10 Apr 2026, 08:49 UTC≈1,670 views28 reactionsread 7 August 2026 ጉዞ
አምላክ ሆኖ ሳለ ከክብሩ ወረደ
እንደ ኃጢአተኛ በዓለም ተቆጠረ
የፍቅሩንም ጥግ ኢየሱስ አሳየ
የስጋን ልባሽ ሞት በጽናት ታገሰ×2
ጉዞ መስቀል ተሸክሞ ጉዞ
ተጉዞ ወደ ቀራኒዮ ጉዞ
ጉዞ ቀንበር ተሸክሞ ጉዞ
ተጉዞ ሞቴን ነው የሞተው ወዶ,,
የሾህ አክሊሊ ደፍተው ሲዘባበቱበት
ራሱን በመቃ መተው ሲያፌዙበት
ወዲህና ወዲያ ጥፊም ታክሎበት
ይህ ሁሉ ለእኔ ነው ምራቅ የተፉበት ×2
ጉዞ መስቀል ተሸክሞ ጉዞ
ተጉዞ ወደ ቀራኒዮ ጉዞ
ጉዞ ቀንበር ተሸክሞ ጉዞ
ተጉዞ ሞቴን ነው የሞተው ወዶ,,
በመስቀል ላይ ጥለው እጆቹን በችንካር
ተጠማሁኝ እስኪል በዚያ በጎልጎታ
ጎኑን በጦር ወግተው ያን ሁሉ መከራ
እኔን ለማዳን ነው ስቃዩን ያበዛ ×2
ጉዞ መስቀል ተሸክሞ ጉዞ
…
❤🔥16❤8🥰4
29 Mar 2026, 18:12 UTC≈1,680 views8 reactionsread 7 August 2026 እንድወድህ ታውቃለህ
ልቤን ውስጠቴን መርምረህ ፈገግ ስትል
ደስ ያሰኘህ ምን እንደሆን አላውቅም ነበር
ከላይ ለሚያየኝ መልኬ እድፌን ሲነግር
አንተ ግን ልቤን እያየህ ደስ ይልህ ነበር
ተንበርክኬ ባለሁበት ከእግሮችህ ስር
እየሱስ እንደምወድህ ትነግረኝ ጀመር
ያኔ ነው ያወኩት የልቤን
ገልጠህ ስታሳየኝ ሃሳቤን
አይኖቼ ተሞሉ በእንባ
የምሬን እወድሃለሁ አባ
ገና ሳልረሳው ሶስት ጊዜ የካድኩህን ቀን
ትወደኛለህ ስትለኝ ሆድ ብሶኝ ነበር
ሀጢያቴን ረስተህ በሰው ፊት ሳታዋርደኝ
ትወደኛለህ ስትለኝ ቃል አጥሮኝ ነበር
ጠላት በክፉ ሲመኘኝ ሊያበጥረኝ
ስለ እምነቴ ስለ ፍቅሬ ስትማልደኝ
ያኔ ነው ያወኩት የልቤን
ፍቅርህን እንደ ተከልክ በውስጤ
አይኖቼ ተሞሉ በዕንባ
የምሬን…
❤5🥰3
3 Feb 2026, 08:16 UTC≈2,010 views16 reactionsread 7 August 2026 በየቀኑ በየለቱ በየማለዳዉ የማየዉ
የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነዉ
በየለቱ በየቀኑ በየማለዳዉ የማየዉ
የየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነዉ
የወደዳቸዉን ፈጽሞ እስከመጨረሻዉ ወደደ
ልጆቹን ከበደል ሊያነጻ በራሱ ላይ ሞትን ፈረደ
ከሞት ይልቅ እጅግ ያየለ የበረታ ፍቅር ይዞት
ኢየሱስ እራሱን ከፈለ የእኔ መጥፋት አሳዝኖት
