እንኳ እርሱ ይፈልግሃል''
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐🌿✨💐
"ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ግንኙነት ለማስተካከል በነገው ቀን አትተማመን፤ ነገ ያንተ አይደለምና። ጠላት ሰይጣን በኋላ ታደርገዋለህ እያለ እሁንህን ሊሰርቅህ ይወዳል፡፡ ዛሬ ለመውደድ፣ ይቅርለማለትና ንሰሐ ለመግባት ያለህ የመጨረሻው ዕድል እንደሆነ አድርገህ ኑር፡፡''
አቡ…
❤2
18 Jul 2026, 06:41 UTC130 viewsread 24 August 2026 Photo
እንኳን #ለመርባስ ከሚባል አገር ሰዎች ለሆኑ #ለቅዱሳን_ዮሐንስና_ለአባቱ_ወንድም_ልጅ_ለስምዖን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና #ለእስክንድርያ_ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ ስምንተኛ ለሆነው #ሊቀ ጳጳሳት_ለቅዱስ_ለአባ_ገብርኤል ለዕረፍቱ በዓል በሰላሞ አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ በአስቄጥስ ገዳም ከነበረው ከቅዱስ አባት ኢሳይያስና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
17 Jul 2026, 09:43 UTC128 viewsread 24 August 2026 Photo
ስምዖን ቀለዮጳ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክንድርያ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ ከላድያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባት መላእክት ይጎበኙት ለነበረ ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ለነበረ ለአባ ብስንዳ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከምትታሰበው፦ ከሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) አብራ ሰማዕትነት ከተቀበለች ከቅድስት ቴዎና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን።
17 Jul 2026, 09:42 UTC106 viewsread 24 August 2026 Photo
እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለኢትዮጵያዊው_ለጻድቁ ለአባታችን #ለአቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ በዐባይ ባሕር ውስጥ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ #ለዘጠኝ_ዓመት ከጸለዩ በኋላ #ከጌታችን_ቃል ኪዳን_ለተቀበሉበት_ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
15 Jul 2026, 06:26 UTC120 viewsread 24 August 2026 Photo
እንኳን #ጌታችን_በአረጀ_መነኲሴ አምሳል ለተገለጸላቸ በጀርባቸው ላዘሉት የሚነድ መለኮት በከንፈራቸው ለሳሙ ለአባታችን #ለአቡነ_ኪሮስ ለዓመታዊ ለዕረፍታቸው በዓላቸው፣ አባ ኪሮስ ለቀበረው ለንጉሥ ልጅ ድኃ ለነበረው #ለአባ_ሚሳኤል ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልእግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
14 Jul 2026, 03:41 UTC137 views0 reactionsread 24 August 2026 እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም አባ_ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ሥሉስ ቅዱስ
በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ :ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው…
14 Jul 2026, 03:38 UTC112 viewsread 24 August 2026 Photo
እንኳን እንደ እርሱ ያሉ #ኤልያስና_ኄኖክ ወደ አሉበት ብሔረ ሕያዋን ለተሰወረው #ለነቢዩ_ለቅዱስ_ዕዝራ_ሱቱኤል_ለዕርገቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
12 Jul 2026, 15:04 UTC89 viewsread 24 August 2026 እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስና ለቅዱስ ጳውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ሐምሌ ፭ ቀን የቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች፣ የዓለም ብርሃናትና የቅዱስ ወንጌል ፋናዎች እንዲሁም ዋነኞቹ ሐዋርያት የሆኑት የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ያረፉበት ታላቅ ዕለት ነው።
ሁለቱም ሐዋርያት በተመሳሳይ ዕለት በሮም ከተማ በግፈኛው ንጉሥ ኔሮን እጅ የክብርን አክሊል ተቀዳጅተዋል።
ቅዱስ ጴጥሮስ (የሐዋርያት አለቃ)
ጥሪውና አገልግሎቱ፦ ቀድሞ ስሙ ስምዖን ይባል ነበር፤ ጌታችን ደግሞ "ጴጥሮስ (አለት)" አለው። የገሊላ ባሕር ዓሣ አጥማጅ የነበረው ጴጥሮስ፣ የጌታችንን ጥሪ ተከትሎ "ሰዎችን አጥማጅ" ሆነ።
ክብሩ፦ የሐዋርያት መሪና የቁልፍ ጠ…
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @amdetewahedo. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.