እነሆ ሲነጋና ሲመሽ ይህን ፍቅር አስታውሰዋለው
ሌላ ምሰጠው የለምና ተመስገን ከፍ በል እለዋለዉ
በየቀኑ በየለቱ በየማለዳዉ የማየዉ
የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነዉ
በየለቱ በየቀኑ በየማለዳዉ የማየዉ
የየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነዉ
ፍቅር ምን እንደሆን ታወቀ በስራዉ በሃይሉ በርትቶ
ሰማይን ከምድር …
❤12🔥4
29 Nov 2025, 04:05 UTC≈2,790 views16 reactionsread 7 August 2026 አባትነትህ
ትልቁ እግዚአብሔር ለኔ ለትንሿ
አባት ነው ዘመድ ኩራት መጏደጃ
ልክ እንደ አንድ ልጅ እንደ ብቸኛ
የምትሳሳልኝ የነፍሴ እረኛ
ትርፍ አይደለሁም ለቤትህ ወይ በጎደለ ልሞላ
ብጠፋ ፈላጊዬ እትተካኝም በሌላ
ዘጠና ዘጠኝ እያሉህ ሞልቶ እያለ በመንጋ
አይኖችህ ክርትት እያሉ እኔን አንዲቷን ፍለጋ
ባጠፋም ልጅህ ነኝ ባለማ
በመልካም በክፉ ብታማ
ውድ ነው የእኔ ልጅነት
በደል ያልፋል አባትነትህ
ነፍሴን መለስካት ስለ ስምህ
በፅድቅ መራኸኝ ስለ ስምህ
ቀንና ለሊት ስለ ስምህ
ተከታተልከኝ ስለ ስምህ
ልክ እንደ አንድ ልጅ እንደ ብቸኛ
የምትሳሳልኝ የነፍሴ እረኛ
አባ …
❤13🔥3
18 Nov 2025, 07:12 UTC≈2,640 views16 reactionsread 7 August 2026 ለትንሽ
[ቁጥር 1]
እሹሹ የለመደች ሀጥያት
በአንቀልባ ያዘልኳት አመፅ
እግር አብቅላ አይኔ አያት
ብኩን ነፍሴን ልታመስ
ልታፈርስ ልታርደኝ መጣች
አባብላ በማር አፏ
በደላይ ቃሏ
በደል ኋላ ልወድቅ በሷ
አጥቼው ነበር ነፃነቴን
የህፃንነት ልብ ቅንነቴን
ቀን የሰጠው ቅል ቀና ልቤን
እንዳይሰብርብኝ ለትንሽ
ለትንሽ አስመለጥከኝ
ሽሽ እያልከኝ ስተሻሽ
ልክ እንደጨው ሳልሟሽሽ
አስመለጥከኝ ለትንሽ
አስመለጥከኝ ለትንሽ
[አዝማች]
ለትንሽ ለትንሽ
ለትንሽ ለትንሽ
አስመለጥከኝ ለትንሽ
አስመለጥከኝ ለትንሽ
[ቁጥር 2]
ስነከፍ ተገኘሁ ከሲኦል አፍ
እራሴን ሳሳንቅ ለሞት መዳፍ
ቀን ቀጥሮ ቆሞ አንዲት ነፍሴን
ሳይወስድብኝ
ለቲኒሽ
ለቲኒሽ አስመለጥከኝ
ታዲጊዬ እግዚአብሔር…
❤12🥰3👍1
23 Aug 2025, 07:35 UTC≈3,910 views42 reactionsread 7 August 2026 አታፈግፍጊ
መረብሽን የጣልሽለት
እናት አባትሽን የተውሽለት
መረብሽን የጣልሽለት
እናት አባትሽን የተውሽለት.
ዛሬስ ምነው ነፍሴ ደከመሽ
እንደ አዳም ከአምላክሽ ትሸሽጊያለሽ
ዛሬስ ምነው ነፍሴ ደከመሽ
እንደ አዳም ከፊቱ ትሸሽጊያለሽ
ነፍሴ ሂጂ አታፈግፍጊ
የምህረት ደጁን አንኳኪ
እጄን ወደኋላ አትበይ እንጂ
የምህረት ጨርቆቹን ንኪ
ምህረትን ፈልገው የሄዱ
መቼ እንዳቀረቀሩ ቀሩ
ምህረትን ፈልገው የሄዱ
አልከሰሩም ከደጅ አልተጣሉም
የምህረት አምላክ ቸሩ ጌታ
እንባሽን ያብሳል እንደገና
የምህረት አምላክ ቸሩ ጌታ
ኃይልሽን ያድሳል እንደገና
ሰውን ባያፋር ጌታን ባይፈራ
ያ ክፉ ዳኛ ልቡ ባይራራ
ምስኪኗ ልመናዋ ቢያደክመው
ፊረደላት ደጋግማ እንዳታውከው
ምስኪኗ ልመ…
❤32👍3🔥3😍3👏1
7 Aug 2025, 15:59 UTC≈3,880 views19 reactionsread 7 August 2026 ሙሉ ቤት
ያን ጉባኤ አያለው ያንኑ ሙሉ ሰው
ሁሉ በአንድነት ገብቶ ወደታነፀው
ልቤ ለዚያ ፅኑ ነው ዛሬ እንኳ ባይደላው
አልከፋም በዚያ ሁሉን እረሳለው
ተጠላልፎ የወደቀው የምድር ህይወት ድካም ነው
ማን ተስፋ ሊያረገው ነገው እንፋሎት ነው
አዬ በጥቂት መዛሌ ደክሜ መሰበሬ
ተስፋዬ በላይ እንጂ በዚህ አይደለም ክብሬ
ከቀናቴ ደመና ከፍ ልበልና
ልታገስ ደጅም ልጥና ተስፋዬ ቀርቧልና
ውርደት ሀጥያት ውድቀት ከቶም የሌለበት
ውዴ ራስ የሆነበት ናፍቆኛል ያ ሙሉ ቤት
ያን ጉባኤ አያለው...
ስጋ ተዋርዶ ሲዘራ መች ይመስላል ሚነሳ
እንኳን ሰዉ ላይከብር አይቀርም ዛፍ እንስሳ
ሞት እንደው ልማዱ ነው ስንቱን ከእኛ ወሰደው
ያ ቀን ግን በደጅ ነው ትን…
❤16🔥2🥰1
24 Jul 2025, 13:18 UTC≈3,350 views8 reactionsread 7 August 2026 ይደምቃል
ይታያል ኢየሱስ በእኔ ላይ
ይታያል መልኩ በህይወቴ
ይታያል በእርሱ ውስጥ መኖሬ
ይታያል ተወካይነቴ
ምኞት ብቻ አይደል በውስጤ
የሚቀር በውስጤ
የተፃፈልኝን አየዋለሁኝ በህይወቴ
ይታያል ኢየሱስ በእኔ ላይ
ይታያል መልኩ በህይወቴ
ይታያል በእርሱ ውስጥ መኖሬ
ይታያል ተወካይነቴ #1
የማንነቴ ምንጭ ክርስቶስ ነውና
ዘሩን በእኔ አኑሮአል አፈራለሁ ገና
ከምድር አይደለም የተገኘሁበት
ይታያል የምለው የሚታየው እውነት(ውበት)
የክብሩ ጫፍ ያ መገለጡ
አይቀር በእኔ ላይ መታየቱ
የእርሱ ጠረን የእርሱ ፀዳል
በህይወቴ ዛሬም ይደምቃል
ኢየሱሴ ገና ይደምቃል ኢየሱሴ በጣም ይደምቃል ኢየሱሴ ሁሌም ይደምቃል ኢየሱሴ …
❤8
23 Jul 2025, 19:47 UTC≈2,690 views4 reactionsread 7 August 2026 ➠Old Group ላላችሁ በጣም በአሪፍ ዋጋ እየገዛን ነው
ግሩፓችሁ የተከፈተበት አመተ ምህረት ከታች ከተዘረዘሩት ውስጥ ከሆነ አሁኑኑ ያናግሩን...
2016 - 1000 ብር
2017 - 1000 ብር
2018 - 1000 ብር
2019 - 900 ብር
2020 - 900 ብር
2021 - 800 ብር
2024 - 200 ብር(January & February)
➠የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ይሁን ዋጋው እኩል ነው እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ
📌 NOTE: ከድሮ ጀምሮ Public እና የነበረ Chat History Hidden/Cleared ያልሆነ መሆን አለበት❗️
📌 two step …
❤4
20 Jul 2025, 10:35 UTC≈3,120 views19 reactionsread 7 August 2026 መስዋዕት
ከተከሸኑ እልፍ ቃላት
ከተመረጠ የቅኔ ብዛት
ሀገሩን ከሞላው ዜማ
የኔ ሕይወት ላንተ ይሰማ/ይሰዋ
ቢዘምርልህ ይህ አንደበቴ
መልክህ በራቀው የእለት እለት ህይወቴ
መስዋዕቴ ላንተ እኮ ነው
የሌለህበት ላንተ ምንህ ነው
መስዋዕቴ ላንተ እኮ ነው
ያልከበርክበት ሁሉ ድካም ነው
ይዘምር የእልፍኝ ሕይወቴ
አምልኮዬ ይቅደም በቤቴ
ልሁነው የዘመርኩትን
በቃላት ያሰፈርኩትን
ያምልክህ የጓዳ ህይወቴ
ይዘምር ይቅደም በቤቴ
ልሁነው የዘመርኩትን
በዜማ ያመለኩትን
ላምልክህ በህይወቴ በህይወቴ
ይገዛ መላው እኔነቴ ላምልክህ በህይወቴ
ላምልክህ በህይወቴ በህይወቴ
ያምልክህ መላ'ው ሰውነቴ ላምልክህ በህይወቴ
ላንተ መስዋዕት ይህ አይደል ወይ
ያንተ ምስጋና ህይወት አይደል …
❤18🥰1
16 Jul 2025, 17:17 UTC≈2,780 views19 reactionsread 7 August 2026 ልኑርልህ
(Chorus)
የእግዝአብሔር ልጅ እየሱስ
አንተ ሞትክልኝ እኔ ደግሞ ልኑርልህ
እግዝአብሔር ወልድ እየሱስ
አንተ ሞትክልኝ እኔ ደግሞ ልኑርልህ
እኔ ደግሞ ልኑርልህ x4
የፈገግታህ ነዕብራቅ የፍቅርህ ፍሰት
የማንነትህ ሙላት የርህራሄ ምልክት
የፈገግታህ ነዕብራቅ የመንፈስህ ፍሰት
የማንነትህ ሙላት የምረትህ ምልክት
ልሁንልህ x8
(Verse 1)
መሞትማ ቀላል ነው ወደ አንተ መሰብሰብ
ክብር እና ግርማህ ውስጥ ለዘላለም ‘ማምለክ
መኖር ግን እድል ነው ክርስቶስን መልበስ
በዚች ምድር ስመላልስ ህይወትህን መኖር
ህይወትህን መኖር x2
መስቀልህን መስበክ x2
(Bridge)
ሁለት እግሮቼን ውሰድና ተራመድበት ውረስና
ሁለት እጆቼን ውሰድና ዕድቅን ስራበት ው…
❤16👍2🥰1
16 Jul 2025, 13:29 UTC≈2,880 views12 reactionsread 7 August 2026 ነፍሴ ባንተ ላይ
ጭው ባለው በረሃ ደረቅ ምድረበዳ
ከቶ ማን ደርሶልሽ ነፍሴ አንቺ ሊረዳ
ተሸክሞ አሳለፈሽ ስለተስፋው ቃል ታምኖ
ከቦሽ የነበረውን ሰልፍ ከዙሪያሽ በትኖ
እስከ ሽበት ሊሸከምሽ ደግሞም/ዛሬም የታመነ ነው
ላንቺ ያለውም ሃሳብ ፍፃሜና ተስፋ አለው
ዛሬ ነፍሴ ተይ አትዛዬ እንጂ
ስፍራን ለቀሽ አትሂጂ
ምኞትሽን ከበረከቱ ሁሌም የሚያጠግባት
ላንቺ እሱ ብቻ ነው የዘላለም አባት
ግራ ቀኝ በማየት ትጥቅሽ አይላላ
የልቦናሽ አይኖች አይሄዱ ወደሌላ
ኢየሱስን ይዞ ከቶ ማን ያፈረው
ስፍራውን ለቆ እንጂ ሰነፍ የከሰረው
ዛሬ ነፍሴ ተይ አትዛዬ እንጂ
ስፍራን ለቀሽ አትሄጂ
ነፍሴ ያስጨነቀሽን በጌታሽ ላይ
ጣል አድርጊ ሁሉን ለእርሱ ተይ
የከበደሽን በአባትሽ ላይ…
❤10🥰2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @adadismezmurlyrics. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.